ጅማ ማእከል ፴፫ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በተገኙበት እያካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ።
ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን የጅማ ማእከል ከማኅበረ ቅዱሳን ምሥረታ ጀምሮ የነበረ ማእከል መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከሐምሌ 11 - 13 ቀን 2017 ዓ.ም 33ኛ የማእከሉን ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በጉባኤው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ የክፍል ኃላፊዎች፣ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ት/ቤት አንድነት ተወካዮች፣ የሰበካ ጉባኤና የመንፈሳዊ ማኅበራት ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በመርሐ ግብሩ የማእከሉ የ2017 ዓ.ም ሥልታዊ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የፋይናንስ አገልግሎትና የኦዲት አገልግሎት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በዋናው ማእከል ልዑክ ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳን መልእክትና ሪፖርት ቀርቧል።
በጉባኤው የጅማ፣ የየም፣ የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል።

❤48🥰3🙏3
አሜሪካ ማእከል የምሥራቅ ማስተባበሪያ 2ኛውን ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ !!!
በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ለአገልግሎት ቅልጥፍና እና አመችነት ሲባል በሶስት ማስተባበሪያ ከተዋቀረ በኋላ ማስተባበሪያዎቹ በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ::
የምእራብ ማስተባበሪያ ባለፈው ሳምንት ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ የምሥራቅ ማስተባበሪያ ተረኛው ጠቅላላ ጉባኤ አካሄጅ ሆኗል :: በቀጣይ ሳምንት ደግሞ የመካከለኛው ማስተባበሪያ በሚኒሶታ ያካሂዳል ::
ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የምሥራቅ ማስተባበሪያ ጠቅላላ ጉባኤ በርካታ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል ተብሎ ይጠበቃል :: በልጆች አያያዝ እና አስተዳደግ : ቴክኖሎጅ ለቤተክርስቲያን የሚሉ እና ሌሎች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች በጉባኤው ይዳሰሳሉ :: የባለፈው ዓመት ክንውን ሪፖርት እና የቀጣይ ዓመት እቅድ በጉባኤው ሰፊ ጊዜ ከተመደበላቸው ፕሮግራሞች መካከል ተጠቃሾች ናቸው :: ቃለ እግዚእብሔር : ውይይት እና መዝሙርም የጉባኤው አካል ናቸው ::
በምሥራቅ ማስተባበሪያ ሥር የሚገኙ 4 ንዑሳን ማእከላትና 4 ግንኙነት ጣቢያዎች በጉባኤው ተሳታፊ ይሆናሉ ::
ጉባኤው በ4 ደረጃዎች የተከፈለ ሲሆን የሕጻናት የታዳጊዎች ና የወጣቶች ጉባኤም ጎን ለጎን የሚካሄዱ ይሆናል ::
መክፈቻውን በጸሎተ ወንጌል በሜሪላንድ ኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ያደረገው 2ኛው ዙር የምሥራቅ ማስተባበሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ና እሑድ በባልቲሞር ከተማ በመካነ ሰላም ኢየሱስ ቤተክርስቲያን አዳራሽ ቀጥሎ ይውላል ::
ዘገባው የአሜሪካ ማእከል ሚዲያ ክፍል ነው

❤27🙏3👏2