Telegram Web Link
ደብረ ብርሃን ማእከል 27ኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ እንደሚገኝ አስታወቀ

ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯  ዓ/ም

ማኅበረ ቅዱሳን ደብረ ብርሃን ማእከል ለሁለት ቀናት የሚቆይ የ2017 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤውን የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መጋቢ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ፣ የዳግማዊ ጎልጎታ ደ/ከርቤ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም አበምኔት ፣ የደ/ሰላም ጠባሴ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የአራቱ ጉባኤ መምህር መራኄ ሊቃውንት ያዕቆብ ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ፣ የዋናው ማእከል ልዑካን ፣ የወረዳ ማእከላት ልዑካን ፣ የማእከሉ የሥራ አስፈጻሚ አባላት እና የማእከሉ አባላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው በጸሎት ወንጌል የተከፈተ ሲሆን የማእከሉ መደበኛ መምህር ሊቀ ሊቃውንት ይባቤ አበራ "እኔም_እሠራለሁ"  በሚል ኃይለቃል ትምህርት አስተምረዋል።

በመርሐ ግብሩ  የማእከሉ የበገና መዘምራን በበገና ዝማሬ እግዚአብሔርን ያመሰገኑ ሲሆን የማእከሉ ሰብሳቢ ዲ/ን አድማሱ አበራ የእንኳን ደኅና መጣችሁ እና አጭር የሥራ ሪፖርት አቅርበው፣ የዋናው ማእከል ልዑክ ዲ/ን አንድነት የማኅበረ ቅዱሳንን መልእክት እና ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት አቅርበዋል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት መጋቢ ሐዲስ ነቅዐጥበብ አባቡ ይህ ጉባኤ ታላቅ ጉባኤ እንደ መሆኑ ማኅበሩ አሁን ከሚሠራው ተግባራት በተጨማሪ ወደፊት ወጣቱ ላይ እና ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት አለበት የሚል መልእክትና የሀገረ ስብከቱን መመሪያ አስተላልፈዋል።
40🙏5👍4
በደሌ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ እንደሚገኝ ተጠቆመ

ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን የበደሌ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

በመርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ የሀገረ ስብከቱና የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣የየወረዳ ቤተ ክህነት ሊቃነ ካህናት፣ የሰ/ት/ቤት እና  የማኅበራት ተወካዮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
35👏3🙏3
አዳማ ማእከል 27ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያከናወነ እንደሚገኝ ገለጸ

ሐምሌ ፲፪/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን አዳማ ማእከል የ2017 ዓ.ም የአገልግሎት ዘመን የሚገመግምበትና  የ2018 ዓ.ም የአገልግሎት አቅጣጫ የሚያስቀምጥበት ዓመታዊ ጉባኤውን በመ/ሸዋ ሀገረ ስብከት አዳራሽ እያከናወነ እንደሚገኝ ማእከሉ ገልጿል።

ሁለተኛውን ቀን የያዘው ጠቅላላ ጉባኤው  የም/ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሳህል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ፤የም/ሸዋ ሀ/ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ  መ/ጥ/ቀ/ጌቱ ሞቲ፣ የም/ሸዋ ሀ/ስብከት የመምሪያ ኃላፊዎች፤ የገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤ የአዳማ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ተወካዮች፤የተለያዩ የማኅበራትና ሰ/ት/ቤቶች ተወካዮች፣የወረዳ ማእከላት ፣ ግቢ ጉባኤያት ተወካዮች፣ ማእከሉ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።

በደ/ና/ኢየሱስ ቤ/ክ ካህናት አባቶች ጸሎተ ወንጌል  የተጀመረው የጠዋት መርሐ ግብር  ትምህርተ ወንጌል በደ/ፀ/ቅ/ማርያም ካቴድራል አስተዳዳሪ  መ/ሰ/ቆሞስ አባ ማርቆስ ብርሃኑ  ተሰጥቶ የማእከሉ የ2017 ዓ.ም የአገልግሎት አፈፃፀም ሪፖርት ፣የኦዲት እና ኢንስፔክሽን ሪፖርት፤የውጭ ኦዲት ሪፖርት  ቀርቧል።

በመጨረሻም የም/ሸዋ ሀ/ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሳህል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል።

የማእከሉ ጠቅላላ ጉባኤ እስከ ነገ ሐምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል።
  
28🙏4
2025/09/16 19:49:38
Back to Top
HTML Embed Code: