Telegram Web Link
እግዚአብሔርን ማሰብ ማለት ህጉንና ትእዛዙን በቤት ሲቀመጡ፣ በመንገድ ሲሄዱ፣ ሲተኙና ሲነሱም መጫወት ማለት ነው፡፡ ዘዳ 6፡4-9 በተጨማሪም ቃሉን በልቦና መያዝና በፍጹም ነፍስ እግዚአብሔርን መውደድ ማለት ነው፡፡ በዚህ መልኩ ፈጣሪን ማሰብ ይገባል፡፡ ለምን ቢባል? ነብዩ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔርን የሚረሱ ይጠፋሉ፡፡›› ብሏልና፡፡

ፈጣሪን ማሰብ ማለት ‹‹ሕጉን በቀንና በሌሊት ያስባል›› በማለት ቅዱስ ዳዊት እንደ ተናገረው የእግዚአብሄርን ህግ በደስታ ማሰብ ማለት ነው፡፡ መዝ1፡2 ተግባር የተለየው ማሰብ ብቻውን ምግባር የተለየው እምነት ሆነ ማለት ነው፡፡ ምግባር የተለየው እምነት ደግሞ ነፍስ እንደተለየው ስጋ የሞተ መሆኑ በግልጽ ተነግሯል ያዕ 1፡26

እግዚአብሔርን ማሰብ ማለት በሥራ በሚገለጥ ነገር እግዚአብሔርን ማክበር ማለት ነውእንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን አስበዋለሁ ማለት በሥራ ካልተገለጠ ምንም አይጠቅምም፡፡ ሚስት ለባሏ ‹‹ሁል ጊዜ አስብሃለሁ እናፍቅሃለሁ ከራሴ አብልጬ እወድሃለሁ›› ብትለው ነገር ግን ባሏ ከሚወደው ነገር አንዱንም ባትሰራ ‹‹እወድሃለሁ›› ማለቷ ብቻ ባሏን ሊያስደስተው ይችላልን? ፈጣሪንም ብዙ ትእዛዙን ወደ ኋላ ጥሎ ‹‹አስብሃለሁ›› ማለት ብቻ ምንም አያስደስተውም፡፡

ሩቅ ሀገር ያለ ወዳጃችንን በደስታው ጊዜ እንኳን ደስ ያለህ በሀዘኑ ጊዜ ደግሞ እግዚአብሔር ያበርታህ ለማለት ካልጣርን በሚያስፈልገውም ሁሉ የማንረዳው ከሆነ ‹‹ሁል ጊዜ አስብሃለሁ›› ማለት ብቻ ይጠቅመዋል፡፡ በዚህ መል መራራቅ የሞት ያህል ነውና ያረሳሳል፡፡ ፍቅርንም ያጠፋል እንጂ መተሳሳብም አይባልም፡፡ ፈጣሪንም ቢሆን ጠዋት ማታ ካልፀለዩ ካላመሰገኑት፣ ሕጉን ካላከበሩ ‹‹አስብሃለው›› ቢሉት ጨርሶ በዚህ አይደሰትም፡፡

የያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ የጠጅ አሳላፊዎችን አለቃ ‹‹ነገር ግን በጎ በተደረገልህ ጊዜ እኔን አስበኝ›› ሲል ምን ማለቱ ነበር ‹‹ምህረትን አድርግልኝ የእኔንም ነገር ለፈርኦን ነግረህ ከዚህ ቤት አውጣኝ›› በማለት በግፍ ከተጣለበት ወኅኒ ቤት እንዲያስወጣው መናገሩ አልነበረም ዘፍ40፡14 ስለዚህ ‹‹በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› ማለትም አንድ ተገቢ ነገር ሥራ ማለት ነው እንጂ በሕሊና ፈጣሪህን አሰላስለው ማለት ብጫ እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡

ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቀኝ ተሰቅሎ የነበረው ሸፍታ ‹‹አቤቱ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ›› ሲል ምን ማለቱ ነበር ጌታ የማያውቀው ሆኖ ራሱን ማስተዋወቁ ነበርን ወይስ ፈጣሪ በመጣ ጊዜ ‹‹አስበኝ ብልኽኝ ነበር›› እንዲለው ብቻ ነበርን ይቅርታ እንዲያደርግለትና መንግስቱን እንዲያወርሰው መለመኑ እንደ ነበር አያጠራጥርም ፡፡ ሉቃ23፡42-43 ታድያ የ‹‹ማሰብ›› ትርጓሜ እንዲህ ከሆነ ‹‹በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› ሲባልም ሕጉን ጠብቅ ጸልይ ፤ አመስግን ፣ ማለት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹አቤቱ በመንግሥትህ በመጣ ጊዜ አስበኝ›› በማለት ለለመነው ወንበዴ ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ›› ብሎ የመለሰለት መልስ ‹‹ማሰብ›› የሚለውን ቃል በሌላ መልኩ እንዳየው ግድ ይለናል፡፡

‹‹አስበኝ›› ላለው ወንበዴ ‹‹ከእኔ ጋር ትኖራለህ›› ካለው ማሰብ ማለት ከራስ ጋር አብሮ ማኖር የሚል ትርጓሜ እንዳለው ያስረዳል፡፡ ፊያታዊ ዘየማንም (በቀኝ የተሰቀለው ሽፍታም) ‹‹አስበኝ›› ሲል ‹‹ከራስህ ጋር አኑረኝ›› ማለቱ እንደ ነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ከእኔ ጋር ትኖራለህ›› ማለቱ እንደነበር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ከእኔ ጋር ትኖራለህ›› በማለት ከመመልከት መልስ እንገነዘባለን፡፡ ሉቃ2342-43

ከላይ በተሰጠው ሀተታ መሠረት ‹‹ማሰብ›› ማለት ‹‹ከራስ ጋር ማኖር›› ማለት ከሆነ ‹‹በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን ማሰብ›› ማለት ምን ማለት ሊሆን ይችላል በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህ ካንተ የማይለይበትን ሥራ አድርግ ማለት ነው፡፡ ማለትም ሰውን ከፈጣሪው የሚለየው ሀጥያት ነውና ከሀጥያት ሽሽ፣ ኢሳ 59፡2 በአንጻሩ ደግሞ መልካም ሥራን ሁሉ አድርግ፡፡ በደልህን ሁሉ አምነህ ንስሐ ግባና ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀበል፡፡ በዚህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሆናል፡፡ ዮሐ 6፡56 ይህን ሁሉ አድርገህ እግዚአብሄር ከአንተ ጋር ሲሆን ‹‹በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› የሚለውን ትእዛዝ በእውነት የፈፀምክ ትሆናለህ፡፡

ምንጭ ፡ ሕይወተ ወራዙት (የወጣቶች ሕይወት)ክፍል አንድ ገጽ 279 -282 ዲ.ን ኅብረት የሺጥላ ነሐሴ 1997
👍10
በጅማና አካባቢዋ ለምትገኙ ወጣቶች ከኅዳር 26- ታኅሣሥ 2 የሚቆይ የሙሉ ቀን ሥልጠናና ጉባኤ ተዘጋጅቶአል:: በብፁዕነታቸው ትእዛዝ በቅርቡ የተጠናቀቀውን ሕንፃ ቤተ መቅደስ ቅዳሴ ቤቱን ከመባረክ በፊት ትውልዱን ለቤተ መቅደሱ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ ከጅማ ወጣቶች ጋር እንሰነብታለን::

የጅማ ልጆች በትምህርቱ ላይ ለመሳተፍ የቦታ ውስንነት በመኖሩ በተገለጹት አድራሻዎች ከወዲሁ ተመዝገቡ::

ለበለጠ መረጃ የሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይን ገጽ በዚህ ሊንክ ተጭናችሁ ላይክ በማድረግ መከታተል ትችላላችሁ::

https://www.facebook.com/kesistagaytadele
👍1
👍6
.    #ሺኖዳ_ካልዕ (#ብፁዕ_ሱኑትዩ)
┄–┉┉✽»✧†✧«✽┉┉–┄

ሺኖዳ (ሱኑትዩ) ﺷﻨﻮﺩﺓ ፣ Ϣⲉⲛⲟⲩϯ ፣ Shenouda ፣ Shenoute ፣ Sanitius …

"ወፈጸመ ግብረ እጓለ እመሕያዋ ዘእንበለ ኃጢኣት ወተወልደ እም ብእሲት ድንግል እንተ እምዘመድነ ወተወክፈ ረሀበ ወጽምዐ… ከኃጢኣት ብቻ በቀር የሰውነትን ሥራ ሠራ ከእኛ ወገን ከምትሆን ከድንግል ማርያም ተወለደ ተራበ ተጠማ" (ሃይ አበው ፻፲፥፵፱)

ከድንግል ማርያም ወገን ያልሆኑ ክርስቶስን የእኛ ማለት እንደምን ይቻላቸዋል? በመልአኩ ብስራት "እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው" ተብላ፣ ቃልን ተቀብላ፣ ጸንሳና ወልዳ "ከእናንተም ጋር ይሁን" ብላ #አማኑኤል ን የሰጠችን ደገኛይቱ እናት የተስፋ ፍጻሜ ወገናችን ናት!  ከእኛ ጋር ሆነ ያልነው የእኛ የሆነችውን እናት ስለያዝን ነው እኛ ከእርሷ ሆነን ልጇን ከእኛ ጋር ነው እንላለን፣ እርሱም ከእናቱ ጋር ሆኖ ከሁላችን ጋር ሆነ ተባለ፤ ሊቁ ከእርሷ ተወልዶ ያለ ኃጢአት ኖረ …ተራበ፣ ተጠማ ሲል ወደእኛ መቅረቡን ገለጠ፤ ለስደታችን ካሳ ከሆነ ከከበረ ስደቱ በረከት ይክፈለን (አሜን)።

የዚህ ክፍል የሃይማኖተ አበው ጸሐፊ ዛሬ ሕዳር ፪ ዕረፍቱን የምናስበው ሊቁ የእስክንድርያ ፷፫ኛው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባ ሱኑትዩ ካልዕ ነው።

ቅዱስ ሱኑትዩ [St. Sanitius] በግብፃውያኑ አጠራር ሁለተኛው ሺኖዳ በመባል የሚታወቅ ሲሆን በእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ከሊቁ ጋር በሺኖዳ ስም የተጠሩ ሌሎች ሁለት "ፓትርያርኮች" ነበሩ።

የመጀመርያው ፶፭ኛው ፓትርያርክ ሱኑትዩ ቀዳማዊ ሲሆን [St. Sanitius I (Shenudi) 55th patriarch of Alexandria]

👌 ሦስተኛው ደግሞ ፻፲፯ኛው ፓትርያርክ ተወዳጁ ሱኑትዩ (አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ) ናቸው [ Pope Shenouda III 117th Coptic Orthodox Pope of Alexandria]

ሺኖዳ (ሱኑትዩ) ማለት ምን ማለት ነው?

ለስሙ መጠሪያ የቁብጡ ሼኖዴ ወይም ሼኖውቴ [ Ϣⲉⲛⲟⲩϯ ] የሚለው መነሻ ስያሜ ነው፤ ይኸውም

🔑 ሼ ϣⲉ (ልጅ) ፣
🔑 ኤን ⲉⲛ (የ) ፣
🔑 ኖውቲ Ⲛⲟⲩϯ (እግዚአብሔር) ከሚሉ ሶስት ቃላት የተገነባ ሆኖ #የእግዚአብሔር_ልጅ ማለት ነው!

ቅዱሱ ሊቅ ለቅዱስ ሰውነታችን በማሰብ (ኀበ ቅድሳቲክሙ እያለ) በጻፈልን ድርሳኑ ተከታዮቹን ፍሬ ነገሮች ነግሮናል ፤ ለበረከት በጥቂቱ እነሆ ፦

🔐  "ከመጠል ውስተ ጸምር ከማሁ ኀደረ ውስተ ከርሠ ድንግል በኩሉ ጊዜ እንተ ይእቲ ዘበአማን ወላዲተ እግዚአብሔር ቃል ማርያም ቅድስት … ጠል ከፀምር እንደተስማማው እንዲሁ ሁልጊዜ ንጽሕት በምትሆን በድንግል ማኅፀን አደረ ይኽችውም እግዚአብሔር ቃልን የወለደችው ቅድስት ማርያም ናት " (ቁ ፲፭)

🔐  "በከመ መሀሩነ አበው ለባስያነ እግዚአብሔር እስመ መንክርሰ ወዕፁብ እስመ ድንግል ኮነት ታውኅዝ ሐሊበ ምስለ ድንግልናሃ ዝንቱ ግብር ይትሌዐል ወይትዐዶ እምልቡና እጓለ እመሕያው … እግዚአብሔር ያደረባቸው አባቶቻችን እንዳስተማሩን የሚደንቅ የሚጨንቅ ነገርስ ድንግል በድንግልናዋ ሳለች እነሆ ወተትን አስገኝታለችና ይህ ሥራ በሰው ልቡና ከመመርመር ፈጽሞ የራቀ የረቀቀ ነው! (ቁ ፲፯)

🔐 "ዐቀባ ለድንግል ንጽሕት ማርያም እንዘ ኢያርኁ ማኅተመ ድንግልናሃ እምድኅረ ልደተ ሕፃን እምኔሃ ወውእቱ ይእዜ ንጹሕ እም ፫ቱ ግብራት እለ ሥሩአን በዕጓለ እመሕያው ወእሙራት ቦሙ ዘውእቶሙ ሩካቤ ወዘርዕ ወሰስሎተ ድንግልና … ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከእርሷ ከተወለደ በኋላ ድንግል ንጽሕት ማርያምን ጠበቃት እርሱ በሰው ዘንድ ከተሠሩ ከታወቁ ከሦስቱ ግብራት ንጹሕ ነው እነዚህም ሩካቤ ዘርና የድንግልና መለወጥ ናቸው " (ቁ ፳፱)

ከዘመነ ጽጌው ስደት ከቅዱስ ሱኑትዩ ካልዕ ዕረፍት ረድኤት በረከት ያሳትፈን!

[~~~> ከቴዎድሮስ በለጠ ሕዳር ፪ ቀን ፳፻፲፩ ዐ.ም]
👍6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👍1
꧁༺༒༻꧂
«ነአኵቶ…»
በነአኵቶ ለአብ!

በላስታው ሥርወ መንግሥት ታሪክ ውሥጥ የ፬ ነገሥታት ታሪክ በሀገር ታሪክ መዝገብ እንደ ዜና መዋዕል (Chronicle) የሚተረክ ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ታሪክ በመጽሐፈ ገድል ጭምር ተጽፎ የሚሰበክ ሆኖ እናገኘዋለን።

(ያው ዛሬ ላስታ የላሊበላን ወረዳ ብቻ የሚተካ ሆኖ ይነገር እንጂ እንደ ቀደመው አከላለል ቡግና ፣ መቄት ፣ ላሊበላ ፣ ደላንታ … የላስታ ግዛቶች ነበሩ)

በዛግዌ (ዘአገው) ቀዳሚው ንጉሥ መራ ተክለሃይማኖት የንጉሠ አክሱም የድልነዓድን ልጅ መሶበወርቅን አግብተው ፬ ልጆችን ወልደዋል
✧ ጠጠውድምን
✧ ግርማ ሥዩምን
✧ ዣን ሥዩምን እና
✧ ሴቷ ትርድአነ ገበዝን
የመራ ተክለሃይማኖት ሦስቱም ወንዶች ልጆቻቸው ጠጠውድም፣ ግርማ ሥዩምና ዣን ሥዩም አገራችንን ያስተዳደሩ ነገሥታት ነበሩ፡፡

የግርማ ሥዩም ልጅ ☞ ይምርሃነ ክርስቶስ
የዣን ሥዩም ልጆች ☞ ገብረማርያም (ሐርቤ) እና ላሊበላ
የገብረ ማርያም ልጅ ☞ ነአኵቶ ለአብ
የላሊበላ ልጅ ☞ ይትባረክ ሀገር መሪ ነገሥታት ነበሩ።

(ጠጠውድም ደግሞ የታላቁን ቅዱስ አሮን መንክራዊ ዘመቄት አባት ገብረ መስቀልን የወለዱ ናቸው)

ዛሬ ህዳር ፫ ቀን ቤተክርስቲያን ወደ ብሔረ ሕያዋን መጠራቱን የምትዘክረው ታላቁ ቅዱስ ንጉሥ ነአኵቶ ለአብ ነው።

አባቱ በስመ ንግሥና ገብረ ማርያም ይባል እንጂ የቀድሞ ስሙ ሐርቤ ነው እናቱ ደግሞ መርኬዛ ትባላለች።

(ሐርቤ የሚለው ለግእዙ መነሻ የቀረበ ነው፤ በእብራይስጡ ኼሬብ ( חָרַב ⇨ kheh'-reb ) ሠይፍ ማለት ሲሆን ይህን በመሰለ አቻ ፍቺ በግእዙ ሐርብ ማለት ጦርነት ውጊያ ሰልፍ ነው። ዐማርኛውም ዐ(ሐ)ርበኛ ማለትን ከዚህ አውጥቶታል። ሐርቤ ማለት ዐርበኛዬ ማለት ነው!)

ሐርቤ (ገብረ ማርያም) በቅንነት ለ፵ ዓመታት ሀገር ሲመራ ኖሮ ልጅ ስላልነበረው መንግሥቱን ለወንድሙ ላሊበላ (ቅዱስ ንጉሥ) አስረክቦ ወደ ኢየሩሳሌም በመኼድ መንኗል። እግዚአብሔር ግን "ክብሩ ከመ መላእክተ ሰማይ የሆነ ልጅ ትወልዳለህና ወደ መርኬዛ ተመለስ አለው" እየተደነቀ ወደቤቱ ተመለሰ። በጌታችን ልደት ቀን ካህናቱ ቅዳሴ ገብተው መርኬዛ መውለጃዋ ደረሰ አሐዱ ከተባለ ሠዓት አንስቶ የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን በሰላም ተገላገለች:: ሕጻኑን አንስታ በደስታ ስትታቀፈው ቅዳሴ የገባው ዲያቆን ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ…" እያለ ሲዞር ሰማችው፤ በዚህ መነሻ ልጇ «#ነአኵቶ_ለአብ» ተባለ!

በምግባር በሃይማኖት በአጎቱ ላሊበላ (ንጉሥ ቅዱስ) ተኮትኩቶ ያደገው ነአኩቶ ለአብ በምናኔ መኖር እጅጉን ይሻ/ይመኝ ነበር፤ እመቤታችን ግን "ክብርህ ከደናግላን አያንስም አግባ" ብላዋለች። አግብቶም ዲሜጥሮስና ልዕልተ ወይን ለ፵፰ ዓመት እንደኖሩት ከሚስቱ ጋር በግብር ሳይተዋወቁ በትዳር ለ፳፭ ዓመት በድንግልና ኖረዋል።

መልአከ እግዚአብሔር «መጋባታችሁ ዘር ለመተካትም ነውና» ብሎ ስላዘዛቸው ለአንድ ቀን ብቻ በግብር ተዋውቀው መልከመልካም ልጅ ወለዱ። ይሁንና በንግሥና ዙፋኑ ሲቀመጥ ግብሩ እንደ መልኩ እንደማይሆን ቢገለጥለት በክብር ቀድመህ ከምርጦቹ ደምርልኝ ብሎ ስለልጁ እረፍት አምላኩን አብዝቶ ተማጸነ፤ የካቲት ፲፮ በክብር አርፎ ሔሮድስ ካስፈጃቸው ሕጻናት ተደምሮለታል።

ይኽ ነገር በእጅጉ ይደንቀኛል! ለአንድ ልጁ የሥጋ ሕይወት ያልሳሳ አባት በነፍስ የሚጠቅመውን ለመነለት።

ሰሎሞን በመጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፬ እንዲህ ይላል፦
" እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ይወደዳል በኃጢአተኞች ፡ መካከል ሳለም በሞት ይሄዳል ። ክፋት ዕውቀትን ሳትለውጥበት ይህም ባይሆን ሐሰት ሰውነቱን ሳታስትበት በሞት ተነጥቆ ይሄዳል። የክፋት ቅንዓት በጎ ሥራዎችን ያጠፋልና ወጪ ወራጅ ፈቃድም የዋህ ልቡናህ ያሳዝናልና በሞት ፈጥኖ ይሄዳልና ።ሰውነቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደደች ሆናለችና በጥቂት ዘመንም ቢሞት ብዙ ዘመን ጨረሰ። ስለዚህም ነገር ኃጢአት ከሚሠራበት ከዚህ ዓለም በሞት ቸኩሎ ሄደ ይህን ግን ልዩ የሆኑ ሰዎች አይተው ልብ አላደረጉትም። የእግዚአብሔር ፍርዱ ለወዳጆቹ ነውና በይቅርታውም መጐብኘቱ ለመረጣቸው ሰዎች ነውና። የዚህን ትርጓሜ በልቡናቸው አላሳደሩትም ። ደግ ሰው ግን ከሞተ በኋላ በደኅንነት ሳሉ እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎችን ይገዛል። ጐልማሳ ሰውም ፈጥኖ በሞተ ጊዜ በደል በተደረገበት የዕርግና ዘመናቸው የበዛ እግዚአብሔርን የዘነጉ ሰዎችን ይገዛል።"

የሁላችን መምህር አባ ጊዮርጊስ በዛሬው የቀዳሚት ተአምኆ ቅዱሳን ይህን ብሏል "ወለነኒ እግዚኦ… ረስየነ ከመ ንፍረይ ፍሬ ምግባረ ዘይሠምረከ እስመ መኪነ ፍሬ ምግባር የአኪ እመኪነ ፍሬ ውሉድ ⇨ አቤቱ ለእኛም… አንተን ደስ የሚያሰኝ የምግባር ፍሬ ለማፍራት የበቃን የተገባን አድርገን የልጅ ፍሬ መኻን ከመሆን የምግባር ፍሬ መኻን መሆን ይከፋልና"

ያን ጊዜ መኳንንቱና መሳፍንቱ "ንጉሣችን ልጁ ሞቶበት ሐዘን ደርሶበታልና ልቅሶ እንድረስ" ብለው ቢመጡ ለክብር ስለበቃው ልጁ እግዚአብሔርን በፍጹም ደስታ ሲያመሰግን አይተው "ሞተ መባሉ ውሸት ነው" እስከሚሉ ተደንቀዋል።

ነአኵቶ ለአብ እንደ ላሊበላ (ንጉሥ ቅዱስ) እና እንደ ይምርሐነ ክርስቶስ ዋሻ በመገልፈል ቤተመቅደስ በማነጽ ይታወቃል። በ፲፪፻፲፩ ዓ·ም· አሸተን ማርያምን አንጾ ከቤተ መንግሥቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት ይቀድስባትም ነበር፤ ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ሥውራን ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ:: እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መወጣችሁ?" ቢላቸው "መዓዛ ዕጣንህን አሽትተን (አሽ’ተን) መጣን" ብለውታል:: በዚህም መነሻ "አሽ’ተን (አሸተን) ማርያም" ተብላ ስትጠራ ትኖራለች::

ቅዱሱ ነአኵቶ ለአብ በነገሠበት ፵ ዓመት ውሥጥ ዐርብ ዐርብን የክርስቶስን ሕማም እያሰበ
👑 በዘውዱ ፋንታ የእሾህ አክሊል ደፍቶ
⇢ በጌታችን ፭ቱ ችንካር ምሳሌ ፭ ጦር ዙሪያውን ተክሎ እየደማ እያለቀሰ ሲጸልይ ሲሰግድ ይውል ነበር።

ከእለታት በአንዱ ቀን ጌታችን ተገለጸለት እንዲህም አለው ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ እኔ ለዓለም ደሜን ያፈሰስኩት አንድ ቀን ነው፤ አንተ ግን ፵ ዓመት ሙሉ ደምህንንና እንባህን ስታፈስ ኖርክ ይበቃሃል አሁን ወደ እኔ ልወስድህ ነው ይለዋል፤ነአኩቶ ለአብም ጌታችንን “ጌታዬ ሆይ እዚህ ቦታ እኔን ብለው የሚመጡ ወገኖቼን ማርልኝ ይለዋል” ጌታም "እውነት እልሃለው ቦታህን ባይረግጥ ዝክርህን ባያዘክር እንኳን ዝናህን ሰምቶ ያሰበህን ኃጢያቱ ምን ቢበዛ እምርልሃለው፤ ዳግመኛም እልሃለው ፵ ዓመት ሙሉ እንባህን ያፈሰስክባት ይህች ድንጋይ እስከ እለተ ምጽአት እያነባች ትኖራለች ከዚህ ለሚጠጡ ለሚጠመቁ ድኅነት ይሁናቸው" ብሎታል።

ዛሬም ድረስ የነአኵቶ ለአብ ቤተክርስቲያኑ ባለበት ከጣራው ስር ጠበሉ እየቆየ ጠብ ጠብ ይላል፤ ክረምት ከበጋ ሳይጎድል ሳይተርፍ ይኽ ተአምር ምስክር ሆኖ አለ!

ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠው በ፴ ዓመቱ ሲሆን ለ፵ ዓመታት ነግሦ በ፸ ዓመቱ የሥጋ ድካም ካለበትና ገቢረ ኀጢኣት ከሠለጠነበት ከዚህ ዐለም ወደብሔረ ሕያዋን ህዳር ፫ ቀን ተጠርቷል።

ልደቱ ከጌታው ልደት አንድነት ታኅሳስ ፳፱ ስለዋለ በተውላጥ ህዳር ፩ ቀን ይዘከራል።

✍️ ከቴዎድሮስ በለጠ ህዳር ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም. ከላሊበላ ነአኵቶ ለአብ Na'akueto La'ab
👍54
ተፈፀተፈፀመተፈፀመ
እነሆ የተወደደ ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ

" ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር
ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር
ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር
አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር
ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር”
※ ※ ※ ※ ※ ※
የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፤ እነሆ የተወደደ ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ በዕቅፍሽ እንዲጠጋ እንዲደገፍ፣ እንዲንተራስ በርሱ ዐማጽኚ።

እመቤታችን ሁላችንን በምልጃዋ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ፣ከመርገም ወደ በረከት፣ ከርኵሰት ወደ ቅድስና ትመልሰን።

እንኳን አደረሳችሁ።
👍2715
👍21
"ወማዕነቅኒ (ረከበት ቤተ) ኀበ ታነብር እጎሊሃ = ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች" መዝ. 83(84):3
⇌⇋ ♧ ⇌⇋

ህዳር ፮ ድንግል እናታችን ከስደት በደብረ ቁስቋም የማረፏን ዜና የሰማንበት ዕለት ነው:: አስቀድሞ መልአኩ ለአረጋዊው ፃድቅ ዮሴፍ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ " (ማቴ.2:20) ብሎ እንደነገረው ዕለቱ ማረፊያ አጥታ በበረሃ የተንከራተተች የተስፋ ስዱዳን እናት ድንግል ብቻ ያይደለች ከእርሷ ለሚጠለሉ ሁሉ ማረፊያ የተገኘበት ልዩ ዕለት ነው::

ነቢዩም ይህን እያየ በደብረ ቁስቋም ማረፊያ ያገኘች ርግብ ናትና "ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ" አላት:: ገላግልት የተባሉ ልጆቿን ያስጠለለች እመ ምዕመናን ዋኖስም እርሷ ናትና "ወማዕነቅኒ ኀበ ታነብር እጎሊሃ" ብሎ አመጣት::

ስለእርሷ በኅብረ ትንቢትና በኅብረ አምሳላት የተነገረውን ሳስብ ኅሊናየን እነዚህን አይዘነጋቸውም ፦

♚…ኢትዮጵያዊው ሐዋርያ ብርሃነ ዓለም ፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ስለ ድንግል ሊናገር አንስቶ አቻ ባያገኝላት ማብራሪያ መንገድ ቢያጣ "ኅጥእተ አምሳል እምነ አምሳላት .... ከምሳሌዎች ሁሉ ምንም ምሳሌ የሌላት" ብሎ አስቀመጣት::

♚…ቅዱስ ሕርያቆስ ዘብህንሳም ብዙ አምሳላት እያነሳ ሲያመሰግናት ቆየ ያም አላጠግበው ቢል የሚገልጥበት ቢቸግረው አላጠግብህ ቢለው "በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ ... በማንና በምን እንመስልሽ?" ብሎ ጠቀለለው::

♚…አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ምስጋናዋ እንደ ከዋክብተ ሰማይ እንደ ኆፃ ባህር በዝቶልኝ ጠጥቸው ረክቼ በልቼው ጠግቤ እያለ ሲመኝ ኖሮ "አይ ልሳን ዘይክል ነቢበ ዘይትነገር በእነቲአኪ.... ስላንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚችል አንደበት እንዴት ያለ ነው?" ብሎ በማድነቅ አረፈው::

✧ እንገዲህማ እነርሱ እንዲህ ካሉ እኛ ምን እንል ይሆን "ይኼይሰነኑ አርምሞ" ዝም ብንል ይሻለናል?

ኧረ የለም ሰውን ወደ ዝምታ የሚያደርሰው እኮ እንዲህ ያለ ስንፍናው ሳይሆን መደነቁ በዝቶ ከኅሊናው በላይ ቢሆንበት ነውና ታዲያ ምን አውቀን በምኑስ ተደንቀን ዝም እንላለን? ባይሆን እድሜ ዘመን የተቻለንን ጥቂት ስለ እርሷ እንናገራለን፤

↣ ሊቁም እንጂ እንዲህ ይላል "እለ ትነብሩ ተንስኡ ወእለ ታረምሙ አውስኡ ማርያምሃ በቃለ ስብሃት ፀወዑ..... የምትቀመጡ ተነሱ : ዝምም የምትሉ መልሱ: በምስጋና ቃላት ጥሩና ማርያምን አወድሱ"::

እንግዲህ ለዛሬው ከቅዱስ መጽሐፍም አውስተን በብዙ ሥፍራ ከተጠቀሱት ምሳሌዋች መካከል ሁሉን ለማየት ደካማው እውቀትና አጭሩ ጊዜም ባያደርሰን በጥቂቱ ግን ከሰማይ አእዋፋት በልዩ አምሳላትና ኅብር ስለ እርሷ የተነገረውን እያነሳን እናያለን::

ለነገሩ ያም ከነክብሯ ባይገልጣት ዝም ከማለት ይሻል እንደሆነ ብለን በምስጢርም ወደ እርሷ ቢያደርሰን እየተመኘን አጣን ብለን ሳናርፍ ቃሉን አንጠቅሳለን እንጂ እርሷን የሚመስላት (ስ ላልቶ ይነበብ) ቀርቶ የሚመስላት (ስ ጠብቆ ይነበብ) ከምንም አይገኝ :-

ከአእዋፍ ወገን መጽሐፍ ድንግል ማርያምን ርግብ ይላታል ዋኖስም እንዲሁ ፈጣኑ ንስርም ለእርሷ ምሳሌዋ ነው::

☞ እጓለ ርግብ ወይም ዘውገ ማዕነቅ በኦሪቱ የወለደች ሴት ስለ ሥርየተ ኃጢዓት ወደ ደብተራ ኦሪት ይዛ እንድትቀርብ ሥርዓት ተሰርቷል:: "የርግብም ግልገል ወይም ዋኖስ ለኃጢአት መሥዋዕት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታምጣለት።" እንዲል (ዘሌ. 12:6) በፍጻሜው በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ ለተሠራች አዲስ ኪዳን የርግብ ልጅ የተባለ ክርስቶስ ግን ካሳዋ ነው:: ስለዚህ በምስጢር እርሷ ድንግል የሆነች እናቱ "ርግብ" እርሱም አንድያ ወልደ እጓለ እመሕያው መድኅን የሆነ ልጇ "እጉለ ርግብ" መሰኘቱ ቅሉ ለዚህ ነው::

☞ ቅዱስ ዳዊት ከዲያብሎስ ማሳት ከሞት ግዞት እየበረረ የሚያመልጥበትን በገነት ተድላ ርስት የሚያርፍበትን ክንፍ ከየት ባመጣሁ እያለ ፈለገ "መኑ ይሁበኒ ክንፈ ርግብ ከመ እስርር ወአእርፍ…በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ!" (መዝ.54(55):6 )

↳ ታዲያማ ያ ክንፍ ከድንግል ውጪ ከቶ ለማን ተሰጠ? "ወተውኅባ ለይእቲ ብእሲት ክልኤ ክንፍ ከመ ዘዓቢይ ንስር = ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።" ብሎ ፈለገ ሃይማኖት ዮሐንስ ስለዚች ለባሲተ ፀሐይ ብእሲተ ሰማይ ናዛዚተ ኃዘን ወብካይ ይመሰክርልናልና:: (ራእ. 12:14)

↳ ልበ አምላክ ንጉስ ዳዊትስ መች አስችሎት በዚህ ብቻ ዝም ይላል "ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ ሐመልማለ ወርቅ" እያለ ያን ከብር የተሠራ ክንፏን በወርቅ ሐመልማሎ የተሸለመ ላባዋን በልዩ ኅብር እየፈታ ያመሳጥረዋል እንጂ "... ከብር እንደ ተሠሩ እንደ ርግብ ክንፎች፥ በቅጠልያ ወርቅም እንደ ተለበጡ ላባዎችዋ ..." (መዝ. 67(68):13)

↳ መልሶም በተነሳንበትም ኃይለ ቃል ያለውን ፍሬ ምስጢር ያስቀመጠው ራሱ ልበ አምላክ ነው "ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች፥ ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች" (መዝ.83(84):3)ይለናል።

⇝ "ወፍ" የሚላት የመለኮት ማደርያውን ድንግልን ነው "ለራስዋ ማደርያ አገኘች" ማለቱም ለጊዜው ከግብጽ ስደት በደብረ ቁስቋም እንድታርፍ ቢያይ እንዲህ አለ:: ይህችውም "ዋኖስ" ለራስዋ ብቻ ያይደለ እርሷን ብለው የወጡ "ግልገሎችዋን" ዮሴፍና ሰሎሜን አስጠልላለችና "ዋኖስም" ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች ይላታል::

∽⇦⇨∽ መች ቸርነትዋ በዚህ ያበቃና "ኄርት ይእቲ በሃበ ኩሎሙ… " ተብላለችና ለኛም ቢሆን "ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት ወንርአይ ብኪ ሰላመ...." እያልን ለምንጠራት ለገላግልት ልጆችዋ ከጠላት ማሳት እንድንጠበቅ የምንጠለልበትን ልጇ ያነጸልንን የሰላም ቤት ማረፊያ ያገኘችልን ዋኖሳችን እርሷው ናት።

°°° ♚ °°°
ሊቁም በተፈጸመ የጽጌ ማኅሌት ዚቅ ምስጋናው መካከል የአብን መርዓት የበጉን እናት መልካሞቹን
መልታሕት ያማሩ ጉንጮቿን እየጠቀሰ በዋኖስም እየመሰለ እንዲህ ያነሳሳታል "ሃሌ ሃሌ ሉያ ጥቀ አዳም መላትሕኪ ከመ ማዕነቅ ይግበሩ ለኪ ኮስኮሰ ወርቅ" አኛም ካወደሷት ጋር በምስጋና ለእመ ወንጌል ምክንያተ ድኂን ለውዳሴዋ በማኅሌት እንቆማለን::
" ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፥ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው? " ( ኢሳ. 60:8) እያሉ እስኪደነቁብን ርግቧን ተከትለን ወደ ሰማያዊው ርስታችን በማኅሌቱ ኅሊናችንን እንሰቅላለን!

☞ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞንም በናፍቆት እየጠራት የዲያቢሎስ ዝናመ መከራው እንዲያልፍ ጽጌ ክርስቶስ ለቤዛ ዓለሙ እንዲተርፍ ከዓለት ንቃቃት ርደተ መቃብርና ከገደሉ ግዞት ርደተ ሲኦል መሰወርያ መሸሸጊያ ማምለጫ ያለሽ ሰናይት ርግብየ ነይ ። መልአኩ እንዳየሽ መልክሽን አሳዪኝ መልክሽ ያማረ ነውና። ኤልሳቤጥንም እንዳስደሰትሽ ድምጽሽን አሰሚኝ ድምጽሽ ጥዑም ነውና ። ይላታል ፦
👍32
"በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ቃልሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ። " (መኃ. 2:14)::
ስለዚህች "ርግብ" እርሱም እንደ አባቱ ይጨምራል እንጂ መች በዚህ ብቻ ይብቃኝ ይልና! ምን ብሎ አትሉም? ጠቢቡ ይህችን ተቀዳሚ ተከታይ የሌላትን በፍጥረት ሁሉ የምትመሰገን… የሕይወት ፍሬ መገኛ …የሕይወት መጠጥ መፍለቂያ… ብቸኛዋን ወለተ ቅድስት ሃና…ብቻዋን ምክሐ ትዝምድና… ብቸኛዋን የአካላዊ ቃል ዙፋን …ብቻዋን ካሣ ለእምነ ሔዋን… እንዲህ እያለ ከፍ ከፍ ያደርጋታል:: "ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥ ንግሥታትና ቍባቶችም አመሰገኑአት።" መኃ. 6:9 እስኪ ይህስ ከዚህ ይቆየንና ....

……… ↻†↺………
ታዲያ ከዚች ርግብ ለኛ ምን ይትረፈን? ትሉኝ እንደሆን
……… ↻†↺………

ሁላቸውም ከአምላካቸው ፍቃድ ርቀው ከገደል በወደቁበት ዘመን ርግቢቱ ግን ከአፋፉ ላይ ቤቷን ሠርታ በንጽህና ወደ ፈጣሪዋ ቀርባ ልጇን ወደ ዓለም በፍቅር ስባ አቅርባዋለችና ታዲያ እኛም ከኃጢዓት የምንርቅበትን ከጠላት ማስት የምንጠበቅበትን የሰማዩ ቤታችንን በንሰሃ እንሥራ።

☞ ነቢየ እግዚአብሔር ኤርምያስ እንደዚህች ርግብ ሁኑ እያለ መክሮናልና "በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ።" (ኤር. 48:28)

ዳግመኛም ከእርሷ እንደተማሩ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ናጥሪ እንከ አፍቅሮ ወየዋሃተ እንግዲህ ፍቅርና የዋሃት ገንዘብ እናድርግ። እነርሱ በፍጹም የዋህነት ተጉዘው የዋህና በልቡ ትሁት የሆነ ልጇን ጌታቸውን ቢወዱት የአመፃን ሁሉ ማሰሪያ ይፈቱ ዘንድ ሥልጣንን ተቀብለዋልና፤ ቀድሞ ጌታችን በወንጌል ስለራሱ "እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥" (ማቴ.11:29) አለ ከኔም ተማሩ አላቸው። እርሱ እንደእናቱ የዋህ ነው። የሷም የዋህነት ምንጩ እርሱ ነው ነውና እናቱ መልካሟ ርግብ ማርያምም ሃሳብዋ እንደ አምላክ ሃሳብ ነውና የዋሂት ርግብ ይላታል እኛንም እንደርሷ የዋህ እንድንሆን ልንጠጋት ይገባል።

☞ ከሷም ምን ልንማር እንዲገባ ልጇ ሲያስተምረን ".... እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።" (ማቴ.10:16) ብሎናልና::

እንግዲህ ማረፊያ ያገኘች ርግብ ባላክንፏ ንስር ዋኖስም የተሰኘች ድንግል እኛ ጫጩቶቿን በምልጃዋ በቤቱ አጽንታ ታኑረን:: ሁላችንን አዛኝቱ እመ መለኮት በምልጃዋ ከክንፎቿ በታች ታሳርፈን። ይቆየን

~~~> (ከአግናጥዮስ ህዳር 6 ቀን 2008 ዓ.ም.ጅማ)
👍161
ለራስ ይቅርታ አለማድረግ

ከመንፈሳዊ ትምህርት ጋር በማቀላቀል የቀረበ ነው  

አዳምጡ  እስከ መጨረሻው ደስ የሚል ትምህርት ታገኛላቹው 


አመሰግናለሁ መልካም ቀን

https://youtu.be/bTt91J2WujE
https://youtu.be/bTt91J2WujE
https://youtu.be/bTt91J2WujE
👍5
꧁༺༒༻꧂
. ቅድስት ሐና

ሐና የሚለውን ስም እስከ ክርስቶስ መምጣት በቅዱሳት መጻሕፍቱ ለአራት የከበሩ አንስት በስመ ተጸውኦነት መጠሪያ ሆኖ መገለጹን እንረዳለን።

① እመ ሳሙኤል ፣ ብእሲተ ኤፍሬማዊ ሕልቃና ሐና ፣
② እመ ጦቢያ ፣ ብእሲተ ጦቢት (ዘእምነገደ ንፍታሌም) ሐና ፣
③ ወለተ ፋኑኤል (ዘእምነገደ አሴር) ነቢይት ሐና ፣ እና
④ ወለተ ማጣት (ዘእምነገደ ሌዊ) ብእሲተ ቅዱስ ኢያቄም ቅድስት ሐና

ከእኒህ ሐናት («ሐናውያት») ሁሉ እጅግ የከበረችውና ለወላዲተ አምላክ እናቷ ለክርስቶስ የሥጋ ልደት አያቱ የሆነችው ቅድስት ሐና የማርያም (የቅድስት ሰሎሜ እናት) እና የሶፍያ (የቅድስት ኤልሳቤጥ እናት) እሕታቸው ናት።

ሐና ለሚለው ስም የእብራይስጡ ሐናህ ( חַנָּה) መነሻ ነው ጸጋ ሥጦታ ፣ ሀብት በረከት ማለት ነው።

መጻሕፍቱም ይሕችን የአዳም ዘር ሀብት የፍጹም በረከት የበጎ ሥጦታ መገኛ እንዲህ እየገለጡ በምስጋና ተባብረው ያከብሯታል ፦

🍀 "ወለዛቲ ቅድስት ሐና ኢያእመርነ ገድላቲሃ ወትሩፋቲሃ ዘትገብሮን በኅቡእ ከመንዝክሮን ዳእሙ ነአምር ወንጤይቅ ከመ ይእቲ ተአቢ ወትከብር እምኩሎን አንስት እስመ ለዛቲ ደለዋ ትኩን ወላዲታ ለወላዲተ አምላክ በሥጋ ወለእመ ኢኮና ላቲ ትሩፋት ብዙኃት ወገድል ዐቢይ ዘይፈደፍድ እምገድለ ኵሎን አንስት እምኢደለዋ ዝንቱ ጸጋ ዐቢይ"
. (ስንክሳር ዘሕዳር ፲፩)

የዚህችን ቅድስት ሐናን በስውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋትዋን እንዳናስታውሰው አናውቀውም። ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደች ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባች ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር
━━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━━

🍀 ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኵሉ ምዕራጋ፡
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ፡
ሐና ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ፡
እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ፡
እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ፡፡
(ዐርኬ ዘሕዳር ፲፩)

ሰላም ላንቺ ይሁን ሐና : መንገድ ለሁሉ ጸሎት
ልክ እንደ ወይን ነሽና : በሐረጓ ላይ ፍሬ እንዳላት
ብፅዕት ሐና ሆይ ደስ ይበልሽ : ያለ ነቀፋ ያለ ጉድለት
ሞገስን ብታገኚ ከአምላክ : ጸጋው ቢሆንሽ ጉልላት
ለመሆን የበቃሽ ሆነሻል : በሥጋ የአምላክ አያት
━━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━━

🍀 ወኮና ኤልሳቤጥ ወሰሎሜ ወሐና አዋልደ አሐቲ ብእሲት። ወዛቲ ቅድስት ሐና እስመ ኮነት ክብርተ እምኔሆን ኵሎን አንስተ ዓለም እስመ ኮነት ድሉተ ከመ ትለዳ ለወላዲተ አምላክ በሥጋ ወአዕሚሮ ጽድቃ ወክብራ እምኵሎን አንስት
. (ድርሳነ ኢያቄም ወሐና ዘረቡዕ ቁ ፶፩)

ኤልሳቤጥ ሰሎሜና ሐናም የእኅትማማች ልጆች ናቸው ይህች ቅድስትሐናን ግን ጽድቋንና ከሴቶች የሚበልጥ ክብሯን አውቆ በሥጋ አምላክን ለወለደች ለድንግል ማርያም እናት ለመሆን የተገባች አደረጋት። ከሴቶች ሁሉ የተከበረች ናት።
━━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━━

🍀 ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እምኀላዌ ሥጋ ተዋህዶታ
ኀበ ተስፋ ሕይወት ተሠርዓ ወተደለወ በበፆታ
ሊተ ሐና ለነፍስየ አመ ፀዓታ
አስተዳልዊ አስበ ዚአየ ከመ ታስተዳሉ ማርታ
ማዕደ ፈቃድ ለክትስቶስ በቤታ
. (መልክአ ሐና)

በሥጋ ተዋሕዶ በዚህ ዓለም ከመኖር በየክፍሉ ወደተዘጋጀ ተስፋ ሕይወት ለነፍስሽ መውጣት ሰላም እላለሁ
ቅድስት ሐና ሆይ ነፍሴ ከሥጋዬ በተለየች ጊዜ ማርታ ለክርስቶስ ማዕድን በቤትዋ እንዳዘጋጀች ለእኔም በአማላጅነትሽ ዋጋዬን አዘጋጂልኝ
━━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━━

🍀 ሰላም ለነፍሳቲክም እለ እም ሥጋ ፈለሳ
ከመ በሰማያት ይንግሣ
ኢያቄም ወሐና ብርሃናት ዘደወለ ምሕሳ
በረከተ ሥጋክሙ ወነፍስክሙ ዘኢይበጽሖ ኀሠሣ
ለነፍሰ ዚአየ አንብሩ በርእሳ
. (መልክአ ኢያቄም ወሐና)

ከሥጋችሁ የተለየች ትነግሥ ዘንድ በሰማያት
ለነፍሳችሁ ሰላም እላለሁ ነፍሳችሁ ክብርት ናት
ወሰንና መስፈሪያ ኢያቄምና ሐና ብርሃናት
ፍለጋው የማይደረስበት የሥጋና የነፍሳችሁ በረከት
በኔም ላይ እንዲያድርብኝ በነፍሴ ራስ ላይ አኑሩት
━━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━━

ሰላም ለሕፅንከ ምርፋቀ ንጽሕና ወቅድስና
አዕዳዊከኒ ዘርኅቁ እምርስሐተ ጌጋይ ወሙስና
ኢያቄም አቡነ መራሔ ሕይወት ዖፈ ብርጋና
አበዊነ እስራኤል ከመ ተሴሰዩ መና
ሴስዩነ ከመ እሉ ኢያቄም ወሐና
. (መልክአ ኢያቄም)

የቅድስናና የንጽሕና ማረፊያ ለሆነው ፡ ሰላም እላለሁ ላንተ እቅፍ
እጆችህ የራቁ ናቸው ፡ ከጥፋትና በበደል ከማደፍ
ወደሕይወት የምትመራን ፡ ኢያቄም የብርጋና ወፍ
መና እንደበሉ አባቶቻንን ፡ የሲናን በረሀ ለማለፍ
ኢያቄምና ሐናም እንደነርሱ ፡ መግቡን ነፍሳችን እንድታርፍ
━━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━━

🍀 ወበዛቲ ዕለት በዓልኪ ንበል በልሳነ ሥጋ ወኅሊና፡
እንዘ ናነክር በዜና፡
እመሰ ተመክሐት ብእሲቱ ለሕልቃና፡
በረኪበ ሳሙኤል ፍሬ ማኅፀና፡
እፎኬ ፈድፋደ ይሤኒ ትምክሕት በእምኪ ሐና፡
ዘፈረየት ኪያኪ ተስፋ ልቡና፡
እስመ ኢያቄም አቡኪ ዘሐፀና፡
አኮ ዘረከበኪ እምኔሃ በውርዝውና፡
አላ እምድኅረ ልህቀት ወርስዕና፡ አሜን፡
(ነገረ ማርያም ዜና ጽንሰታ ብራና)

በዚች በበዓልሽ ቀን : በሥጋና በኅሊና አንደበት
በነገሩ እንደነቅበት
የማፀኗ ፍሬ ሳሙኤል : ልጇ ሆኖ ስለተሰጣት
ለሕልቃና ሚስት ለሐና : መመኪያዋ ሆናት
መመካትስ እጅግ የሚልቀው : በቅድስት ሐና ነው ባንቺ እናት
የልባችን ተስፋ የምትሆኝ : አንቺ ፍሬዋ ሆንሻት
አባትሽ ኢያቄም : ጠብቆ ያሳደጋት
ከእርሷ የተቀበለሽ : መች ሆነና በወጣትነት
ካረጀች በኋላ ነው እንጂ : ሙቀት ልምላሜ ከተለያት ።
━━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━━

የመድኃኔዓለም አያት
የድንግል ማርያም እናት
ለቅድስት ሶፍያና ለቅድስት ማርያም እሕት
ለቅድስት ሰሎሜና ለቅድስት ኤልሳቤጥ አክስት
ከምትኾን ከቅድስትና ብፅዕት ሐና ከዕረፍቷ መታሰቢያ ረድዔትና በረከት ያሳድርብን።

☞ ከቴዎድሮስ በለጠ [ሕዳር ፲፩ /፳፻፲፫ ዓ.ም.]
👍91
💐የሕፃናት የምስጋና ቃል 💐

ሰአል ለነ
ሰአል ፡ ለነ ፡ ሚካኤል
መልአከ ፡ ምክሩ ፡ ለልዑል /2/

ንሥረ   እሳት ፡ ዘራማ
ጸሎታችንን ፡ የምትሰማ
የምታማልድ ፡ ከአምላክ
በመስቀልህ ፡ እኛን  ባርክ

    ፨ ሰአል ሚካኤል ሰአል
    ፨ ነዓ መልአኩ ለቃል

ቅዱስ ፡ ሚካኤል ፡ መራሔ
ልማድህ ፡ ነው ፡ ርኅራኄ
የሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ረዳት
በሌትና ፡ በመዓልት

    ፨ ሰአል ፡ ሚካኤል ፡ ሰአል
    ፨ ነዓ ፡ መልአኩ ፡ ለቃል

ሰአሌ ፡ ምሕረት ፡ ወሣህል
የምትታደግ ፡ ገባሬ ኃይል
የተጎናጸፍክ ፡ መብረቅ
በክንፍህ ፡ እኛን ፡ ጠብቅ

    ፨ ሰአል ፡ ሚካኤል ፡ ሰአል
    ፨ ነዓ ፡ መልአኩ ፡ ለቃል

ሥዩመ ፡ አእላፍ ፡ ነገድ
ለሥዕልህ ፡ እንስገድ
የተላፊኖስ ፡ አጋዥ ረዳት
ነፍሳችንን ፡ ታደጋት

     ፨ ሰአል ፡ ሚካኤል ፡ ሰአል
     ፨ ነዓ ፡ መልአኩ ፡ ለቃል

🔴 አዲስ ዝማሬ "ሰአል ለነ ሚካኤል"
https://youtu.be/zVf7KyC81_g
👍8👏21
👍8
╔​✞═ ●◉ ↺†↻ ◉● ══ ✞╗
✥ "#በእንተ_ቅዱሳን_ነቢያት" ✥
╚✞═ ●◉ ↺†↻ ◉● ══​ ✞╝

ይኽ ወቅት «ሊመጣ ያለውን አምነው ያስተማሩ ክቡራን የሚሆኑ ነቢያትን አንስተንና አውስተን ከእነርሱ ጋር አንድ አድርገን ብለን እንለምንሐለን»… የሚለውን የ"በእንተ ቅድሳት" ተማጽኖ በጉልህ የምንዘክርበት የጾመ ነቢያት ወቅት ነው!

«በእንተ ቅድሳት» ከ፯ቱ ኪዳን አንዱ የሆነ ጌታችን ቅድመ ዕርገት፣ ድኅረ ትንሣኤ ያስተማረው ትምህርት ነው።

"#በእንተ_ነቢያት_ቅዱሳን ናስተበቍዕ ከመ እግዚአብሔር ምስሌሆሙ ይኈልቈነ … ቅዱሳን ስለሚሆኑ ነቢያት ከእነርሱ ጋር እግዚአብሔር ይቆጥረን ዘንድ እንማልዳለን!" (አሜን!)

ስለ ጾመ ነቢያት ፍትሐ ነገሥታችን እንዲህ ይላል፦

✧ ወይከውን ከመ ረቡዕ ወዓርብ፤
✧ ወውእቱ ጾም ዘይቀድም እምልደት፤
✧ ወጥንተ ዚኣሁ መንፈቀ ህዳር ወፋሲካሁ በዓለ ልደት። ⇋↴
የነቢያት ጾም እንደ ረቡዕና እንደ ዐርብ የሆነ፤ ይኸውም ከልደት አስቀድሞ የሚጾም መጀመሪያው የሕዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል የሆነ ጾም ነው። (፲፭፥፭፻፷፰)

« እንደ ዓርብ ረቡዕ ዘጠኝ ሰዓት የሚጾም ጾም አለ፦ ይኸውን ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾመ ስብከት (ጾመ ነቢያት) ነው ። መጀመሪያው የህዳር እኩሌታ (ሕዳር ፲፭) ፋሲካው በልደት በዓል(በየዓመቱ ታኅሳስ ፳፱ እና በየ፬ ዐመቱ ታኅሳስ ፳፰) ነው »

ይህነንም፦
#ጾመ_አዳም ይለዋል ፦ ለአዳም የተነገረው ትንቢት ስለ ተፈጸመለት፤
#ጾመ_ነቢያት ይለዋል ፦ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት።
#ጾመ_ሐዋርያት ይለዋል፦ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጹመን እናከብራለን ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብራለን ብለው ሐዋርያቱም ጹመውታልና።
#ጾመ_ፊልጶስ ይለዋል ፦የአፍራቅያ ሰዎች ፊልጶስን በህዳር በ፲፯ ቀን ገደሉት ደቀመዛሙቱ እንቀብራለን ብለው ቢሔዱ ተሠወራቸው ሱባዔ ገቡ በለው ቢሔዱ ተሠወራቸው ሱባዔ ገቡ በሦስተኛው ቀን ትገለጸላቸው እሱን ቀብረው ጾሙን ጀምረን አንተውም ብለው ጹመውታል።
#ጾመ_ማርያም ተብሏል፦ እመ ትሕትና እመቤታችን ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ ብላ ጹማለች።

በብዙዎቻችን ዘንድ ጾመ ነቢያት በሚለው የሚገለጽ በመሆኑ ይህን ይዘን ክብረ ነቢያትን በጥቂቱ እንመለከታለን።

በመንፈቀ ሌሉቱ የኪዳን ምስጋና ክፍል እንዲህ የሚል ቃል ይገኛል ፦
✧ ዘበመስቀልከ አቅረብከነ ኀበ አቡከ መልዕልተ ሰማያት
✧ በወንጌል መራሕከነ
#ወበነቢያት_ናዘዝከነ
✧ ዘለሊከ አቅረብከነ አምላክ ⇋↴
በመስቀልህ በጌትነት ወዳለ ወደባሕርይ አባትህ ያቀረብከን አምላክ በወንጌል (ፍኖተ ሕይወትን) መራኸን ፣ በነቢያት ያረጋጋኸን ራስህ (በሥጋ ተገልጠህ በኩነት) ወደራስህ ያቀረብከን አምላክ ፈጣሪ … " ነቢያት እግዚአብሔር በተስፋ ፍጥረትን ያረጋጋባቸው «የሕዝብ ዐይኖች» ፣ ከሰው ልጆች ጋር የተነጋገረባቸው «የእግዚአብሔር አፎች» ናቸው!

ነቢያት ያለው የነቢይን ብዙ ቁጥር ነው:: መነሻ ግንዱ ተነበየ ትንቢት ተናገረ : ሊመጣ ያለውን አወቀ ማለት ነው:: ሀብተ ትንቢት ያለፈውን ያለውንና ሊመጣ ያለውን የሚያውቁበት ሰማያዊ ስጦታ ነውና ምንጩ የሚለምኑትን በልግስና ለሁሉ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው::( "ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።"ያዕ. 1:5)
ማንም በዘፈቀደ ከልቡ ሰሌዳ ከህሊናው ጓዳ አፍልቆ ከራሱ አንቅቶ ሊናገረው የማይችል ይልቁንም እምነት ከምግባር እንደነፍስና ሥጋ ተዋህዶላቸው የሚኖሩ መንፈሳውያንና መንፈሳውያት ልዑካነ እግዚአብሔር ከሣቲ በተባለው ምስጢር ገላጭ ጰራቅሊጦስ ተመርተው የሚናገሩት መልእክት ነው ትንቢት የሚባለው! (2ኛ.ጴጥ. 1:21 "ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።")::

አናጋሪው የእግዚአብሔር አካላዊ እስትንፋስ(መንፈስ ቅዱስ) ነውና በጸጋ "እስትንፋሰ እግዚአብሔር" ይባላሉ ለዚህም ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ ዳግማዊ ያሬድ ዘጋስጫ አባ ጊዮርጊስ በሰአታት ምስጋናው "እግዚአብሔር ዘበነቢያት አስተንፈሰ ከመ ያስምዕ ቃሎ ለሕዝብ" ሲል ገልጧል::

በትንቢት ሀብት ተናጋሪዎቹም ወንዶች አልያም ሴቶችም ሊሆኑ ይችላሉ በክብራቸውም የተለዩ፣ የተመረጡ፣ የተመሰገኑ፣ የተባረኩ በመሆናቸው በማዕረግ #ቅዱሳን..... #ቅዱሳት..... እየተባሉ ይጠራሉ:: (ሉቃ 1:69 "ከጥንት ጀምሮ በነበሩት በቅዱሳን ነቢያት አፍ እንደ ተናገረ....." 2ኛ.ጴጥ. 3:2 "በቅዱሳን ነቢያትም ቀድሞ የተባለውን ቃል በሐዋርያቶቻችሁም ያገኛችኋትን የጌታንና የመድኃኒትን ትእዛዝ እንድታስቡ.......")

ይህ ቅዱስ የሚለው ቅጽል ሀብቱ ሳይሰጣቸው በሃሰት ትንቢት ከሚናገሩት ነቢያተ ሀሰት ለይተን እንድናውቃቸው የሚረዳን ነው ምክንያቱም በመንፈስ ቅዱስ ሳይቃኙ ከንቱነትን የሚያስተምሩ : ሃሰት የሚናገሩ "ነቢያት" አሉና( ኤር: 23:16,25 "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ ከንቱነትን ያስተምሩአችኋል ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ ልባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።…አለምሁ አለምሁ እያሉ በስሜ ሐሰትን የሚናገሩትን የነቢያትን ነገር ሰምቻለሁ።")

በዚሁ ንጽጽር ጌታችንንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም በነጠላው "ኢየሱስ" አልያም "ክርስቶስ" ብቻ እያልን የማንጠራው ክብሩን ገልጠን ለመክበር እንድንበቃ ከመሻት ብቻ የመነጨ ሳይሆን በስሙ ከሚመጡ ሃሳውያን ለመለየትም ጭምር እንጂ (ማቴ. 24:24 "ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ።" 2ኛ . ቆሮ. 11:4 " ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ......") ይላል። በዚኽ መነሻ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስንለው ለእርሱ መገዛታችንን መመስከር፣ ክብሩንና ማንነቱን መግለጽ ብቻ ሳይሆን ከሀሳዊ መሲህ ለይተን ማመልከታችንም በውስጡ ይገኝበታል።

ቅዱሳን ነቢያት የእግዚአብሔር ታማኝ አገልጋዮችና እውነተኛ ወዳጆች ናቸው:: እርሱም እጅግ ያከብራቸዋልና ምስጢሩን እየገለጠ ይነግራቸዋል እንዲያውም ሊያደርግ "ካሰበው" አንዳች ከእነርሱ የሚሰውረው እንደሌለ ሲናገር "እስመ አልቦ ዘይገብር እግዚአብሔር ዘኢነበበ ወዘኢከሰተ ለአግብርቲሁ ነቢያት"( በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።) ይላል አሞ. 3:7..... ለዚህም ነው ቤተክርስቲያናችን በቅዳሴዋ ላይ በዲያቆኑ መሪነት እንዲህ እያለች የምታውጀው "እመቦ ዘያስተሃቅር ነቢያት ያግህስ ርእሶ እምመአተ ዋህድ ወያድህን ነፍሶ...."(ነቢያትን የሚያቃልል ቢኖር ከአንዱ ወልድ መአት ራሱን ያርቅ ነፍሱንም ያድን).... ልበ-አምላክ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊትም "የቀባኋቸውን አትዳስሱ፥ በነቢያቴም ክፉ አታድርጉ ብሎ፥ ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።" እያለ በዝማሬ ስለክብራቸው መሰከረ ( 1ኛ.ዜና መዋ. 16:21-22)
👍91
በጉልህ ነቢያት እያልን የምንጠራቸው ብዙኃኑ በዘመነ ብሉይ ተነስተው ~~~> ስለ ዓለም ድኅነት መገለጫ : ስለጽድቅ ፀሐይ መውጫ : ስለ አዳም ተስፋ ፍጻሜ : ስለ ሰው ልጆች ሁሉ እርቅ ድምዳሜ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው የተናገሩትን ነው! (1ኛ .ጴጥ. 1:10 "ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት") በአጠቃላይ "ተስፋሆሙ ለነቢያት= መድኃኒት እንተ ዖድዋ ወሃሰስዋ ነቢያት" ስለተባለች ስለ እመቤታችን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም አብዝተው የተነበዩ እኒሁ ቅዱሳን ነቢያትን ናቸው፤ መጽሐፍ «ንግርት በነቢያት» እንዲላት እርስዋ፦ ወለተ ነቢያት፣ ዜና ነቢያት፣ ትንቢቶሙ ለነቢያት፣ ውድስት በአፈ ነቢያት፣ አርጋኖነ ስኩራነ መንፈስ ነቢያት፣ ተብላለችና!

ቢሆንም ግን አገልግሎቱና በሀብቱ የሚያገለግሉ ነቢያቱ በክብራቸው በብሉይ ያለፉ ለሀዲስ ኪዳን የወንጌል ክብር ያልተረፉ የሚመስላቸው አሉ፤ ነገር ግን ጌታችን የትንቢት እና የነቢያቱ ክብር የማይሻር መሆኑን በወንጌል እንዲህ ያስተምረናል፦ "ኢመጻእኩ ከመ እስአሮሙ ለኦሪት ወለነቢያት ዘእንበለ ዳእሙ ከመ እፌጽሞሙ… እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም" (ማቴ. 5:17 ) በተለይ እኛ በዘመነ ሀዲስ ያለን ምዕመናን የሃይማኖታችን መሠረት የነቢያት ትንቢትና የሐዋርያት ስብከት ነውና ቦታ ሰጥተን ልናስባቸው ይገባል "በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤" እንዲል (ኤፌ.2:20) ......ታዲያ ክርስቶስ ለቅዱሳን ነቢያቱና ሐዋሪያቱ መሠረታቸው ሆኖ እነርሱን ለእኛና ለቤተክርስቲያን መሰረት ባደረገልን (አንተ መሠረት ነህ ባንተ መሠረትነት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ እንዳለው ማቴ 16:18) በክርስቶስ የምንታመን ውሉደ ጥምቀት የቤተክርስቲያን ልጆች እነዚህን መሠረቶች ልንዘክራቸውና ዘወትር ልናስባቸው ወደ እነርሱም ልንመለከት ይገባል።

ምክንያቱም፦
እነርሱን መዘከርና ማክበር ዘክሯና አክብሯቸው ካለ የክብር ባለቤት አምላካቸው ዘንድ ለእኛ የእነርሱን ዋጋ ያሰጣልና "ዘተወክፈ ነቢየ በስመ ነቢይ አስበ ነቢይ ይነስእ"(ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል " እንዲል። (ማቴ. 10:41)

በመከራና በትእግስት ጸንተው ከማእከለ እሳት :ከአፈ አናብስት: ከጽኑ ስለት ሊያድናቸው የሚችል አምላካቸውን አምነውና ለተሰጣቸው አገልግሎት ታምነው በጽኑ ተስፋ ሃይማኖታቸውን የጠበቁ እነዚህን ነቢያት መመልከት ደግሞ ከህይወታቸው ለመማር የቀረልን ምሳሌ ነው:: ለዚህም ሐዋርያው እንዲህ ሲል እንዳዘዘን “አርአያሃሰ አኀዊነ ለትዕግስተ ተጽናስክሙ ብክሙ ነብያት እለ ተናገሩ በቃሉ ለእግዚአብሔር… ወንድሞች ሆይ፥ የመከራና የትዕግሥት ምሳሌ የሆኑትን በጌታ ስም የተናገሩትን ነቢያትን ተመልከቱ።"ያዕ 5:10

በጾመ ነቢያት ነቢያቱን በማዘከርና በስማቸው በመማጸን ደጅ እየጠናን እንድንቆይ አምላከ ቅዱሳን ሁላችንንም ያበርታን! ካህኑ በቅዳሴው ፍፃሜ ⇋↴
«#ያብእክሙ_ኀበ_ሀለዉ_ማኅበረ_ነቢያት_ቅዱሳን» እንደሚል ቅዱሳን የሚሆኑ ነቢያቱ ወዳሉበት ማኅበር በቸርነቱ ሁላችንን ያግባን!

(ከቴዎድሮስ በለጠ ~~~> ሕዳር ፲፬ ቀን ፳፻፲፩ ዐ.ም )
👍6👏52
2025/07/14 21:55:12
Back to Top
HTML Embed Code: