በመንገድ ላይ በማለፍ ላይ እያለ አንድ ወጣት በኤሌክትሪክ ምሰሶ ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየ።

ቀረብ ብሎም ማንበብ ጀመረ....

"ትናንት ሃምሳ ብሬ እዚህ መንገድ ላይ ጠፍቶብኛል። እኔ አይኖቼ ስለደከሙና በትክክል ማየት ስለማልችል ላገኘው አልቻልኩም። ብሬን ያገኘ ሰው እባካችሁ እዚህ በተቀመጠው አድራሻዬ አምጡልኝ!!" ይላል።

ይህን ካነበበ በኋላ፣ ወጣተየ ‘’50 ብር በጣም ትንሽ ብር ሆኖ ሳለ አንድ ሰው እንዴት ይህንን ማስታወቂያ ሊለጥፍ ይችላል?’’ ብሎ እራሱን ጠየቀ።
---------------------------
ብዙም ሳይቆይ ‘’ብሩ ትንሽ ቢሆንም፤ ይህን መልእክት ላስቀመጠው ሰው በጣም አስፈላጊ መሆን አለበት።’’ ብሎ አሰበ።
---------------------------
ወዲያውኑ በተጠቀሰው አድራሻ መሰረት አንድ ቤት ደረሰና በሩን አንኳኳ።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንዲት አሮጊት ሴት በሩን ከፍተው ብቅ አሉ።

ትንሽ ካወሩ በኋላም ወጣቱ አሮጊቷ በዚች ቤት ውስጥ ብቻቸውን እንደሚኖሩ ተረዳ።
---------------------------
ወጣቱም "እማማ የጠፋብዎትን 50 ብር ስላገኘሁት ልሰጥዎ ነው የመጣሁት። ‘’ አላቸው።

አሮጊቷም ወጣቱ ይህን ሲላቸው ማልቀስ ጀመሩ።

"ልጄ እስካሁን ከ70-75 የሚጠጉ ሰዎች 50 ብሩን አግኝተናል እያሉ እቤት እየመጡ ሰጥተውኛል። እኔ ግን ማንበብ አልችልም፤ ብቻዬን ነው የምኖረው፤ ዓይኖቼም ደካማ በመሆናቸው ይህ የተለጠፈው የት እንደ ሆነ አላውቅም። ይህንን ሁኔታዬን የተረዳ አንድ ሰው እኔን ለመርዳት ያን ወረቀት ለጥፎት መሆን አለበት። እኔ የጠፋብኝ ብር ስለሌለ አልቀበልም።’’ በማለት መለሱለት።
---------------------------
ወጣቱ ግን አሮጊቷን በማጽናናት ብሩን እንዲቀበሉት ያደርግና ተመልሶ እንደሚመጣና እንደሚጎበኛቸው ቃል በመግባት ተሰናበታቸው።

እሳቸዉ ግን ‘’ ልጄ እባክህ የተለጠፈውን ወረቀት ቀደህ ጣልልኝ። እኔ ይህን ማድረግ ስለማልችል ነው የምጠይቅህ። ‘’ ብለው ለመኑት።

ወጣቱም ‘’እሽ! እማማ። ‘’ ብሎ ተሰናበታቸው።
---------------------------
እሽ ቢላቸውም እንዲህ ሲል ግን አሰበ፡- “ከዚህ በፊት ወረቀቱን እንዲቀዱላቸው የመጡትን ሰዎች ሁሉ ጠይቀው መሆን አለበት። ግን ማንም ሰው ወረቀቱን ሳይቀደው እኔ ለምን እቀደዋለሁ?’’

ከዚያም ይችን ደካማ ሴት ለመርዳት ይህን መንገድ ያሰበው ሰው ምን ያህል ደግ ሊሆን እንደሚችል አሰበ። አደነቀም።
---------------------------
ፍላጎቱና ተነሳሽነቱ ካለ አንድን ሰው ለመርዳት ብዙ መንገዶች አሉ!!!
---------------------------
መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎች ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share እያደረጋችሁ🙏
----------------------------------
በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8liGZZvXfIT&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
የህንዱ ቢልየነር ራታን ታታ በአንድ የሬዲዮ አቅራቢ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ፡-

"ጌታዬ… በህይወትዎ ደስታን ለማግኘት ያደረጉትና የሚያስታውሱት ነገር ምንድነው…?"

ቢሊኒየረር ራታኒጂ ታታ እንዲህ አለ፡-

<<እኔ በህይወቴ ደስታን ለማግኘት አራት ደረጃዎችን አልፌያለሁ … እናም በመጨረሻ ትክክለኛውን የደስታ ጣዕም ነው ያገኘሁት።

የመጀመሪያው ደረጃ:- ገንዘብ እና የሀብት ምንጮችን መሰብሰብ ነበር፡፡ ግን በዚህ ደረጃ እኔ የምፈልገውን ደስታ ላገኝ አልቻልኩም፡፡

ከዛም ወደ ሁለተኛው ደረጃ ቀጠልኩኝ…

ውድ የሆኑ ዕቃዎችንና ነገሮችን መሰብሰብ…ግን አሁንም የገባኝ ይሄን ጊዜያዊ ስሜት እንደሆነ ነበር… በውድ ነገሮች የሚመጣ ደስታ ዘላቂ አልነበረም፡፡"

ቀጥዬ ወደ ሶስተኛ ሂደት ገባሁኝ…

ትልቅ የቢዝነስ ፕሮጀክት በእጄ ማስገባት ነበር፡፡ ይሄ ማለት 95% የነዳጅ ገበያ በህንድና በአፍሪካ መያዝ ነበር፡፡ እሱ ብቻ አልነበረም እኔ በእሲያ እና በህንድ ያለ በጣም ትልቅ የብረት ፋብሪካ ባለቤት ነበርኩኝ፡፡ ግን እንዳለምኩት የሚሆን ደስታን ማግኘት አልቻልኩም፡፡

አራተኛው ደረጃ:-

አንድ ጓደኛዬ የሆነ የጠየቀኝ ነገር ነበር … ይህም መራመድ ለማይችሉ ለተወሰኑ ልጆች ዊልቸር እንድገዛ ነበር፡፡

ወደ 200 ዊልቸር ይሆናል የገዛሁት… በጓደኛዬ ትዕዛዝ ዊል ቸሮችን በፍጥነት ገዛሁኝ፡፡

ግን ጓደኛዬ አሁንም አለቅህም አለኝ… ዊልቸሮችን አብረን ሄደን ለልጆችሁ እንድንሰጥ አጥብቆ ጠየቀኝ፡፡

እኔም ከእሱ ጋር ለመሄድ ተስማማሁ፡፡ ቦታው ድረስ በመሄድ ለልጆቹ ዊልቸሮቹን በእጄ ሰጠሁኝ፡፡

በልጆቹ ላይ የሚገርም የሚበራ ደስታ አየሁኝ፡፡ ሁሉም ዊልቸሩ ላይ በመቀመጥ በደስታ እያሽከረከሩ ሲደሰቱ ተመለከትኩኝ፡፡ እነሱ ከፍተኛ የደስታ ጫፍ ላይ ደርሰው ነበር…

እኔም ልክ ለመሄድ ስነሳ… አንድ ህፃን ልጅ እግሬን ያዘኝ፡፡ በቀስታ እግሬን ለማስለቀቅ ስሞክር ግን ልጁ ፊቴን በትኩረት እያየ እግሬን ይበልጥ ወደ ራሱ በማስጠጋት ያዘኝ፡፡

እኔም ወደ ልጁ ዝቅ በማለት ተጠግቸው ምን እንደሚፍልግ ጠየኩት…

ልጁ የመለሰልኝ መልስ እኔን ማስገርም ብቻ አልነበረም ህይወትን የምመለከትበትን መንገድ ሙሉ በሙሉ ነበር የቀየረው… ልጁም እንዲህ ነበር ያለኝ፡-

"በገነት ሳገኝህ ፊትህን ለይቼ ላስታውሰው እፈልጋለሁ… ያኔ በድጋሚ ላመሰግንህ እፈልጋለሁ።"

እናም በመጨረሻ ትክክለኛውን የደስታ ጣዕም ያገኘሁት በዚህ ጊዜ ነበር።>> ሲል ተናግሯል።

(ብዙ ሰው ሊያስተምር የሚችል ታሪክ ነው ብለን ስላመን በድጋሚ የተለጠፈ።)
------------------------------
ከዚህ ታሪክ ምን ተማራችሁ? comment በማድረግ ሃሳባችሁን አጋሩን።
------------------------------
ታሪኩን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎች ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share እያደረጋችሁ🙏
----------------------------------
በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8liGZZvXfIT&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
በድህነትና በውድቀት የታጠረውን ህይወቱን በስራ ፈጠራ ሰባብሮ ያለፈውና በዚህ ሰዓት ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ሀብት እንዳለው የሚነገርለት ቻይናዊው ቢሊየነር “ጃክ ማ” እንዲህ ይላል፡-

‘’ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም!

አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው።

ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው።

ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት መሆኑን ነው። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል!

እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል።

በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰአት እስከ 12 ሰአት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም።’’
-----------------------------------
[በዚህ የጃክማ እይታ #ትስማማላችሁ? ሃሳባችሁን #comment በማድረግ አጋሩን፤ #እንወያይበት!]

ከወደዳችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ 🙏
የ93 አመት እድሜ ባለጸጋ አዛውንት በድንገት ራሳቸውን ይስቱና መተንፈስ አቅቷቸው ወደ ሆስፒታል ይወስዳሉ። እናም ለ 24 ሰዓታት ኦክስጅን ተሰጥቷቸው ይቆያሉ። ከጥቂት ሰዓት በኋላ ተሽሏቸው ወደቤታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ። ዶክተሩም ‘’እስካሁን ለተደረገልዎት የህክምና እርዳታ 5000 ዶላር መክፈል ይጠበቅብዎታል’’ ይልና ሂሳቡን ያሳያቸዋል።

አዛውንቱም ሂሳቡን አይተው ማልቀስ ጀመሩ። ዶክተሩ በሂሳቡ ምክንያት ከሆነ እንዳያለቅሱ ነገራቸው። አዛውንቱ ግን "በገንዘብ ምክንያት አላለቅስም። ገንዘቡን በሙሉ መክፈል እችላለሁ። ያለቀስኩበት ምክንያት ለ 24 ሰአታት ኦክሲጅን በመጠቀሜ 5000 ዶላር መክፈል አለብህ አላችሁኝ። ነገር ግን 93 አመት ሙሉ ፈጣሪዬ የሰጠኝን አየር ስተነፍስ ቆይቻለሁ። ግን ይህን ያህል ዘመን ምንም አልከፍልም ነበር። ከፈጣሪዬ ምን ያህል ዕዳ እንዳለብኝ ታውቃለህ? ይህ ቸርነቱ ነው ያስለቀሰኝ።’’ ብለው መለሱለት።

ዶክተሩም አንገቱን ደፍቶ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ።

ይህን ለምታነቡ ሁሉ፣ ለፈጣሪ ምንም የምንከፍለው ነገር ሳይኖር ለዓመታት ነፃ አየር ስንተነፍስ ኖረናል፣ እንኖራለንም።

በህይወታችን ውስጥ ይህን ሁሉ በገንዘብ የማይተመን አገልግሎት በነፃ ለሰጠን ፈጣሪያችን 2 ሰከንድ ብቻ ወስደን ማመስገን ይከብደናል?

እስቲ ፈጣሪያችንን እናመስግነው!
-----------------------------
ታሪኩን ከወደዳችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ
-----------------------------
በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8liGZZvXfIT&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
የላቁ ዕይታዎችና እሳቤዎች የሚጋሩበትን
ይህን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8liGZZvXfIT&_r=1#tiktok ገፅ ተከተሉት ታተርፉበታላችሁ። ለሌሎችም አጋሩት
አንድ የስነ-ሰብ (Anthropology) ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል።

ጨዋታውም፣ በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው:-

"እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል:: "

ጨዋታው ተጀመረ።

ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።

ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ::

የስነ-ሰብ ተመራማሪውም በመገረም "ለምን እንዲህ አደረጋቹ?"ሲል ጠየቃቸው።

ሁሉም በአንድነት "ኡቡንቱ! " በማለት መለሱለት።

በመቀጠል አንዱ ህፃን እንዲህ አለው:-

"እንዴት ሌሎች ጓደኞቻችን ተከፍተው አንድ ልጅ ብቻውን ይደሰታል? ይሄ ባህላችን አይደለም::"

"ኡቡንቱ" የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪቃው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም:-

“ለመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ!” የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው።

-----------------------------
ታሪኩን ከወደዳችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ
-----------------------------
በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8liGZZvXfIT&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
አንድ ሰው ብዙ ሰው ነው፡፡ ብዙ ሰው ግን አንድ ሰው ሊሆን አይችልም፡፡

የአንድ ሰው ብዙነት ከዕድሜው የሚያገኛቸው ብዝሃ ማንነቱ ነው፡፡ አንድ ሰው በልጅነቱ የልጅነት አስተሳሰብና ማንነት አለው፤ በወጣትነቱም የወጣትነቱን ሰውነትና የትኩስነት ማንነቱን ይይዛል፡፡ ያው አንዱ ሰው ሲጎለምስም የጉልምስና ሰውነትን ያንፀባርቃል፡፡ በአዛውንትነት ዕድሜውም በተረጋጋው ማንነቱ ሰውነቱን ያበጃጃል፡፡ በስተመጨረሻም በዘመነ እርጅናው ትናንቱን እየወቀሰና እያሞገሰ፣ ዛሬ ላይ መካሪና ዘካሪ እየሆነና ወዳለፈው ጊዜ በሃሳብ ፈረስ እየጋለበ፣ ትዝታውንም እያቀነቀነ ወዳማይቀረው ይሄዳል፡፡

እነዚህ ሁሉ የተለያዩ ማንነቶች በአንድ ግለሰብ ህይወት ላይ ወጥተው የሚገቡ፤ ገብተው የሚወጡ ማንነቶች ናቸው፡፡

አምላክ የሰው ልጅ ተፈጥሮን አንድ ጊዜ ቢሰራውም ሰው ግን ማንነቱን ብዙ ጊዜ ያበጃጃዋል፡፡ እንደእውቀቱ መጠን፤ እንደአስተሳሰቡ ደረጃ፣ እንደሕይወት ገጠመኙ፣ እንደአኗኗር ሁኔታው፣ እንደአስተዳደግ ዘዬው ራሱን ይለዋውጣል፤ አዕምሮውን ያድሳል፤ ሃሳቡን ያገላብጣል፡፡

ከተፈጥሯዊው የእድሜ ጉዞው በተለየም ሰው ዕውቀትን ሲጨምር፣ አስተሳሰቡን ሲያድስ፣ ኑሮውን ሲቀይር አዲስ የአኗኗር ዘይቤን ሲከተል አዲስ ሰውነትን ይጎናፀፋል፡፡ ያው አንዱ ሰው ብዙ የተለያዩ ማንነቶችን ለራሱ ይጋብዛል፡፡ ታዲያ አንድ ሰው ስንት ነው? ብዙ ነዋ!

አንድ ጥንታዊ ፈላስፋ ያነሳው ግሩም ጥያቄ ነበር፡፡ ጥያቄውም፡-

‹‹እኔ ራሴ አንድ ሰው ሆኜ አላውቅም፡፡ ምክንያቱም አስቀድሞ እንደህፃን፣ ቀጥሎም እንደወጣት፣ ከዚያም እንደጎልማሳ፣ በመጨረሻም እንደሽማግሌ ኖሬአለሁ፡፡ ከሞት በኋላ ሕይወት ቢኖር እንኳን ዘላለማዊውን ሕይወት እንደማን ሆኜ ነው የምኖረው? እኔ የሕይወት ተሞክሮ ውጤት ነኝ፡፡ ስለሆነም ሁለትና ሶስት ወይም ከዚያ በላይ የሰው ባሕሪያትን በውስጤ ይዤ በምድር ላይ ከኖርኩ በኋላ ብሞት በምኖረው ሕይወት የመገለጫዬ ባህርይ ማን ሊሆን ነው?›› ሲል ይጠይቃል፡፡

ጥያቄው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡

ሰው ከሞት በኋላ የማንነት መገለጫው ማን እንደሆነና በየትኛውስ ማንነቱ ሊፈረጅ እንደሚገባ ማወቅ አጓጊ ነው፡፡ እንደእኔ ግን ሰው ከሞት በፊት በመጨረሻ ሕይወቱ የያዘው ማንነቱ በዕድሜው ሙሉ ያያቸውና የተለዋወጠባቸው ማንነቶች ድምር ውጤት በመሆኑ የሚፈረጀውም፣ የሚከሰሰውም፣ የሚደነቀውም ሆነ የሚከበረው በኋለኛው የህይወት ማንነቱ ነው፡፡ ምክንያቱም የመጨረሻው ሕይወቱ የዕድሜው ሁሉ መጠቅለያ ማንነት ነው፡፡

ሰው በዕድሜው ካያቸው የራሱ የተለያዩ ማንነቶች የሚወሰደውን ወስዶ፣ የሚጣለውን ጥሎ መልካሙን ማንነት መያዝ የእሱ ድርሻ ነውና፡፡ ከራስ መማርን የመሰለ ምን ወሳኝ ትምህርት አለ?! ምንም!

እድሜ ካልተማርንበት ቁጥር ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ቁጥር ብቻ ደግሞ ዋጋ የለውም፡፡ ዋጋ ያለው ሕይወት እውን የሚሆነው የሰው ልጅ ዕድሜ በበጎ ስራ ሲቆጠርና ሲተመን ብቻ ነው፡፡ በዚች አስገራሚ ዓለም ሽማግሌ ሆነው እንደ ልጅ የሚኖሩ፤ ልጅ ሆነው እንደአዋቂ የሆኑ መኖራቸው ሃቅ ነውና፡፡

ከሞት መለስ በሕይወት እያለ የሰው ልጅ መጠየቅም፣ መኮነንም፣ መደነቅም ሆነ መከበር ካለበት በአሁናዊው ማንነቱ ነው፡፡ ዛሬ ማንነቱን በበጎ አስተሳሰብ የዋጀ ሰው ትናንት ባጠፋው መወቀስ የለበትም፡፡ የትናንቱ ጥፋት በትናንት ማንነቱ ነው ሊፈረጅ የሚገባው፡፡ ዛሬ አዲስ ሰው ነውና!

የአመክንዮ ሕግም በትናንት ማንነቱ የዛሬውን አዲስ ማንነቱን የሚደመድሙ ሰዎች ልክ እንዳልሆኑ ይናገራል፡፡ ይሄንንም Miss-representation Fallacy ሲል ይገልፀዋል፡፡ ዛሬ አዲስ ሰው ነውና የትናንቱን ሽሯል፡፡ የትናንት አሮጌ አስተሳሰቡን በአዲስ አስተሳሰብ አድሷል፡፡ የትናንት አላዋቂነቱን በዛሬ ዕውቀቱ ቀይሯል፡፡ ትናንት ያልገባው ዛሬ ገብቶታልና፡፡

ታላቁ የነፃነት ታጋይ የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ እንዲህ ይሉናል፡-

‹‹በስኬቴ አትዳኙኝ፡፡ ይልቁንስ ምን ያህል ጊዜ ወድቄ ምን ያህል ጊዜ መልሼ እንደተነሳሁ አይታቹህ ፍረዱኝ ›› ይላሉ፡፡

አዎ! የአወዳደቅህ ሳይሆን የአነሳስህ ሁኔታ ያንተን ማንነት አጥርቶ ያሳያል፡፡ የወደቁ ሳይሆን ከውድቀታቸው የተነሱ አዕምሯቸው ሰፊ ስለመሆኑ ክርክር አያሻውም፡፡

በጠባቡ አስተሳሰባቸው ወድቀው በሰፊ አስተሳሰባቸው ሕይወታቸውን ያሰፉና ከውድቀታቸው የተነሱ ትንሳኤ ብሩሃን የሆኑ ሊደነቁ ይገባል፡፡ ምክንያቱም በመውደቅ መነሳታቸው መካከል ያገኙት ትምህርት እንዴት ከውድቀት መነሳት እንደሚቻል አዲስ ዕውቀት አስጨብጧቸዋል፡፡ ተስፋ ቆርጠው ወድቀው አለመቅረታቸው የሚያሳየው የአስተሳሰባቸው ጮራ ምን ያህል የበራ እንደነበረ የሚያሳይ ነውና፡፡

አዎ! ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችን በተለያዩ ውድቀቶችና አወዳደቆች ተፍገምግመናል፡፡ የሚያሳፍረውና የሚያስፈራው ነገር ከውድቀታችን ለመነሳት ፍላጎቱም ሆነ ቁርጠኝነቱ የሌለን መሆኑ ነው፡፡

👉 አንዳንዶች በዘረኝነት ወድቀዋል፣ 👉 ጥቂቶች በትእቢት በአፍጢማቸው ተተክለዋል፡፡
👉 ቀላል ቁጥር የሌላቸው አወቅን ብለው ደንቁረዋል፤ ሰፋን ብለው ጠብበዋል፡፡
👉 ሰለጠንን ያሉት እቡያን ሰይጥነዋል፡፡
👉 ከዕድሜአቸው ያልተማሩ፤ ከብዝሃ ማንነታቸው ቀለም ያልቆጠሩ፣ መልካሙን ያልኮረጁ ቆመ-ቀሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡
👉 ከብዝሃ ማንነታቸው ያልተማሩ በአንዱ ማንነታቸው የሙጥኝ ያሉ አዲስ ሃሳብ ያስደነግጣቸዋል፤ ለውጥ ይቀፋቸዋል፤ አዲስ ማንነት ያስፈራቸዋል፡፡

አዎ! አንድ ሰው ብዙ ነው፡፡ ብዙነቱን ግን እውን የሚያደርገው በሰፊው አስተሳሰቡ ሲሰፋ ነው፡፡

ከተፈራረቁበት ማንነቶቹ ጠቃሚውን ማንነት ፈልቅቆ የሚያወጣ ብልህ ሰው ከብዙነቱ እልፍ ትምህርት ቀስሟል፡፡ ቅስሙን የሚሰብር ሳይሆን ቅስሙን በአዲስ አስተሳሰብ የሚጠግን ጀግና ካለፈው ሕይወቱ ብዙ የተማረ ነው፡፡ ከውድቀቱ የሚማር መላልሶ መነሳት አይቸግረውምና፡፡

ወዳጄ ሆይ…

👉 አንተ አንድ ሰው አይደለህምና እንደብዙ ሰው አስብ!

👉 መውደቅን አትፍራ! ነገር ግን እንዴት ከወደቅበት ቦታ መነሳት እንደምትችል አዕምሮህን አሰራ፡፡

👉 መውደቅ በማንም ላይ የሚደርስ ነው፡፡ ከዛ ይልቅ ወድቆ መቅረት ነው አሳፋሪው ነገር፡፡

ቸር መነሳት! ቸር ትንሳኤ! ቸር ብዝሃነት!

✍️ እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

ይህን ፅሁፍ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ
-----------------------------
በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8liGZZvXfIT&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤው አደረሳችሁ።
ወተት ከተበላሸ እርጎ ይሆናል፤ እርጎ ግን ከወተት የበለጠ ዋጋ አለው። ወተት የበለጠ የከፋ ከሆነ ወደ አይብነት ይቀየራል። አይብ ግን ከእርጎ እና ከወተት የበለጠ ዋጋ አለው።

የወይን ጭማቂ ወደ ጎምዛዛነት ከተለወጠ ወደ ወይን ጠጅ ይለወጣል፤ ይህም ከወይኑ ጭማቂ የበለጠ ውድ ያደርገዋል።

ስህተት ስለሰራህ አበቃልህ ማለት አይደለህም። ስህተቶች እንደ ሰው የበለጠ ዋጋ እንዲኖርህ የሚያደርጉ ልምዶች ናቸው።

ክሪስቶፈር ኮሎምበስ አሜሪካን እንዲያገኝ ያደረገው በአሰሳው ወቅት ስህተት በመስራቱ ነው።

የአሌክሳንደር ፍሌሚንግ ስህተት ፔኒሲሊን እንዲፈጥር አድርጎታል።

ስህተቶችህን እንድትወድቅ ሳይሆን የተሻለ እድሎችን የምትፈልግባቸው መሰላል አድርጋቸው።

ፍጹም የሚያደርገን ልምምድ አይደለም። ፍፁም የሚያደርገን የተማርንባቸው ስህተቶች ናቸው!

አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share #ማድረግን አትርሱ 🙏
1. ‹‹መከራ ሠውን ይሠራዋል፤ ቁሳዊ ብልፅግና ግን አስፈሪ ጭራቅ ያደርገዋል፡፡››

2. ‹‹ከሁሉ መጀመሪያ ሠው ሁን! የሠብዓዊነትን ቀንበር ለመሸከም አትፍራ፡፡››

3. ‹‹መሞት ምንም አይደል፡፡ አለመኖር ግን አስከፊ ነው፡፡››

4. ‹‹ብልህ ሠዎች ከሕይወት መከራ መፅናኛቸውን የሚፈልጉት ከመፅሐፍ ነው፡፡››

5. ‹‹ጊዜው ከደረሠ ሃሳብ በላይ ሃይለኛ የለም፡፡››

6. ‹‹ሌላ ሠው ማፍቀር የፈጣሪን ሌላኛውን ፊቱን ማየት ነው፡፡››

7. ‹‹የሃብታሞች ገነት የተሠራው ከደሃዎች ሲዖል ነው፡፡››

8. ‹‹የማያለቅሱ ማየት አይችሉም፡፡››

9. ‹‹ምንም ዓይነት ጦር ወይም መሣሪያ ጊዜው የደረሠ ሃሳብን ሊያስቆመው አይችልም፡፡››

10. ‹‹ሠዎች ጥንካሬ አላጠራቸውም፡፡ ያጠራቸው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ብቻ ነው፡፡››

11. ‹‹ሕሊና ማለት በሠው ውስጥ የፈጣሪ መኖር ነው፡፡››

12. ‹‹ልማድ ወይም ሱስ ስህተቶችን መንከባከቢያ ስፍራ ነው፡፡››

የትኞቹን አባባሎች ወደዳችኋቸው? comment አድርጉልን።

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mB3JiCSMbO&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
በአንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጉድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች፡፡ በጣም መጮህ ጀመረች፡፡

ባለቤቱም እሷን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ አደረገ አልተሳካለትም ፤ አህያዋ አርጅታለችና እዚያው ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብራት አሰበ።

ጎረቤቶቹንም ጠራና ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመሩ፡፡ አህያዋ ይህንን ስተመለከት እየቀበራት መሆኑን ተረዳችና እጅጉን አዘነች፡፡

ይሁን እንጂ አፈር በተደፋባት ቁጥር አህያዋ አንድ ነገር ታደርግ ነበር። አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ነበር። በተደጋጋሚ በተደፋው አፈር ላይ መቆም ትጀምራለች።

በሂደት በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች በመጨረሻም ከጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መውጣት ቻለች፡፡

በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ስዎች ሁሉ በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
------------------------------
የአህያዋ ታሪክ ሁላችንንም ይመለከተናል። የሚጫንብን አፈር በየጊዜው የሚያጋጥሙንና ዝም ብንላቸው በመጨረሻ ሊቀብሩን የሚችሉ ችግሮች ወይም መሠናክሎች ናቸው፡፡

አፈሩን የሚጭኑት ሰዎች በዙሪያችን ያሉ ሰዎች፣ ነገሮች፣ በህይወታችን ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩብን አዳዲስ ለውጦች እንዲሁም የራሳችን አፍራሽ ስሜቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

ጉድጓዱ ደግሞ አሁን ያለንበት ግራ የተጋባንበት! ተስፋ ቢስ የሆንበት፡ መላ ያጣንበት ህይወት ወይም ገጠመኝ ሊሆን ይችላል፡፡
------------------------------
በእርግጥም እኛ ሰዎች በጤናችን! በኢኮኖሚ ህይወታችን፤ በትዳርና ፍቅር ህይወታችን በተለያየ አጋጣሚ ልክ እንደ አህያዋ ጉድጓድ ውስጥ የመግባት ዕድላችን ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ጠንካሮች እንደ ጠንካራዋ አህያ ከገቡበት ጉድጓድ ውስጥ መውጣት ሲችሉ አንዳንዶቹ በዚያው ተቀብረው ቀርተዋል፡፡
------------------------------
በህይወታችን ውስጥ ያለው አማራጭ! ወደ ላይ መውጣት አልያም ደግሞ ወደ ታች ወርዶ ከጥልቅ ጉዳጓድ ውስጥ ተቀብሮ መቅረት ብቻ ነው!

ልክ እንደ አህያዋ (የሚጫንባትን አፈር እየረገጠች ወደ ላይ ከፍ እንዳለችው) ሁሉ እኛም በየጊዜው የሚያጋጥሙንን ችግሮች እንደ ድጋፍ እየተጠቀምን በጥንካሬ ወደ ላይ መነሳት ያስፈልገናል።
------------------------------
ከጥልቁ ጉድጓድ ውስጥ ለመውጣት የምንችለው ለመውጣት የምናደርገውን ጥረት ባለማቆም ብቻ ነው!

ምንጊዜም በጠንካራ ውስጣዊ ቁርጠኝነትና እምነት ችግሮችን እንደ መወጣጫ ደረጃ በመጠቀም ከታች ወደ ላይ እንጓዝ!!
------------------------------
እያንዳንዱን ችግር እንደ መሰላል ከተጠቀምክበት ከስኬት ጫፍ ትደርሳለህ!

------------------------------
መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎች ይማሩበት ዘንድ #like #repost #copylink #share ማድረግን አትርሱ!

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mB3JiCSMbO&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
"የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እያለሁ ሁለት ቁልፍ ፈተናዎች ነበሩብኝ ሆኖም ሁለቱንም ወደኩ….

የመካከለኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁም ፈተና ከመውደቅ አልዳንኩም ለውድቀት ሶስት ጊዜ እጄን ሰጠሁ፡፡

👉 ኮሌጅ ለመግባት ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም መግቢያ ፈተናዎቹን ሁለቴ ወስጄ በሽንፈት ተመለስኩ፡፡ የሚገርመው ደግሞ ያመጣሁት ውጤት አሳዛኝ ነበር። መውደቅ አንድ ነገር ቢሆንም በሂሳብ ትምህርት ከ120 ነጥብ 1 ማምጣት ግን በርግጥም ከባድ ነበር፡፡

ውድቀቴ ይቀጥላል…

👉 ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ 10 ጊዜ አመልክቼ ውድቅ ተደርጎብኛል፡፡

👉 ከኮሌጅ ተመርቄ ከወጣሁ በኋላ ስራ የመቀጠር ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም 30 ስራ እድሎች በተከታታይ ብሞክርም አልተሳካልኝም፡፡

KFC ስራ አወጣ ተደሰትኩ በዚህኛው ግን ስራ ለማግኘት የማደርገው ጥረት በድል እንደሚደመደም አስቤ ተራመድኩ፡፡

ኦብዙ ፈተናዎችን አልፈን ለስራ የመጣነው 24 ነን፡፡ 23 ሰው አለፈ በሚደንቅ ሁኔታ የወደቀው አንዱ ሰው እኔ ነበርኩ፡፡"

ይህንን ያለው ጃክ ማ ነው።

ይህ ሰው ከዚህ ሁሉ ውድቀት በኋላ ቻይናን የቀየረ አማዞንን መሰል የአሜሪካ ካምፓኒዎችን የሚገዳዳረውን አሊባባን የመሰረተ እና እዚህ ያደረሰ ስኬታማ ሰው ነው፡፡

"በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ዛሬ ከባድ ነው…ነገም የከፋ ሊሆን ይችላል… ከነገወዲያ ግን መልካም ይሆናል!!!"
– Jack Ma

------------------------------
መልእክቱን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎች ይማሩበት ዘንድ #like #copylink #share ማድረግን አትርሱ!

በርካታ አስተማሪና የላቁ ዕይታዎችን በምናጋራበት ወደ #tiktok አካውንታችን 👉 https://www.tiktok.com/@higherperspective1?_t=8mB3JiCSMbO&_r=1 እየገባችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፦
ከንባብም ሆነ ከህይወት ተሞክሮ ያገኛችሁትን ሌሎችን ሊያስተምር የሚችል ማንኛውንም #እይታና #እሳቤ ይህን 👉 https://www.tg-me.com/higher_perspective_group የቴሌግራም ግሩፕ በመቀላቀል #አጋሩን! እርስበርስ እንማማር!

ወዳጅ ጓደኞቻችሁ ይህን ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ዘንድ #ሊንኩን👆 #copylink #share በማድረግ ጋብዟቸው🙏
2024/05/17 10:01:35
Back to Top
HTML Embed Code: