Telegram Web Link
የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፴፭ኛ ዓመት መታሰቢያ መርሐ ግብር ተካሄደ

ሐምሌ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፴፭ኛ ዓመት መታሰቢያ መርሐ ግብር በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 11:00 ሰዓት በማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ንቡረ እድ ዲሜጥሮስ አዳራሽ የማኅበሩ ነባር እና አዳዲስ አባላት በተገኙበት ተካሄዷል።

የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት መምህር ዋሲሁን በላይ በመርሐ ግብሩ ላይ  መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን ታሪክ ባለፉት 35 ዓመታት ብፁዕነታቸውን ጨምሮ ሌሎች አባቶችም ሲዘከሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በየአምስት ዓመቱ የአቡነ ጎርጎርዮስን መታሰቢያ እንደሚደረግ የገለጹት   ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለማኅበሩ መመሥረትና እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ትልቁን ድርሻ ከተወጡ አባቶች  መካከል ቀዳሚው አባታችን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ናቸው በማለት ተናግረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ብፁዕነታቸው ከነበራቸው ርእይ መካከል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማረውን ትውልድ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማሰለፍ በከፊል በማኅበረ ቅዱሳን መሳካቱን ገልጸው በ467 ግቢ ጉባኤያት ውስጥላ ከ210 ሺህ  ተማሪዎች በላይ ስለ መንፈሳዊ ሕይወት እና ስለ ቤተክርስቲያን አገልግሎት እየተማሩ ይገኛሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ማኅበሩ በ24 ከተሞች ላይ በብፁዕነታችው ስም ባቋቋማቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከ35ሺህ በላይ ተማሪዎች በሥነ ምግባር ታንጸው ቤተ ክርስቲያን እና አገር ተረካቢ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል።
36🙏8
በመርሐ ግብሩ  ላይ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም  ብፁዕነታቸው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር የነበራቸው ግንኙነት ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን አቡነ ጎርጎርዮስ ትውልዱን በመቅረፅ ወደ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ለማሰማራት የጣሉት መሠረትና የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ዜና ሕይወቱ ለብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ  በሚል ርእስ ተጨማሪ ጽሑፍ  ያቀረቡት ቀሲስ ሰሎሞን ወንድሙ  በበኩላቸው ብፁዕነታቸው መምህር፣ ሕጻናት አሳዳጊ፣ የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ከቅዱስ ሲኖዶስ ተቀብለው በኃላፊነት የሠሩ፣ሥርዓተ ትምህርት ይቀርጹ የነበሩ አባት መሆናቸውን ከሠሯቸው ሥራዎች መካከል የጠቀሱ ሲሆን በአጠቃላይ"ቤተ ክርስቲያን ሰው በሚያስፈልጋት ዘመን አባት ሆነው የተገኙ ናቸው።" በማለት ተናግረዋል።

👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
43🙏6👍3
በሁለንተናዊ አቅሙ የዳበረ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ  ተገለጸ

ሐምሌ ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሥልታዊ ዕቅዱ ትኩረት አድርጎ ከሚሠራባቸው አገልግሎቶች መካከል መንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት በመስጠት ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን የሚያጠናክሩ  ካህናትና ባለሙያዎችን አሠልጥኖ ማሰማራት አንዱ ሲሆን በዚህ  ከጌዲዮ፣ ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ለተውጣጡ በቁጥር 24 ለሚሆኑ ካህናት፣መምህራንና የዘርፉ ባለሙያዎች በዲላ  ዋለሜ ደብረ ሰላም ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ሥልጠና መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

በሥልጠናው   ለምክክር አገልግሎት የሚረዱ ክብረ ክህነትና አበ ነፍስ፣ መንፈሳዊ የምክክር አገልግሎት አሰጣጥ፣ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻና የልጆች አስተዳደግ፣ ሱስና መሰል ተግዳሮቶች እንዲሁም ምጣኔ  ሐብትና  ማኅበራዊ  ዕድገት ጉዳዮች ተዳሰውበታል፡፡

በመርሐ ግብሩ  የተገኙት የጌዲዮ፣ኮሬና ቡርጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገሪማ ባስተላለፉት መልእክት ካህናትና ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች ኦርቶዶክሳዊ የመሪነት ጥበብን ከራሳቸው ቤተሰብ በመጀመር ለምእመናን አርአያ መሆን ይገባቸዋል ያሉ ሲሆን አክለውም አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የሉላዊነት አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም ከዘመኑ ጋር በመራመድ በሁለንተናዊ አቅሙ የዳበረ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መገንባት ላይ ማተኮር እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

በሥልጠናው ጥሩ ግንዛቤና ልምድ እንዳገኙበት የገለጹት ተሳታፊዎቹ  ወደ መጡበት አካባቢ ሲመለሱ ምእመናን ያለባቸውን ዘርፈ ብዙ ማኅበራዊ ቀውስ  እንዲቋቋሙ  ለማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡
23👍4🙏3
ማኅበረ ቅዱሳን  ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብን ለማጠናከር  የአመካካሪዎች ሥልጠና እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ሥልጠናው ባልተዳረሰባቸው አካባቢዎች ለመስጠት እንዲቻል ምእመናን የተለመደ ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪውን ያቀርባል፡፡


ይህን የሥልጠና መርሐ ግብር በገንዘብ መደገፍ ለምትፈልጉም፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 መጠቀም  የምትችሉ  መሆኑን እንገልጻለን።

👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://www.tg-me.com/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
            :- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
43🙏4
ማስታወቂያ

እሑድ ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ሊደረግ የነበረው መደበኛው የማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ወርኃዊ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች አማካኝነት የማይደረግ መሆኑን እየገለጽን በቀጣይ የሚከናወንበትን ቀን እናሳውቃለን።
69👍18🙏14🤔7
57 የደረጃ ሁለት የአፋን ኦሮሞ ተተኪ መምህራን መመረቃቸው ተገለጸ

ሐምሌ ፳፭/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን ከሚያስተምራቸው ከአገር ውስጥ ግቢ ጉባኤያት የተውጣጡ በመሐል ማእከላት አስተባባሪነት በአዳማ አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ሲሠለጥኑ የቆዩ 57 የደረጃ ሁለት የአፋን ኦሮሞ ተተኪ መምህራን በአዳማ (ናዝሬት) ደብረ አሚን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አስመርቋል።

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ምክትል ሥራ አስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ጌቱ በንግግራቸው ማኅበረ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባልደረሰችባቸው የተለያዩ ቦታዎች እና በግቢ ጉባኤያት እየሠጠ ባለው አገልግሎት አመስግነዋል፡፡

ምክትል ሥራ አስኪያጁ በገለጻቸው የሠለጠኑት አዳዲስ መምህራን ባለው የአገልግሎት ክፍተት በተለይ በቋንቋ ለትውልዱ በማዳረስ ረገድ ቅድሚያ ሰጥተው በመሥራት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ  እንዲወጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ መጋቤ ጥበባት ጌቱን ጨምሮ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ተወካዮች፣የዋና ማእከል ተወካዮች፣የአዳማ ማእከል ሥራ አስፈጻሚና አባላት፣የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋዮች እና ምእመናን ተገኝተዋል።
🙏4038👍12🥰1
2025/09/15 18:22:55
Back to Top
HTML Embed Code: