አሚር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥71 ምእመናን እና ምእምናት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ

"አምር" أَمْر የሚለው ቃል "አመረ" أَمَرَ ማለትም "አዘዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ትእዛዝ" ማለት ነው፥ በመልካም የሚያዙ አዛዥ "አሚር" أَمِير ሲባሉ የሚታዘዙ ታዛዥ ደግሞ "መእሙር" مَأْمُور ይባላሉ፦
3፥104 ከእናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነርሱ የሚድኑ ናቸው፡፡ وَلْتَكُن مِّنكُمْ أُمَّةٌ يَدْعُونَ إِلَى الْخَيْرِ وَيَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ ۚ وَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
9፥71 ምእመናን እና ምእምናት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ

በደግ ነገር በማዘዝ እና በክፉ ነገር በመከልከል የምታዝ ሴት አማኝ "አሚራህ" أَمِيرَة ትባላለች፥ አሏህ በከለከለው መጥፎ ነገር የሚከለክል እና ባዘዘው መልካም ነገር የሚያዝ አሚርን መታዘዝ ግዴታ ነው፦
4፥59 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ! መልእክተኛውን እና ከእናንተ የትእዛዝ ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ وَأُولِي الْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ

"ከ" የሚለው መስተዋድድ ያለበት "እናንተ" የሚለው ተውላጠ ስም የሚያመለክተው ምእመናንን ብቻ ሲሆን "ኡውሊል አምር" أُولِي الْأَمْر የተባሉት አሚራት ከምእመናን ብቻ መሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። አሚራትን መታዘዝ በእርግጥ ነቢያችንን"ﷺ" መታዘዝ ነው፥ አሚራትን ማመጽ ነቢያችንን"ﷺ" ማመጽ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 33, ሐዲስ 46
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እኔን የሚታዘዝ በእርግጥ አሏህን ታዘዘ፥ እኔን የሚያምጽ በእርግጥ አሏህን አመጸ። አሚር የሚታዘዝ በእርግጥ እኔን ታዘዘ፥ አሚርን የሚያምጽ በእርግጥ እኔን አመጸ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ مَنْ أَطَاعَنِي فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ وَمَنْ يَعْصِنِي فَقَدْ عَصَى اللَّهَ وَمَنْ يُطِعِ الأَمِيرَ فَقَدْ أَطَاعَنِي وَمَنْ يَعْصِ الأَمِيرَ فَقَدْ عَصَانِي ‏"‏

አምላካችን አሏህ አሚራትን የምንታዘዝ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
●▯ውይይት ▯●

"የነብያችን ጣኦት ያመልኩ ነበርን?"

◍ ወንድም ሳላህ
🆅🆂
◍ ወገናችን ኢሳያስ
ቁርአንን በተጅዊድ አሳምረን እናምብብ

@slmatawahi
ቅጣት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥40 የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا

"ቂሷስ" قِصَاص የሚለው ቃል "ቋሶ" قَاصَّ ማለትም "አመሳሰለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማመሳሰል" ማለት ነው፦
2፥179 ባለ አእምሮዎች ሆይ! ለእናንተም በማመሳሰል ሕግ ውስጥ ሕይወት አለላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ፡፡ وَلَكُمْ فِي الْقِصَاصِ حَيَاةٌ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማመሳሰል" ለሚለው ቃል የገባው "ቂሷስ" قِصَاص መሆኑ ልብ አድርግ! ሰው ጤናማ ሕይወት ይኖር ዘንድ አምላካችን አሏህ ቂሷስን ደንግጓል፥ በቂሷስ ነፍስ ያጠፋ ነፍሱ ይጠፋል፣ ዓይን ያጠፋ ዓይኑ ይጠፋል፣ አፍንጫም ያጠፋ አፍንጫው ይጠፋል፣ ጆሮም ያጠፋ ጆሮው ይጠፋል፣ ጥርስ የሰበረ ጥርሱ ይሰበራል። እነዚህ ቁስሎችን በቂሷስ ይፈታሉ፦
5፥45 በእነርሱም ላይ በውስጧ፦ «ነፍስ በነፍስ ዓይንም በዓይን አፍንጫም በአፍንጫ ጆሮም በጆሮ ጥርስም በጥርስ ይያዛል፥ ቁስሎችንም "ማመሳሰል" አለባቸው» ማለትን ጻፍን፡፡ وَكَتَبْنَا عَلَيْهِمْ فِيهَا أَنَّ النَّفْسَ بِالنَّفْسِ وَالْعَيْنَ بِالْعَيْنِ وَالْأَنفَ بِالْأَنفِ وَالْأُذُنَ بِالْأُذُنِ وَالسِّنَّ بِالسِّنِّ وَالْجُرُوحَ قِصَاصٌ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ማመሳሰል" ለሚለው ቃል የገባው "ቂሷስ" قِصَاص መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። መጥፎ ለሠሩ ሠዎች መጥፎ ቅጣት መቅጣት ቂሷስ ነው፥ የአሏህ መጽሐፍ ጭብጡ ቂሷስ ነው፦
42፥40 የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 26
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የአሏህ መጽሐፍ ቂሷስ ነው"። أَنَّ أَنَسًا، حَدَّثَهُمْ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كِتَابُ اللَّهِ الْقِصَاصُ ‏”‌‏.‏

የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ስለሆነ በአንድ ወቅት ነቢያችን"ﷺ" እረኛቸውን ለዑረይናህ ሰዎች እንዲንከባከባቸው ሰተዋቸው ሳሉ የዑረይናህ ሰዎች ግን በተቃራኒው የነቢያችንን"ﷺ" እረኛ እጅና እግር ቆርጠው እና ዓይን አጥፍተው በመግደላቸው ቂሷስ ተደርጎ እጃቸውንና እግራቸውንም እንዲቆረጥ እና ዓይኖቻቸውም እንዲጠፋ ተደርጓል፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 62
አነሥ እንደተረከው፦ "ሰዎች ከዑክል ወይም ከዑረይናህ ወደ ነቢዩ"ﷺ" መጡ፥ የመዲናህ አየር ንብረት ተጨናንቋል። ነቢዩም"ﷺ" ለእነርሱ፦ "ወደ ግመሎች ሂዱና ወተታቸውን ጠጡ እንዲሁ ሽንታቸውን ለመድኃኒት ተጠቀሙ" ብለው አዘዟቸው፥ እነርሱ ግን እረኛውን ገድለው ግመሎቹን ሰረቁ። ነቢዩም"ﷺ" ከኃላቸው ሰው ልከው እጃቸውን እና እግራቸውንም ቈረጡ፥ ዓይኖቻቸውም አጠፉ"። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم نَفَرٌ مِنْ عُكْلٍ أَوْ عُرَيْنَةَ فَأَمَرَ لَهُمْ - وَاجْتَوَوُا الْمَدِينَةَ - بِذَوْدٍ أَوْ لِقَاحٍ يَشْرَبُونَ أَلْبَانَهَا وَأَبْوَالَهَا فَقَتَلُوا الرَّاعِيَ وَاسْتَاقُوا الإِبِلَ فَبَعَثَ فِي طَلَبِهِمْ فَقَطَّعَ أَيْدِيَهُمْ وَأَرْجُلَهُمْ وَسَمَلَ أَعْيُنَهُمْ ‏.‏

"ሠመለ" سَمَلَ ማለት "አጠፋ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ፦ "ዓይንም በዓይን ይያዛል፥ ቁስሎችንም "ማመሳሰል" አለባቸው" ስላለ እነዚህ ሰዎች የእረኛውን ዓይን ስላጠፉ ዓይናቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፦
ሡነን ነሣኢይ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 78
አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" የእረኛውን ዓይኖች በማጥፋታቸው ምክንያት የእነዚያን ሰዎች ዓይኖች ብቻ አጥፍተው ነበር"። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ إِنَّمَا سَمَلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم أَعْيُنَ أُولَئِكَ لأَنَّهُمْ سَمَلُوا أَعْيُنَ الرُّعَاةِ ‏.‏

በኪታቡ አት-ተሕሪሙ አድ-ደም ዐውድ ውስጥ "እነዚያ" የተባሉት የዑረይናህ ሰዎች እንደሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። በባይብልም ቢሆን ዓይን ያጠፋ ዓይኑ እንዲጠፋ ትእዛዝ አለ፦
ዘጸአት 21፥23-25 ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት፣ ዓይን በዓይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር፣ መቃጠል በመቃጠል፣ ቍስል በቍስል፣ ግርፋት በግርፋት ይከፈል።

በባይብል የገደለ ብቻ ሳይሆን አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደላል፦
ዘሌዋውያን 27፥17 ሰውንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ፈጽሞ ይገደል።
ዘጸአት 21፥17 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል።

ኢየሱስ ሲመጣ ደግሞ ሕጉ ጠብቆ እና አጥብቆ የሞት ፍርድ የሚገባው የገደለ ብቻ ሳይሆን በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ የሞት ፍርድ እንደሚገባው አበክሮ እና አዘክሮ ተናግሯል፦
ማቴዎስ 5፥21-22 ለቀደሙት፦ አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።

"የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" ማለት በዘሌዋውያን 27፥17 "ፈጽሞ ይገደል" የሚለው ከሆነ "በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" ማለት "ፈጽሞ ይገደላል" ማለት ነው። እንደውም ኢየሱስ እንቅጩን ፍርጥ አርጎ፦ "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል" ብሏል፦
ራእይ 13፥10 "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል"።

በተጨማሪ ሬካብ እና ወንድሙ በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት ገብተው ኢያቡስቴን ገድለዉት እራሱን ቆረጡት፥ ዳዊትም ሬካብን እና ወንድሙ በዓናን አስገድሎ እጃቸውን እና እግራቸውን እንዲቆረጥ አድርጓል፦
2 ሳሙኤል 4፥7 ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ እርሱ በእልፍኙ በምንጣፉ ላይ ተኝቶ ሳለ መቱት፥ ገደሉትም፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱት።
ሳሙኤል 4፥12 ዳዊትም ጕልማሶቹን አዘዘ፥ ገደሉአቸውም፤ እጃቸውን እና እግራቸውን ቈርጠው በኬብሮን በውኃ መቆሚያ አጠገብ አንጠለጠሉአቸው።

ነቢያችን"ﷺ" በቂሷስ ፍርድ እና ቅጣት ማድረጋቸው ነቢይ ላለመሆናቸው መስፈርት ከሆነ እንግዲያውስ በነካ አፋችሁን ሙሴ፣ ኢየሱስ፣ ዳዊት የፈጣሪ ነቢይ አይደሉም በሉና! ምን ይሻላችኃል ግን? ባይብል ሲጠቀስ እንቡርና ፒርር እንዲሁ ቡፍና ኩፍ ከምትሉ ቁርኣንን እና ሐዲስን ለማሳለጥ ፊጥና ቁጢጥ የምትሉትን ተዉ!
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውይይት
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
●▯ውይይት▯●

- "እኛነት በቁርዓን"
- "የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ"

◍ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
🆅🆂
◍ ወገናችን አብርሽ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Surat Al-Kahf - Mishary Rashed Alafasy الشيخ مشاري راشد العفاسي سورة الكهف
Audio
የጌታዬ የአላህ ቃል ቁርአኔ

من سورة الأنفال || القارئ فيصل الرشود
ጂብራኢል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥97 “ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት” በላቸው፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ

ጂብሪል ከመላእክት አለቆች አንዱ ነው፦
2፥97 “ለጂብሪል ጠላት የኾነ ሰው በቁጭት ይሙት” በላቸው፡፡ قُلْ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّجِبْرِيلَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 47
ሠሙራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፥ ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ “ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን የእሳት ዘበኛ ነው፥ “እኔ ጂብሪል ነኝ”። ይህ ሚካኢል ነው”። عَنْ سَمُرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ‏”‌‏.‏

“ኢል” ئِيل የሚለው ቃል “ኢላህ” إِلَـٰه ለሚለው ምጻረ ቃል ሲሆን “አምላክ” ማለት ነው፥ “ኢል” ئِيل የሚለው ቃል በመላእክት ስም መዳረሻ ቅጥያ ሆኖ ይመጣል። ለምሳሌ “ሚካ-ኢል” مِيكَائِيل እና “ጂብራ-ኢል” جِبْرَائِيل ተጠቃሽ ናቸው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 196
ዘይድ ኢብኑ ሓሪሳህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ጂብራኢል ስለ ውዱእ አስተማረኝ”። زَيْدِ بْنِ حَارِثَةَ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ عَلَّمَنِي جِبْرَائِيلُ الْوُضُوءَ

“ጂብሪል” جِبْرِيل “ሀምዘቱል ወስል” هَمْزَة الوَصْل ተውጦ ሲነበብ ሲሆን “ሀምዘቱል ወስል” هَمْزَة الوَصْل በግልጽ ሲመጣ ደግሞ “ጂብራ-ኢል” جِبْرَائِيل ይሆናል፥ ይህንን በዐረቢኛው ባይብልም ማየት ይቻላል፦
ሉቃስ 1፥19 መልአኩም መልሶ፦ እኔ በአሏህ ፊት የምቆመው ጂብራኢል ነኝ። فَأجَابَهُ المَلَاكُ: «أنَا جِبْرَائِيلُ الَّذِي أقِفُ فِي حَضْرَةِ اللهِ
ዳንኤል 9፥21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው “ሰው” ጂብሪል እነሆ እየበረረ መጣ። أيْ بَيْنَمَا كُنْتُ أُصَلِّي هَذِهِ الصَّلَاةَ – طَارَ الرَّجُلُ جِبرِيلُ الَّذِي رَأيْتُهُ قَبْلًا فِي الرُّؤيَا مُسرِعًا فَوَصَلَ إلَيَّ فِي وَقْتِ ذَبِيحَةِ المَسَاءِ.

“ጂብራ-ኢል” جِبْرَائِيل ወይም “ጂብሪል” جِبْرِيل የሚለው ቃል “ጂብር” جِبْرَ እና “ኢል” ئِيل ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ “ጂብር” جِبْرየሚለው ቃል “ጀበረ” جَبَرَ ማለትም “ጀገነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ጀግና” ማለት ነው። “ጂብራ-ኢል” جِبْرَائِيل ማለት በጥቅሉ “የአምላክ ጀግና” ማለት ነው፥ በተመሳሳይ በዕብራይስጥ “ገብር-ኤል” גַּבְרִיאֵל ነው። “ጌቤር” גָּבַר ማለት “ጀግና” “ኃያል” “ብርቱ” ማለት ነው፦
2 ሳሙኤል 1፥23 ከአንበሳም ይልቅ “ብርቱዎች” ነበሩ። קלו מאריות גברו׃

“ገበር” גֶּבֶר ሲሆን ደግሞ “ሰው” ማለት ነው፦
ኢዮብ 34፥7 እንደ ኢዮብ ያለ “ሰው” ማን ነው? מי־גבר כאיוב

“ገብር-ኤል” גַּבְרִיאֵל በዚህ ትርጉሙ “የአምላክ ሰው” ማለት ነው፥ “ኤል” אֵל የሚለው ቃል “ኤሎሃ” אֱלוֹהַּ ለሚለው ምጻረ ቃል ሲሆን “አምላክ” ማለት ነው። ጂብሪል በሰው አምሳል ወደ ሰዎች ስለሚመጣ የአምላክ ሰው ነው፥ ወደ መርየም የመጣው ትክክለኛ ሰው ተመስሎ ነው፦
19፥17 ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا

ጂብሪል ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚመጣው በሚወዱት ባልደረባ በዲሕያህ ኢብኑ ኸሊፋህ በሚባል ሰው ተመስሎ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 2
አቡ ዑስማን እንደተረከው፦ “ጂብሪል ወደ ነቢዩ”ﷺ” ሲመጣ ኡሙ ሠላማህ ከእርሳቸው ጋር ነበረች፥ ጂብሪል መናገር ጀመረ። ነቢዩም”ﷺ”፦ “ኡሙ ሠላማህ ይህ ማን ነው? አሉ፥ እርሷም፦ “ይህ ዲሕያህ ነው” አለች። ጂብሪል በሄደ ጊዜ እርሷም፦ “ወሏሂ! በነቢዩ”ﷺ” ሑጥባህ ላይ ስለ ጂብሪል ዜና እስኪነግሩን ድረስ ከዲሕያህ በስተቀር ሌላ ማንንም አላሰብኩም ነበር”። عَنْ أَبِي عُثْمَانَ، قَالَ أُنْبِئْتُ أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَعِنْدَهُ أُمُّ سَلَمَةَ فَجَعَلَ يَتَحَدَّثُ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لأُمِّ سَلَمَةَ ‏ “‏ مَنْ هَذَا ‏”‌‏.‏ أَوْ كَمَا قَالَ قَالَتْ هَذَا دِحْيَةُ‏.‏ فَلَمَّا قَامَ قَالَتْ وَاللَّهِ مَا حَسِبْتُهُ إِلاَّ إِيَّاهُ حَتَّى سَمِعْتُ خُطْبَةَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم يُخْبِرُ خَبَرَ جِبْرِيلَ أَوْ كَمَا قَالَ،

በባይብልም ቢሆን ገብርኤል በሰው አምሳያ ወደ ዳንኤል ስለመጣ “ሰው” ተብሏል፦
ዳንኤል 9፥21 ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው “ሰው” ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ።

ምነው አብርሃም ቤት የገቡት ሦስቱ መላእክት “ሰዎች” ተብለው የለ እንዴ?፦
ዘፍጥረት 18፥2 ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ “ሦስት ሰዎች” በፊቱ ቆመው አየ።
ዘፍጥረት 18፥16 “ሰዎቹም” ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ።
ዘፍጥረት 18፥22 “ሰዎቹም” ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ።

እንዲሁ ከአብርሃም ቤት ወደ ሰዶም ያቀኑት ሁለቱ መላእክት ሁለቱ ሰዎች ተብለዋል እኮ፦
ዘፍጥረት 19፥1 “ሁለቱም መላእክት” በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ።
ዘፍጥረት 19፥10 “ሁለቱም ሰዎች” እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ እነርሱ ዘንድ ወደ ቤት አገቡት መዝጊያውንም ዘጉት።
ዘፍጥረት 19፥12 “ሁለቱም ሰዎች” ሎጥን አሉት። እኛ ይህን ስፍራ እናጠፋለንና፥ ጩኸታቸው በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል።

እንግዲህ ተረጋግተን ልጡ የተራሰ ጉድጓዱ የተማሰ ምርምር ስናረግ “ገብርኤል” ማለት “የአምላክ ሰው” ማለት መሆኑን እና ገብርኤል በሰው አምሳል ስለሚመጣ “ሰው” መባሉን አስረግጠን እና ረግጠን ካስረዳን ዘንዳ “ጂብራኢል እንዴት በሰው አምሳል ይመጣል” ብላችሁ የተቻችሁት ትችት የጨባራ ለቅሶ እና ተስካር ነው፥ ዙሪያ ገቡን ሳትመረምሩ መተቸት እንዲህ ድባቅ ያስገባል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት ጌድዮን ወሒድ
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
●▯ጥያቄዎችና መልሶቻቸው▯●

- "ስግደት በስንት ይከፈላል?"
- "ኢብሊስ መልዓክ ነበርን?"
- "ነቢያት ነቢይ ለመሆናቸው መስፈርቱ ምንድነው?"
- "አይሁዶች ለምን ተረገሙ?"

ጠያቂ
◍ አይሁዳዊው ወገናችን ጌዲዮን
መላሽ
◍ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
{ #تلاوة_خاشعۃ_من_سورة_المعارجِ }

🎤°•القارئ ⁖ ⟨ #عبدالرحمن_العوسي

#እነዚያም እነርሱ አደራዎቻቸውንና ቃል ኪዳናቸውን ጠባቂዎች የኾኑት።

#እነዚያም እነርሱ በምስክርነታቸው ትክክለኞች የኾኑት፡፡

#እነዚያም እነርሱ በሶላቶቻቸው ላይ የሚጠባበቁት፡፡
أولئك في جنات مكرمون
#እነዚህ (ከዚህ በላይ የተወሱት ሁሉ) በገነቶች ውስጥ የሚከበሩ ናቸው፡፡#

@slmatawahi
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኔ የዋሆች ምስጥ ብለው ነው የሚሰሙት
የተደበቀው እውነት በምህራችን ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም ሸር ለሁሉም።

"የስላሴ እሳቤ" እና "የተደበቀው እውነት" መጻሕፍ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ አዳማ እና ደሴ ይገኛሉ።

አዳማ ማግኘት የምትፈልጉ call +251966640370

ደሴ ማግኘት የምትፈልጉ፦
አረብገንዳ ሸህ አብዱ መክተባ
ሸርፍተራ ፋጡማህ መክተባ
አሕመድ መክተባ ይገኛል

መጽሐፉን መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ያገኙታል፥ የበለጠ ለመረጃ +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ!
የኢየሱስ ወላጆች?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ ስለ እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ الْحَقِّ الَّذِي فِيهِ يَمْتَرُونَ

አንጢዲቆማርያጦስ"Antidicomarianites" በ 428 ድኅረ ልደት የተጀመረ እንቅስቃሴ ሲሆን "ኢየሱስ ማርያም እና ዮሴፍ ተራክቦ አርገው የወለዱት የአብራካቸው ክፋይ ነው" የሚል ትምህርት ነው፥ ይህ ትምህርት መሠረቱ እራሱ ባይብል ነው፦
ሉቃስ 2፥33 "አባቱ" እና እናቱ ስለ እርሱ በተባለው ነገር ይደነቁ ነበር። καὶ ἦν ὁ πατὴρ αὐτοῦ καὶ ἡ μήτηρ θαυμάζοντες ἐπὶ τοῖς λαλουμένοις περὶ αὐτοῦ.
And "his father" and his mother marveled at what was said about him. English Standard Version

ዐማርኛው ላይ "ዮሴፍ" ቢለውም ግሪኩ "ፓተር" πατὴρ ብሎ አስቀምጦታል፥ እንዲሁ English Standard Version "his father" በማለት አስቀምጦታል። "ፓተር" πατὴρ ማለት "አባት" ማለት ሲሆን "ሜቴር" μήτηρ ማለት ደግሞ "እናት" ማለት ነው፥ እዚህ ጥቅስ ላይ ማርያም የኢየሱስ "እናት" እንደተባለች ሁሉ ዮሴፍ የኢየሱስ "አባት" ተብሏል። ዮሴፍ የኢየሱስ "አባት" እንደሆነ የሚናገረው ሉቃስ ብቻ ሳይሆን ማርያምም ዮሴፍ የኢየሱስ "አባት" እንደሆነ ለማሳየት ኢየሱስን "አባትህ" ብላዋለች፦
ሉቃስ 2፥48 ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ "አባትህ" እና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን፡ አለችው።

ዮሴፍ ለኢየሱስ የተባለው "አባት" ብቻ ሳይሆን "ጎኒዩስ" ተብሏል፥ "ጎኒዩስ" γονεύς የሚለው ቃል "ጊኖማይ" γίνομαι ማለትም "ተወለደ" "ተገኘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ወላጅ"parent" ወይም "አስገኝ"begetter" ማለት ነው፦
ሉቃስ 2፥27 በመንፈስም ወደ መቅደስ ወጣ፤ "ወላጆቹም" እንደ ሕጉ ልማድ ያደርጉለት ዘንድ ሕፃኑን ኢየሱስን በአስገቡት ጊዜ። καὶ ἦλθεν ἐν τῷ Πνεύματι εἰς τὸ ἱερόν· καὶ ἐν τῷ εἰσαγαγεῖν τοὺς γονεῖς τὸ παιδίον Ἰησοῦν τοῦ ποιῆσαι αὐτοὺς κατὰ τὸ εἰθισμένον τοῦ νόμου περὶ αὐτοῦ,
ሉቃስ 2፥41 "ወላጆቹም" በያመቱ በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ነበር። Καὶ ἐπορεύοντο οἱ γονεῖς αὐτοῦ κατ’ ἔτος εἰς Ἱερουσαλὴμ τῇ ἑορτῇ τοῦ πάσχα.
ሉቃስ 2፥43 ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ "ወላጆቹም" አላወቁም ነበር። καὶ τελειωσάντων τὰς ἡμέρας, ἐν τῷ ὑποστρέφειν αὐτοὺς ὑπέμεινεν Ἰησοῦς ὁ παῖς ἐν Ἱερουσαλήμ, καὶ οὐκ ἔγνωσαν οἱ γονεῖς αὐτοῦ.

"ጎኒኢስ" γονεῖς የሚለው ቃል "ጎኒዩስ" γονεύς ለሚለው ቃል ብዜት ሲሆን "ወላጆች" ማለት ነው፥ የኢየሱስ ወላጆቹ የተባሉት ማርያም እና ዮሴፍ መሆናቸው የሚደንቅ ነው፦
ሉቃስ 2፥16 ፈጥነውም መጡ ማርያምን እና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ። καὶ ἦλθαν σπεύσαντες, καὶ ἀνεῦραν τήν τε Μαριὰμ καὶ τὸν Ἰωσὴφ καὶ τὸ βρέφος κείμενον ἐν τῇ φάτνῃ·

"ዮሴፍ" የተጸውዖ ስም ሲሆን ከፊት ለፊቱ "ቶን" τὸν የሚል አመልካች መስተአምር መግባቱ በራሱ የሰዋስው ችግር አለበት፥ ጽንፈኛ(ወጋዊ) የአዲስ ኪዳን ምሁር ፕሮፌሰር ዳንኤል ዋላስ ከለዘብተኛ(ሐራዊ) የአዲስ ኪዳን ምሁር ከፕሮፌሰር ባርት ሔርማን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ፕሮፌሰር ዳንኤል ዋላስ፦ "ውስን አመልካች መስተአምር በተጸውዖ ስም ላይ ለምን እንደመጣ አላውቅም" ብለዋል።
በመጀመሪያ መቶ ክፍለ ዘመን ኢቦናይተስ የሚባሉ ክርስቲያኖች፦ "ዮሴፍ የኢየሱስ ወላጅ አባት ነው" የሚለውን ትምህርታቸው መሠረት ያረጉት ከላይ ባሉት አናቅጽ ነው፥ ቅሉ ግን አምላካችን አሏህ ዒሣ ከመርየም የተወለደው ያለ አባት እንደሆነ ይነግረናል፦
3፥47 ፦"ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፥ "ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ "ኹን" ይለዋል፥ ወዲውኑም ይኾናል" አላት፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

መርየም ወንድ ሳይነካት በተአምር ዒሣን ፀንሳ ወልዳለች፥ አሏህ ያለ ወንድ ዘር እንቁላሉን "ኹን" በማለት ሰው መፍጠር ይችላል። ስለዚህ የዒሣ ልጅነት የሚጠጋው ወደ መርየም ብቻ ስለሆነ አሏህ በ 23 ቦታ ዒሣን "የመርየም ልጅ" ብቻ ብሎታል፦
19፥34 ይህ የመርየም ልጅ ዒሣ ነው፡፡ ያ ስለ እርሱ የሚከራከሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ ذَٰلِكَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ ۚ قَوْلَ الْحَقِّ الَّذِي فِيهِ يَمْتَرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ፊ” فِي የሚለው መስተዋድድ “ዐን” عَنْ ማለትም “ስለ”about” በሚል የመጣ ነው፥ ስለ ዒሣ የሚከራከሩበትን ነገር አሏህ በቁርኣኑ የነገረን ሁሉ እውነተኛ ቃል ነው። በትንሳኤ ቀን እየተከራከሩ በሚወዛገቡት ነገር አሏህ ይፈርዳል፦
3፥55 ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፥ በእርሱ ትለያዩበትም በነበራችሁት ነገር በመካከላችሁ እፈርዳለሁ፡፡ ثُمَّ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأَحْكُمُ بَيْنَكُمْ فِيمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት
የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
●▯ውይይት ▯●

◍ ወንድም ዒምራን
◍ ወንድም ሳላህ
🆅🆂
◍ ወገናችን አብርሽ
◍ ወገናችን ጌዲዮን
Audio
አህሉል ቁርአን

📌 فَلَوْلَآ إِذَا بَلَغَتِ ٱلْحُلْقُومَ
(ነፍስ) ጉረሮንም በደረሰች ጊዜ፡፡  📌

- القــارئ ؛ عبدالرحمن أبا الخيل
ቃሪእ- ዓብዱረህማን አበልኸሊል
ሳጥናኤል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥162 «ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

"ሳጥናኤል" የሚለው የግዕዝ ቃል በዕብራይስጥ "አዛዝኤል" עֲזָאזֵל ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "አዛዝ" עֲזָא ማለት "ጥንካሬ" ማለት ሲሆን "ኤል" זֵל ማለት አምላክ ማለት ነው። በጥቅሉ "አዛዝኤል" ማለት "አምላክ ጥንካርዬ ነው" ማለት ነው፥ ይህ ስም ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን የሚባል ጂን ከመሰይጠኑ በፊት የነበረው ስም እንደሆን በአፈ ታሪክ ይነገራል። ይህ ጋኔን በመጽሐፈ ሄኖክ ላይ ከሃያ አንዱ አጋንንት አንዱ ሆኖ ተገልጿል፦
ሄኖክ 3፥10 በአዛዝኤል ሥራ እና ትምህርት ምድር ሁሉ ጠፋች፥ የሰውን ሁሉ ኃጢአት በእርሱ ጻፍበት አለው።
ሄኖክ 15፥7 "በአዛዝኤል" ይፈረድበታል፥ በወገኖችሁ ሁሉ እና በመላእክት ጌታ ስም ባላመኑ በሰራዊቱም ሁሉ ይፈረድባቸዋል።
ሄኖክ 19፥10-12 የእነዚያ የአጋንንት ስማቸው እንደዚህ ነው፦አለቃቸው ስማዝያ፣ ሁለተኛውም አርስጢኪፋ ነው፣ ሥስተኛውም አርሚን ነው፣ አራተኛውም ኮክብኤል ነው። አምስተኛውም ጡርኤል ነው፣ ስድስተኛውም ሩምያል ነው፣ ሰባተኛውም ዳንኤል ነው፣ ስምንተኛውም ምቃኤል ነው፣ ዘጠነኛውም በራቃኤል ነው፣ አስረኛውም “አዛዝኤል” ነው፣ አስራ አንደኛውም አርማሮስ ነው፣ አስራ ሁለተኛውም በጠርያል ነው።

አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ ለአዛዝኤል ይሆናል፦
ዘሌዋውያን 16፥8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥልባቸዋል፥ አንዱን ዕጣ ለያህዌህ ሌላውንም ዕጣ "ለአዛዝኤል"። וְנָתַן אַהֲרֹן עַל-שְׁנֵי הַשְּׂעִירִם, גֹּרָלוֹת–גּוֹרָל אֶחָד לַיהוָה, וְגוֹרָל אֶחָד לַעֲזָאזֵל.

ዐማርኛው ላይ "ሚለቀቅ" ብሎ ቢያስቀምጠውም ዕብራይስጡ ግን እንቅጩን ፍርጥ አርጎ "አዛዝኤል" עֲזָאזֵל ብሎ አስቀምጦታል። ዐረቢኛውም ባይብል ሳያቅማማ "ዐዛዚል" عَزَازِيل ብሎታል፥ እንዲሁ በእንግሊሹ Good News Translation በትክክሉ "Azazel" ብሎታል። ከሥነ አምክኖ አንጻር እስቲ እዩት! አንዱ ለፈጣሪ ሁለተኛው ለሳጥናኤል ፍየል ይገበራል? "ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ" ተብሏል እኮ፦
ዘጸአት 22፥20 ከያህዌህ በቀር ለአንዳች አምላክ የሚሠዋ ፈጽሞ ይጥፋ።

ከአንዱ አምላክ ውጪ ለሌላ ማንነትና ምንነት መስዋዕት መሰዋት ይህንን ያክል ከባድ ወንጀል ከሆነ እንግዲያውስ ለሳጥናኤል የፍየል መስዋዕት ይቀርባል የሚለውን የብርዘት ውጤት ትታችሁ ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ብቻ እንድትሰዉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሙሥሊም መስዋዕቱ ለፈጠረው ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ ብቻ ነው፦
6፥162 «ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡ قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://www.tg-me.com/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውይይት
husu negn ሁሱ ነኝ
●▯ውይይት ▯●

◍ ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
🅅🅂
◍ አይሁዳዊው ወገናችን ጌዲዮን
سوره النور🥀

🌠የብረሀን/ ምዕራፍ🏞
🌇

🕌በመድና፣የወረደ🕌

ራሀቱል፣ቀልብ❤️
@slmatawahi
2024/04/29 08:06:32
Back to Top
HTML Embed Code: