Telegram Web Link
ይገርማል ያ ሁሉ ልጃገረድ ባንተ ሃብትና ዝና ሲነሆልል ያቺ “ኬቲ” ብቻ ጥብርር ማለቷ ይገርማል። አትጠቀሚ ቢላት ነው እንጂ አንተን የመሰለ ሸበላ፣ መለሎ፣ ዲታ፣ ተጨዋች ጠይቋት እምቢ ማለቷ ካሰገራሚ ነገሮች ውስጥ እጅግ በጣም አስገራሚው ነው – ለበርካቶች። ሴቱ ሁሉ ያንተን ቀላል ሰላምታ ለማግኘት ስንት እንዳልተራኮተ እሷ ግን በስንት ምልጃና ልመና ልትነካ አልቻለችም። በርግጥ ውብ ነች – ውብ የሚለው ቃል ከገለጻት። ቁመናዋ ሌላ ነው። ጨዋታ አዋቂ ናት። ሳቅና ፈገግታዋ ልብን ይንጣል። እንደዘመኑ ሴቶች መልክ ብቻ ሳትሆን ቁም ነገረኛም ነች። አስተሳሰቧ ለነገሮች ያላት ምልከታና ትንታኔ አጃኢብ ያሰኛል። አንተንስ የማረከህ ምን ሆነና። የሷን ይሁንታ ለማግኘት ያልከፈልከው መስዋዕትነት መች አለና። ህይወትህን ገብር ብትባልስ ወደ ኋላ የምትል ይመስልሃል? እርግጠኛ አይደለህም። ዛሬ ግን ልዩ ቀን ነው ላንተ። “ኬቲ”ን የመሰለች ሸጋ ልጅ የግልህ አድርገሃል። ከስንት ስቃይና ልፋት በኋላ ከቅፍህ ገብታለች። ውበቷ ደግሞ ከወትሮው ተለየብህ። ይበልጥ ውብ ይበልጥ ትሁትና አስተዋይነቷ ተገለጠልህ። ከዚህ በኋላ ምን የቀረ ነገር አለ? ምንም! ወደ ገደለው . . . ነዋ! . . . ምክሬን ግን አትዘንጋ! ሙት ብያሃለሁ ሙት – ከዚና በፊትም ቢሆን!

ከተማው መሐል ላይ የሚገነባው ባለ ሀምሳ ምናምን ሰማይ ጠቀስ ፎቅ የሰው መነጋገሪያ ከሆነ ቆዬ። ስምህና ዝናህም የዛኑ ያክል በየ ጋዜጣው፣ በየ መጽሄቱ፣ በራዲዮና ቴሌቭዥን ሁሉ ተወራልህ። ያንተን ፎቶ ሳይዝ የወጣ ጋዜጣ፣ ያንተን ስም ያልጠቀሰ መጽሄት ምን ያማረ ስራ ይዞ ቢወጣ ዞሮ የሚያየው ገዥ የለም። አንተ በምታልፍበት ጎዳና ሁሉ ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባልተናነሰ መልኩ መንገድ ይዘጋልሃል፤ አጃቢ ይመደብልሃል። ምክንያቱም የሀገሪቱ ዋልታና መከታ ሆነሃል። ያንተ ቢዝነስ ማትረፉ የሀገሪቱ ማትረፍ ነው። ኪሳራህም እንደዛው። በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ታላላቅ ፕሮጅክቶች በሙሉ ያንተ አሊያም ያንተ አሻራ ያረፈባቸው ናቸው። ተፅዕኖህ ከሀገር ውስጥ አልፎ አለማቀፍ ይዘትን መጎናጸፍ ጀምሯል። በቅርቡ በተከናወነው የዓለም መሪዎች ጉባዔ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን ተጋብዘሃል። በዚያ ስብሰባ ላይም የነበረው አቀባበልና ከበሬታ ከጠበከው በላይ ነበረ። እነዚህና መሰል ጉዳዮች ተደማምረው አንተ ላይ ተፅዕኖ ማሳደራቸው አልቀረም። ከዚህ የተነሳም በሀገሪቱ ለሚከናወኑ የልማት ተግባራት ጠቀም ያለ ድጎማ አድርገሃል። ከውጭ ሀገር በመግባት ላይ ያሉት ውድ እቃዎች ወደብ ቢደርሱም ባንዳንድ ያሰራር ሂደቶች በታሰቡበት ሰዓት ወደ ገበያ ሊገቡ አልቻሉም። ይህና ሌሎች መሰል ክስተቶች የስራ ማስኬጃ ገንዘብ እጥረት እንዲከሰት ምክንያት ሆነዋል። ስራዎች መጓተት የለባቸውም። በተለይ ደግሞ የህብረተሰቡ ዓይን ያረፈበትና የሀገሪቱ መለያ ይሆናል ተብሎ የታሰበው ህንጻ በምንም መልኩ ስራው ዝንፍ ማለት የለበትም። ጭራሽ በገንዘብ እጥረት ነው የቆመው ተብሎ እንዲወራማ በፍጹም አትፈልግም። እንዲህ ተወርቶ ሰውስ ምን ይላል? ለክብርህ አይመጥንም። ባይሆን አማራጮችን መጠቀም ጥሩ ነው። ለዚህ ደግሞ ዓይነተኛው አማራጭ ባንክ ነው። ምንም እንኳ የሚፈለገው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ ቢሆንም አንተ ጠይቀህ መከልከል ቀርቶ ማቅማማት አይታሰብም። እንደውም የመበደርህ ወሬ ከደረሳቸው ራሳቸው መጥተው ምን ያህል እንፍቀድልህ ብለው ባለ በሌለ አቅማቸው ይሽቀዳደማሉ። መቼም አራጣ ክፉ መሆኑን ብታውቅም ከዚህ አጣብቂኝ መውጣትህ ግድ ነውና . . . ለማንኛውም ምክሬን ደግመህ ደጋግመህ ስማ – ሙት! መቼ? አሁኑኑ!!!

አሁን ላይ የምትሰራውን ስራ አሁኑኑ እንደምትሞት ሆነህ ካልሰራኸው ልታበላሸው፣ ወይም ልትተወው፣ ወይም ሌላን በሚጎዳ መልኩ ልታጣምመው ትችላለህ። ይህችን የሰከንድ ሽርፍራፊ እንዴት ካለብክነት ልትጠቀምባት እንደምትችል ለመጠበብ ከፈለግህ ሞትህን አሁን አድርገው።

ወንድሜ ሆይ! የሚሻለው ይኼ ነው – መሞት – አሁኑኑ። አለበለዚያማ መቼም ላትሞት ትችላለህ – በሃሳብህ ማለቴ ነው እንጂ በዟሂርማ ምን ጥያቄ አለው። አሁን ላይ የምትሰራውን ስራ አሁኑኑ እንደምትሞት ሆነህ ካልሰራኸው ልታበላሸው፣ ወይም ልትተወው፣ ወይም ሌላን በሚጎዳ መልኩ ልታጣምመው ትችላለህ። ይህችን የሰከንድ ሽርፍራፊ እንዴት ካለብክነት ልትጠቀምባት እንደምትችል ለመጠበብ ከፈለግህ ሞትህን አሁን አድርገው። አሁን ልትሞት ነውና ባለችህ ጥቂት ሰከንድ ወይም ደቂቃ ለሞትህ ምን ማድረግ እንዳለብህ በደንብ ትገልጽልሃለች። ዋጋዋ ምን ያህል እንደሆነና እሷን ማባከን ምን ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል በደንብ ትገነዘብበታለህ። ከወንጀል ራስህን ማስገዛት ካማረህ አሁኑኑ ከመሞት የተሻለ አማራጭ ከየት ታገኛለህ። የሚሞት ሰው ወንጀል ለምን ይሰራል? ጌታውን ሊያስደስት አትለኝም መቼም። ለመልካም ነገር ተሸቀዳደሙ ተብሎ የለ እስቲ ሞትህን አሁን አድርገው . . . የትኛውን መልካም ስራ ጠበቅ ታደርግ ነበር? የትኛውን ክፉ አመል እርግፍ አርገህ ትተው ነበር?

መሞትህ እርግጥ ሆኖ ሳለ ሞትህን እሩቅ አድርገኸው የማትሞት እየመሰለህ ተታለሃል። ሞትህን አሁን አድርገው። ያኔ ጊዜና ንብረትህን ባግባቡ ትጠቀምበታለህ፤ መልካም ስራ ላይ ትዘወትራለህ፤ እኩይ ባህሪዎችህን ትተዋለህ፤ የራስህን፣ የወላጆችህን፣ የቤተሰብህን፣ ባጠቃላይ የህብረተሰቡን ሀቅ ጠባቂ ትሆናለህ። ይህን ሁሉ ማድረግ ከቻልክ ምን ያላደረከው ነገር አለህ? “ምንም” አትለኝም። ስለዚህ ሙታ!

@smithhk
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

አሥሩ የዙል-ሒጃ ቀናት
*******
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦቹ
****
አላህ ሲያስብልን፣ ሲወደን እና ሊጠቅመን ሲፈልግ ምንዳዉና ችሮታው የሚነባበርባቸዉን ቀናትና ጊዜያት ጠቆመን፡፡
አስተዋይ ልቦና የሠጠው ሰው በትኩረት ይጠቀምባቸዋል፡፡ እንደዋዛ አያሳልፋቸዉም፡፡

አሥሩ ምርጥ ቀናት ነገ ሀሙስ ይጀምራሉ፡፡ ስለ ምርጥነታቸው በቁርኣን ተመስክሮላቸዋል፣ አላህ ምሎባቸዋል፣ የአላህን ቤት ጎብኝዎችምን ወደተከበረዉና የተቀደስው ሥፍራ መካ እና ዙርያው በመጉረፍ የሐጅን ሥርዓት ያከናዉኑባቸዋል፡፡

በቀናቱ ዉስጥ መሥራት እንችላለን?
1- ከልብ ተፀፅቶ ወደ አላህ መመለስ፤
2- አላህን ማውሳት ማብዛት፣
3- መፆም፣
4- ኢስቲግፋር ማብዛት፣
5- መመጽወት
6- ዱዓእ ማድረግ፣
7- ሶላትን በወቅቱ መስገድ፣
8- ከኃጢኣት መራቅ፣
9- ስለ ቀናቱ ምርጥነትና እንዲጠቀሙባቸው ሌሎችን ማስታወስ፣
10- በነቢዩ ላይ ሶላዋት ማውረድ፣
11- መልካም ሥራዎችና ንግግሮች ለምሳሌ - ወደ አላህ መንገድ መጣራት፣ ዝምድናን መቀጠል፣ ለጎረቤት መልካም መዋል፣ ወላጆችን ማስደሰት፣ አስቸጋሪን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ፣ የታመሙትን መጎብኘት፣ ለሙታን ዱዓ ማድረግ፣ ወንድም እህቶችን በሌሉበት በዱዓ ማስታወስ፣ የባለዕዳን ዕዳ መሰረዝ፣ የተቸገረን መርዳት፣ የታሠረን መጠየቅ፣ ሰዎችን አለማስቸገር፣ ቤተሰብን መንከባከብ፣ ለሠራተኞች ማዘን ...ሌሎችም ።

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#share #ሼር
#join

Https://www.tg-me.com/smithhk
◾️በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው

#አስሩ_የዙልሒጃ_ቀናት

♦️ዙልሒጃ ብሎ ማለት የዐረበኛ 12ኛ ወር ሲሆን የዚህ ወር 10ቀናት ልዩ ትሩፋት እንዳላቸው ነቢያችን - ﷺ - ተናግረዋል። እንደዚሁ ቁርአን ላይም እነዚህ ቀናት ተጠቅሰዋል። አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - ከፈጠራቸው ፍጡር ውስጥ አንዱን ከሌላኛው አበላልጧል። የረመዷን ወር ከወሮች ሁሉ በላጭ ነው። የረመዷን የመጨረሻዎቹ 10ቀን ለሊቶች ከለሊቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ምክንያቱም ለይለተል ቀድር በውስጧ ስላለ ነው።
°
♦️የዙልሒጃ አስሩ ቀናት ደግሞ ከቀናቶች ሁሉ በላጭ ናቸው። ለዚህም ነው ሸይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያ - ረሒመሁላህ - ከረመዷን የመጨረሻዎቹ 10 ቀናቶች የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናቶች እንደሚበልጡና ከዙልሒጃ10 ለሊቶች ደግሞ የረመዷን 10 የመጨረሻ ለሊቶች እንደሚበልጡ ተናግሯል። 📒(መጅሙዓል ፈታዋ 25/287)
°
♦️አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - በተከበረው ቁርአኑ ላይ እንዲህ ይላል ፦

{ لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ }

[| ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል)፡፡ ከርሷም ብሉ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ፡፡ |] 📒(ሐጅ ፥ 28)
°
♦️እነዚህ ቀናት ብሎ ማለት ዐብደላህ ኢብኑ ዓባስ እንደገለፁት አስሩ የዙልሒጃ ቀናት እንደሆኑና በነሱም ላይ አላህን በጣም ማውሳት እንዳለብን ተናግረዋል።
°
♦️ከዚህም በተረፈ ዐብደላህ ኢብን ዓባስ - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ባስተላለፈው ነቢያችን - ﷺ - ሐዲስ እንዲህ ብለዋል ፦ [ ከዙልሒጃህ 10 ቀናት የበለጠ አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆኑባቸው ምንም አይነት ቀናቶች የሉም።] በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን! ተብለው ሲጠየቁ ፦ [ አዎ. በአላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን , ነገር ግን ንብረቱንና ነፍሱን ይዞ ወጥቶ ከዛ በምንም ነገር ያልተመለሰ ሰው ሲቀር ብለዋል። ] 📒(ቡኻሪ ፥ 969)
°
♦️ኢብኑረጀብ - ረሒመሁላህ - እነዚህ አስር ቀናት ከሌሎቹ ሊበልጡ የቻሉበት ምክንያት ሲናገሩ ፦ | በጣም ዋና የሚባሉት የዒባዳ አይነት በአንድ ላይ ስለሚሰባሰቡበት ነው እነሱም ሰላት ፣ ፆም ፣ ሰደቃ እና ሐጅ ናቸው ብለዋል። | 📒(ፈትሑልባሪ ፥ 2/460)
°
◾️ዋና ዋና በዚህ ወር ልንሰራቸው ከሚገቡ ተግባራቶች ውስጥ ፦
🔺1️⃣.ፈርድ ሰላትን ወቅት ጠብቆ መስገድ ይኖርብናል። ሱጁድ በማብዛት ወደ አላህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ - መቃረብ ተገቢ ነው። ነቢዩም - ﷺ - [ ሱጁድ በማብዛት ላይ አደራ ; አንተ እኮ ምንም ሱጁድ አታደርግም በሰጁዱህ ልክ አላህ ዘንድ ማእረግህ ከፍ ቢል እና ወንጅልህም ቢራገፍልህ እንጂ ብለዋል። ] 📒(ሙስሊም ዘግቦታል). ሱና ሰላቶችንም ማብዛት ይጠበቅብናል። በተለይም 12ቱ "ራቲባ" የሚባሉትን እነሱም ፦ ከሱብሂ በፊት 2ረከዓ ፣ ከዙሁር በፊት 4ረከዓ , በኋላ 2ረከዓ ፣ ከመግሪብ በኋላ 2ረከዓ እና ከዒሻእ በኋላ 2 ረከዓ ናቸው።
°
🔺2️⃣.ፆም መፆምም ተገቢ ነው። አላህ ዘንድ መልካም ስራዎች ተወዳጅ ሚሆንባቸው ቀናቶች የሉም ከነዚህ 10 ቀናቶች የበለጠ ሰለተባለ ፆም ደግሞ ከመልካም ስራ ስለሚገባ መፆም ተገቢ ነው። ኢማሙ ነወዊም አስሩ የዙልሂጃን ቀን መፃም የጠበቀ ሱና ነው ብለዋል።
🔺3️⃣.ሰደቃ በመስጠት ላይም መጠናከር ይኖርብናል።
°
🔺4️⃣.ተክቢር እና ተህሊልልን ማብዛትም ተገቢ ነው። ሰሓባዎችም በነዚህ ቀናት ውስጥ ተክቢርና ተህሊልን ያበዙ ነበር። በአሁን ሰአት ግን በጣም ከተረሳ ሱናዎች ውስጥ አንዱ ነው። ኢማም አል-ቡኻሪም እንዲህ ብለዋል ፦ | ኢብኑ ዑመርና አቡሁረይራ ወደገበያ ቦታ በመውጣት በነዚህ ቀናቶች ውስጥ ተክቢር ይሉ ነበር ሰዎችም በነሱ ተክቢራ ማለት ተነሳስተው ተክቢራ ይሉ ነበር። |. አባባሉም ፦ አሏሁ አክበር , አሏሁ አክበር , ላኢላሀኢለላህ, አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር ወሊላሂል ሐምድ.
ሌሎችም በትክክለኛ ሐዲስ የተዘገቡ ተክቢራዎችን ማለት ይቻላል።
°
🔺5️⃣.ከአስሩ ቀናት በተለየ መልኩ የ9ኛውን ቀንማለትም የዐረፋን ቀን መፆም ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ -  ስለዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል ፦ [ ያለፈውን አመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ] 📒(ሙስሊም ዘግቦታል). በዚህም ቀን ዱአን ማብዛት አስፈላጊ ነው።
°
🔺6️⃣.ሌላኛው 10ኛው ቀን ላይ ሚተገበሩ ተግባሮች ናቸው። እነሱም ፦ ዒድ ሰላት መስገድ ፣ ኡድሂያን ማረድ ... ሐጅ ላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ጀመራት ይወረውራሉ ፣ ፀጉራቸውን ይላጫሉ ፣ ሀድይ የያዙ ሰዎች ሀድያቸውን ያርዳሉ ፣ ወደ መካ ተመልሰው ጠዋፈል ኢፋዷ ያደርጋሉ። በአጠቃላይ 10ኛው ቀን አላህ ዘንድ በጣም ትልቅ ነው።
°
♦️ስለዚህ ጠቅለል ባለ መልኩ እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎችን በምናገኝበት ጊዜ ተውበት አድርገን ራሳችንን ለኸይር ስራ ዝግጁ አድርገን ከወንጀላችን ታቅበን ሌሎችንም ከዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ይሄን እድል እንዲጠቀሙ መገፋፋት ያስፈልጋል ። እንደዚህ አይነት እድል በሚመጣ ጊዜ ሳናውቀው ስለሚያልፈን መስነፍ አያስፈልግም መጠንከር እና ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል።
°
♦️በመጨረሻም ኡድሂያን ማረድ የፈለገ ሰው ከሰውነቱ ላይ ፀጉሩንም ሆነ ጥፍሩን እስኪያርድ ድረስ መቁረጥ የለበትም። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ - ኡሙሰለማ ባስተላለፈችው ሀዲስ እንዲህ ስላሉ ፦ [ የዙልሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና , ከእናንተ አንድኛችሁ ኡድሂያን ማረድ ከፈለገ ፀጉሩን እና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ። ] 📒(ሙስሊም ፥ 1977 ላይ ዘግቦታል). አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገን።

#ሼር #share
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
عن أنس بن مالك رضي الله عنه قال :
قال رسول الله ﷺ :

((مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً وَاحِدَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ عَشْرَ صَلَوَاتٍ ، وَحُطَّتْ عَنْهُ عَشْرُ خَطِيئَاتٍ ، وَرُفِعَتْ لَهُ عَشْرُ دَرَجَاتٍ))

رواه النسائي.

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ»
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#ምርጦች

ኢብን መስኡድ እንዲህ ይላሉ አላህ ከቀናት አራት , ከወራት አራት ከሴቶች አራት, የጀነት ቀዳሚዎችን አራት, ጀነት የምትናፍቃቸውን አራት ሰዎች መርጧል
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🗓ከቀናት
1— የጁምዐ እለት
2— የዐረፋ እለት
3— የውመ ነህር( የእርድ ቀን)
4— የውመል ፊጥር( የረመዳን ዒድ)
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

📆ከወራት
1—ረጀብ
2—ዙልቂዕዳ
3—ዙልሂጃ
4—ሙሀረም
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

🌷ከሴቶች
1—መርየም ቢንት ዒምራን
2— ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ
3— አሲያ ቢንት ሙዛሂም
4— ፋጢቲመቱ ዛህራእ ቢንት ሙሀመድ
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

⚡️የጀነት ቀዳሚዎች
1— ሀቢቢ ሙሀመድ (ሰዐወ) የአረቦች ቀዳሚ
2—ሰልማን የፋርስ ቀዳሚ
3—ሱሀይብ የሮም ቀዳሚ
4— ቢላል የሀበሻ ቀዳሚ
🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

ጀነት የናፈቀቸቻቸው
1—ዐሊ ኢብን አቢጧሊብ
2—ሰልማነል ፋሪሲ
3—ዐማር ኢብን ያሲር
4—ሚቅዳድ ኢብን አስወድ



🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

#Share #ሼር
#join

Https://www.tg-me.com/smithhk
روى الحاكم أن النبيَّ ﷺ قال :

«سُورَةُ تَبَارَكَ هِيَ المَانِعَةُ مِنْ عَذَابِ القَبْرِ»
የባከኑ ቀናት ትዝታዎች . . .

ሜክሲኮ አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብዬ ጓደኛዬን እየጠበቅኩ ነው፡፡ ከተቀጣጠርን ሳፊ አንድ ሰዓት ሆኗል፡፡ ወዳጄ ግንእስካሁን ብቅ አላለም፡፡ ያዘዝኩት ሻይ ቀዝቅዞ የድመት አፍንጫ ሆኗል፡፡ አንድ ሻይ አዝዤ ይህን ሁሉ ሰዓት መቀመጤያበሳጫቸው አስተናጋጆች ደግሞ በዓይናቸው እያነሱ ይጥሉኛል፡፡ እኔን እያዩ ከርቀት ሲንሾካሸኩ እንደ ዕድር ዳኛ ወንበርይወዳል የሚሉኝ ይመስለኛል፡፡ ሰዎች ይገባሉ – ይወጣሉ … ሙዚቃው ጆሮን ይበጥሳል፡፡

መቼም ወዳጄ ኔትዎርክ ተመችቶታል፡፡ ደጋግሜ ብደውልም ስልኩ አይነሳም፡፡ መንገዱ ተዘጋግቶ፣ ታክሲ አጥቼ፣ ስልኬን ረስቼ፣የቤት ወጪ ሳልሰጣት ወጥቼ፤ ….. የማያልቁ መቶ ምክንያቶቹን እያሰብኩ ፈገግ አልኩ፡፡ መቀመጡ ሲሰለቸኝ ሰዓቴን አየሁ፡፡ ያአላህ .. የሀኪም ቤት ቀጠሮዬ ደርሷል፡፡ አስተናጋጆቹ ሳያዩኝ ተነስቼ ሹልክ አልኩ፡፡ የታክሲው ወረፋ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ቢሆንምምርጫ የለኝም፡፡ እየተንፏቀቀ የሚሄደው ሰልፍ ላይ ከኋላ ተሸጎጥኩ፡፡ ወጪ ወራጁን እየታዘብኩ ከሃያ ደቂቃ በኋላ ታክሲ ውስጥገባሁ፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡

እድሌ ሆኖ ጋቢና ደርሶኝ አያውቅም፡፡ አራተኛው ወንበር ላይ ተኮራምቼ ቁጢጥ አልኩ፡፡ አዲስ አበባ ዕድሳት ላይ ናት፡፡የትናንት መንገዶቿ ሁሉ ወደ ሰው ሰራሽ ገደልነት ተቀይረዋል፡፡ መኪኖቿም ቢሆን ሬሳ የጫኑ ይመስል እየተንፏቀቁ ነውየሚሄዱት፡፡ ከሰለሳ ሶስት ደቂቃዎች በኋላ ከታክሲ ወረድኩ፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡

ቤት ገብቼ ብርድልብሴ ውስጥ እስክሸሸግ ቸኩያለሁ፡፡ ህሊናዬ ግን አላረፈም፡፡ ውሉዬን ደጋግሞ ያስታውሰኛል፡፡ያለአንዳች ፋይዳ የባከኑብኝ ሰዓቶች ነገ በአላህ ፊት እንደሚያስጠይቁኝ ሹክ እያለ ጭንቀቴን ያብሰው ጀመር፡

ያአላህ.. ሆስፒታሉ ተጨናንቋል፡፡ ካርድ ሳስወጣ ሰራተኛዋ ሳይገርማት አይቀርም፡፡ “ነገ ጠዋት ይሻልሃል” ብትለኝም”እጠብቃለሁ” ብያት ሞባይሌን አውጥቼ ጌም እየተጫወትኩ መጠበቅ ጀመርኩ ሰላቴን እንደነገሩ ወጋ ወጋ አድርጌቦታዬ ተመለስኩ፡፡ ሰዓቱ እየሮጠ ነው፡፡ ወረፋው ግን ንቅንቅ አላለም፡፡ ሞባይሌ ባትሪ ጨርሷል፡፡ አንዲት ጀማሪ ነርስምንም ሳይመስላት ዶክተሩ እንደወጣና ተረኛ ሌላ ዶክተር ሊያየን እንደሚችል አሳስባን ሄደች፡፡ ያአላህ.. አንድም የረባቁምነገር ሳላከናውን ፀሀይ ወጥታ ጠለቀች…!

ቤት ገብቼ ብርድልብሴ ውስጥ እስክሸሸግ ቸኩያለሁ፡፡ ህሊናዬ ግን አላረፈም፡፡ ውሉዬን ደጋግሞ ያስታውሰኛል፡፡ያለአንዳች ፋይዳ የባከኑብኝ ሰዓቶች ነገ በአላህ ፊት እንደሚያስጠይቁኝ ሹክ እያለ ጭንቀቴን ያብሰው ጀመር፡፡ ውዱዕአድርጌ ሁለት ረከዓ ሰገድኩና መስገጃዬ ላይ ተደፍቼ ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ አዛኝ የሆነውን አምላኬን ማረኝ እያልኩእስቲግፋር ሳደርግ ረጅም ሰዓታት ቆየሁ፡፡

ቀልቤ ሲረጋጋ ውሎዬን ተመልሼ ቃኘሁት፡፡ ጓደኛዬን ስጠብቅ ከአባከንኩት ሰዓት ጀምሬ እስካሁን ያለውን ደቂቃ በሙሉአሰላሁት፡፡ በትንሹ በጉዞና በጥበቃ ከስምንት ሰዓታት በላይ አባክኛለሁ፡፡

ያአላህ በነዚህ ሰዓታት ስንት ጁዝ ቁርአን መቅራት እችል ነበር? በቀላሉ ዚክር ባደርግ እንኳ ስንት ዛፍ ጀነት ውስጥእተክል ነበር?

ሃዘኔን ውጬ ራሴን ማረጋጋት ጀመርኩ፡፡ ከተውበት ሸርጦች አንዱ መጸጸት መሆኑ ታወሰኝ፡፡ ልክ ነኝ.. ጸጸትተሰምቶኛል፡፡ ሌላኛው ሸርጡ ደግሞ ትዝ አለኝ… ድርጊቱን ዳግም አለመፈጸም ጥሩ ከነገ ጀምሮ እያንዳንዱን ደቂቃበዚክርና በቂርዓት ብሎም ለሎች መልካም ስራዎችን በመስራት ለማሳለፍ በቻልኩት ሁሉ ጥረት ለማድረግ ነየትኩ፡፡

ዛሬ አዲስ ቀን ነው፡፡ ብሩህ ዕለት፡፡ ማለዳ ወደ ስራ ለመሄድ ታክሲ ጥበቃ ስቆም ተወዳጄን ዚክር .. “ሱብሃነላህወቢሃምዲሂ.. ሱብሃነላል-ዓዚም” ከመቶ ጊዜ በላይ ማለት ችዬ ነበር፡፡ አልሃምዱላሊህ! ታክሲ ውስጥ ሆኜ በዛ ያለእስቲግፋር ለማድረግ ታድዬ ነበር፡፡ ዛሬ የመንገድ መዘጋጋትም ሆነ ወረፋው ትዝ እንኳን አላለኝም፡፡ ሆስፒታል ቁጭ ብዬሞባይሌን ያወጣሁት እንደትላንቱ ጌም ለመጫወት ሳይሆን ቁርአን ለመቅራት ነበር፡፡ አልሃምዱሊላህ፡፡ በአላህ ፈቃድከእንግዲህ የሚባከኑ ቀናት አይኖሩኝም፡፡

እናንተም ይህንን መንገድ በቀላሉ ልትሞክሩት ትችላላችሁ፡፡ እስቲ ከዚህ ጀምሩ

ሞባይላችሁ ላይ ቁርዓን አስጭኑበት፣ በማንኛውም ሁኔታ ለመቅራት ይረዳችኋል፡፡
ቦርሳችሁ ውስጥ ለዚክር የሚረዳችሁ ሙስበሃ ወይም ሌላ የመቁጠሪያ መሳሪያ አይጥፋ፡፡
በመጠናቸው አነስ ብለው የተዘጋጁ ሁስኑል ሙስሊም ወይም ሌላ የአዝካርና የዱዓ መጽሃፍትንየመታወቂያችሁን ያህል ዋሌታችሁ ወይም ቦርሳችሁ ውስጥ ቦታ ያዙላቸው፡፡
ዚክሮች ላይ ጎበዝ የሆኑ ወዳጆችን በመግባባት ባህሪያቸውን ለመውረስ ጣሩ፡፡
እጅግ በርካታ ጥቅሞች ምንጭ የሆነውን ሰለዋት በየቀኑ ከሰላሳ ያላነሰ ለማለት ሞክሩ፡፡
#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
عن أنس بن مالك رضي الله عنه ،
أن رسول الله ﷺ مَرَّ بشجرةٍ يابسةِ الورقِ فضرَبها بعصاهُ ، فتَناثرَ الورقُ ،
فقال :

((إنَّ الحَمْدَ للهِ ، وَسُبْحَانَ اللهِ ، وَلَا إلَهَ إلَّا اللهُ ، وَاللهُ أكْبَرُ لَتُسَاقِطُ مِنْ ذُنُوبِ العَبْدِ كَمَا تَسَاقَطَ وَرَقُ هَذِهِ الشَّجَرَةِ))

رواه الترمذي.
﴿وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَى تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ﴾

- «سُبْحَانَ اللهِ»
- «الحَمْدُ للهِ»
- «لَا إلَهَ إلَّا اللهُ»
- «اللهُ أكْبَرُ»
- «سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ»
- «سُبْحَانَ اللهِ العَظِيمِ»
- «لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ»
- «أسْتَغْفِرُ اللهَ وَأتُوبُ إلَيْهِ»
- «لَا إلَهَ إلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ»
🌹አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ🌹
ወንድም እህቶቼ አደራችሁን ነገ ዱአ ከማድረግ እንዳንሳነፍ ወላሂ በአላህ ይሁንብኝ አላህ ነገ የምትደረግን ዱአ አልመልስም ብሏል ወንጀል ውስጥ የተዘፈቅንም ሰዎች አላህን ምህረት ለምነን በንፁህ ልብ የምንፈልገውን እንለምነው።
መረሳት የሌለባቸው ዱአዎች
-ጤንነትን
-ሪዝቅን
- በረካን (በልጅ፣በቤተሰብ፣በገንዘብ)
-ሁስነል ኻቲማን(መጨረሻችንን እንዲያሳምርልን)
-ቀብራችን በብርሀን እንዲሞላልን
-በእኛ እና በአላህ መካከል ያለውን ወንጀል እንዲምረን
-ከረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ጋር አላህ ጎረቤት እንዲያደርገን
-የአላህን ፊት በማየት የሚገኘውን ጣእም እንድናገኝ
-ጀነትን እንዲያስገባን ከጀሀነም እንዲጠብቀን
~~እንዲሁም ለመላው በስቃይ እና በችግር ውስጥ ያሉት ሙስሊም እናት አባቶች፣እህት ወንድሞች በዱአችን እናስታውስ፤ሌሎች ያሉብንን እና የምንፈልጋቸውን ነገሮችም በማብዛት አላህን እንለምን።
#የፆሙን ጉዳይም እንዳንዘነጋ
ከአስሩ ቀናት በተለየ መልኩ የ9ኛውን ቀን ማለትም የዐረፋን ቀን መፆም ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ነቢዩ - ﷺ -  ስለዐረፋ ቀን ፆም እንዲህ ብለዋል ፦ [ ያለፈውን አመት እና የወደፊቱን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ አላህ ላይ ተስፋ አደርጋለው ] 📒(ሙስሊም ዘግቦታል). በዚህም ቀን ዱአን ማብዛት አስፈላጊ ነው።

እኛ ተጠቅመን ሌሎችንም ጠቅመን ምንም ሳንሰራ ሌሎች በሰሩት ተጠቃሚ እንድንሆን ሁላችንም ሼር ወደ ግሩፕ ወደ ቻናል በማድረግ የአጅር ተካፋይ እንሁን

ለአላህ ብዬ እወዳችዋለሁ
🌼ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ 🌼
#share #ሼር
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ምርጥ የዐረፋ ቀን ዱዓ
——————
በዛሬው የአረፋ ቀን በብዛት መባል ያለበት ዱዓ /ዚክር
ﻻَ ﺇِﻟَـﻪَ ﺇِﻻَّ ﺍﻟﻠﻪُ ﻭَﺣْﺪَﻩُ ﻻَ ﺷَﺮِﻳْﻚَ ﻟَﻪُ، ﻟَﻪُ ﺍﻟْﻤُﻠْﻚُ ﻭَﻟَﻪُ ﺍﻟْﺤَﻤْﺪُ، ﻭَﻫُﻮَ ﻋَﻠَﻰ ﻛُﻞِّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻗَﺪِﻳْﺮٌ
‹ላኢላሀ ኢልለሏሁ ወህደሁ ላ ሸሪከለሁ፣ ለሁል ሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ
ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር ።
› «ከአላህ ውጭ በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም፡፡ እርሱ አንድ ነው ፡፡
ለርሱ አጋር የለውም ፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ለረርሱ
ብቻ ነው ፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው››!!!

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌ይች #ሃገር_ሶስት/③ቀናት_አሏት 📌

🚫ትናንት ኑረነዋል መዝገቡን ይዞ ላይመለስ ሄዷል፤

🚫ዛሬ አብሮን ነው አይዘወትርም ፤

🚫ነገ ለመኖራችን ዋስትና የለንም ፤
ስለዚህ

#ያለንበትን #ጊዜ ጌታችንን በማጥራት

በማመስገን እና ምህረት በመጠየቅ እናሳልፍ። ያረብ ያአላህ ማረን🤲🤲

https://www.tg-me.com/smithhk
عن أبي هريرة رضي الله عنه ،
عن النبي ﷺ أنه قال :

((إنَّ فِي الجُمُعَةِ لَسَاعَةً لَا يُوَافِقُهَا مُسْلِمٌ يَسْألُ اللهَ فِيهَا خَيْرًا إلَّا أعْطَاهُ إيَّاهُ))

رواه مسلم.
﷽ { የጁምዓ ቀን ሱናዎች }
1 ገላን መታጠብ
2 ሽቶ መቀባት (ለወንድ)
3 ጥርስ መፍቂያ መጠቀም
4 የክት ልብስ መልበስ ለወንድ (ነጭ ልብስ)
5 በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ
6 በእግር ወደ መስጂድ መሄድ
7 መስጂድ ውስጥ የሰዎችን ትከሻ አለመረማመድ
8 ኹጥባ እየተደረገም ቢሆን ተህየቱ መስጂድ መስገድ
9 ኹጥባ ወደ ሚያደርገው ኢመም መዞር እና ኢማሙን እያዩ ኹንባን ማዳመጥ
10 ኹጥባ በሚደረግበት ወቅት ፀጥታን መላበስ
11 ሰደቃ ማብዛት
12 ከሀሙስ ማታ እስከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱል ካፍ መቅራት
13 ድዓ ማድረግ
14 የአላህ መልክተኛ(ሠ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ማብዛት

https://www.tg-me.com/smithhk
2025/07/05 21:39:01
Back to Top
HTML Embed Code: