Telegram Web Link
"መጽሐፈ ግንዘት" እና ˝የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅጽ ሁለት‌  መጻሕፍት የምረቃ መርሐ ግብር ተከናወነ።

ጥቅምት ፱ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ  ያስተረጎመውን "መጽሐፈ ግንዘት" እና  ˝የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ቅጽ ሁለት‌  መጻሕፍትን በትናትናው ዕለት ጥቅምት 8 ቀን 2018 ዓ.ም  በዋናው ማእከል ሕንጻ 3ተኛ ወለል ንቡረ እድ  ድሜጥሮስ አዳራሽ አስመርቋል።


በመርሐ ግብሩ ላይ ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ የሊቃውንት ጉባኤ አባልና  የአራቱ መጻሕፍት ጉባኤያት የትርጓሜ መምህር "መጽሐፈ ግንዘት" የተሰኘውን እንዲሁ። መምህር ቀሲስ ዐቢይ ሙሉቀን የሐመር መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ ˝የዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ቅጽ ሁለት‌"  በተመለከተ የመጽሐፍ ዳስሳ አድርገዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ በበኩላቸው ማኅበረ ቅዱሳን ከሚሠራቸው ሥራዎች መካከል መጽሐፍትን በማዘጋጀት ለምእመናን ተደራሽ ማድረግ ሲሆን በዚህም በርካታ መጽሐፍት ተጽፈው፣ ተተርጉመው፣ ታትመው ለአገልግሎት መዋላቸውን ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም መጻሕፍቱ እዚህ እንዲደርሱ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋናን አቅርበዋል።

በመጨረሻም መጽሐፍቱ በአባቶች የተመረቁ ሲሆን  መጻሕፍቱን በመተርጎም ኃላፊነታቸውን ለተወጡ አካላትም የምስክር ወረቀትና የስጦታ መርሐ ግብር ተከናውኗል።
12👍8
የ2018 ዓ.ም የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጸሎት ተጀመረ።

የጸሎት መርሐ ግብሩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተካሂዷል።
1🙏1
“ከአባቶቻችን ለልጆቻችን” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓም በቦናንዛ አዲስ ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገለጸ።

በመግለጫው የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔ ዓለም የ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት የ72 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

"በኦርቶዶክሳዊ ትውፊትና ትምህርት ዓለም አቀፍ በጎ ተጽዕኖበመፍጠር ትውልድ አሻጋሪ የልሕቀት ጉባኤ ቤት መሆን" የሚል ታላቅ ርዕይ ያለው ጉባኤ ቤቱ ይህ ርዕይ እውን እንዲሆን ዓለም አቀፍ መንፈሳዊ ትምህርት ማዕከል ግንባታ ለማጠናቀቅ አቅዷል።

የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔ ዓለም የ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት መምህር መምህረ መምህራን በጻሕ ዓለሙ ጥቅምት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ገቢ መሰብሰብ እንዳቀዱ ገልጸዋል።

በ1851 ዓ.ም በአጼ ቴዎድሮስ አማካኝነት በቅኔ እና መጻሕፍት ጉባኤው እንደተጀመረ ገልጸው በ2011 ዓ.ም አምስተኛ የወንበር መመህር ሁነው መመደባቸውን ተናግረዋል።
ከቦታዊ ታሪካውነት አንፃር እና ካሉ ነባራዊ ችግሮች ተነስተው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እንደቀረፁ ተናግረዋል።

የመጀመሪያው ፕሮጀክትም ከ300 በላይ የትርጓሜ ደቀ መዛሙርትን ማስተናገድ የሚችል መማሪያ፣ ቤተ መጻሕፍት እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ አዳራሾች ያሉት ሲሆን ግንባታው ተጀምሯል ብለዋል።

ሁለተኛ ፕሮጀክትም ይህ ዓለም አቀፍ የትምህርት ማዕከል ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሚመጡ ደቀመዛሙርት ነጻ የትምህርት እድል ይሰጣል፤ተማሪዎቹ ጥልቅ የሆነውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶቤተክርስቲያንን ትምህርትና ትውፊት ከምንጩ ቀስመውካጠናቀቁ በኋላ ወደየሀገራቸው ተመልሰውቤተክርስቲያንን በብቃት እንዲያገለግሉ ያግዛል፤ ከዚህ በፊት በአገር ውስጥ ከተለያዩ የዜማ ትምህርትቤቶች ተምረው ያስመሰከሩ ደቀመዛሙርት የወንጌልን ትምህርት በብቃትማስተማር እንዲችሉ ተጨማሪ የማብቂያ ትምህርት መስጠትና ሌሎች አገልግሎቶችን ይዟል።

በሦስተኛነትም ቋሚ የገቢ ምንጭ ማስገኛ ፕሮጀክቶች ናቸው።

21 የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ጉባኤ ቤቱ ተቀብሎ በማስተማር ለአገልግሎት ማሰማራቱን ገልጸዋል።

የደቀ መዛሙርቱ በተለያዩ ጊዜያት በምግብ እጦት እና አካባቢው ብርዳማ በመሆኑ መቋቋም እያቃታቸው በበሽታ እየተጠቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት ከ80 በላይ ደቀ መዛሙርት የሚገኙ ሲሆን ከ200 ሺህ በላይ ወርሃዊ ወጭ ቢኖርም ከምእመናን እርዳታ ውጭ ምንም ገቢ አለመኖሩን በመግለጽ ጉባኤ ቤቱ ላለበት ችግር እና ላቀዳቸው ዘላቂ ፕሮጀክቶችን እንዲደግፉ ለምእመናን ጥሪ አቅርበዋል።

በመግለጫው የተገኙት የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ስዩማን ቀሲስ ምኅረት ሞላ ደቡብ ጎንደር የድጓ ምስክር ቤት የሆነው ቅድስት ቤተልሔም፣ የዙር አምባ የዝማሬ መዋስዕት ምስክር ቤት፣ ቅዱስ ያሬድ ለ3 ዓመታት ጉባኤ ዘርግቶ ያስተማረበት፣ ከ300 በላይ መጽሐፍት የጻፉት መምህር ኤስድሮስ የነበሩበት ሀገረ ስብከት ነው ብለዋል። የዚህ ታሪክ አካል የሆነው የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔ ዓለም የ፬ቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤትም የቀደሙትን በመከተልና ታሪክ በማስቀጠል በስብከተ ወንጌል ከእግዚአብሔር ወቀሳ እንድንድን እየሠራ ያለ ነው። ተማሪዎቹ በመቃብር ቤት እስከመኖር በጤናም እጦት የሚያጋጥማቸውንም ችግር ተቋቁመው
እዚህ በመድረሳቸው ቋሚ ፕሮጀክቶች ለውጤት እንዲበቁ በሀገረ ስብከቱ ስም ጥሪ አቅርበዋል።

ጥቅምት 16 ቀን በግዮን ሆቴል በሚኖረው ገቢ አሰባሰብም ሊቃውንት እና ምእመናን እንደገኙ አደራ ብለዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን የኤድቶሪያል ቦርድ አባል መልአከ ታቦር ኃይለ ኢየሱስ ፋንታሁን በበኩላቸው የተገናኘነው በአንድ አጥቢያ ጉዳይ ሳይሆን ስለሦስት ነገር ነው ብለዋል። ይኸውም የቅባት እና ጸጋ ትምህርትን በጉባኤ የተረታበት ቦታ በመሆኑ ታሪክን ማዘክር፣ የድጓ መምህራን መፍለቂያ እንደመሆኑ ይህንን ትምህርት እና መምህራንን ማስቀጠል እና የሀገርን አንድነት መጠበቅ ነው።

በመግለጫው የተገኙት መምህር ያረጋል አበጋዝ ጉባኤ ቤቶች ሲጠነክሩ ቤተ ክርስቲያናችን ትጠነክራለች፤ እነሱ ላይ መሥራት የነገዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ መሥራት ነው። ሌሎች ለምን ሠሩ ከምንል ክፉን የሚያርሙ እና ዘመኑን ዋጅተው ምእመናንን የሚያስተምሩ መምህራንን ማዘጋጀት አለብን። መምህር በጻሕ ዓለሙ ይህንን ተረድተው ይህን እድል ስለሰጡን ለእኛ እድልም በረከትም ነው በማለት ምእመናን መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሊቀ ሊቃውንት ቀለመወርቅ ቢራራ በበኩላቸው ብዙ ሥራው የተሠራ በመሆኑ የቀረውን ለመጨረስ ምእመናን መትጋት እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል።፣
8
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

• ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
• ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣
• ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣
በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ ቅዱስ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፤
የጎደለብንን እየሞላ አገልግሎታችንን እያቃና ከዚህ ላደረሰን፣ ይህንን ዓመታዊና ሐዋርያዊ ጉባኤያችንን ለማካሄድም ለሰበሰበን ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ምስጋና እናቀርባለን፡፡
“ወእፌጽም ታሕጻጸ ሕማሙ ለክርስቶስ በሥጋየ በእንተ ሥጋሁ እንተ ይእቲ ቤተ ክርስቲያኑ፡- ስለ አካሉ ማለትም ስለ ቤተክርስቲያኑ ስል በሥጋዬ በክርስቶስ መከራ የጎደለውን እፈጽማለሁ” (ቈላ.፩÷፳፬)
ያለንበት ዓለም በሁሉም ነገር በጉድለቱ የሚታወቅ ነው፤ ጉድለት ባይኖርና ሁሉም የሞላለት ቢሆን ኖሮ ፍጥረት እርስ በርስ የሚተረማመስበት ሁኔታ አይኖርም ነበር ወይም አሁን ባለበት ደረጃ የከፋ አይሆንም ነበር፡፡
እግዚአብሔር ሁሉንም አሟልቶ መፍጠር ወይም መስጠት የሚችል ከሃሊ አምላክ ቢሆንም፣ እሱ ባወቀ ፍጥረትን ሁሉ ጉድለት ያለበት አድርጎ ፈጥሮታል፤ በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ጉድለቱን ለመሙላት በሚያደርገው ፍትጊያ እየተጋጨ እርስ በርስ ሲተረማመስ ማየቱ የተለመደ ነው፡፡ ምድራዊቷ ቤተ ክርስቲያንም በጐዶሎው ዓለም እስካለች ድረስ ከሚመጣው ፈተና አታመልጥም፤ ይህም በመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ ለቈላስይስ ሰዎች “የጎደለውን እፈጽማለሁ” በማለት ሲጽፍ እናስተውላለን፡፡
4🕊1
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የመጀመሪያ ቀን ውሎው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ ሰጠ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በሰጠው ዕለታዊ መግለጫ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜ የሚከናወነው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የጥቅምት ወር ምልዓተ ጉባዔውን ጥቅምት 11 ቀን በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመክፈቻ ጸሎት መጀመሩን አስታውሷል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትን በመወከል መግለጫውን የሰጡት መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ምልዓተ ጉባዔው ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን የመጀመሪያ ቀን ጉባዔውን ያከናወነ ሲሆን 16 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቁን ገልጸዋል።

በጠዋቱ ውሎ 7 ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አጀንዳ እንዲቀርጹ ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን እነዚህም ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፣ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ናቸው ፡፡ ኮሚቴው በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በሰብሳቢነት በብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ በአስረጂነት ተሰብስቧል።

ምልዓተ ጉባኤው በከሰዓቱ ውሎም ከ16ቱ አጀንዳዎች በ4ቱ ላይ ውሳኔ የሰጠ መስጠቱን ያስታወቀ ሲሆን እነዚህም ውሳኔዎች፦

1 ቅዱስነታቸው በጠዋቱ የመክፈቻ ጸሎት ያስተላለፉት መልዕክት በቀጣይ የሥራ መመሪያ አድርጎ ምልዓተ ጉባዔው አጽድቋል፡፡

2 ከጥቅምት 4-10 በነበረው የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ የነበሩ የቡድን ውይይቶች በቃለ ጉባኤ ቀርቦ ቃለ ጉባዔውን ምልዓተ ጉባዔው የ2018 ዓ.ም የሥራ መመሪያ አድርጎ አፅድቋል፡፡

3 ሀገራዊ ሰላምን አስመልክቶ ምልዓተ ጉባዔው በግንቦት ወር ተወያይቶ ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘ ኮሚቴ ያዋቀረ ሲሆን ኮሚቴው የተሰጠውን ኃላፊነት አጠንክሮ እንዲቀጥል ተወያይቶ አጽድቋል፡፡
7
2025/10/27 03:24:05
Back to Top
HTML Embed Code: