ደብረ ዘይት የዐብይ ጾም አምስተኛ ሳምንት
ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል።
ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው።
በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል።
የደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነው። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥ ፩
ከዚሁ ተራራ ላይ ነው ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያረገው። ኋላም በዳግም ምጽአት እዚሁ ተራራ ላይ ነው ለፍርድ የሚመጣው። /ሐዋ ፩፥፲፫/። "
" በዚህ ቀን ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ወደ ምድር ስለመምጣቱ (ዳግም ምፅአቱ ) ይሰበካል።
ይህን ዓለምንም አሳልፎ ለመረጣቸውና ላከበራቸው ዘላለማዊ መንግሥትን ሊያወርሳቸው እንደሚመጣ ይነገርበታል። ይህ ቀንም እኩለ ፆም በመባል የሚታወቅ ሲሆን በዚህች በተለየች ቀንም ሁሉም እንደ የሥራው ፍርዱን ከአምላክ የሚቀበልበት መሆኑ፤ መልካም ላደረጉ መልካም እንደሚመለስላቸ ክፉም ላደረጉ የክፋታቸውን ዋጋ እንደሚያገኙ ይሰበካል።
ጌታም የአባቴ ቡሩካን የተዘጋጀላችሁን የክብር ቦታ ውረሱ በማለት ወዳጆቹን እንደሚጠራ ይነገራል።
" እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል " ማቴ.፳፬፡፩-፴፮ ኢየሱስም ከመቅደስ ወጥቶ ሄደ፥ ደቀ መዛሙርቱም የመቅደሱን ግንቦች ሊያሳዩት ቀረቡ።
እርሱ ግን መልሶ፦ ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው። እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ። ብዙዎች። እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።
ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው። በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል ይገድሉአችሁማል፥ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ።
በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። "
" እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም እሳት ይነድድ ቅድሜሁ "
መዝ.፵፪÷፱
" እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም አይልም እሳት በፊቱ ይነድዳል፣ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡ "
@ortodoxtewahedo

👍18❤5🥰1👏1🙏1
#እኩለ ጾም ደብረ ዘይት
#ምስባክ
እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ።
ትርጉም፦እግዚአብሔር ግልጥ ኾኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት እፊቱ ይቃጠላል።
(የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5)
📜3፤ በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
📜4፤ የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።
📜5፤ የዋሆች ብፁዓን ናቸው፥ ምድርን ይወርሳሉና።
📜6፤ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።
📜7፤ የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፥ ይማራሉና።
📜8፤ ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ እግዚአብሔርን ያዩታልና።
📜9፤ የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
📜10፤ ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።
📜11፤ ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።
📜12፤ ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።

👍24👏3❤2😍1
Audio
❤3👍2💯2
ስለ ራሔል አንባ አስራኤልን ከባርነት ነፃ ያወጣ አምላክ ስብዙሃኑ ለቅሶ ብሎ በቃ ይበለን ከዚ ክፊ ዘመን ከዚ ባርነት።
“ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።”
— ማቴዎስ 2፥17-18
@ortodoxtewahedo
“ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።”
— ማቴዎስ 2፥17-18
@ortodoxtewahedo
👍32😢21👏1
🔴 አልጋ ተሸክሞ መሔድ || የዐቢይ ጾ...
ፈውስ መንፈሳዊ ጣና ቅ/ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fews Menfesawi
✝አልጋ ተሸክሞ መሄድ ✝
የዐቢይ ጾም ጉዞ
ክፍል 3
Size:-105.4MB
Length:-1:53:50
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@ortodoxtewahedo
የዐቢይ ጾም ጉዞ
ክፍል 3
Size:-105.4MB
Length:-1:53:50
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@ortodoxtewahedo
❤3👍3
Audio
👍9
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
💁♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል። ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
ክፈት ክፈት
👍3
አውነት በድራማ አይደበቅም
ስለ ራሔል አንባ አስራኤልን ከባርነት ነፃ ያወጣ አምላክ ስብዙሃኑ ለቅሶ ብሎ በቃ ይበለን ከዚ ክፊ ዘመን ከዚ ባርነት ።
“ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።”
— ማቴዎስ 2፥17-18
@ortodoxtewahedo
ስለ ራሔል አንባ አስራኤልን ከባርነት ነፃ ያወጣ አምላክ ስብዙሃኑ ለቅሶ ብሎ በቃ ይበለን ከዚ ክፊ ዘመን ከዚ ባርነት ።
“ያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ፥ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትም አልወደደችም፥ የሉምና የተባለው ተፈጸመ።”
— ማቴዎስ 2፥17-18
@ortodoxtewahedo
👍18❤1🙏1🤣1
ገብርኤል ያየው ምስጢር
በህጻንነቴ ቤት ውስጥ ለሰው የማይወራ ነገር ቤት ውስጥ ከተወራና በሰው ፊት ሳወራ ከተገኘሁ ወይም እንደዚህ ብሎኝ እኮ ሲባል እናቴ ከሰማች “አይ... ገብርኤል ያየው ምስጢር” ትለኝና ትቆጣ ነበር፤ ለምን እንደሆን እንደዛ የምትል አይገባኝ ነበር ያኔ... መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ አንድ ክፍል ላይ ግን “እውነትም ገብርኤል ያየው ምስጢር” የሚያስብል ነገር አለ ለካ...
እስከ ሽምግልና ወራቱ ድረስ ልጅን ያልተሰጠው የብሉይ ኪዳኑ መቅደስ ሊቀ ካህን ለነበረው ዘካርያስ ከመላዕክት አለቆች አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጦ እንደተነጋገረው የሉቃስ ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ክፍል ይናገራል፤ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ የተባለላቸው ዘካርያስ እና ሚስቱ ኤልሳቤጥ ልጅ አልነበራቸውም በእድሚያቸውም አርጅተው ነበር ይለናል ሉቃስ፤
ዘካርያስም ቤተ መቅደስን የሚያገለግልበት ተራው በደረሰ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለማገልገል ወደ መቅደስ ገባ በዕጣን እግዚአብሔርን በሚያገለግልበት ጊዜም “በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው እኔ ገብርኤል ነኝ” ብሎ የተናገረው ቅዱስ ገብርኤል በመሰዊያው ቀኝ ቆሞ ታየው፤ ዘካርያስ ከብዙ ዘመናት በፊት “ልጅን ስጠኝ” ብሎ እግዚአብሔርን ለለመነው፡ እንዲሁ እንድኖር ፈቅዷል በቃ ብሎ ጠይቆ እንደነበርም ለረሳው ልመና ቅዱስ ገብርኤል “ልመናህ ተመቶልሀል፤ ሚስትህም በመወለዱ ብዙዎች ደስ የሚሰኙበት ልጅን ትወልድልሃለች” የሚል ብስራትን ነገረው፤ ዘካርያስ ግን “እኔም ሚስቴም ሸምግለናል ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ...?” የሚል የእግዚአብሔርን መቅደስ ዘወትር ከሚያገለግል፤ እልፍ የእግዚአብሔር ተአምራትን ሲያነብ ከሚውል ካህን ይጠየቃል ብለን የማናስበውን ጥያቄ አነሳ፤ ቅዱስ ገብርኤልም “ይህንን ነገርም ልነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬ ነበር፤ ይህን ቃሌንም ስላላመንህ ይህ እስኪሆንም ዲዳ ትሆናለህ አለው”፤
ይህ ሊቀ ካህን ዘካርያስም የአገልግሎቱ ወራት ከተፈጸመ በኋላ ወደቤቱ ሄደ፤ ሚስቱ ኤልሳቤጥም ጸነሰች፤
ኤልሳቤጥም እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎልኛል ስትል ራሷን አምስት ወር ያህል ሰወረች፤ ቅዱስ ኤፍራም ይህን ሲተረጉም እግዚአብሔር አንድን ጸጋ ቢሰጥህ ራስህን መሰወር ይሆንልሀልን? ራስህን ካልገለጠክ እንዲህ እኮ ነኝ እንዲህ እኮ ማድረግ እችላለሁ ብለህ ለመናገር አትቸኩልምን? ኤልሳቤጥ ግን በሽምግልናዋ ወራት የተደረገላትን በሁሉ ዘንድ ድንቅ የሚሆን ነገር ሁኖ እንኳ ሳለ በዚህ ወራት ስድቤን ከሰው ያርቅልኝ ዘንድ እግዚአብሔር በረድኤት በጎበኘኝ ጊዜ እንዲህ አደረገልኝ ስትል አምስት ወር ጽንሷን ሰወረች ይልሃል ሉቃስ፤
እንግዲህ ጉዳያችን ከዚህ በኋላ ይመጣል፤ ዘመናቸውን ሙሉ ልጅን ስጠን ብለው እግዚአብሔርን ሲለምኑ የኖሩት ካህኑ ዘካርያስ እና ቅድስት ኤልሳቤጥ የመውለጃ ዘመናቸው ካለፈ ከሸመገሉም በኋላ “በመወለዱ ብዙዎች ደስ የሚሰኙበትን” ልጅ ኤልሳቤጥ መጽነሷን የሚያውቁት ከእግዚአብሔር በታች ሦስት አካላት ብቻ ነበሩ፤ ቅዱስ ገብርኤል ፤ ካህኑ ዘካርያስ እና ቅድስት ኤልሳቤጥ፤ ለአንድ ምስጢር ምስጢር ሆኖ መቆየት ሁሉም ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁ አካላት የሰሙትን ያወቁትን ነገር ለራሳቸው ይዞ መቆየት ግድ ይላል፤
ወደዚህም ስንመጣ ቅድስት ኤልሳቤጥ እግዚአብሔር ይህንን አደረገልኝ ስትል ራሷን እንደሰወረች፤ ካህኑ ዘካርያስ ደግሞ የካህኑን ቃል በምን ላምን እችላለሁ ብሎ በመጠራጠሩ ልጁ እስኪወለድ ዲዳ ትሆናለህ እንደተባለና መናገር እንደማይችል ቅዱስ ሉቃስ ነግሮናል፤ ስለዚህ የቀረው የቅዱስ ገብርኤል ድርሻ ነው...
ይህ ኤልሳቤጥ ራሷን የሰወረችበት አምስት ወር ሲፈጸም፤ በስድስተኛ ወር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ንጽሕት ድንግል እግዚአብሔር ላከው፤

👍12❤3
ተአምረ ማርያም ይህን ክፍል እንዲህ ይገልጸዋል...
ይህን ንባብ ሳስብ እና "ዲዳዎች የሚናገሩበት ጊዜ ደረሰ" የሚለውን ስሰማ ስለ ዘካርያስ ይሆን እላለሁ፤ ያለማመን ጥያቄ በመጠየቁ የተቀጣው ዘካርያስ የሚናገርበት ጊዜ ደረሰ እያለ ይሆን እላለሁ፤ እኔስ መቼ ነው አንተን ባለማመን ካለሁበት የልብ ዲዳነት የምፈታበት ጊዜ የሚደርሰው ጌታ ሆይ.... እላለሁ፤
ወደ ሉቃስ ንባብ ልመሳችሁና ቅዱስ ገብርኤል እንግዲህ ከእግዚአብሔር የተባለው ነገር ለሰው ልጅ የጀመርኩትን ቸርነት ድኅነት የምፈጽምበት ጊዜ ደረሰ ብለህ ለፅዮን ልጅ ንገራት አብስራት ነው፤ የቅዱስ ገብርኤልን ወደ እመቤታችን መላክ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፤
እዚህ ክፍል ላይ ሌላው የሚያስደንቀን የሆነው ነገር ደግሞ ስንነሳ ያልነው የቅድስት ኤልሳቤጥ መጽነስ ካወቁት ሦስት አካላት በምስጢር ተይዞ እንዲቆይ የቀረው ቅዱስ ገብርኤል እንደሆነ አንስተን ነበር፤ ብርሃናዊው መልአክ ግን "እህቶሙ ለመላእክት" ለተባለች ለንጽሕት እኅቱ ለድንግል ይህን ምስጢር አለመናገር አልቻለም፤
ገብርኤል ያየው ምስጢር ይሏል ይህ ነው.... እሱ ብቻ ያውቅ የነበረውን ምስጢር አውጥቶ የተናገረው፤ የአምላክን ሰው የመሆን ምስጢርም ከእርሱ ሌላ ማንም መልአክ እንኳ ሳያውቅ ተሽቀዳድሞ መጥቶ ለቆንጆይቱ የነገረልን ይላሉ አለቃ ዘነብ በመጽሐፈ ጨዋታ መጽሐፋቸው፤
የድንቅ ድንቅ የሆነው ነገር ደግሞ ፈጣኗ ደመና ድንግል ማርያም ይህን ምስጢር ስትሰማ የአምላክ እናት ነኝ ንግሥት ነኝ ሳትል "በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።"(ሉቃስ 1፥48)
በእውነት በእግዚአብሔር ፊት የምትቆም ቅዱሱ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ የሕይወታችንን ምስጢር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀብለህ ለድንግል ንገርልን ፈጥና መጥታ በረድኤት በበረከት ትጎበኘን ዘንድ፤ እውነት ነው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን እንደነበሩት እንደ ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ያለ ሕይወት የለንም፤ እግዚአብሔር ግን ወደእኔ በእምነት የመጣውን ወደውጭ አላወጣውም አልጥለውም ብሏልና እንደማይተወን እናምናለን፤
ቅዱስ ገብርኤል የሕይወት ምስጢራችንን ፤ ሕይወት ቋጠሯችንን ሁሉ ፍታልን፤😍
ድንግል ሆይ በምሕረት ትጎበኝን ዘንድ ወደኛ ዘወትር ነይልን😍
ሐቢብ ጊዮርጊስ
የካቲት ፳ ፳፻፲፯ ዓ.ም
፭ ኪሎ
አ/አ
@ortodoxtewahedo
እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ገብርኤልን ሒደህ ለጽዮን ልጅ ለድንግል የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጅ ወዳንቺ ይመጣል ሥጋሽን ይለብሳል ብለህ ንገራት። ይኸውም ካንቺ የሚወለደው ጽኑዕ ነው ብለህ ንገራት አለው።
ደንቆሮዎች የሚሰሙበት ዲዳዎች የሚናገሩበት ዕውራንም የሚያዩበት ሙታንም የሚነሡበት ለምፃሞችም የሚነጹበት ሐንካሳንም የሚሔዱበት በጨለማ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ብርሃን የሚያዩበት ጊዜ እነሆ ደረሰ ብለህ ንገራት አለው።
ይህን ንባብ ሳስብ እና "ዲዳዎች የሚናገሩበት ጊዜ ደረሰ" የሚለውን ስሰማ ስለ ዘካርያስ ይሆን እላለሁ፤ ያለማመን ጥያቄ በመጠየቁ የተቀጣው ዘካርያስ የሚናገርበት ጊዜ ደረሰ እያለ ይሆን እላለሁ፤ እኔስ መቼ ነው አንተን ባለማመን ካለሁበት የልብ ዲዳነት የምፈታበት ጊዜ የሚደርሰው ጌታ ሆይ.... እላለሁ፤
ወደ ሉቃስ ንባብ ልመሳችሁና ቅዱስ ገብርኤል እንግዲህ ከእግዚአብሔር የተባለው ነገር ለሰው ልጅ የጀመርኩትን ቸርነት ድኅነት የምፈጽምበት ጊዜ ደረሰ ብለህ ለፅዮን ልጅ ንገራት አብስራት ነው፤ የቅዱስ ገብርኤልን ወደ እመቤታችን መላክ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፤
ቅዱስ ገብርኤል ያለ መዋለጃ ዘር የሚሆን ፅንሷን ያለሩካቤም የሚሆን መውለዷን ይነግራት ዘንድ ወደ ማርያም ተላከ ገብርኤል ሳያበስራት በሥጋ ይወለድ ዘንድ እግዚአብሔር ቢወድ ኖሮ በቻለ ባደረገም ነበር። ነገር ግን በየጥቂቱ ሲያድግ ስለፅንሷ በልቧ ይህ ከጽኑ ደዌ የመጣ ነውን ወይስ የሰውን ልጅ ከሚተነኳኰሉት ከመናፍስት ብላ #እንዳትደነግጥ_ለእናቱ_አሰበላት
እዚህ ክፍል ላይ ሌላው የሚያስደንቀን የሆነው ነገር ደግሞ ስንነሳ ያልነው የቅድስት ኤልሳቤጥ መጽነስ ካወቁት ሦስት አካላት በምስጢር ተይዞ እንዲቆይ የቀረው ቅዱስ ገብርኤል እንደሆነ አንስተን ነበር፤ ብርሃናዊው መልአክ ግን "እህቶሙ ለመላእክት" ለተባለች ለንጽሕት እኅቱ ለድንግል ይህን ምስጢር አለመናገር አልቻለም፤
ሉቃስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁶ እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤
³⁷ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።
³⁸ ማርያምም፦ እነሆኝ የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ አለች። መልአኩም ከእርስዋ ሄደ።
ገብርኤል ያየው ምስጢር ይሏል ይህ ነው.... እሱ ብቻ ያውቅ የነበረውን ምስጢር አውጥቶ የተናገረው፤ የአምላክን ሰው የመሆን ምስጢርም ከእርሱ ሌላ ማንም መልአክ እንኳ ሳያውቅ ተሽቀዳድሞ መጥቶ ለቆንጆይቱ የነገረልን ይላሉ አለቃ ዘነብ በመጽሐፈ ጨዋታ መጽሐፋቸው፤
የድንቅ ድንቅ የሆነው ነገር ደግሞ ፈጣኗ ደመና ድንግል ማርያም ይህን ምስጢር ስትሰማ የአምላክ እናት ነኝ ንግሥት ነኝ ሳትል "በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥ ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።"(ሉቃስ 1፥48)
በእውነት በእግዚአብሔር ፊት የምትቆም ቅዱሱ ብርሃናዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ የሕይወታችንን ምስጢር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀብለህ ለድንግል ንገርልን ፈጥና መጥታ በረድኤት በበረከት ትጎበኘን ዘንድ፤ እውነት ነው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን እንደነበሩት እንደ ዘካርያስ እና ኤልሳቤጥ ያለ ሕይወት የለንም፤ እግዚአብሔር ግን ወደእኔ በእምነት የመጣውን ወደውጭ አላወጣውም አልጥለውም ብሏልና እንደማይተወን እናምናለን፤
ቅዱስ ገብርኤል የሕይወት ምስጢራችንን ፤ ሕይወት ቋጠሯችንን ሁሉ ፍታልን፤😍
ድንግል ሆይ በምሕረት ትጎበኝን ዘንድ ወደኛ ዘወትር ነይልን😍
ሐቢብ ጊዮርጊስ
የካቲት ፳ ፳፻፲፯ ዓ.ም
፭ ኪሎ
አ/አ
@ortodoxtewahedo
👍6👏4🙏1
🍁🍁🍁 ኦ ገብርኤል መልአክ አድኅኖ ፍንው
አድኅነኒ ዘአድኅንኮሙ በአክናፊከ ምንትው
አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ ዕደው
⚜️⚜️ገብርኤል ሆይ!
ክጭንቅና ከመከራ ለማውጣት የተላክህ መልአክ ነህና
ሠለስቱ ደቂቅ በእሳት ጉድጓድ በተጣሉ ጊዜ ሁለቱን ክንፎችህን ጋርደህ ከመቃጠል እንዳዳንሃቸው እኔንም አገልጋይህን በረድኤትህ ኃይል አድነኝ
⚜️⚜️⚜️ገብርኤል ሆይ!
የማንችለው እሳት በሀገራችን አለና ውሃ አድርግልን
እንደ ሦስቱ ሕጻናት ያለ እምነትን ስጠን
አቤቱ እግዚአብሔር የቅዱሳን አምላክ ሆይ ጾመን ጸልየን ከእሳት ውስጥ የምንወጣበትን መንገድ አሳየን።
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ጠብቆትህ አይለየኝ ከፊት ምራኝ ሁል ጊዜ በልቤ ንገስ ለእኔ የደረስክ መልአክ ለተቸገረው ለተራበው ለተጠማው ለታረዘው ለስደተኛው ለሁሉም ............ ረዳትነትህ አይለየው

👍5🥰2👏2
# መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል
❖ ከ7ቱ ሊቀነ መላእክት አንዱ ነው።
❖ ገብርኤል ማለት የስሙ ትርጉም የእግዚአብሔር ልጅ የሚመስል የእግዚአብሔር ሰው ማለት ሲሆን
ት.ዳን 3+25ሕዝ 9፥2 በተጨማሪም መጋቤ ሐዲስ( የሐዲስ ኪዳን አስተማሪ) እግዚእ ወገብረ (እግዚአብሔር አደረገ ) ማለት ነው።
❖ ብስራታዊ (አብሳሪው) መልአክ ነው። እመቤታችንንና ዘመዷ ኤልሳቤትና አብስሮአልና።
❖ ቅዱስ ገብርኤል አርባብ የተበለው ነገደ መላእክት አለቃ ነው።
❖ በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ፀንተን እንቁም በማለት መላእክት ያፀናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው።
❖ ተራዳዩ መልአክ ነው።
ዳን ፫፥፲፱-፳፯፣ዳን ፰፥፲፭ ዳን፱፥፳፩-፳፯
❖ ቅዱስ ገብርኤል ከ፯ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው።
❖ በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም መልካሙን የምናደርግበት መልካም ቀን ይሁንልን።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
#መልካም እለተ ይሁንልን
ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ
ለመቀላቀል 👉
@ortodoxtewahedo
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

👏8👍3❤1
ገብርኤል ሆይ፤ ከሰው ወገን ጠዋትና ማታ ከቶ እንደ እኔ ኀዘንና ትካዜ የሚበዛበት የለም፣
ከመላእክትም ወገን እንደ አንተ ያዘኑትን የሚያረጋጋ የለም፣
ገብርኤል ሆይ፤ ስለዚህ እኔም አውቄና አንተን አምኜ ያቀረብኩትን ይህን ጸሎት እንደ ትልቅ ዋጋ ቆጥረህ የሚያረጋጋ ቃልህን አሰማኝ።
መልክአ ገብርኤል
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም አደረሰን።

❤15👏3👍2
ቅዱሳኑን ያዳነ ቅዱስ መልአክ እኛንም ያድነን ዘንድ እንደ አባቶቻችን "አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው:: አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ሠለስቱ እደው::" እያልን እንለምነው::
(መልክዐ ገብርኤል)
"በአምላኬም በእግዚአብሔር ፊት ስለ ተቀደሰው ስለ አምላኬ ተራራ ስለምን: ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ:: በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ:: አስተማረኝም ." †
(ዳን. ፱፥፳)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
#አቤቱ የሆነብንን አስብ
#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው ከፍ ከፍ አድርጋቸው።

👍15👏7❤4
ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና።...
#ማለዳ_ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።
ነፍሴ፦ እግዚአብሔር እድል ፈንታዬ ነው፤ ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ አለች።
እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ መልካም ነው።
ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።
ሰቆቃወ ኤርምያስ 3-22
ሰናይ ዕለተ ቀዳሚት
@ortodoxtewahedo
❤7👍3👏2