Telegram Web Link
If the Lord shall break your heart, consent to have it broken; asking that he may sanctify that brokenness of spirit to bring you in earnest to a Savior.

እግዚአብሔር ልብህን ሊሰብር ከፈለገ፣ እንዲሰብረው ፍቀድለት። የመንፈስህን መሰበር ቀድሶ፣ ፍጹም ወደ ታዳጊህ እንዲያስጠጋህም ተማጸነው
Spurgeon.
7
መክብብ 1:1-11 (Part 2)

1, በኢየሩሳሌም የነገሠው፣ የዳዊት ልጅ፣ የሰባኪው ቃል

መክብብ / Qohelet ማለት በቀጥታ ሲተረጎም the assembly speaker/ one who gathers people together ወይንም የንግግሮች ጥርቅም ማለት እንደመሆኑ የመፅሀፉ ተራኪ በቅድሚያ ፀሀፊውን በማስተዋወቅ ይጀምራል።

2, ሰባኪው፣ “ከንቱ፣ ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው” ይላል።

ከንቱ የሚለው ቃል መክብብ ውስጥ 38 ጊዜ ተጠቅሷል። It expresses vanity, utter emptiness, ultimate absurdity and its written in hebrews superlative degree. የማይጨበጥና ቶሎ እንደሚጠፋ እንፋሎት መሆኑ makes life is as meaningless as it could possibly because its fleeting.

ከንቱ የሚለውን ቃል ሂብሪው ባይብል የሚገልፀው ብዙ ጊዜ ከጣዖታት ጋር በተገናኘ መንገድ ነው። (ኤር 16:19; ዘካ 10:2) ይህ ደግሞ ለመክብብ አውድ አግባብ ነው ምክኒያቱም ሰዎች በተፈጠሩ ነገሮች እርካታን ለማግኘት መሞከራቸው ከንቱ ነው። Its meaningless because things are created as means not ends.

3, ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?

ቆም ብለን ልፋታችንን እንመዝን። Is it worth it? ጥቅሙ ወይንም የምናገኘው gain calculate ሲደረግ ምንድነው ትርፉ? ልፋት የሚለው ቃል ቶሎ ዘፍጥረት ሶስትን ያስታውሰናል። በምድር መኖር በሀጥያትና ተያያዥ ምክኒያቶች የሚያለፋና የሚያታግል ነው።

በዚህ መፅሀፍ ብቻ "ከፀሀይ በታች" የሚለው ሀረግ ወደ 30 ጊዜ ተጠቅሷል። ምክኒያቱም ጠቢቡ እያስተማረ ያለው ከምድራዊ ንፅረተአለም ወይም earthly perpective ስለሆነ ይመስለኛል። አንዳንድ ቦታ ላይ ደግሞ በግልፅ ስለዘላለማዊና መንፈሳዊ ነገሮች አለማወቁንም (ማወቅ እንደማይቻል እንደሚያስብ) ይናዘዛል። ስለዚህ if this world is all there is—if there is no God, no afterlife, and no final judgment ሁሉም ነገር ትርጉምየለሽ ይሆናል።

ምክኒያቱም ቀጥሎ እንደሚያብራራው ሰው የለፋበትን ሁሉ ሲሞት ትቶት ይሄዳል። ሰው አለምን ሁሉ አትርፎ ነፍሱን ግን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል? ማርቆስ 8:36 መልሱ ምንም ነው። ቲም ኬለር እንደሚለው የንግድ ስራዎች ወይም ባለን ማህበራዊ መስተጋብር ላይ "ይሄ ለኔ ምን ጥቅም አለው/
What’s in it for me? ብለን እንደምንጠይቀው ሁሉ ስለአጠቃላይ ህይወታችን አንጠይቅም። However many years ስንኖርና እየለፋን ስንሰነብት ከህይወት ምን እናገኛለን ብለን ነው?

ቁጥር 4-7

የመጀመርያው ንፅፅር እኛ ስንሞትም አለም መቀጠሏ ነው። ይሄን dispute ለማድረግ ምድርን በእድሜ የሚበልጥ ሰው ማምጣት ይጠይቃል። Jerome እንዳለው ለሰው ልጅ መጠቀሚያና መኖርያ ተብሎ የተፈጠረው አለም ፀንቶ በፍጥረት ሁሉ ላይ ገዢ ሊሆን የተሾመው ሰው ግን ወደትቢያነት መቀየሩ የከንቱነቱ ማሳያ ነው።

በመቀጠል ሳያቋርጡ የሚንቀሳቀሱ ሶስት ምሳሌዎች አሉ። ያለ ለውጥ ሁሌም በዑደት ላይ መሆናቸው አድካሚ ነው። ይህ አጭር ግጥም በተፈጥሮ ያለውን ድግምግሞሽና አዙሪት በማሳየት የልፋትና ጥረትን ከንቱነት ያስረዳል። It paints the picture that we are trapped in a monotonous prison portrait of life in world broken by sin and death. በሶስቱ ምሳሌዎች የሰው ልጅ ህይወት ይንፀባረቃል። ምንም accomplish ሳያደርግ እንደሚንቀሳቀሰው ፍጥረትና እንደማይሞላው ባህር ሰውም የማያገኘውን እርካታ ፍለጋ circle ውስጥ ይሽከረከራል።

ቁጥር 8-11

የማይረካ appetite በሰው ልብ ውስጥ አለ። እንደባህር ሰውም በውስጡ ሁሌ ሊካብት የሚችል ሀብት፣ ሊጠመድ የሚችል ወዳጅ፣ የተሻለ መጠለያና ሌላ ጠቃሚ ኮተት ይኖራል ። እንደ ባህሩ ሰው በእንቅልፍ ልቡና በእለት ተለት ህይወቱ የሚለፍፈው ሳያንስ በነፍስወከፍ ፖድካስት መስርቶ በትጋት ያወራል። 24 ሰዓት ብቻ እንደተመደበለት እያወቀ ከ10 ሰዓት በላይ screen time ይዞ አሁንም የበለጠ ነገሮችን ማየት የሚችልበትን VR system, 3d glasses እና ሌሎች መንገዶችን ይፈጣጥራል። ጆሮም ከመስማት አይሞላም። የረባ ያልረባውን ብቻ ድምፅ ይኑረው እንጂ ሁሉን ያዳምጣል። ፀጥታውን ሽሽት ሁከትን በቀጭን ገመድ ጎትቶ ወደራሱ ያስጠጋል።

ህይወት predictabile ስትሆንና ሁሉም ነገር መገመት ከተቻለ፣ ዛሬ ላይ ሆኖ ነገ፣ የዛሬ ሳምንትና አመትን በትክክል ማወቅ ቢቻል መኖር ሙሉ በሙሉ ትርጉም አይኖረውም። በዛ ልክ የሚሆነውን ባናውቅ እንኳን ግን ከታሪክ የምንማረው ነገር ያኔ የተደረጉ ነገሮች አይነታቸውን ቀይረው ዛሬ እንዳሉ ነውና ለወደፊቱ ምን ሊመጣ እንደሚችል መተንበይ ብዙ አይቸግርም። አዲስ ነገር ሳይሆን የተረሳና እንደአዲስ የመጣ ነገር ወይ ያለው ላይ የተደረገ መሻሻል ነው ያለው። Begg አንዴ እንዳለው አዲስፈጠራ ብለን ሰውን ጨረቃ እንኳ ስንሰድ..ሰው ከጨረቃ ሆኖ ምድርን ነው ሚታዘበው።

oblivion/ መረሳት is inevitable ወይንም የማይቀር ሀቅ ነው። ጀግኖች ሁሉ አይዘከርላቸውም። የተዘፈነላቸው ራሱ የሚረሱበት ወይንም የሚኮነኑበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። ታሪክ ወደድንም ጠላንም በአሸናፊዎች የምትዘገብ ስለሆነች ለስም፣ ለመታወስ ብሎ መኖር ከሁሉ በላይ ከንቱነት ነው። መረሳትን መፍራትም ከንቱ ነው።  Death is the great equalizer, and that is the ultimate absurdity. ላለመረሳት ዜና ለመሆን ለመታወቅ ብዙ ብንጥርና ብንለፋም እንኳ ሞት ሲመጣ ልፋቱ ከሰሞነኛ ወሬ የማይዘልቅ መነጋገርያነት የተሻለ ሌጋሲ አይሰጠውም።
8👍2
እግዚአብሔር ሆይ
ምሕረትህ እስከ ሰማያት ይደርሳል ታማኝነትህም እስከ ጠፈር ይመጥቃል
ጽድቅህ እንደ ታላላቅ ተራሮች
ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው


እግዚአብሔር ሆይ
አንተ ሰውንም እንስሳንም ታድናለህ።
አምላክ ሆይ
ምሕረትህ እንዴት ክቡር ነው!
የሰዎች ልጆች ሁሉ፣ በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ።

ከቤትህ ሲሳይ ይመገባሉ
ከበረከትህም ወንዝ ይጠጣሉ።
የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና በብርሃንህም ብርሃንን እናያለን።

(The immense beauty of psalms)
13
Pursuing Holiness
መክብብ 1:1-11 (Part 2) 1, በኢየሩሳሌም የነገሠው፣ የዳዊት ልጅ፣ የሰባኪው ቃል መክብብ / Qohelet ማለት በቀጥታ ሲተረጎም the assembly speaker/ one who gathers people together ወይንም የንግግሮች ጥርቅም ማለት እንደመሆኑ የመፅሀፉ ተራኪ በቅድሚያ ፀሀፊውን በማስተዋወቅ ይጀምራል። 2, ሰባኪው፣ “ከንቱ፣ ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው”…
Meditation Prompts
1, Everything is vanity. ሁሉ ያልፋል። ሁሉ አይጨበጥም። What feels like its eternal to you? is it pain? comfort? loneliness? luxury, relationships , fun.. everything.
2, እየለፋን ነው? ለምን/ ለማን ነው የምንለፋው። calculate ቢደረግ is it worth it? ያዋጣል?
3, Do you know that you're dying? ስንሞት አለም ምንም እንደማትሆን እናስባለን? As if nothing happened ይቀጥላል።
4, ፀሀይ ነፋስ ወንዝ ሳይቀየሩ ይኖራሉ። በዑደት/ በመሽከርከር ላይ ናቸው። What are the basic cycles I haven't been able to escape?
5, Are you seeking for something new?
6, Do you fear oblivion or are you still searching for being a legend?
3
Pursuing Holiness
መክብብ 1:1-11 (Part 2) 1, በኢየሩሳሌም የነገሠው፣ የዳዊት ልጅ፣ የሰባኪው ቃል መክብብ / Qohelet ማለት በቀጥታ ሲተረጎም the assembly speaker/ one who gathers people together ወይንም የንግግሮች ጥርቅም ማለት እንደመሆኑ የመፅሀፉ ተራኪ በቅድሚያ ፀሀፊውን በማስተዋወቅ ይጀምራል። 2, ሰባኪው፣ “ከንቱ፣ ከንቱ፣ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው”…
God only You are eternal. አንተ ብቻ የማትሞት ነህ። ያልነበርክበት ቅፅበት የለም። የማትኖርበት ቅፅበት የለም። ሁሉ በሚጠወልግበት አለም ውስጥ ብቻህን የማታልፍ አምላክ ነህ። አንተን ማወቅ ዘለዓለምን ማወቅ ነው። አንተን ማየት ዘለዓለምን ማየት ነው። ስለዚህ ትልቅ እድል አመሰግንሀለው።

ብዙ ነገር አቅሜን ቢበዘብዘውም እንኳ በድካም ይሄን አስተውላለሁ። ለአንተ መልፋት ብቻ ትርፍ አለው። ሚስዮናዊው ኤልየት እንዳለው የእርሱ ያልሆነውን ጠፊ ህይወት ለዘላቂው እርስቱ የሚሰዋ ተላላ አይደለም። How does the old poem go?
Only one life, it will soon be past
Only whats done to Christ will last
ሌላው ሁሉ ኪሳራ ነው። ምንም በምድር ባለው ሁሉ ብሸለም..የቀደሙኝ እንዳለፉ እኔም አልፋለው። አንተ ግን ትፀናለህ። ብቻህን። ሁሉን አጊኝቶ አንተን ያጣ በእርግጥም ከስሯል። Let me treasure the fact that I have the privilege of living for you. And to be used by you. What an honor it is! Who is qualified ፀጋህ ሳይገንለት?

You're self sufficient. ማንንም ምንንም ሳትፈልግ ትኖራለህ። ፍጥረትህ እርካታን እያሳደደ ሲቅበዘበዝ አንተ ብቻ ያለምንም need ትኖራለህ። ስጋ ለባሽና ፍጥረትህ ሁሉ በአንተ ላይ ጥገኛ ነው። ባያውቀው ነው እንጂ እውነተኛ እርካታና ጥጋብ ልትቸረው የምትችለው አንተ ብቻ ነህ። ይህንን እውነት እንደሚያውቅ ሰውና አንተን በፀጋ እንደወረሰ ነው እንድረካ እርዳኝ። እንደማይሞላው ባህር በጥም ከመቅበዝበዝ አሳርፈኝ።

አንተ አትለወጥም። የምታልፍበት evolution የለም። ግን ሁሌም አዲስ ነህ። ይህ ታላቅ ሚስጥር ነው። How are you always new without ever changing? I dont know. But I know ከአንተ በቀር አዲስ የሆነ ምንም እንደሌለ። አዲስነትህ ራሱ በየዕለቱ አዲስ ነው። አዲስ ነገርን ከአለም ከመጠበቅ ኪሳራ ሰውረኝ። ሳትለወጥ ታውቆ የማያልቅ አዲስነት ያለህን አንተን ለማወቅ እንድተጋ እርዳኝ።

ሁሉም በተተኪው ይረሳል አንተ ግን ከዘለዓለም የነበርክ ሆነህ ራሱ አላረጀህም። እስከ ለዘለዓለም ትወሳለህ። ጀብዱህ ይዘከራል። Occupy my mind with your thoughts. ስራህን እያስታወስኩ፣ ውለታህን እየተረኩ በምስጋና እንድኖር አበርታኝ። ፈተና በመጣ ቁጥር እንዳልፍገመገም የታማኝነትህ ዝና አለማመኔን ይርዳው።
9👍1😢1
ስለእግዚአብሔር የሚናገሩ ብዙ ሰዎች አሉ.. እስቲ እኛ እግዚአብሔርን የምር ማናገር እንጀምር..
9
እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ምን ዓይነት ጸሎት ነው? | ሰኔ 19

“ነገር ግን እኔ ወደዚህ፣ ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።” (ኢሳይያስ 66፥2)


ቀና የሆነ ልብ የመጀመሪያው ምልክቱ በእግዚአብሔር ቃል መንቀጥቀጡ ነው።

ኢሳይያስ 66፣ እግዚአብሔርን በሚያስደስተው መንገድ በሚያመልኩት ሰዎች እና በማያስደስተው መንገድ በሚያመልኩት ሰዎች መካከል ያለውን ችግር ይመለከታል። ቁጥር 3 መሥዋዕታቸውን ስለሚያቀርቡ ጠማማ ሰዎች ሲናገር፣ “ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ ሰው እንደሚገድል ነው” ይላል። መሥዋዕታቸው ከነፍስ ግድያ እኩል በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነበር። ግን ለምን?

በቁጥር 4 ላይ እግዚአብሔር፣ “በተጣራሁ ጊዜ የመለሰ፣ በተናገርሁ ጊዜ ያደመጠ ሰው የለምና” በማለት ያስረዳል። የሕዝቡ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ የነበረው የእርሱን ድምፅ ስላልሰሙ ነበር። ታዲያ ግን ለምን እግዚአብሔር የሌሎቹን ሰዎች ጸሎት ሰማ? በቁጥር 2 ላይ እግዚአብሔር፣ “ነገር ግን እኔ ወደዚህ፣ ትሑት ወደ ሆነና መንፈሱ ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ” ይላል።

ከዚህ በመነሳት፣ እግዚአብሔር በጸሎታቸው የሚደሰትባቸው ቅን ሰዎች እነማን ናቸው ከተባለ፣ በእግዚአብሔር ቃል የሚንቀጠቀጡ ናቸው ብለን መደምደም እንችላለን። ጌታ የሚመለከተው እንዲህ ያሉትን ሰዎች ነው።

ስለዚህ፣ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበት የቅኖች ጸሎት የሚመጣው በእግዚአብሔር መገኘት ፊት ሲሆን ከሚጠነቀቅ ልብ ነው። እንዲህ ያለ ልብ በውድቀቱ ስለሚጸጸት፣ ከእግዚአብሔር አሳብ እጅግ መራቁን ስለሚያውቅና ሊፈረድበት የሚገባ አቅመ ቢስ እንደሆነ ስለሚሰማው፣ የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰማ ይንቀጠቀጣል።

ዳዊት በመዝሙር 51፥17 ላይ ያለው ይህንኑ ነው፦ “እግዚአብሔር የሚቀበለው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም” ይላል። ጸሎታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው፣ በተሰበረና በተዋረደ ልብ በፊቱ ስንቀርብ ነው። የትሁታን ልብ በእግዚአብሔር ቃል ፊት ዘወትር ይንቀጠቀጣል።

Telegram
| YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | Website

#ለዛሬ
6👍1
Take your mind captive with higher thoughts..
10
አብ እንደ ወደደኝ ሁሉ እኔም ወደድኋችሁ ፤ በፍቅሬ ኑሩ።
As the Father has loved me, so have I loved you. Now remain in my love. ( John 15:9 )
13
“እጅግ ክቡር የሆንህ ጌታ ሆይ ፤ ከባባድ ኃጢአቶቼን ሁሉ ይቅር በለኝ ፣ ከወደፊት ኃጢአቶች ጠብቀኝ ፣ ከተረሱት ኃጢአቶቼ ሁሉ አድነኝ ፣ በዘመኔ ሁሉ አንተን በቅንነት እና በፍቃደኝነት እንዳገለግልህ ሞገስና ፀጋን ጨምርልኝ።” አሜን።
ማርትን ሉተር እንደጸለየው
13👍2
መዝሙር 16

አምላክ ሆይ፤ መጠጊያዬ ነህና፣ በከለላህ ሰውረኝ።

Who God is to His people give us a clue about what He does. መጠጊያ መሸሸጊያ ዋሻ safe space hiding place ነው። ከለላ ይሆናል። መከታ ነው። ይጠብቃል።

እግዚአብሔርን፣ ‘አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም” አልሁት።

እርሱ ጌታ እኛ ባርያዎቹ ነን። What a privilege it is to have such a kind master? አሳዳሪ ጌታችን በርህራሄ የታወቀ፣ በልቡ ትሁት የሆነ የዋህ ነው። አለን ብለን የምንቆጥረው በረከታችን፣ ደስታችን፣ በጎነታችን፣ በህይወታችን ያለ ብቸኛ ultimately መልካም ነገር እርሱ ነው። የበጎነቱ በረከቶችም ሲበዙልን ምንጩን ሁሌ recognize ማድረግ አለብን።

በምድር ያሉ ቅዱሳን፣ ሙሉ ደስታ የማገኝባቸው ክቡራን ናቸው።

አብረውን በዙርያችን ያሉ..በሰንበት የምናገኛቸው እንደኛው imperfect የሆኑ ሰዎችን እግዚአብሔር የሚያያቸው እንደከበሩ ቅዱሳን ነው። ከእነርሱ ዙርያ/ company መራቅ የራስን ደስታ ነው የሚዘርፈው።

ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣ ሐዘናቸው ይበዛል፤ እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስም፤ ስማቸውንም በአፌ አልጠራም

እግዚአብሄርን በክርስቶስ በኩል የማያውቅ ሁሉ በዚህ ምድብ ውስጥ ይገባል። Their rebellion multiplies their sorrow. እኛ ግን የተለየን ስለሆንን በድርጊታቸው ላንተባበር መወሰን፣ እንደውሳኔያችንም መኖር አለብን። በዚህም የሚመጣውን ሀዘን እንቀንሳለን።

እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ዕጣዬም በእጅህ ናት።መካለያ ገመድ ባማረ ስፍራ ተጥሎልኛል፤ በርግጥም የተዋበች ርስት አግኝቻለሁ

እግዚአብሔር ራሱ እርስታችን ነው። He is our portion. Our treasure. Our possession. ማንም የማይወስድብን ድርሻችንና ፅዋችን ነው። He secures our lot. God is in control. This is why we were told not to be anxious. እድለኞች ነን! እኛ passive ሆነን የተቀበልነው ውብ ርስት አለ።

የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤ በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል

ሰው ለምክር እውቀቱ ውስን የሆነን ሰው በሚከፍልበት ጊዜ..ብዙ ከጥፊ ምክሮችን ፅፈው የሚቸበችቡ በፈሉበትም ዘመን ጠቢብ ነኝ ባዮቹን የሚያሸማቅቅ እውነተኛው የጠቢባን ጠቢብ ይመክረናል ማለት ይህ ነው የማይባል እድል፤ የምስጋናም ምክኒያት ነው። በለሊት ከልቡ ስለመማሩ ነብዩ ኢሳያስ እንዲህ ብሏል “.. በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።” (50፥4)

እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።

ማየት፣ መከተል የሚሉት ግሶች የተቀመጡት በactive voice ነው። በየዕለቱ ማድረግ ያለብን ነገር እንጂ እንዲወርድብን የምንጠብቀው ነገር አይደለም። If we are in Christ God is already at our right hand. On our side. We can decide to not be shaken because of that truth.

ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ ነፍሴም ሐሤት አደረገች፤ ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤ በሲኦል ውስጥ አትተወኝምና፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አታደርግም።

እግዚአብሔር በፊታችንና አብሮን ስላለ ልንደሰትና ሀሴት ልናደርግ ይገባል። ከስጋትና anxious ከሆነ ጭንቀት የሚያሳርፈው የእግዚአብሔርን አብሮነት ማመንና መረዳት ነው። ለስጋ የመጨረሻው ክፉ የሚመስለው ሞት እንኳን ሊያሰጋን አይገባም ምክንያቱም ትንሳኤ አለ። እርግጠኛ የሆነ የሙታን ትንሳኤ የክርስትና ተስፋ ነው። This reminds us ultimately about Christ በኩር ሆኖ ስለተነሳው ታላቅ ወንድማችን ያስታውሰናል።

የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

ከሞት እስከ ትንሳኤ የሚመራውን መንገድ ያሳየናል ብለን ያመንነው እርሱን ነው። እርሱ ባለበት መሆን መልካም ነው። በዚያ ሙሉ ደስታና ዘላቂ ፍስሀ አለ። Recognize who God is to you (in Christ) እርስታችን ነው። መጠጊያችን ነው። እጣችን በእጁ ነው። መካሪያችን ነው። ለዘለዓለም አብሮን ነው። We have plenty reasons to rejoice and be glad.
9
Forwarded from Mahlet Mesfin
ዻውሎስ ስለመዳን እና ፀጋ ከማውራቱ በፊት ስለጨለማውና ስለሀጢያታችን በጥልቀት እንደሚነግረን ሰለሞንም ከፀሀይ በላይን ከመናገሩ በፊት ከፀሀይ በታች ስላለው ነገር ተስፋ እንድንቆርጥ almost እርማችሁን አውጡ አይነት ነገር ነው የሚለን::

ጥያቄ የፈጠረብኝ ነገር ለምንድነው ግን እኛ የሰው ልጆች አዲስ ነገር ለማግኘት እንዲህ የምንጏጏው? ለምን በድግግሞሽ ውስጥ መርጋት or content መሆን ለምን አልቻልንም? የወቅቶች መደጋገም ለመኖራችን ችግር እስካልሆነ ድረስ ቢደጋገም ምን ችግር አለው? ለምን እንደ ከንቱ ቆጠርነው?

እንዲያውም ሰው የአዲስ ነገር ናፍቆት ብቻ ሳይሆን የአዲስ ነገር ፍርሀትም ስላለበት እንዲያውም የሚደረገው ሁሉ ከዚህ ቀደም ከተደረገ ላለመናወጥና በጥንቃቄ ለመጠበቅ ይረዳዋል እኮ? ሞትስ ቢሆን ሁልጊዜ እንደአዲስ ለምን ያስደነግጠናል? በህይወት እያለን አሪፍ የሚባል ኑሮን እስከኖርን ድረስ ከዚያ ደብዛችን ቢጠፋ ምን አስጨነቀን?

መልሱ እግዚአብሔር ሲፈጥረን ከእርሱ ባነሰ በማንኛውም ነገር content መሆን ወይም መርጋት እንዳንችል አርጎ ስለሆነ ነው::

በመሰረቱ አዲስ ነገር ፍለጋ መባዘናችን የስሪታችን ውጤት ነው ልንቀይረውም አንችልም:: ሰው ከሌላው ፍጡር ሁሉ ልዩ ነው:: በእግዚአብሔር አምሳል ከኛ ውጪ የተፈጠረ የለም:: ሌላው ፍጥረት ከፀሀይ በታች ባለው ነገር content መሆን ይችላል:: ሰው ግን ላቅ ያለ ነው:: origin ኑ እግዚአብሔር ነው:: ከመጀመሪያም እቅዱ ሁሌ በመገኘቱ ውስጥ እየኖርን ሁል ጊዜ አዲስ በሚሆነው ማንነቱ እንድንደነቅና እንድንረጋ ነበር:: በሀጢያት ጠንቅ ምክንያት አእምሮችን ከፀሀይ በታች ብቻ እንዲያስብ corrupted ሆነ:: So, ከስሪቱ በእግዚአብሔር ባነሰ እንዳይደሰት የተፈጠረው ነፍሳችን ባነሱ ነገሮች ልናረጋው ስንሞክር ስቃዩ በዝቶ ሰለሞን ሁሉ የሞላለት ሰው መሆኑ በሰው ብቻ ሳይሆን ሰማይ ሳይቀር የመሰከረለት ሰው ከንቱ የከቱ ከንቱ አስባለ::

እንኳን ግን ከሰለሞን የሚበልጥ ኖረ!! እርሱ ሲመጣ ከፀሀይ በላይ ያለውን ነፍሳችንን የሚያረካውን እግዚአብሔር አብን አሳየን:: አሁን ከፀሀይ በታች እየኖርን ቢሆንም ከፀሀይ በላይ በሆነው የሰማይ ስርዐት እንመላለስ ዘንድ ተችሏል:: ደግሞም ከፀሀይ በታች ቀርቶ ፀሀይ የሚባል የማይኖርበት ጊዜ ይመጣል ራዕ 21:23 :: There will come a time for a full restoration!! ከፀሀይ በታች በአካል እየኖርን በሰማይ ስርአት ወይም rhythm መኖር አስችሎናል ኢየሱስ. Jesus has brought the flavor of heaven that we were meant to live in to the world. Therefore, we can find satisfaction and contentment in this world by enjoying heaven while living under the sun. ስሙ እራሱ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው አይደል? Emmanuel!! በእርሱ ምክንያት እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ወደአለም ወርዷል He is available and Jesus also said እስከአለም ፍፃሜ ከእናንተ ጋር ነኝ::
4👍3
እምነት የሚታመነውን አካል ያከብራል | ሰኔ 25

ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጠ እንጂ፣ የእግዚአብሔርን ተስፋ አልተጠራጠረም። (ሮሜ 4፥20)


አቤት፤ ቅድስናን እና ፍቅርን ለመያዝ በምናደርገው ሩጫ እግዚአብሔር ከብሮ ምነኛ ደስ ባለን? ነገር ግን ሩጫችን በተስፋ ቃሎቹ ላይ በመታመን ካልተደረገ በቀር እግዚአብሔር አይከበርም።

ስለ ኃጢአታችን በተሰቀለውና ለጽድቃችንም በተነሣው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ራሱን ሙሉ በሙሉ የገለጠልን አምላካችን የሚከብረው የተስፋ ቃሉን በደስታና በጽናት ስንቀበል ነው። ለእነዚህ ተስፋዎች ያወጣው ዋጋ ውድ ነው፣ የልጁን ደም አስከፍለውታል (ሮሜ 4፥25)።

ድካማችንን እና ውድቀታችንን አምነን ራሳችንን በፊቱ ስናዋርድ እና በሚያስፈልገን ጊዜ ሁሉ ጸጋን እንደሚሰጠን በእርሱ ስንታመን እግዚአብሔር ይከብራል። በሮሜ 4፥20 ላይ፣ ጳውሎስ ስለ አብርሃም እምነት ሲናገር፣ “ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጠ እንጂ፣ የእግዚአብሔርን ተስፋ አልተጠራጠረም” ይላል።

በእምነቱ በመበርታት እግዚአብሔርን አከበረ። በእግዚአብሔር ተስፋዎች ላይ የምንጥለው እምነት ጥበቡን፣ ኃይሉን፣ መልካምነቱን እና ታማኝነቱን ስለሚያውጅ አምላካችንን እጅግ ያከብረዋል። ስለዚህም፣ በእግዚአብሔር የጸጋ ተስፋ በመታመን መኖርን ካልተማርን፣ ምንም ያህል ትጉ የኀይማኖት ሥርዓት ፈጻሚዎች ብንሆን እንኳ፣ እግዚአብሔር ግን አይከብርም።

በሚሰጠን ጸጋ ላይ በትሕትና ተደግፈን ለመቀደስ ስንተጋ፣ ያኔ እግዚአብሔር ይከብራል።

የተሃድሶ አባት የሆነው ማርቲን ሉተር እንዲህ ይላል፦ “እምነት የሚታመንበትን አካል እውነተኛ እና እምነት ሊጣልበት የተገባ አድርጎ ስለሚቆጥረው፣ በጥንቃቄና በታላቅ አክብሮት ያከብረዋል።” እውነት ነው፤ ታማኝ ሆኖ የሰጠው ሰጪ ክብርን ይቀበላል።

ለእግዚአብሔር ክብር እንዴት መኖር እንዳለብን እንማር ዘንድ እንመኝ፣ እንጓጓ፣ እንጸለይ። ይህም የሚሆነው እግዚአብሔር በሚሰጠን ጸጋ በእምነት ስንኖር እና አለማመንን ስንዋጋ ነው።

Telegram
| YouTube | Facebook | Instagram | TikTok | Website

#ለዛሬ
"Blessed is the crisis that made you grow, the fall that made you gaze up to heaven, the problem that made you look for God."

ያሳደገን ቀውስ፣ ወደላይ እንድናይ ያስገደደን ውድቀት፣ እግዚአብሔርን እንድንፈልግ ያደረገን ችግር... (ለ)በረከት ነው።

St Pio
23👍1
ታስበው (በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው)
ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጐበኘውም (ትጠነቀቅለትም) ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? መዝሙር 8፥4

This is really the only natural, rational and emotional response for our how GOOD God is to us in Christ.
16👍1
አስባችሁታል???
እኔ በመካከላችሁ ያለሁ ቅዱስ አምላክ ነኝ እንጂ፣ ሰው አይደለሁምና፣ በቊጣ አልመጣም። (ሆሴዕ 11፥9)

እንደሰው የምንሰራው ትልቁ ስህተት እግዚአብሔርን እንደሰው መገመታችን ነው። ሰው ከእርሱ በቅድስና የሚያንሰውን ይኮንናል፣ በሀብት የሚበልጠውን ያንቋሽሻል፣ በውበት የሚያሸማቅቀውን ለመመልከት አይፈቅድም።

እግዚአብሔር ግን እንደሰው አይደለም። (Thankfully!) ቅዱስ ነው ስንል እያልን ያለነው ከእኛ ፍፁም የተለየ በራሱ class ያለ አምላክ ነውም ጭምር ነው። በመካከላቸው ፈቅዶ ለሚኖረው ለህዝቦቹ ቅድስናው ከእነሱ እንዲርቅ የሚገፈትረው ሀይል ወይንም በቁጣ እንዲገለጥ የሚያደርገው ነገር አይደለም። ይልቁንም በዚህ ምዕራፍ እንደምናየው በሀጥያት የወደቁትን ልጁቹን በርህራሄና በምህረት ሊያቆማቸው እንደሚንደረደር ነው።

ሰይጣን፣ የራሳችን depravity፣ ስንሰበክ የኖርነው one sided የእግዚአብሔር ምስል እግዚአብሔር የእርሱ ለሆኑት (ለተዋጁ) ሀጥያተኞች ያለውን ልብ (ሩህሩህና ትሁት ነኝ ያለውኝ ጌታ ኢየሱስ) እንድንመለከት አያደርገንም። We think, if we sin we shouldn't pray, read or fellowship with saints in church for a while until God is less disgusted with us. But thats the opposite of His heart towards us when we're weak and miserable He us drawn to us to save us.

ኢየሱስ ሊያድነን መለኮትነቱ እንዳለ ሰው ቢሆንም ግን እንደሰው አይደለም። ይህንን ወንጌላት በደንብ ያሳዩናል። ጌታ ያኔ ላላመኑበት እንኳ የነበረው ርህራሄ እንዲያድናቸው ሲያደርግ ስናይ...በውድ ዋጋ የእርሱ አድርጎን አካሉ ላደረገንማ እንዴት በየዕለቱ ሊያድነን አይፈቅድም?
10
2025/07/14 11:12:09
Back to Top
HTML Embed Code: