Telegram Web Link
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 3


ከቆረብኩ በኋላ በኃጢአት ብወድቅስ ብሎ ከቁርባን መሸሽ አያስፈልግም። ሐዋርያት እኮ ሐሙስ ምሽት ከቆረቡ በኋላ ነው አርብ ቀን ክርስቶስ ሲሰቀል ሁሉም በፍርሃት ክደውት የሄዱት።
ሰይጣን ከቁርባን እንድንርቅ የሚያመጣብንን እያንዳንዱን ሀሳብ መቃወም ያስፈልጋል !
32👍8🥰2
Forwarded from ታዚ (እንደ ልቤ)
ብዙ በጎችን የሚጠብቅ አንድ እረኛ ነበር። ታዲያ ከመንጋው ውስጥ አንድ በግ ሁልጊዜ ራቅ ብሎ፣ ተነጥሎ ይዞር ነበር። እረኛውም ይህንን በተደጋጋሚ ስለሚመለከት የበጉ እጣ ፈንታ አሳሰበው፣ በተኩላዎች እንዳይበላበት ተጨነቀ። ስለዚህ እያዘነ በራሱ እጆች የበጉን እግሮች ሰበራቸው። በመጀመሪያ ህመሙ ስለጠናበት በጉ እጅግ ተሰቃየ፣ አዘነም። ስለምን እረኛው በርሱ ላይ ይህንን እንዳደረገበት አላወቀምና።

ታዲያ እረኛው በጉን ተሸክሞት በሄደበት ሁሉ ይዞት ይዞር ነበር። በራሱ እጆች እያበላው፤ በፍቅር እየተንከባከበው  ከስሩ መዋልን አለመደው። በጉም ከእረኛው ስር መዋል ሲጀምር ፍቅርና እንክብካቤውን አስተዋለ።ከዚያ በኋላ ግን እግሩ ከዳነም በኋላ  ከእረኛው ስር መዋሉን መረጠ፣ እረኛው እንደሚወደውና እንደሚጠብቀው ስለተረዳ አመነው።

ወደራሱ ሊያቀርበን ሲፈልግና ከጎኑ እንዳያጣን ሲሻ አንዳንድ ጊዜ እግዚዓብሔር መሰበራችንን ይፈቅዳል። በፍቅሩ፣ በታማኝነቱና በቸርነቱ አብረነው እንድንኖርለት ሲፈልግ ልክ እንደ ሳምሶን ለህመምና ስቃይ አሳልፎ ሰጥቶ ወደራሱ ይመልሰናል።

በእግዚዓብሔር እጅ መውደቅ በዚች ዓለም ሀብትና ዝና ከሚገኘው ተድላ እጅግ ብዙ ይልቃል።

For comment inbox me @umbeya
በኃይሉ(ታዚ)
60🔥1🥰1
‎ ምንም ባንዛመድ በደም እና ስጋ
‎ ብንኖር ለየቅል እዚጋና እዛጋ
‎ ከተዋደደ ልብ ከተቀራረበ
‎     አንድ ሆኖ ካሰበ
‎ ወንድም እና ወንድም
‎   እህት እና እህት
‎ ወንድም እና እህት
‎             ለመሆን ከበቃ
‎ መወለድ ቋንቋ ነው
‎             እህቴ ነሽ በቃ።

🥰🥰🥰
46👍15
ቀረቤታችን በልክ ይሁን
መልካም ቀን🖐️
24👍3
የማርያም ንግስ ዕለት

(ኤፍሬም ስዩም)

የማርያም ንግስ ዕለት...
አዳፋ ነጠላ
የቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ...
ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፣ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች...
ከቤተስኪያን አጸድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ሚስኪን ባልቴት ...ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም ፣ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ፣ ጀርባዬ ተራቁቷል፡፡
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ፣ ትለምናት ነበር
ከቤተስኪያን ጎሮ ፣ ቆማ ከዋርካው ስር፡፡
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ፣ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ፣ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምእመን ፣ ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል

የመቅደሱ ቀለም ፣ ሊታደስ ይገባል
የካህናት ደሞዝ ፣ ሊጨመር ግድ ይላል
ደጀሰላም ወንበር ፣ እጅጉን ያንሰናል
እናም...
ከዚህ ታላቅ ደብር ፣ ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን ፣ እጃችሁ የታለ? እያለ፡፡
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል፡፡
ለንግሱ የመጡ
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች...
ጥለት የለበሱ ፣ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ ...እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ ፣ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሰላሙ ፣ ደሞም ለወንበሩ
በሺ...የሚቆጠሩ
ብሮች ወረወሩ"
የደብሩ አለቃ ፣ ግንባር በጣም ወዛ
የሚወረወረው ፣ ብሩም በጣም በዛ፡፡
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካው ስር
ተስፋዋ ማርያምን ፣ ትለማመን ነበር
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም ፣ መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ፣ ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ፣ ጀርባዬን በርዶታል

አንቺ ነሽ 'ተስፋዬ' ፣ የኔ 'ተስፋ 'ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እንባ እያፈሰሰች፡፡
ግና -ግን ለዛሬ ፣ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ፣ ውሰጂ እንባዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ ፣ የአንገት ሀብሌን

መልካም ቀን
60👍10🔥2
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 4

እግዚአብሔር ስጠኝ ሚሉት ብዙ ልጆች አሉት የናፈቀው ልስጥህ ሚለው ነው።

እግዚአብሔር ብዙ ተገኝልኝ የሚሉት አሉ የናፈቀው ልገኝልህ የሚሉት ናቸው። 
15👍1
የዕለቱ መልዕክት ቁጥር 5


"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
21👍7
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
[13/12 07:56] Sedal Sedal: አሜን አሜን አሜን
[13/12 07:57] Sedal Sedal: ምስጋናነው ስራዬ በዘመኔ በእድሜዬ
ለዋ

Downloaded by: @VKmusicTopbot
1👏1
ይኸው ነጋ ጎህ ቀደደ🙏
አዲሱ ቀን ተወለደ😊
መኖር ቻልን በእርሱ ፈቃድ
እናመስግን በትህትና ትተን ልማድ

ያለ ዋጋ እንዲው ቻለን
ሳንከፍል ዛሬን አየን
ስንቶች ሽተው ያልቻሉትን
ቸርነቱን አብዝቶልን
ዛሬን በቃን ለምስጋና
አሳደሮን በአማን ደህና

ታዲያ ሰቶን አዲሱን ቀን እንደምንስ እናበላሽ?????🤨
ስለምንስ እናሳዝን በሀጢያት ወድቀን
ለእርሱ ምላሽ?????😔
መልካም ማድረግ ምን ባንችል ደግ ደጉን ባንሰራ
ከክፉነት እንታቀብ ጨለማነትን አንዝራ

መልካም ዕለተ ሰኞ
17👍2👏1
------- ቀን --------

ቀን ቀንን አርግዞ
ቀን እየወለደ፣
አንድ ቀን ሌላን ቀን
አልፎት እየሄደ፤

በቀናት መካከል
ቀናት ተደራርቦ፣
የቀናት ክምችት
የቀናት ርብራቦ፤

ቀናቶች ስንቆጥር
ቀናት ስንመነዝር፣
ቀናት ስንዘራዝር
ቀናቶች ስንገብር፤

ቀኖች እያሰብን
ዝክር ስናዋጣ፣
ቀንን ሳንጠቀም
ምፅአት ቀን መጣ።
39
ቦግ.....እልም
.
.
ጭላንጭል ብርሃን በጽልመት ተከባ፤
ቦግ...እልም ስትል ስትወጣ ስትገባ፤
አለች እንዳይሏት በርታ ትጠፋለች፤
ከሰመችም ሲሏት ከሩቅ ትታያለች፤

ቦግ.......እልም፤
ጭልም......ጭልምልም፤
ብልጭ.....ድርግም፤

የኔም ህይወት እንዲሁ......

አይሆንላት ተሸነፈች፤
አይሳካም ተሰበረች፤

አበቃላት ወድቃ ቀረች፤
ብለዉ ሲናገሩኝ..........

የሩቋ ወጋገን ጎልታ 'ምትታየኝ፤
በተነሳሁ ቁጥር ወደኔ 'ምትቀርበኝ፤
ጠፍታ የማትጠፋዉ ያቺ ብርሃን ነኝ።
..............................
በዔደን ታደሰ
36🥰5
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን ! †



💒 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን የጠበቁ፦
•➢ የተለያዩ ትምህርቶች የሚሠጡበት፤ መዝሙሮች እና ግጥሞች የሚለቀቁበት፤
•➢ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎችን የምናገኝበት ግሩፕ ነው። እናንተም ኦርቶዶክሳውያን ቤተሰቦችን በማስገባት ኃላፊነትዎን ይወጡ።

ለተዋሕዶ ልጆች በመላክ ኃላፊነታችንን እንወጣ!

https://www.tg-me.com/rebunimedia21
2
Forwarded from Semahegn Demeke
ሀበነ እግዚኦ አዕይንተ አእምሮ ወትረ ኪያከ ይርአያ: ወአዕዛንነሂ ቃለ ዘባሕቲትከ ይስምዓ

አቤቱ አንተን ብቻ ያዩ ዘንድ የዕውቀት ዓይኖችን
ያንተንም ብቻ የሚሰሙ ጆሮዎችን ስጠን🙏


ዛሬ ተርኅዎተ ሰማይ ነው🤗። (የሰማይ መከፈት) ውዝፍ የዓመት ጸሎትዎን ያሳርጉ🙏

እንኳን አደረሰዎ ወዳጄ💙
4
መስከረም አቅጄ ••••
                                  በሞራል ሞልቼ
ጥቅምትን አስቤ••••
                                   ለመስራት ወጥቼ
ህዳር ላይ ደርሼ••••
                                   ልሰራ አሰብኩና
ታህሳሰን መረጥኩኝ••••
                                    መንገዴን ላቀና
ጥምቀት ደርሷል ብዬ••••
                                     ጥርን ትቼ አለፍኩ
የካቲት ልዘጋጅ ••••
                                ብዬ ራሴን ሸወድኩ
መጋቢት ፀሀዩ••••
                              ከብዷል ልሻገር
ሚያዚያ ደረሰ••••
                             ፋሲካን ላክብር
ግንቦት ደብሮኛል ••••
                                 ቆይ ትንሽ ልፍታታ
ሰኔ ዘነበብኝ ••••
                          ልጠለል ለአንዳፍታ
ሐምሌ ጎርፉን ፈራው ••••
                                ተኝቼ ሰነበትኩ
በባከነ መንፈስ ••••
                               ነሀሴንም ጨረስኩ
                               •
                               •
                               •
                               •
                               •
ሆኗል የኔስ ኑሮ እንዲያው የእንጉርጉሮ
ተግባር ያጣ ህይወት የቀረ ከአዕምሮ


ብሩክ ተፈራ
87👏16👍7🥰4
አንዱ ለአገሩ ፤
አንዱ ለ'ርስቱ ፤

አንዱ ለልጁ ፤
አንዱ ለሚስቱ ፤

ጥይት ወልውሎ ፤ ጎራዴ ስሎ ፤
በዱር በገደል ይከታከታል ፤

ሲሻው ይገድላል ፤ ሲሻው ይሞታል ።

እኔ ግን ወዲህ . . .

ወይ አገር የለኝ ፤
ወይ ርስት የለኝ ፤
ወይ ልጅ አልወለድኩ ፤ ሚስት አላደለኝ ፤

ጎራዴ ሳልስል ፤ ጥይት ሳልገዛ ፤ በተኛሁበት ሀሳብ ገደለኝ ።

By Tewodros kassa
12👎3👍2
ከሞትኩኝ ቆይቷል ብዙ ዘመን ሆኗል
መቅደሱ ገላዬ
ተስፋ ገለባዬ ራሱን በትኗል፡፡
ቆይቷል ከሞትኩኝ ከሀቀኛ ሳቅ

ህይወት አይታዘዝ እንደይስሀቅ፡፡
አይለየኝም ዛሬ ከነገዬ
ያልተፈሰከ ጾም ህይወት መዲናዬ
መኖር እዳዬ
መሄድም መቆምም እኩል ነው ሚያዝለኝ ድፍረት ካልሆነብኝ ጌትዬ እዘለኝ፡፡
አንተ ትከሻ ላይ ሁሉ ቀሏል አሉ ስሰማ በዝና
መስቀልህን ስጠኝ ህይወቴን ያዝና፡፡
የመስቀልን ክብደት
ከገዛ ሕይወቴ ለክቼ ባላውቅም መኖር ግን ያዝላል ከቄሳር ፍርድ አቅም፡፡
ትንሽ... ካንተ የምለየው
የተሰቀሉኩበት እንጨት ስላላየው....
እንሽ... ካንተ የምለየው
ከድቶ የሳመኝን ወዳጅ ስላላየው...
እንጂ ከሞትኩኝ ቆይቷል...
ናፈቀኝ የምለው
ባገኘው የምለው
በል ስጠኝ የምለው
አሁን ካለሁኝ ነው፡፡
እኔ ግን የለውም...
ጌታዬ... በሚጸልይ አታስቀናኝ
እንዴት ይብለጠኝ መናኝ፡፡
የምለየው ካንተ አርገኸኝ የሰው ዘር
ቆጥሬው አያልቅም...
ስንት ግርፊያ እንደሆን መኖር ሲመነዘር !
ከሞትኩኝ ቆይቷል
ቆይቷል ከሞትኩኝ
አለ ለመባል ነው እዚህ ጋር የቆምኩኝ

✍️ኤልያስ ሽታሁን
23👍2
Forwarded from ዘ ተዋህዶ (𝕻𝖎𝖑𝖚𝕻ΔDΣR)
Old Group

2023የተከፈተ - 500 ብር
ከ 2018 እስከ 2022 የተከፈተ- 900 ብር

ያላችሁ አምጡ 👉 @pilu_pilu_p

2024 - January February March የተከፈተ ካለም አምጡ

Frist ብርር ላክ ምናምን የምትሉ አትምጡ አልገዛቹ


ልታደክሙ አትምጡ ለስራ ይምጡ 🙄

Old group መሸጥ የምትፈልጉ ተቀላልቀሉ

https://www.tg-me.com/pilu_oldgroup_trader
3
ደገኛ ባልሆንም \ትሁት ሰው አክባሪ
ቅን ታዛዥ መልከኛ \ለሰው ተቆርቋሪ
ጨዋነት የሌለኝ \ምግባሬ የጠለሸ
ሰውን የማስቀይም\ አፌ የተበላሸ
ባልሆንም ሀቀኛ\ ለቃሌ  ታማኝ
ውሸታም ሀሜታም \ውዳቂ የሆንኩኝ
ከጭካኔ ብዛት \የጠላኝ ህዝብ ሁሉ
የጎደፍኩ ያዳረስኩ  \ሀጥያትን በሙሉ
ብሆንም አስታውሱ \አለኝ ግን ህሊና
አምላክ አይጠላኝም \ሰው አይደለምና
እርሱ ቢጠላኝስ ••••ለምን አላጠፋኝ???
መመለሴን ሽቶ ••••ዳግም ዕድል ሰጠኝ

ብዬ የተረዳሁ ዕለት .....

ኮቴውን ተከተልኩ ፈለኩት አምላኬን
እርሱን መፈለግ ውስጥ አገኘሁት እራሴን


ብሩክ ተፈራ
30🥰10
የቅዱሳን ምልጃ

እግዚአብሔርን ፤ አስቀይመነው
ሳንፈራ ንቀነው ፤ ሳንሳቀቅ አፍረነው።
እጅግ የሚያስመካ ፤ በጣም የሚያኮራ
በፊቱ የሚያቆም ፤ ጀብዱ እንደ ሰራ።
ዓይኑን ለማየት ፤ ሳንሸማቀቅ
ብቻዬን እችላለሁ ፤ ከእርሱ ጋር መታረቅ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ።

በበደላችንስ ፤ ማፈር እንኳን ቢቀር
ከእርሱ ባልንጀራው ፤ እንደ ሚሻል ይቁጠር።
ብሎ አስተምሮን ፤ ጌታችን ትህትና
በራሳችን ትምክህት ፤ በትእቢት ልቦና።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።

እኔን በቀጥታ ፤ ቆመህ አትለምነኝ
ይቅርታ አድርጌልህ ፤ ምህረት እንድታገኝ።
ወደ አብርሃም ሄደህ ፤ ጸልይልኝ በለው
ጌታ ለአቤሜሌክ ፤ እየሰማን ሲለው።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።

እኛ የጠየቅነው ፤ ይጉዳንስ ይጥቀመን
ለይተን የማናውቅ ፤ ድኩማኖች ሆነን።
ጊዜያዊውን ሳይሆን ፤ ዘላለማዊውን
ፍቃዱን የሚያውቁ ፤ ለኛ እሚበጀውን።
ለገዛ ነብሳቸው ፤ ቅንጣትም ሳይራሩ
እኔን አጥፋኝ ብለው ፤ እኛን የሚያስምሩ
እንደ ሙሴ አይነት ፤ ደጋጎች ሲኖሩ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።

የቅዱሳን ምልጃ ፤ በመቃብር ድንኳን
በሞት ይወሰናል ፤ ደፍረን ብንል እንኳን።
የህያዋን መላእክት ፤ ልመናና ምልጃ
መቼ ይጋረዳል ፤ በሞት መጋረጃ።
የኤልያስን ፀሎት ፤ የሚከለክለው
የሄኖክን ምልጃ ፤ የለም የሚያስቆመው ።
የሚያምንብኝ አለው ፤ የዘላለም ዋጋ
ሕያው ነው እያለን ፤ ቢሞትም በሥጋ ።
ዓይነ ህሊናችን ፤ የፃድቃኑን ጸጋ
ቢታወር ነው እንጂ ፤ እንዳያይ ቢዘጋ።
ያማልዳሉ ካልን ፤ በአለም ሲኖሩ
ዳግም በሰማያት ፤ ከጸጋ ባህሩ
ከጌታ ጋር ሆነው ፤ ይበልጡን ሲከብሩ።
የቅዱሳን ምልጃ ፤ አያሻኝም ለኔ
እንደ ማለት ያለ ፤ ምን አለ ኩነኔ ።

https://www.tg-me.com/menfesawigetem
https://www.tg-me.com/menfesawigetem
https://www.tg-me.com/menfesawigetem
18👍6
2025/10/21 23:04:41
Back to Top
HTML Embed Code: