#የፋሲካ_ስጦታ| የመልካምነት ትንሽ የለውም
ውድ ቤተሰቦች ፈጣሪ ቢፈቅድ ለፋሲካ ልዩ የሆነ ዝግጅት አቅደን በተግባር ላይ እንገኛለን። ለዚህ ዝግጅት ስኬት ደግሞ ከኛ ይልቅ የናንተ መልካምነት ጎልቶ ሲታይ የነበረና ያለም ነው። ሁላችንም የምንችለውን በማድረግ እለታዊ ሳይሆን ቢያንስ ለቀናት የሚቆይ ፈገግታን #ለባለውለታ እናቶች ገፅታ ልናኖር ተዘጋጅተናል።
ዝግጅቱ ስጦታው በዋናነት የሁለት እናቶችን ችግር ቀለል ማድረግ ነው።
1ኛ. የጋሽ ዮሴፍ ወልዴ ሴተሰብ (ልጃቸው) የሚኖሩበት አሳዛኝ ሁኔታ ሲሆን የቀበሌ ቤታቸው ውሐ በማስገባት ከነሱ አልፎ ሁሉ ነገራቸውን እያበላሸ ስለተመለከትን ቤታቸውን በዘለቄታው ማደስ ነው። ጋሽ ዮሴፍ በህይወት ባይኖሩም በኛ ትውልድ ላይ ያሳረፉት የመልካምነት አሻራ "መልካም መሆን ሲሞቱ የማይሞት" ተግባር መሆኑን ማሳያ ነው። ቆርቆሮ ይቀየራል። ኮርኒስ ይሰራል። ቀለም ይቀባል። በተጨማሪም የፋሲካ አስቤዛ ይሟላል።
2ኛ. ማየት የተሳናቸው እናት ያለጧሪ የልጅ ልጅ ለማሳደግ በልመና ህይወታቸውን የሚገፉ ናቸው። እኝህ እናት የሰባት አመቷ ህፃን መማር አለባት በማለት "አዲስ ዘመን መዋዕለ ህፃናት ድረስ በህፃኗ መሪነት ከሄዱ በኋላ ህፃኗ ተምራ እስክትወጣ ት/ቤቱ በር ላይ እየለመኑ ይጠብቋታል። እድል ከቀናቸው ከልመና ባገኙት ገንዘብ የሚቀመስ ነገር ገዝተው በልጃቸው መሪነት ወደ ቤታቸው (የቀበሌ ቤት) ይሄዳሉ።
የሐዋሳ ትዝታ በተማሪ ልጄ ፕሮግራም ህፃኗን በትምህርትና አልባሳት እየደገፈ የሚገኝ ሲሆን፤ እኝህን ጀግና እናት ለፋሲካ አስቤዛ እና አልባሳት በማቅረብ በአልን ደስ ለማሰኘት አቅዷል።
3ኛ. እንደተለመደው በጎዳና ለሚኖሩ 50 ሴቶችና ታዳጊዎች ምገባ ሲሆን ከናንተ የሚገኘውን #አልባሳትም በማጋራት ከብርድ እንታደጋቸው።
ውድ ቤተሰቦች "የመልካምነት ትንሽ የለውምና በተቻለን ያህል በመሳተፍ ካዛውንቶቹ ምርቃት ከፈጣሪም በረከቱን እንካፈል ጥሪያችን ነው።
በአካል መገኘት የሚችል አብሮን ፕሮግራሙን በአካል ቢሳተፍ ደስ ይለናል። በተቀመጠው ስልክ ቁጥር ይደውሉልን።
የፍቅር የሰላምና የአንድነት አርበኞች!
#አሌክስ ግምባር ቀደም በጎነትህን ስላሳየኸን በሐዋሳ ትዝታ ቤተሰብ ስም ከልብ እናመሰግናለን።
0916291568/0911700123/0916863959
የመልካምነት ትንሽ የለውም! መልካምነት ይከፍላል።

#የሚደንቅ_ሰብዓዊነት!| ፋሲካን በምርቃትና ደማቅ ፈገግታ
#hawassa| ቃል በተግባር #4_ጉብኝቶች
እኔ ከምናገር ፎቶው ያውራ! ነገር ግን እናንተ የሐዋሳ ቅን ልቦች ፈጣሪ ያክብራችሁ። በተለይ የጋሽ #ዮሴፍ_ወልዴን ቤት ቀላል ባልሆነ ወጭ የቤቱን ጣሪያና ቆሮቆሮ በመቀየር፣ቀለም በመቀባት፣ ማብራት በማስተካከል ቤተሰቡን ከዝናብና ብርድ ንብረታቸውን ከብልሽት ለመታደግ #ከልብ_በመነጨ_ደግነት በገንዘብ ብቻ ሳይሆን በጉልበትም ጭምር የለፋችሁ #ለአለማየሁ_ቤተሰቦች እንዲሁም ወዳጆችና ጓደኞች በሙሉ ፈጣሪ ብድራቱን ይክፈልልን።
አሁንም ለበአል ጤፍ በማስፈጨት፣ ዶሮና ቂቤ፤ ዘይትና እናቶች አብልጠው የሚወዱትን #ቡና ጨምሮ በመግዛት በአልን በማድመቃችሁ የአባቶቻችንና እናቶችን ልብ አውቃ የሞላችሁ እናንተ ልባም ወጣቶች #አሌክስ_ቾምቤ ጓደኞችና ወዳጆች ክበሩልን።
ምን ይሄ ብቻ አቅመ ደካማን ለመደገፍ የማትለመኑ፣ ከልብ የመነጨ ደግነታችሁ ፊታችሁ በደስታ የሚሞላ ምርጦች በግለሰብ ደረጃ የማይታሰበውን #ለጋሽ_ለአሰፋ_ልጅ ወ/ሮ #ሃምሳል በየወሩ ሁለት ሺህ ብር (2000 ብር) በመስጠት አስደንቃችሁኛል። #አሌክስ
የየሐዋሳ ትዝታ ቤተሰቦች መርቁልን...
አረ ሌላም አለ... በድህነት በርካታ ቤተሰብ ይዘው ለማኖሩ #በተማሪ_ልጄ የሚደገፉ ተማሪ ህፃናት ቤተሰቦች አካባቢውን ሳትፀየፉ ከልብ በመነጨ ወዳጅነት ለአምስት ቤተሰቦች ከኛ ጋር በመሆን በየቤታቸው በመሄድ "እንኳን አደረሳችሁ በማለት #ዱቄት፣ #ዘይትና #የጥሬ ገንዘብ ስጦታ በማበርከት ድንቅ ስራ ሰርታችኋል። ከአምስቱም ቤተሰብ የጎረፈው በደስታና "ድንገቴ ፈንጠዝያ' አስፈንጥዛችሁ የምላችሁን ቃል አሳጣችሁን። ጠላታችሁ ቃል ይጣ😘
**
3. ጋሽ ደጀኔ የጎደለውን ይሙሉበት በማለት ለጋሽ ዮሴፍ ልጅ የ2000 ብር ስጦታ በልጃቸው አማካኝነት ስንሰጥ ወ/ሮ ሃምሳል ምርቃት አልቆባቸው ፊታቸው በእንባ ተሞላ። "ለካስ አባቴ ወዳጆች አሉት!" ጋሼ ሰላምዎ ይብዛ!
****
ውድ ቤተሰቦች ማለት ያለብኝን አላልኩም! እኔም ቃል አጥቻለሁ። የሐዋሳ ትዝታ በክፋት ተሞልቶ የነበረው ማህበራዊ ሚዲያ ዛሬ በፍቅርና በማካፈል፤ በመረዳዳትና በመደናነቅ መሞላቱ ትልቁ ግቡ ስኬት ነውና እነዚህን መሰል እንቅስቃሴዎች የምታደርጉ ብሎም ለምታካፍሉ በመላ የሐዋሳ ቤተሰብ ስም እናመሰግናለን።
****
ነገ ደግሞ በአሉን ኑሯቸውን ጎዳና ካደረጉ ወጣቶች፣ ሴቶችና ህፃናት ጋር የፆም ማስፈታት የምሳ ግብዣ እናደርጋለን። በዚህም የተሳተፉ ምርጥ ወገኖች እናከብራለን😍
ደግነቻችሁ ከልብ የመነጨ ይሁን! መልካምነት ይከፍላል!
መልካም ፋሲካ! 2015

#አድኑኝ! መኖር ፈልጋለሁ እባካችሁ ወገኖቼ
#hawassa| በአስቸኳይ 560000 ካላገኘች 😭
"ወገኖቼ_በገንዘብ_ምክንያት_መሞት_የለብኝም"
በለጋ እድሜዋ በልብ ህመም ምክንያት ቤቷ በስቃይ ስትማቅ ወላጆች የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ሲጨነቁ ማየት በእውነት ልብ ይሰብራል። አስቸኳይ ህክምና ካላገኘች ሁለተኛው ቫልቭ ስራ ያቆማል። ልብ ስራ ካቆመ ምን ማለት እንደሆነ ይገባናል።
የዛሬ 11 ዓመት ገና በጨቅላ እድሜዋ በትምህርት ላይ እንዳለች ነበር የልብ ህመም እንዳለባት የተረዳችው። ችግሩ የልብ የደም ቱቦ መጥበብ (Redo Mitral Valve) ሲሆን በወቅቱ በሙሉወንጌል ኮምፓሽን ድጋፍ ወደ ህንድ ተወስዳ በቀዶ ጥገና ሰው ሰራሽ ቫልቭ ተገጥሞላት ወደ መደበኛ ጤናዋ ተመለሰች።
ነገር ግን ያ የተገጠመላት ቫልቭ ከእድሜዋ (የአካል እድገት ጋር) አስፈላጊውን የደም ዝውውር ለማድረግ የማይችል በመሆኑ አንዱ ቫልቭ ስራ ማቆሙን ሁለተኛውም ሊያቆም ጥቂት ጊዜ እንዳላት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሐኪሞች አሳወቁ። ህክምናውን በጥቁር አንበሳ ማድረግ የሚቻል ቢሆንም የግድ 600 ወረፋ መጠበቅ ግድ ይላታል። በዚህ መሐል ህይወቷ አደጋውስጥ እንደሆነ ያሰዱት ሐኪሞቹ አቅም ካለ ወደ ግል ተቋም አፋጣኝ የቀዶ ጥገና እና የነበረው ቫልቭ እንዲቀየር አሳሰቡ።
ለቃል ቤተሰቦቿም ያላቸውን ሁሉ ለልጃቸው ህክምና ያዋሉ ቢሆንም ይህንን ቀዶ ጥገና ለማስደረግ በግል የህክምና ተቋሙ የወጣውን ተመን ለመክፈል አቅሙ እንደሌላቸው ያውቃሉ። በአካል ባገኘኋቸው ወቅት ልጃቸውን በገንዘብ ምክንያት ሊያጧት እንደተቃረቡ በማሰብ በከፍተኛ ጭንቀት ተወጥረው ይገኛሉ።
ወጣት ፍሬወይኒ "ጤነኛ ሆና እንደእኩዮቿ የቤተሰብ ብሎም ለሀገር አለኝታ መሆን ህልም እንዳላት ስትገልፅ የቤተሰቦቿን ጭንቀት ማየቱ የከበደ ህመም ከማስተናገድ የላቀ ህመም ሆኖባታል።
በአሁኑ ሰዓት ፍሬወይኒ የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን በህመሙ ምክንያት አቋርጣለች። ህልሟ ተስፋዋ ወደ መጨለም እንደተቃረበ ሁኔታዋ ያሳብቃል። ለመንቀሳቀስም ሆነ ተፈጥሯዊ ግብሮቿን ለመፈፀም የሰው ድጋፍ ግድ ብሏታል። ይሁን እንጅ ተስፋዋ አልከሰመም። የጤናዋ ሁኔታ በህክምና የሚድን ሆኖ በገንዘብ ችግር ለሞት የተቃረበን የኢትዮጵያ ደግ ህዝብ ከጎኗ ሊሆን እንደሚችል ታምናለች። ጤናዬን እንዳገኝ፣ ህልሜን እንዳሳካ ከኔ አልፌ ለሌሎች ወገኖቼ አለኝታ እሆን ዘንድ እርዱኝ ስትል በተማፅኖ ፊታችን ቀርባለች።
560000 ብር ህይወቷን ይታደጋል። ከተባበርን ደግሞ ነገ ያለመችውን ስታሳካ የምንኮራባት እናደርጋታለን።
"TO WHOM IT MAY CONCERN
FREIWOT TESFAYE came to Efouzeir cardiac center and she needs open heart surgery for Redo Mitral Valve Replacement. The total cost for the surgery is:
560,000Birr (Five sixty Twenty Thousand Birr only).
The center will perform the surgery when the total payment is made. This letter was written upon her request."
ህክምናዋንና ለበርካታ አመታት ወላጇቿ ያደረጉላትን ማስረጃ አያይዘናል። በገንዘብ ባንችል እንኳ በመደወል እናፅናናት።
ውድ ኢትዮጵያውያን አነሰ በዛ ሳንል በመደገፍ ህይወቷን እንታደግ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን።
የወላጆቿን ስልክና የባንክ አካውንት ከስር አስቀምጠናል።
CBE-1000187280595 /0930958512 ( 0912184652 እናት ሁሌ ጌታቸው CBE- 1000252939818 አባት ጌታቸው ወጋሳ አየለ)