4. በትግራይ የተፈጠረው ወቅታዊ ክፍፍልን አስመልክቶ የተወያየ ሲሆን በውይይቱም ሕዝቡ ሕዝባችን አብያተ ክርስቲያናቱም የቤተክርስቲያን ሀብት እንደመሆናቸው ቀደም ብሎ የተዋቀረው የሰላም ኮሚቴ ሥራውን አጠንክሮ እንዲቀጥል በምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
ጉባዔው በነገው ዕለትም ቀጥሎ በቀሪዎቹ 12 አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል፡፡

❤15👍5
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ውሎ በተለያዩ አጀንዳዎች ውሳኔ አሳለፈ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በዛሬው ሁለተኛ ቀን ውሎው በአጃንዳ ቁጥር ፭ እና ፮ ላይ በሁለት አጀንዳዎች ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ አጀንዳ ቁጥር ፭ የነበረው ውይይት ከተለያዩ የቤተክርስቲያኒቷ አህጉረ ስብከቶች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንዲመደብላቸው ጥያቄ የቀረቡትን የተመለከተ ነበር፡፡
ይህንንም ጥያቄ መልስ ለመስጠትና ውሳኔ ለማሳለፍ አስቀድሞ ምልዓተ ጉባኤው አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ለኮሚቴነት በመሰየም የቀረቡትን ጥያቄዎች በማየት የውሳኔ ሐሳብ ለምልዓተ ጉባኤው እንዲያቀርቡ በማድረግ አምስት አባቶችን ሰይሟል፡፡
የተሰየሙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም ከምልዓተ ጉባኤው ጎን ለጎን የቀረቡትን ሦስት ጥያቄዎች በኮሚቴው በማየት የምክረ ሐሳብና የውሳኔ ሐሳብ ለምልዓተ ጉባኤው አቅርበዋል፡፡
ብፁዓን አባቶችም ባቀረቡት የውሳኔ ሐሳብም ምክንያት ምልዓተ ጉባኤውም ሰፊ ውይይት በማድረግ አሳልፏል።
በዚህም መሠረት፡-
፩ኛ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ያቀረበውን አባት ይመደብልን የሚል ጥያቄ በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና የመተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን ደርበው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን እንዲመሩና እንዲይዙ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
በ፪ኛ ደረጃ ደግሞ ከደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ያቀረቡት እንዲሁ አባት እንዲመደብ ጥያቄ ነው፡፡

❤2
ብፁዕነታቸው በሚመሩአቸው የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የከሚሴ የደቡብ ወሎ ልዩ ዞን ሁለቱን ሀገረ ስብከቶች አባት እንዲመደብላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት የብፁነታቸውን ጥያቄ ተቀብሎ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአቀረቡት የውሳኔ ሐሳብ መሠረት ለአግልግሎትም እንዲመች በአቅራቢያ የሚገኙትን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ደርበው እንዲመሩ ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
በ፫ኛ ደረጃ ከምሥራቅ ወለጋ፣ ከምዕራብ ወለጋ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ አባት እንዲመደብ የቀረቡ ጥያቄዎችን በአጀንዳ ቀርጾ በብፁዓን አባቶች በቀረበው የውሳኔ ሐሳብ መሠረት የምሥራቅ ወለጋንና የሆሮ ጉድሩን ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ጳጳስ ሀገረ ስብከታቸውን እንደያዙ ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
የምዕራብ ወለጋን በተመለከተ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ኤውስጣቴዎስ የኢሊባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ ወለጋን ደርበው እንዲመሩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
በ፮ኛ ተራ ቁጥር የነበረው አጀንዳ የኢትዮጵያ ገዳማት ኅብረት ያቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ ውይይት የተደረገበት አጀንዳ ነው፡፡
በዚህ አጀንዳ ላይ የገዳማቱ የሥራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት አባቶች ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው ጥያቄአቸውን በንባብ አሰምተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ገዳማት ከ፳፻፲ ዓ.ም ጀምሮ ያደረጋቸውን ሥራዎች የሚገልጽ በዚያም በየደረጃው በገዳማት መምሪያና በቋሚ ሲኖዶስ በተሰጡአቸው የመተዳደሪያ ደንቦች ሥራቸውን እያካሄዱ እንደሆነ ከዚያም ደግሞ የገዳማቱ አባቶች ለተልዕኮና ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ አዲስ አበባ በሚመጡበት ጊዜ ማረፊያ ስለሚያስፈልጋቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረቡት መሠረት ይህን የመሰለውን አጀንዳዎቻቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ በንባብ አሰምተዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስም የአባቶችን ጥያቄ በመስማት ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት በአንደኛ ደረጃ የገዳማቱ ኅበረት ያቀረቡት ከገዳም ለአገልግሎትና ለተለያየ ተልእኮ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የሚያርፉበት ቦታ ያለውን አስፈላጊነት ምልዓተ ጉባኤው በመገንዘብ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ተመቻችቶ በዚያ መልስ እንዲሰጣቸው ወስኗል።
በሁለተኛ ደረጃ የታየው የገዳማት ኅብረቱ ለገዳማት ዘላቂ ልማትና ራስን ለመቻል በልማት ለሚያካሂዷቸው እንቅስቃሴዎች ጥያቄዎችን የተመለከተ ነው፡፡
ይህንንም ጥያቄ ምልዓተ ጉባኤው በሰፊው በመወያየት ጉዳዩ ጥናት የሚያስፈልገው፣ የሕግ አስተያየት የሚያስፈልገው በመሆኑ ጥያቄው ለመንበረ ፓትርየርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በቋሚ ሲኖዶስ ክትትል ወደፊት ውሳኔ ይሰጠዋል በማለት ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
በዛሬው ዕለት በአጀንዳ ቁጥር ፭ እና ፮ ቅዱስ ሲኖዶስ ያደረገው ውይይት ይህን ይመስላል፡፡
በቀጣይ በቀሪዎቹ አጀንዳዎች ላይ ምልዓተ ጉባኤው ውይይቱን የሚቀጥል ይሆናል፡፡

❤13
“ከአባቶቻችን ለልጆቻችን”
“ጉባኤ ቤቶች ሲጠነክሩ ቤተ ክርስቲያን ትጠነክራለች፤ እነሱ ላይ መሥራት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ መሥራት ነው።”
መምህር ያረጋል አበጋዝ
ደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም ቤ/ክ የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርጿል።
G+2 የተማሪዎች መኖሪያ ፣የጉባኤ አዳራሽ፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ሙዚየም እና ቴክኖሎጅ ክፍል
B+ G+4 ዓለም አቀፍ መንፈሳዊ የትምህርት ማዕከል
የመምህራን መኖሪያ
ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች
ለበለጠ መረጃ
0918523699
0918062008 ይደውሉ።
ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ በእነዚህ ቁጥሮች ይደግፉ።
ኢ/ንግድ ባንክ 1000727772727
ዓባይ ባንክ 4659412373459012
ብርሃን ባንክ 1132060391976
አቢሲኒያ ባንክ 208943774
አማራ ባንክ 9900045603575
አዲስ ኢን/ ባንክ 1180892429203001
አሐዱ ባንክ 0018263111702
ሕብረት ባንክ 2240415455416012
እናት ባንክ 1281231251813001
ዳሽን ባንክ 5110902732011
ፀሐይ ባንክ 1008312261
ወጋገን ባንክ 1106107030301
አዋሽ ባንክ 013521664644700
ቡና ባንክ 2769527000100

❤8
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በ2018 ዓ.ም ማኅበራዊ ቀውስ ያለባቸውን አካባቢዎች ለመርዳት ከአጋር አካላት ጋር አጠናክሮ እንደሚሠራ አስታወቀ
ጥቅምት ፲፬/፳፻፲፰
ማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በ2018 ዓ.ም በተለያየ ምክንያት ማኅበራዊ ቀውስ ያጋጠማቸውን አካባቢዎች ለማገዝ ከአጋር አካላት ጋር አጠናክሮ እንደሚሠራ አስታውቋል።
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት በማኅበረ ቅዱሳን የሙያ፣ ማኅበራዊና እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ም/ኃላፊ ዲ/ን ንጉሤ ባለውጊዜ ማኅበሩ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በማኅበራዊ ቀውስ፣ በድርቅ ፣በጦርነት፣ በጎርፍና በተለያዩ ሃይማኖት ተኮር ግጭቶች ለተጎዱ ወገኖች አስቸኳይ ሰብአዊ ርዳታዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በየዓመቱ በማኅበራዊ ቀውስ ለተጎዱ አዳጊዎችና ሕጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ፣ወርኃዊ የት/ት ድጎማ እና ሌሎች ቋሚ ድጋፎች እያደረገ እንደነበር በመግለጽ በዘንድሮው ዓመት ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ ለመሥራት ቅድመ ዝግጅትን አጠናቆ የድጋፍ ሂደት ላይ እንዳለ ተናግረዋል።
ም/ኃላፊው አክለውም ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ በፈጠረው ቀውስ ምክንያት ተፈናቃዮች ያሉባቸው አካባቢዎች ተለይተው ድጋፍ እንደሚያደረጉ ገልጸው ከምእመናን፣ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ከአጥቢያዎች፣ ከማኅበራትና ከተቋማት ጋር ተባብሮ በመሥራት ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

በ2017 ዓ.ም ከአጋር አካላት በተገኘ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ማኅበራዊ ድጋፍ መደረጉን አንሥተው በ2018 ዓ.ም ከዚህ በላይ ይጠበቃል፣ ያሉት ም/ኃላፊው ዲ/ን ንጉሤ ባለውጊዜ አክለውም የሀገሪቱ ማኅበራዊ ቀውስ እስካልተፈታ ድረስ የነፍስ አድን ድጋፍ ማድረጋችንን ስለሚቀጥል፣ ርዳታውን ለማዳረስም ሁላችንም የበኩላችንን ድጋፍ በማድረግ ሰብአዊ ግዴታችንን መወጣት አለብን ብለዋል።
ማኅበሩ መርዳት ለሚችሉ አጋር አካላት መረጃ በመስጠት፣ የትግበራ ሪፖርቶችን፣ የድጋፍ ደረሰኞችን ፣ የምስጋና ወረቀቶችን ለደጋፊዎች በማቅረብ ምቹ ተቋማዊ አሠራር ያለው ስለሆነ አዳዲስ ድጋፍ ሰጪ አካላት አብረው እንዲሠሩም ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም ም/ኃላፊው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ያበረከቱ አጋር አካላትን ያመሰገኑ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት የተሻለ ሥራዎችን በጋራ እንድንሠራ ሲሉ አሳስበዋል። ድጋፍ ለማድረግም በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 መጠቀም የሚቻል መሆኑም ተገልጿል።
+ ለበለጠ መረጃ ፡- 0984181544/0948506072 መደወል ይችላሉ፡፡

❤7
ቅዱስ ሲኖዶስ በሦስተኛው ቀን ውሎው "ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ" በሚል እየተሠራጨ ያለውን መጽሐፍ አወገዘ፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ በሦስተኛ ቀን ውሎው ከአጀንዳ 7-13 ባሉት ላይ ውይይት ማድረጉና ውሳኔ ሰጥቷል።
ረዳት ፕሮፌሰር መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል የጥናትና ምርምር መምሪያ እና የቅዱስ ሲኖዶስ የኮሚዩኒኬሽን ሓላፊ ዛሬም ማብራሪያውን ሰጥተዋል።
በአጀንዳ ቁጥር 7 ከአርሲ ሀገረ ሰብከት ካህናትና ምእመናን የቀረበውን አቤቱታ በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ የአርሲ ሀገረ ስብከት ካህናት እና ምእመናን ያቀረቡትን አቤቱታ በንባብ በማድመጥ ጉባኤው የቀረበውን አቤቱታ አስተዳደራዊ ብቻ ሳይሆን የሒሳብ ጉዳዮችም ያሉበት በመሆኑ ዝርዝር ማጣራት ስለሚያስፈልገው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት በኩል አጣሪ ተመድቦ በሚቀርበው ሪፖርት ጉዳዩ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲታይ እና ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉባኤው መወሰኑን ጨምረው ገልጸዋል።
በአጀንዳ ቁጥር 8 የተወያየውና ውሳኔ ያሳለፈው የሸካ ዞን ራሱን ችሎ ሀገረ ስብከት እንዲሆን የቀረበውን ጥያቄ በተመለከተ መሆኑን ነው ሓላፊው የገለጹት፡፡
በዚህም የሸካ ዞን ራሱን ችሎ በሀገረ ስብከት ደረጃ እንዲቋቋም በቀረበው ጥያቄ መነሻነት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በግንቦቱ ርክበ ካህናት በሰጠው ውሳኔ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል ተጠንቶ እንዲቀርብ መደረጉን ጉባኤው አስታውሷል፡፡
በተስጠው ውሳኔ መሠረት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የተላኩት ልዑካን ያቀረቡት ጥናት ተቀባይነት ያገኘ በመሆኑ፤ የሸካ ዞን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተብሎ ራሱን ችሎ በሀገረ ስብከት ደረጃ እንዲቋቋም እና ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሊቀጳጳስ ሀገረ ስብከቱ እንዲያደራጁና እንዲመሩ ይደረግ በማለት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ ማሳለፉን በዕለታዊ ማብራሪያቸው ገልጸዋል፡፡
በአጀንዳ ቁጥር 9 በአንድ ግለሰብ ተዘጋጅቶ "ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ" በሚል እየተሠራጨ ያለውን መጽሐፍ አስመልክቶ ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል፡፡
ይኸውም በአንድ ግለሰብ ተዘጋጅቶ "ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ" በሚል እየተሠራጨ ያለውን መጽሐፍ የተመለከቱ የታላቁ ደብረ ሊባኖስ አንድነት ገዳም መምህር የሆኑት መጋቤ ምሥጢር አባ ክንፈሚካኤል ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት መጽሐፉ እንዲመረመር ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት መጽሐፉ እንዲመረመር እና ያለበት ግድፈትና የስሕተት ትምህርት ተለይቶ እንዲቀርብ ወደ ሊቃውንት ጉባኤ የመራው ሲሆን፤ የሊቃውንት ጉባኤውም መጽሐፉን በሚገባ በመመርመር መጽሐፉ ያለበትን ግድፈትና የስሕተት ትምህርት ነቅሶ በማውጣት ከውሳኔ ሐሳብ ጋር አቅርቧል።
ቅዱስ ሲኖዶስም ቀደም ሲል በሊቃውንት ጉባዔ ተመርምሮ ያለበት ግድፈትና የስሕተት ትምህርት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስያንን የማይወክል በመሆኑ "ገድለ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት" በማለት ተጽፎ የቀረበው መጽሐፍ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የሚያዛባ ሆኖ ስለተገኘ በቅዱስ ሲኖዶስ መወገዙ ተገልጿል፡፡
መጽሐፉ በውስጥ የየያዛቸው የተሳሳቱ ትምህርቶች በሙሉ ተቀባይነት የሌላቸው ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ታትሞ ሥርጭት ላይ የዋለው መጽሐፍ ሥርጭቱ እንዲታገድ፣ በድጋሚም እንዳይታተም፣ በማናቸውም ሁኔታ መጽሐፉ ለማጣቀሻም ሆነ ለምርምር እንዳይውል በመወሰን ይህም ውሳኔ ለየአህጉረ ሰብከቱ በሰርኩላር ደብዳቤ እንዲላክ በማለት መወሰኑ ተገልጿል።
ቅዱስ ሲኖዶስ የሊቃውንት ጉባኤ የጀመረውን የማጣራት ሥራ በሌሎችም መጻሕፍት እንዲቀጥል እና ከምስጋና ጋር መመሪያው እንዲደርሰው፤ መጽሐፉን አሳትመው ያሰራጩት ግለሰብ በቋሚ ሲኖዶስ ተጠርተው እንዲጠየቁና የፈጸሙት ስሕተት በተመሳሳይ እንዳይደግሙ ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጣቸው መወሰኑ ተገልጿል።
መጽሐፉ እንዲመረመር ያደረጉት የታላቁ ደብረ ሊባኖስ አንድነት ገዳም መምህር መጋቤ ምሥጢር አባ ክንፈሚካኤልን ቅዱስ ሲኖዶስ ማመስገኑን ሓላፊው ገልጸዋል::
በአጀንዳ ቁጥር 10 በዩናይትድ ኪንግደምና አየርላንድ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ 18 አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ተወካዮች ነን የሚሉ ወገኖች ባቀረቡት ማመልከቻ መነሻነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ጉዳይ መምሪያ ጉዳዩን በመመልከት በሰጠው መግለጫ ላይ ተወያይቷል፡፡
በዚህም ቅዱስ ሲኖዶስ የክፍሉ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የሀገረ ስብከቱን መዋቅር በማጠናከር በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጣቸውን ሓላፊነት በመወጣት፤ በአካል በሀገረ ስብከታቸው በመገኘት አሉ የተባሉ ችግሮችን በመፍታት በግንቦቱ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲያቀርቡ ውሳኔ ማስተላለፉን በመግለጫቸው ገልጸዋል፡፡
በአጀንዳ ቁጥር 11 በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ካልፎርኒያ ኔቫዳና ኦሪዞና ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ሥር መንፈሳዊ ኮሌጅ ለመክፈትና የአብነት ትምህርት ማስመስከሪያ ት/ቤት ለማቋቋም ዕርዳታና እውቅና እንዲሰጠው ባቀረበው የዕውቅና ጥያቄ ላይ በመወያየት መንፈሳዊ ኮሌጁና የአብነት ትምህርት ማስመስከሪያ ት/ቤቱ እንዲከፈት የተፈቀደ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ የትምህርት አሰጣጥ፣ ፖሊሲውንና ሥርዓተ ትምህርቱን፣ የሰው ኃይል ትመናውንና መዋቅራዊ ተጠሪነቱን በተመለከተ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ቀርቦ እንዲመረመርና የመጨረሻ ጥናቱ ለግንቦት 2018 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ሲል ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል::
በአጀንዳ ቁጥር 12 እና 13 በካናዳ በሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ዙርያ ውሳኔ ማሳለፉን የገለጹ ሲሆን፤ በዚህም ውሳኔ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ያቀረቡት ጥያቄ በተመለከተ የኹለቱ አህጉረ ስብከት አስተዳደር ከዚህ ቀደም በግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት እንዲፈጸም ሆኖ አንዱ በአንዱ ጣልቃ ባለመግባት በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ አርባ ንዑስ ቁጥር 3 የተመለከተው ድንጋጌ ተጠብቆ እንዲሠራበት በማለት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መካከለኛው ካናዳ ኤድመንተን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሀገረ ስብከቱ ስያሜ እንዲስተካከል በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ ምልዓተ ጉባኤው ተቀብሎ የሀገረ ስብከቱ ስያሜ የመካከለኛው ካናዳ ኤድመንተንና አካባቢው በሚለው እንዲስተካከል በማለት ምልዓተ ጉባኤው በመወሰን የዕለቱን ስብሰባ ማጠናቀቁን ረዳት ፕሮፌሰር መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ገልጸዋል፡፡

❤31
የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልዓተ ጉባኤ መጠናቀቁን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጠ
ጥቅምት ፲፯/፳፻፲፰ ዓ.ም
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው፣ የሐዋርያት መንበር ወራሽ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ
“ወይኩን ጉባኤ ሊቃነ ኤጴስ ቆጶሳት ወኤጲስ ቆጶሳት ክልዔተ ጊዜ በበዓመት ወይትናገሩ በእንተ ግብረ አብያተ ክርስቲያናቲሆሙ ወያሰስሉ ዕቅፍታተ …
የሊቃነ ጳጳሳትና የጳጳሳት ምልዓተ ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን ስለአብያተ ክርስቲያናት የሚገባውን ሁሉ ይነጋገሩ የሐዋርያዊ ተልእኮ መሰናክሎችንም ሁሉ ያስወግዱ” ተብሎ በመጀመሪያው የሐዋርያት ቀኖና፣ በሁለተኛው ቀሌምንጦስ በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 - ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና የምጣኔ ሀብት ዕድገት፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርና ሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡
ወቅቱን ያማከሉና ዘላቂ የቤተ ክርስቲያንን ተቋማዊ ሕልውና የሚያረጋግጡ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልናንን የሚያስጠብቁ፣ ለምእመናን ደኅንነትና ለአገልጋዮች ሕይወት በሚጠቅሙ፣ መንሳፈዊ አስተዳደርንና ማኅበራዊ ጉዳዮችን መሠረት ባደረጉ አጀንዳዎች ላይ በመንፈስ ቅዱስ አንድነት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-

1.ሁለንተናዊ ሰላምና መረጋጋት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊ መሠረቷ፥ የሥርዓተ ቅዳሴዋና የምሥጢራት አገልግሎቷ አካል፣ የመንፈሳዊና ማኅበራዊ ሥምሪቷ ማእከላዊ ዐምድ በመሆኑ በግንቦት 2017 ዓ.ም. ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሠየመው የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፤ የደረሰበትንም ውጤት ለግንቦት 2018 ዓ.ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲያቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥብቅ መመሪያን አስተላልፏል
2.በትግራይ አህጉረ ስብከት የሚገኘው ሕዝበ ክርስቲያን ሕዝባችንና ወገናችን ስለሆነ አብያተ ክርስቲያናቱና ገዳማቱም የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ሀብቶች በመሆናቸው፣ አህጉረ ስብከቱም የተደራጁት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በመሆኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ተጠብቆ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ተከብሮ፣ የመዋቅር ግንኙነቱን ወደ ቀደመ ቦታው እንዲመለስ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም፣ የአንድነትና የይቅርታ በር ክፍት መሆኑን ከመግለጽ ጋር ቅዱስ ሲኖዶስ በክልሉ ለሚገኙት አባቶች፣ ካህናትና ምእመናን ያልተቋረጠ የሰላም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የቀድሞዎቹ ቅዱሳን አባቶቻችን ዋጋ ከፍለው፣ ቀኖናዊ ሥርዓቷንና ክብሯን ጠብቀውና አስጠብቀው ፣ አንድነቷን አጽንተው ያወረሱንን አሐቲ ቤተ ክርስቲያን የቀደመ ሉዓላዊ ክብሯ እንደተጠበቀ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የበለጠ ዋጋ ያሰጣልና ቀደም ሲል ለዚሁ ጉዳይ የተሠየመው ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ሊቃውንቱ፣ ካህናቱና መላው ሕዝባችንም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት ሁሉ የበኩላችሁን እንድትወጡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በአጽንኦት ያሳስባል፡፡
3.ቅዱስ ሲኖዶስ አባት እንዲመደብላቸው ጥያቄ ባቀረቡ አህጉረ ስብከት ዙሪያ የውሳኔ ሐሳብ የሚያቀርቡ ብፁዓን አባቶችን በመሰየምና ተገቢውን ውይይት በማድረግ፡
ሀ) ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ የኢሉ አባቦራ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣
ለ) ብፁዕ አቡነ ቶማስ የአዊና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የምሥራቅ ጎጃምን ሀገረ ስብከት ደርበው እንዲመሩ፣
ሐ) ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ፣
መ) ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ የምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የምሥራቅ ወለጋና ሆሮ-ጉድሩ ወለጋ አህጉረ ስብከትን ደርበው እንዲመሩ
ሠ) በተጨማሪም የሸካ ዞን ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ተብሎ ራሱን ችሎ በሀገረ ስብከት ደረጃ እንዲቋቋም፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሀገረ ስብከቱን እንዲያደራጁና እንዲመሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.ነባሩና ጥንታዊው የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ገድል እንደተጠበቀ ሆኖ ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሚል ያለአግባብ በአንድ ግለሰብ ተዘጋጅቶ እየተሠራጨ ያለው መጽሐፍ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ ያለበት ግድፈትና የስሕተት ትምህርት በሙሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሰ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ የማይወክል ሆኖ በመገኘቱ ተወግዟል፤
በውስጡ የያዛቸውም የተሳሳቱ ትምህርቶች በሙሉ ተቀባይነት ስለሌላቸው መጽሐፉ ለጥናትና ምርምርም ሆነ ለማጣቀሻ አገልግሎት እንዳይውል፣ በሥርጭት ላይ የዋለው መጽሐፍ እንዲታገድና በድጋሚም እንዳይታተም፣ ለየአህጉረ ስብከቱ ሠርኩላር እንዲተላለፍ፣ የአፈጻጸም ክትትል እንዲደረግና አጠቃላይ ሁኔታው በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚዲያ እንዲገለጽ፣ የአስተምህሮ ስሕተትን በማካተት አሳትመው ያሰራጩት ግለሰብ በቋሚ ሲኖዶስ ተጠርተው እንዲጠየቁና የፈጸሙትን ስሕተት ዐውቀው ወደፊት ተመሳሳይ ስሕተት እንዳይፈጽሙ ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጣቸው፣
መጽሐፉ እንዲመረመር ያደረገው የደብረ ሊባኖስ አንድነት ገዳምና የገዳሙ የቅኔ መምህር መጋቤ ምሥጢር አባ ክንፈሚካኤል ወልደ ገብርኤል የምስጋና ደብዳቤ እንዲጻፍላቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
5.በሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳና አሪዞና ሀገረ ስብከት የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም መንፈሳዊ ኮሌጅና የአብነት ምስክር ጉባኤ ቤት ለማቋቋም በጠየቀው መሠረት እንዲፈቀድ ሆኖ የትምህርት አሰጣጥ ፖሊሲውና ሥርዓተ ትምህርቱ፣ የሰው ኃይል አደረጃጀቱና መዋቅራዊ ተጠሪነቱ ተዘጋጅቶ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተጠንቶ ከውሳኔ ሐሳብ ጋር ለግንቦት 2018 ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
6.በምዕራብና በመካከለኛው ካናዳ የሚገኙት ሁለቱ አህጉረ ስብከት ከአሁን በፊት በ2017 ዓ.ም. በተሰጠው ውሳኔ መሠረት ያለ ጣልቃ ገብነት በየራሳቸው እንዲተዳደሩና የኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የመካከለኛው ካናዳ ኤድመንተንና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሚል ሥያሜ እንዲስተካከል ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡
7.በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓል ለማክበር ሄደው አዲሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በመጐብኘት ላይ እያሉ አደጋ በደረሰባቸው ምዕመናን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተሰማውን ሐዘን እየገለጸ እግዚአብሔር አምላካች ላረፉት ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስ እንዲሰጥልን ከመጸለይ ጋር አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ለማሳከምና የተጎጂ ቤተሰቦችን ለመርዳት የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ ለወደፊቱም በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ በሚገነቡ ሕንጻ ግንባታዎች አደጋ ከመድረሱ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፤
8.በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ገዳማት ያሉት መነኰሳትና መነኰሳይያት ለአገልግሎትና ጉዳይ ለማስፈጸም ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ ክብራቸውና ገዳማዊ ሕይወታቸው ተጠብቆ ጉዳያቸውን እስከሚፈጽሙ ድረስ የገዳማት ኅብረቱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በኩል ማረፊያ የሚሆን ቦታ እንዲዘጋጅላቸው፣

❤3