Telegram Web Link
ቅብዐ በለሳን / ቅብዐ ሜሮን ምንድነው?
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥

የቤተክርስቲያናችን ምሥጢራት ዋናው ጥቅማቸው ማንጻትና መቀደስ ነው። ጥምቀት ያነጻል ሜሮን ይቀድሳል ፣ ንሰሐ ያነጻል ቁርባን ይቀድሳል … ይህን ይዘው ሊቃውንት መንጻት የቤተክርስቲያን አባል መቀደስ የክርስቶስ አካል ወደመሆን ያደርሳል (በጸጋ) ይላሉ።

ያለ ሜሮን (የበለሳን ቅብዓት) የሚሆን የቅድስና ክብር መቀበያ መንገድ አለመኖሩን መጻሕፍቱም ሊቃውንቱም አንድነት ይመሰክራሉ ፤ ለቅድስና የሚሆነው ቅድሳት (ቁርባን) እንኳ በሚሮን በከበረ መንበር ላይ እንደሚፈተት ተመልክቷል " ትረክብ ኅብስተ ዲበ ጠረጴዛሃ ዘኅቱም በቅብዐ ሜሮን ⇨ በሜሮን ዘይት በታተመ በመንበሩ ላይ ኅብስቱን ታገኘዋለህ" ይላል። (መጽሐፈ ምሥጢር)

ወቅቱ የሜሮን ምንጭ የሆነው በለሳን የተገኘበት ዘመነ ጽጌ ነው። በቤተክርስቲያናችን ትውፊት በሐዲስ ኪዳን የሜሮን መገኛ ጌታችን በልጅነት ከእናቱ ጋር ሲሰደድ በመንገድ ከሰውነቱ የወጣው ወዝ የነጠበበት ቦታ ከበቀለ የበለሳን ዛፍ እንደሆነ እንዲሁም ሰሎሜ ልብሱን ስታጥብ ከአካሉ ወደልብሱ ያለፈ ሆኖ ብትጨምቀው ያገኘችው ወዝ ራሱ ሜሮን መሆኑን መጻሕፍት ይነግሩናል (ፍትሐ ነገሥት፣ ስንክሳር ፣ የጽጌ ማሕሌት ክፍል ሰቆቃወ ድንግል… )

ኀበ ሐፀበት በማይ አልባሲሁ ወአባሎ
ለሕፃነ ድንግል ዝኩ ሰሎሜ ዘተሐዝሎ
በለሳነ ኮነ ሐፈ ሥጋሁ በቊሎ
ሜሮን ቅብዕ ዘይቄድስ ኵሎ
ለትእምርት በኀቤነ እስከ ዮም ሀሎ።

(ሰሎሜ የምታዝለው የዚህ የድንግል ማርያም ልጅን ልብሱንና ገላውን በውሃ ባጠበች ጊዜ(እያጠበች ሳለ) የገላው ወዝ ሽቱ በለሳን (ሜሮን) ሆነ ይህም ሜሮን ሁሉን የሚያነፃ፣የሚያከብር ነው በእኛ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድም ለምልክት በጎ ሥርዓት ሆኖ እስከዛሬ ድረስ አለ፡፡)
【ሰቆቃወ ድንግል ክፍል ፴፰】

በቅብጣውያኑ ዘንድ ያለፈው ዓመት ሜሮን ለ፵ኛ ጊዜ መዘጋጀቱን እናስታውሳለን (The preparation of the Holy Chrism) https://fb.watch/gwkFbX6SDZ/

በእኛ ዘንድ ደግሞ ዘንድሮ ዛሬ ሌሊቱን ይኽን ታላቅ ምሥጢር ከተገኘበት ወቅት ጋር በማያያዝ ለ፫ኛ ጊዜ ሲፈጸምልን አድሯል https://fb.watch/gwr0afBuIC/

"ለእኛ ሜሮን ምናችን ነው?"

★ ማኅተመ እምነት ውእቱ
#የእምነታችን_ማኅተም_ነው! 【መጽሐፈ ምሥጢር】
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

"ክርስቶስ ፈጣሪዬና ተስፋዬ ነው የአባቱም ስም የድኅነቴ ዘወድ ነው፤ የመንፈስ ቅዲስም ስም የክብሬ መገኛ ነው፤ የመስቀሉም ክብር የመመኪያዬ ዘውድ ነው። እመቤቴ ድነግል ማርያምም የገነቴ በር ከፋች ናት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም የጥምቀቴ መገኛ ናት፤ ሐዋርያትም አጥማቂዎቼ ናቸው፤ ቅብዓ ሜሮንም የእምነቴ ማኅተም ነው፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡"

★ ኃይለ ሃይማኖት ውእቱ
#የሃይማኖት_ኃይል_ነው 【መጽሐፈ ድድስቅልያ】
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

” ከተጠመቁም በኋላ ኤጲስ ቆጶሱ ቅብዐ ሜሮኑን ይቀባቸው ፤ በክርስቶስ በሞቱ አምሳል ተጠምቀዋልና ። ይኸውም ከበለሳን የተገኘ ቅብዓ ሜሮን የሃይማኖት ኃይል ነው ።”

★ ወቦቱ ይትገበር መድኃኒት ወፈውስ ወምክሆሙ ለኵሎሙ መሲሐውያወን
⇨ ድኅነትና ፈውስ የሚደረግበት የክርስቲያኖች ሁሉ #መመኪያችን_ነው 【መጽሐፈ ስንክሳር】
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

" ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት ። ከዚያም ወጥተው ወደ መጣርያ ደርሰው በውስጧ ታጠቡ ። ይቺም የውኃ ምንጭ አስቀድመን እንደተናገርን ጌታችን ያፈለቃት ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የተባረከችና የከበረች ሆነች ። ከዚያም ጌታችን የተከለው የክርስትና ጥምቀት የሚፈጸምበት በለሳን ቅባት የሚወጣው ነው ። በእርሱም ደግሞ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅድሳትና ታቦተ ሕጉም የሚከብርበት ድኅነትም የሚደረግበት ለክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያቸው ነው ።"

ከዚህ በማስከተል እጅግ ጥቂት ማጎልበቻ ሐሳብ አክዬበት ሀብታችንና ሥርዓቱ በሚል ርእስ ከተዘጋጀ መጽሐፍ በክፍል ስምንት የሜሮን ምሥጢር በሚል የቀረበውን አስተማሪ መልእክተ ቤተክርስቲያን በዐሥር ነጥቦች በመክፈል ላካፍላችሁ

፩) የሜሮን ስያሜና አመዳደብ
ሜሮን በጽርእ ቋንቋ “ሚሮስ” ይባላል። በግእዝም ሆነ በአማርኛ ብዙም ከጽርኡ አባባል ሳይርቅ ሜሮን እየተባለ ይጠራል። 【ሜሮን የሚለውም በጽርእ ይገኛል μύρον ⇝ mýron ራእ ፲፰፥፲፫ 】ቅብዕ ቅዱስ ወይም የተቀደሰ ቅባትም ይባላል።
በቤተክርስቲያናችን ከሰባቱ የቤተክርስቲያን ምሥጢራት አንዱ ነው። በቅደም ተከተል ከሰባቱ ምሥጢራት ሁለተኛው ምሥጢር ምሥጢረ ሜሮን ነው። ከጥምቀት በኋላ ለተጠማቂው የሜሮን ሥርዓት ይፈጸምለታል።

፪) የሜሮን ዝግጅት
ሜሮን «በለሳን» ከሚባል ዛፍና ከልዩ ልዩ የዕጣን እንጨቶች ከሌሎችም ከብዙ ዓይነት 40 ከሚያህሉ መልካም ሽታ ካላቸው እፀዋት ተቀምሞ የሚዘጋጅ ንጹሕና ቅዱስ ቅባት ነው።
እነዚህ እፀዋት ልዩ ልዩ የቤተክርስቲያናችንና ሌሎችም ተቀራራቢ መጻሕፍት እንደሚሉት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሁላችን ቤዛ ለመሆን በለበሰው ሥጋ ምክንያት ከድንግል እናቱ ከቅድስት ማርያምና ከቅዱሳን አገልጋዮቹ ከቅዱስ ዮሴፍና ከቅድስት ሰሎሜ ጋር በሕፃንነቱ በተሰደደ ጊዜ የምታዝለው ሰሎሜ አካሉንና ልብሶቹን በውኃ ባጠበችበት ቦታ በፈሰሰው በአካሉ ወዝ (ላብ) ላይ የበቀለ በለሳን የሚባለው ዛፍ ክፍሎች እንደሆኑ ይገመታል። ስለዚህ ከነዚሁ ከተጠቀሱት እፀዋት ልዩ ልዩ ክፍል ሜሮን ይዘጋጃል ማለት ነው።”

ኀበ ሐፀበት በማይ አልባሲሁ ወአባሎ
ለሕፃነ ድንግል ዝኩ ሰሎሜ ዘተሐዝሎ
በለሳነ ኮነ ሐፈ ሥጋሁ በቊሎ
ሜሮን ቅብዕ ዘይቄድስ ኵሎ
ለትእምርት በኀቤነ እስከ ዮም ሀሎ።
(ሰሎሜ የምታዝለው የዚህ የድንግል ማርያም ልጅን ልብሱንና ገላውን በውሃ ባጠበች ጊዜ(እያጠበች ሳለ) የገላው ወዝ ሽቱ በለሳን (ሜሮን) ሆነ ይህም ሜሮን ሁሉን የሚያነፃ፣የሚያከብር ነው በእኛ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድም ለምልክት በጎ ሥርዓት ሆኖ እስከዛሬ ድረስ አለ፡፡)

፫) በለሳን ምንድር ነው?
በለሳን ዛፍ ወይም የሽቱ እንጨት ነው። ታላቁ ሊቅ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ እንደሚከተለው አብራርተውታል። በለሳን ሽቱ (የሽቱ እንጨት ስም) በይሁዳና በገሊላ ይልቁንም በኢያሪኮ የሚበቅል ከዕፀወ–ዕጣን አንዱ መጀመርያው ነው። ሽታው ከሽቱ እንጨት ሁሉ የሚበልጥ ኤጲስቆጶሳት ቅብዐ ቅዱስ (ሜሮን) የሚያደርጉት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ በልዩ ልዩ ሊቃውንት ቅንጅት የተዘጋጀው «የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላትም» «በለሳን» ከአትክልት ወገን የሚሆን ጥሩ ሽቱነት ያለው ቁጥቋጦ ሙጫው ወይም ዘይቱ ተነጥሮ ለቁስል ማለስለሻ ቅባት ይሆናል። (ይህም ርጢን እየተባለ በሊቃውንቱና በመጻሕፍት ሲጠራ እንሰማለን ቅባቱ ከገለአድ አገር ስለሚገኝ «በገለአድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? » ተብሎ ይተረት ነበር ይላል። "አልቦኑ ርጢን ውስተ ገለዓድ" እንዲል)
👍133
ስለ ሜሮን ዝግጅት በሚናገረው ክፍል ፍትሐ ነገሥቱ በለሳን የጌታችን ወዝ (ላብ) በፈሰሰበት ቦታ የበቀለ እንጨት እንደሆነ የተገለጠውን የሚደግፍ አለቃ ኪዳነ ወልድ ደራሲው የተናገረውን በመጽሐፋቸው እንደሚከተለው አስፍረውታል። «ዝንቱ በለሳን ዘተከልናሁ ይነብር ዝየ እስከ ለዓለም። ቅብዐ በለሳን በእንተ በለሳን ወዕጣን ተኀትመ ገጾ በቅብዐ በለሳን። በለሳነ ኮነ ሀፈ ሥጋሁ በቈሎ።»

፬) የሜሮን ዝግጅት ፦
ዝግጅቱን በሚመለከት መጽሐፈ ሥርዓት ወሕግ ፍትሐ ነገሥት ይህን ይላል  "ሜሮን…  ጌታ ወደ ግብፅ ሲሔድ ሰውነቱ ወዛ (አላበው)  ወዙ ከነጠበበት ቦታም በለሳን የሚባል ዕፅ በቀለ … ሐዋርያት ይህን ቆርጠው ቅርፍቱን ከትፈው በዕለተ ዓርብ ከጎኑ የፈሰሰ ደሙን የመስቀሉን የመግነዙን አግቢ ጨምረው በሐዲስ ሸክላ አድርገው በስኒ ባሥር ቀን ጸለዩበት በመንፈስ ቅዱስ እሳትነት ፈልቶ ሜሮን ሆነ በዚህ አዲስ ታቦት ያከብሩበታል ልጅነት ይሰጡበታል … "

፭) የሜሮን አዘጋጅ
ሜሮንን ማንኛውም ሰው ማዘጋጀት አይችልም ከካህናትም እንኳን ዲቁና እና ቅስና ብቻ ያላቸው ሁለቱ ማለትም ዲያቆንና ቄስ ሜሮንን ማዘጋጀት አይችሉም። ሜሮንን የማዘጋጀት መብትና ሥልጣን ያለው የኤጲስቆጶስነት ሥልጣን ያለው የአንዱ የክህነት ደረጃ ባለቤት ኤጲስቆጶስ ብቻ ነው።

፮) የሜሮን አገልግሎት
ተጠማቂው በጥምቀት አማካኝነት ከአምላኩ ከእግዚአብሔር በጸጋ ሁለተኛ እንዲወለድና የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆኖ እንዲቆጠር፣ በክርስቶስ ክርስቲያን ወይም ክርስቶሳዊ ተብሎ ከስም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም እንዲያገኝ ብሎም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ያባቱን የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲወርስ በአጠቃላይ በአባቱ በአዳም በደል ምክንያት የተወሰደበትን ሀብት ሁሉ መልሶ እንዲያገኝ የሚረዳው መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኋላ ዳግም ልደቱን የሚያረጋግጥበት ማኅተም ነው።” ሜሮን የሰማይና የምድር ንጉሥ እግዚአብሔር በመልኩና በምሳሌው ለፈጠረው ሰው ለሚሰጠው ጸጋ ሁሉ የሚያረጋግጥበት ማኅተሙ ነው።

በዘመነ ሐዋርያት ተጠማቂው ክርስትናውን ወይም ዳግም ልደቱን የሚያረጋግጠው «በአንብሮተ ዕድ» አማካኝነት ነበር። በኋላ ግን ወደ ክርስትናው የሚገባው ሕዝብ እየበዛ ሲሄድ እጅን የመጫኑ ሥርዓት ጊዜ   የሚወስድና ብዙ የሰው ኃይልን የሚጠይቅ በመሆኑ እንደሚታወቀው የካህናት እጥረት ስለ ነበረ ለተቀላጠፈ የሥራ ክንውን ሲባል የአንብሮተ ዕድን ቦታ ሜሮን ያዘ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በሜሮን (በቅብዕ ቅዱስ) መጠቀም ተጀመረ።

፯) ሜሮን በብሉይ ኪዳን
የስያሜ፣ የአጠቃቀም፣ የአዘገጃጀትና የመሳሰሉት ሁኔታዎች የተለያዩ ቢሆኑም በተለይ ሜሮን ከምን ይዘጋጃል? የሚለው ጥያቄ በአዲስ ኪዳን የበለጠ ክብርና ትርጉምን ስላገኘ ከአምላክ ሥጋዌ ጋር የተያያዘ ትንታኔ ቢሰጠውም ቅሉ ቤተክርስቲያን ከብሉይ ኪዳን እንደተረከበቻቸው እንደ አብዛኛዎቹ ንዋያተ ቅድሳት ብሉይ ኪዳናዊ መሠረት ያለው ነው። በመሆኑም በቅዱስ ቅባትነቱ በዘመነ ብሉይም ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ጸጋዎች ይተላለፉበት ነበር። ልዑል እግዚአብሔር ቅዱሳት ሕጐቹን በጣቱ በጽላቱ ላይ ቀርጾ ለሰጠው ለባለሟሉ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ የሜሮንን አሠራር ቅዱስነትና አገልግሎቱን በሚገባ ገልጾለታል። ነቢዩም በታዘዘው መሠረት አሮንንና ልጆቹን ለክህነት ልዩ ልዩ ዕቃዎችን ለቤተ መቅደሱ መገልገያነት ሲለይ በዚሁ ቅዱስ ቅባት አማካኝነት ነበር ስለዚህ ሀብተ ክህነትን ሀብተ መንግሥትን ሀብተ ትንቢትን የሚያገኙት በሜሮን አማካኝነት በሚሰጣቸው መንፈስ ቅዱስ ነው ማለት ነው።

፰) ሜሮን በአዲስ ኪዳን
አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት ይህ ቅዱስ ቅባት እጅ የመጫኑን ቦታ ከመያዙ በፊት የእግዚአብሔር የጸጋው መተላለፊያ እንደሆነ በተለያየ አገላለጽ በመልእክቶቻቸው ጽፈውልናል።'
- የሜሮን ምሥጢርነት ከግዙፍ ነገር በተዘጋጀ በዓይን በሚታይና በእጅ በሚዳሰስ ቅዱስ ቅባት አማካኝነት በሥጋዊ ዓይን የማይታይና በሥጋዊ እጅ የማይዳሰስ ወደር የሌለው የእግዚአብሔር ጸጋ የሚተላለፍበት ስለሆነ ይህ የሚተላለፈው ጸጋ በሜሮን አማካኝነት የሚገኝ በመሆኑ የሜሮን ምሥጢር ተባለ።”

፱) የሜሮን አቀባብ ሥርዓት
የጥምቀቱ ሥርዓት ካለቀ በኋላ ዲያቆኑ የተጠመቁትን ነፍስ ያወቁ ከሆኑ ራሳቸውን ጐንበስ አድርገው እንዲቆሙ ያዛቸዋል። ኤጲስቆጶሱ ወይም ቄሱ ሜሮኑን ይዞ በተጠማቂዎቹ ፊት ለፊት ሆኖ ይጸልይላቸዋል።

☞ የተጠማቂዎቹን ግንባር በመስቀል ቅርፅ እየቀባ እፍፍፍ... ይልባቸዋል።  «የዘለዓለም ሕይወትን ለመቀበል ቅዱስ ቅባትን እቀባሃለሁ (እቀባሻለሁ)» እያለ እያንዳንዱን ተጠማቂ ሁለቱን የአፍንጫ በር ሁለቱን ከንፈሮች፣ ሁለቱን ጆሮዎች፣ ሁለቱን ዓይኖች ደረትን፣ (ልብን) ከመሃል ራስ አስከ ወገብ ድረስ አንድ ጊዜ፣ መሃል ጀርባን፣ እንብርትን ይቀባል። «በማይፈታ በአምላክ መሲህ ማሕተም እቀባሃለሁ (እቀባሻለሁ) አሜን» እያለ ሁለቱን እጆች የሁለቱን እጆች መገናኛዎች ሁለቱን ትከሻዎች ማጅራትን አንገትን የሁለት እጆችን ክርኖች የሁለት እጆችን መዳፍና ጀርባ ይቀባል።  «ቅዱስ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን (የጰራቅሊጦስን) ቅባት እቀባሃለሁ (እቀባሻለሁ)» እያለ ሁለት ዳሌዎችን፣ ሁለት ጉልበቶችን፣ | የሁለት እግሮች ጣቶችን በውስጥም በውጭም ከቀባና ከጨረሰ በኋላ፣ በተጠማቂዎቹ በተራ በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን ጭኖ  «በሰማያውያን መላእክት በረከት የተባረክህ (የተባረክሽ) ሁን (ሁኚ)»  እያለ ይባርካቸዋል። በመጨረሻም ተጠማቂዎች ነጭ በነጭ ለብሰው በራሳቸው ላይ አክሊል'' ያደርጋሉ ወዲያውኑ ሳይውሉ ሳያድሩ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ይቀበላሉ።

፲) የሜሮን ሌላው አገልግሎት:-
  ሜሮን የማይመረመረው የእግዚአብሔር ጸጋ የሚናኝበት ቅዱስ ቅባት እንደ መሆኑ መጠን ጽላትና ታቦት ለሃያሉ አምላክ መገለጫና ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ ዙፋንነት እንዲበቃ የሚከብረው፣ አዲስ ቤተክርስቲያን ከሁሉ በላይ ወደምትሆን አንዲት፣ ቅድስት ዓለም አቀፋዊትና ሐዋርያዊት እንዲሁም ክርስቶሳዊት ወደ መሆን፣ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ከሥጋዊ መገልገያነት ወደ መንፈሳዊ መገልገያነት ከተራ ዕቃነት ወደ ቅዱስና የክብር ዕቃነት የሚለወጡትና የሚከብሩት፣ ሁለት ተቃራኒ ፆታዎች ለቅዱስ ጋብቻ ሲቀርቡ ፍጹም ኣንድነትን የሚያገኙት በሜሮን አማካኝነት በሚተላለፈው ጸጋ እግዚአብሔር ነው።'

ከጽሑፉ ጋር የተያያዘው ቪዲዮ ቅዱስ ቄርሎስ ፮ኛ የኢትዮጵያና የግብፅ ፓትርያርክ በ፲፱፶፱ ወርኃ ሚያዚያ በሰሙነ ሕማማት በካይሮ የቅዱስ ማርቆስ ካቴድራል ኢትዮጵያን ተወካዮች ጭምር በተገኙበት የቅብዐ ሜሮን ዝግጅቱን ሲመሩ የሚያሳይ ነው።  (During Holy Week in April 1967; the procedure was conducted in St. Mark’s Cathedral, in the presence of the representatives of the Ethiopian church, the metropolitans, the bishops, the priests and the monks)

✍️ ከቴዎድሮስ በለጠ (ጥቅምት ፳፪ –  ፳፻፲፭ ዓ.ም በሀገራችን ለሦስተኛ ጊዜ ሜሮን የማፍላት ሥርዓት ሲፈጸም  የተዘጋጀ)
👍83
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
20👍13
የዕርዳታ ጥሪ!
©
የወላጅ እናት የደካማዋ እናት ጥሪ...ህጻን ሴት ልጅዋን እንድንታደግላት!

የደብረ ታቦር ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን "ጽርሐ ጽዮን ሰንበት ትምህርት ቤት" አባል የሆነችው እህታችን እመቤት ደበበ በደረሰባት የልብ ሕመም ምክንያት ለከፍተኛ ሕክምና ተዳርጋለች፤ ስለሆነም ለሕክምናዋ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠን ከ500,000 ሺህ ብር በላይ በመሆኑ ዘመድ አዝማድ አቅም ስለሌላቸው እርዱን ይሉናል...ተስፋ ያላት፣ ታዳጊዋን ሰንበት ተማሪያችንን እንታደጋት። በተቀረውስ እመቤታችን ትቅረባት!

ለበለጠ መረጃ 0919098025/0978742330

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 1000344731776(ፈሰሱ ወ/ፃድቅ ወላጅ እናቷ)

©
👍111
. የዕርቅ ምንጭ ቅብዐ ሜሮን
✥ °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°° ✥

አባ ጊዮርጊስ በሰአታት ምስጋናው ለኢትዮጵያ ገበዟ የሆነውን ጠላት የሚያሳፍርላትን ሊቀ ሰማዕታት በሚያነሳበት "የቅዱስ ጊዮርጊሱ ስብሐተ ፍቁር" ክፍል እንዲህ ይላል

. ጊዮርጊስ ዓምድ
በቅብዐ በለሳን ጽሑድ
ንስእለከ በወልድ
ከመ ትናዝዘነ ነዓ እምኃዝን ክቡድ

«ፍጹም ንጹሕ የሆንክ በሜሮኑ ቅብዓት
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ አምድና መሠረት
ስለ ወልድ ብለህ ስለአምላከ አማልክት
ደርሰህ አረጋጋን ከሐዘናችን ብዛት»
【መጽሐፈ ሰአታት ስብሐተ ፍቁር ዘቅዱስ ጊዮርጊስ】

ጭንቁንና መከራውን ያቀለለልን ኢትዮጵያን ሁሌም የማይረሳት አምላከ ቅዱሳን ፍጡነ ረድኤት ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስንና ማኅተመ እምነት ኃይለ ሃይማኖት ቅዱስ ሜሮንን የሰጠን አምላካችን የተመሰገነ ይሁን። 🙏

ሐዋርያዊቷ ቤተክርስቲያናችን ፣ ሲኖዶሳዊቷ አቅሌስያ ለ፫ኛ ጊዜ ቅብዐ ሜሮንን ለማፍላት በነበረው እጅግ አስደናቂ አገልግሎት ዛሬ ፯ኛ ቀን ጸሎቷ ሲከናወን አይተናል።
(https://youtu.be/4NfWoahoTYk)

(በጸሎቷም አጋማሽ በቅዱስ ጊዮርጊስ መታሰቢያ ዕለት የዕርቅ ዜና መስማታችንን ድንገቴ ነው እንደማንል አምናለሁ)

ቅብዐ ሜሮን የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ የጸጋው ማሻገሪያ ነው። መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ማለት ደግሞ መንጽሒ (የሚያነጻ)፣ መጽንዒ (የሚያጸና)፣ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኃጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የእግዚአብሔር መንፈስ ነው።
【መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት፣ ገጽ ፪፻፹፫)】

በቅዱስ መንፈስ ይኽ ሁሉ ይሠጣል ፦ ደስታን ፣ መረጋጋትን ፣ ጽናትን ፣ ሥርየተ ኃጢዓትን ፣ መንጻትን ፣ ማስተዋልን… እኛስ ከዚህ ውጪ ምን አጣን!?

ኀዘነተኞች አልነበርንም? የተቅበዘበዝን አልነበርንም? የተናወጽን አልነበርንም? በኃጢዓት የተዳደፍን አልነበርንም? የቆሸሽን አልነበርንም? ዞሮ ማየትና አስተውሎ መረዳት የራቀን አልነበርንም? በቸርነቱ ይታረቀን።

ምክንያቱ ደግሞ ይኽ ነው!

" ወእለሰ መንፈስ ቅዱስ አልቦሙ ይከውኑ ማኅደረ ለአጋንንት ርኩሳን፤ እስመ ጰራቅሊጦስ ይጸልእ ሐሰተ ወኵሎ ምግባረ እኩየ፤ ወዲያብሎስ ይጸልእ ምግባረ ጽድቅ ወምግባረ ሠናይ ⇨ መንፈስ ቅዱስ የሌለባቸው ሰዎች ለርኩሳን አጋንንት ማደሪያ ይሆናሉ ፣ መንፈስ ቅዱስ ሐሰትንና ክፉ ሥራን ሁሉ ይጠላልና ፣ ዲያብሎስም የጽድቅ ሥራንና መልካም ሥራን ይጠላል"
【መጽሐፈ ዲድስቅልያ ፴፫ ፥፪፻፱】

በሀገራች የሜሮን ሥርጭት ካለቀ (በተለይ በገጠሩ) 10 ዐመታት በላይ እንዳለፈ ሊቃውንት ይናገራሉ፤ ቅባት አሽገው የሚቸረችሩ ፣ በምግብ ዘይት «አጋንንት የሚያባርሩ» መበርከታቸው … በቅዱስ ቅብዕ ስለሚሠጠው አገልግሎት በመረጃ ማጣት ምእመናን ሲደናገሩ ታይቷል ፤ እንዲሁ ረሃብ ጦርነቱ ደዌ መቅሰፍቱ ከበረታብን መሰነባበታችንንም ልብ ይሏል።

የሥርዓት መጽሐፋችን እንዲህ እያለ ያመሰግናል

"እንደዚህ እናመሰግንሃለን ፦ የሁሉ ፈጣሪ ሆይ በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ስለገለጥክልን ሞት ስለሌለበት ስለዚህ ሜሮን መዓዛ ስለዚህ ዘይት እናመሰግንሃለን ፤ ክብር መንግሥት ኃይል ለእንተ ነውና ለዘለዓለሙ አሜን።"
【መጽሐፈ ዲድስቅልያ ፴፮፥፩】

የሜሮንን ክብር አናውቀው ብለን እንጂ ልጅ በኤጲስ ቆጶስ አልያም በቄስ የተጠመቀን ልጅ በቅብዐ ሜሮን ከብሮ ሲከብር ምዕመን ደፍሮ ሊታቀፈው እንደማይገባ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ያዛል
" ከዚህም በኋላ ዲያቆኑ ወንዶችን ይቀበላቸው ፣ ዲያቆናዊትም ሴቶችን ትቀበላቸው ፣ የተቀበሉት ማኅተም ሜሮን ማንም ማን ሊዳስሰው የማይችል ንጹሕ ቅዱስ ይሆን"
【መጽሐፈ ዲድስቅልያ ፲፮፥፴፭】
👍1
የአንዳንዶቻችን ጥያቄ ፦
"ሜሮን እንዴት በአደባባይ ይዘጋጃል? ¡"

ዛሬ ግን ስለ ሜሮን አፈላል ሳይቀር ከጳጳሳቱና ይኽን አጥንቶ መጽሐፈ ጸሎቱን አዘጋጅቶ ሥርዓቱን መርቶ ከቀረበው ሊቃውንት ጉባኤ በላይ እኔ አውቃለሁ የሚል ሥርዓት ነቃፊ አበውን በአደባባይ ዘላፊ «ተራ ሰው» ማየት በእጅጉ ያሳዝናል!

አንዳንድ መምህራን ግን በቅንነት "ኢትደዩ ባሕርየክሙ ቅድመ አሕርው" ያለውን ይዘው በቅንነት «እንደው በኅቡዕ ቢሆን» ሲሉ ተመልክቻለሁ፤ እንደግል ሐሳብ እኔ ግን ይህን ለማለትም የፌስቡክ አደባባይ ቦታው አይደለም የእናንተም በኅቡዕ ቢሆን እላለሁ።

አንድ አድራጊው መንፈስ ቅዱስ ስለሚያሠጠው ሜሮን አንድ የማያደርገንን የግል ሐሳብ ከማንሳት እንጹም
"ሀበነ ንኅበር በዘዚአከ መንፈስ ቅዱስየ⇨ የአንተ በሚሆን መንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ አንድነቱን ሥጠን"  እንዲል 【ቅዳሴ ሐዋርያት ቁጥር ፶፬】

ምሥጢረ ሜሮንን ምሥጢር የሚያስብለው በምሥጢር በመዘጋጀቱና በምሥጢር በመፈጸሙ ሳይሆን በሚታይ አገልግሎት የማይታይ ጸጋን በማሰጠቱ ፣ ስንቀባው የሚታይ ቢሆን ያደረው ረቂቁ መንፈስ ቅዱስ የማይታይ በመሆኑ ነው" ቀንዲል (የመብራት ዘይት) ፣ ጥምቀት (ማየ ጸሎት) … ሲዘጋጅ ሲፈጸምም ሥርዓቱ በአደባባይ ነው።  (ይህ ግን ለሁሉ አለመሆኑን ልብ ማለት ያሻል፤ እንደ ቁርባን ያለው በአደባባይ አይዘጋጅም አይፈጸምምና! )

ሁሉን አንድ ለማድረግ፣ የተጣሉትን ለማስማማት ለዕርቅ በተሠራው ሥርዓት እኛ ራሱ የሚለያይ ሐሳብ ማቅረባችን አባቶችን ለመንቀፍ ብርዕ ማንሳታችን ጤናማነታችንን የሚያስጠረጥር ነው…  እንደው ምን አይነት ጉደኞች ነን!

ስለ ሁሉ የምናውቅ ሁሉን እኛ ካላጸደቅን እንግዳ ነገር ሲመጣ ከማድነቅ ከመጠየቅ ይልቅ  ተችቶ መናቅ በዐደባባይ መሳለቅ የጤና ምልክት አይመስለኝም…

ይማረን ጥቂት ነጥብ ካለፈው ጽሑፍ ላጋራና ነገሬን ልቋጭ  https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=5579714008743732&id=100001155652281

"ለእኛ ሜሮን ምናችን ነው?"

★ ማኅተመ እምነት ውእቱ
#የእምነታችን_ማኅተም_ነው! 【መጽሐፈ ምሥጢር】
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

"ክርስቶስ ፈጣሪዬና ተስፋዬ ነው የአባቱም ስም የድኅነቴ ዘወድ ነው፤ የመንፈስ ቅዲስም ስም የክብሬ መገኛ ነው፤  የመስቀሉም ክብር የመመኪያዬ ዘውድ ነው። እመቤቴ ድነግል ማርያምም የገነቴ በር ከፋች ናት፤  ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም የጥምቀቴ መገኛ ናት፤  ሐዋርያትም አጥማቂዎቼ ናቸው፤  ቅብዓ ሜሮንም የእምነቴ ማኅተም ነው፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን፡፡"

★ ኃይለ ሃይማኖት ውእቱ
#የሃይማኖት_ኃይል_ነው  【መጽሐፈ ድድስቅልያ】
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

” ከተጠመቁም  በኋላ  ኤጲስ ቆጶሱ ቅብዐ  ሜሮኑን ይቀባቸው ፤ በክርስቶስ በሞቱ  አምሳል ተጠምቀዋልና ። ይኸውም  ከበለሳን  የተገኘ ቅብዓ  ሜሮን  የሃይማኖት  ኃይል ነው ።”

★ ወቦቱ ይትገበር መድኃኒት ወፈውስ ወምክሆሙ ለኵሎሙ መሲሐውያወን
⇨  ድኅነትና ፈውስ የሚደረግበት የክርስቲያኖች ሁሉ #መመኪያችን_ነው 【መጽሐፈ ስንክሳር】
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°

" ያንጊዜም ተመልሰው ወደ ምስር ደረሱ ወደ መዓልቃም በዚያ በዋሻ ውስጥ አደሩ እርሷም እስከ ዛሬ የቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ናት ። ከዚያም ወጥተው ወደ መጣርያ ደርሰው በውስጧ ታጠቡ ። ይቺም የውኃ ምንጭ አስቀድመን እንደተናገርን ጌታችን ያፈለቃት ከዚያች ሰዓት ጀምሮ የተባረከችና የከበረች ሆነች ። ከዚያም ጌታችን የተከለው የክርስትና ጥምቀት የሚፈጸምበት በለሳን ቅባት የሚወጣው ነው ። በእርሱም ደግሞ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅድሳትና ታቦተ ሕጉም የሚከብርበት ድኅነትም የሚደረግበት ለክርስቲያኖች ሁሉ መመኪያቸው ነው ።"

https://www.tg-me.com/An_Apocalypse/21471

"እንደዚህ እናመሰግንሃለን ፦  የሁሉ  ፈጣሪ  ሆይ  በልጅህ በኢየሱስ  ክርስቶስ  ለኛ  ስለገለጥክልን  ሞት  ስለሌለበት ስለዚህ ሜሮን መዓዛ  ስለዚህ  ዘይት  እናመሰግንሃለን ፤ ክብር መንግሥት ኃይል ለእንተ ነውና ለዘለዓለሙ  አሜን።"
【መጽሐፈ ዲድስቅልያ ፴፮፥፩】

✍️ ከቴዎድሮስ በለጠ ከባሌ ጎባ መድኃኔዓለም (ጥቅምት ፳፮ –  ፳፻፲፭ ዓ.ም በሀገራችን ለሦስተኛ ጊዜ ሜሮን የማፍላት ሥርዓት ሲፈጸም በ፯ኛው የጸሎት ቀን የተዘጋጀ)
👍152
ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ

ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን💛💚
11👍8
"ማርቆስ ይበቊዐኒ… ማርቆስ ይጠቅመኛል" (፪ጢሞ. ፬፥፲፩)

ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍፃሜተ ሰማዕት ከመቃብረ #ማርቆስ ወንጌላዊ እየገባ "ኦ እግዚኦ ረስያ ደምየ ማኅትመ ደመ ኵሎሙ ሰማዕታተ አንጾኪያ" እያለ ሲጸልይ #አሜን የሚል ቃል ይሰማ ነበረ፤ ምነው በሰማዕታት ቀንቶባቸው ሰማዕታትን ቀንቶባቸው ነውን ቢሉ ቀንቶባቸው ተመቅኝቷቸው አይደለም ከመከራው ጽናት የተነሣ ይክዳሉ ብሎ ነው እንጂ።

ሊቁ በግፍ ስለሚፈሰው የሰማዕታት ደም መቆም ደሙን እስከማፍሰስ በጽኑ እንደተማጸነ እኛስ መቼ ይሆን በምድራችን የሚፈሰውን የዘረኝነት ጅረት እንባ በማፍሰስ እንዲነትግ ደጅ የምንጠናው?

"ወማርቆስ ወንጌላዊ ውእቱ ሐዋርያ ( ሰባኬ ወመጥምቀ ወሠያሜ ካህናት) በእስክንድርያ ወግብጽ ወኖባ ወምድረ ኢትዮጵያ እስከ ጽንፋ ⇨ ወንጌላዊው ማርቆስ የእስክንድርያ፤ የግብፅ፤ የኖባ |ሱዳን እና እስከ ጫፉ ድረስ የኢትዮጵያ ምድር ሁሉ ሐዋርያ (የሚሰብክ የሚያጠምቅና ካህናትን የሚሾም) ነው።"
【መጽሐፈ ግጽው ፩፥ ፲፩ 】

ነባቤ መለኮት ሐዋርያ ወሰማዕት ፣ ርእሰ ኤጲስቆጶሳት ወሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ይጠቅመናል! ከልደቱ በረከት ያሳትፈን!
13👍10
‹‹በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ››
""""""""""""""""""""""""""""""""(በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ)

ጠቢቡ ሰለሞን ለወጣቶች በሙሉ ዘለዓለማዊ መመርያ የሚሆን የህይወት ቃል ተናግሯል፡፡ ቃሉም ‹‹የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ›› የሚል ነው፡፡ መክ121 ‹‹በጉብዝናህ ወራት›› ያለው ወጣቶችን ለመጥቀስ ፈልጎ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ወጣቶቹ ‹‹ጎበዞቹ›› ይባላሉና፡፡ ቅዱስ ዮሀንስ ወንጌላዊ በመልእክቱ ‹‹ጎበዞች ሆይ ብርቱዎች ስለሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውን ስለአሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡›› ብሎ በጻፈ ጊዜም ወጣቶች ‹‹ጎበዞች›› እንደሚባሉ ማጠናከሪያ ሰጥቷል፡፡ 1ዮሐ314

‹‹ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ›› ማለቱም ‹‹ክፉ›› የሚባለውን የወጣትነት ምኞት ስለ አሸነፋችሁ ማለቱ ‹‹ክፉ›› የሚባለውን የወጣትነት ምኞት ስለ አሸነፋችሁ ማለቱ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ከክፉ የጎልማስነት ምኞት ሽሽ›› በማለት የክርስትና ልጁን ጢሞቲዎስን እንደመከረው የወጣትነት ምኞት ‹‹ክፉ›› ይባላልና፡፡ ወጣቶች ፈጣሪያቸውን ማሰብ እንደሚኖርባቸው ተለይተው የተጠቀሱት ለምንድር ነው?
በመሠረቱ ፈጣሪን ማሰብ የሚኖርባቸው ወጣቶች ብቻ አይደሉም፡፡ ልጆችም ሆኑ አረጋውያን ፈጣሪን ማሰብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን ግን ወጣቶችን ለይቶ ፈጣሪን ማሰብ እንዳለባቸው የተናገረባቸው ምክንያት አለው፡፡ ይኽውም ከልጆችና ከአረጋውያን ይልቅ ወጣቶች እግዚአብሄርን እንዲረሱ የሚገፋፋቸው ብዙ ነገር ስላለ ነው፡፡
👍8
2025/07/14 15:24:26
Back to Top
HTML Embed Code: