Telegram Web Link
ከ53 በላይ ንፁሐን ሙስሊሞች በተወለዱባት ቀዬ በፆመኛ አንጀታቸው
እንደ ቅጠል ረግፈዋል፤ (አላህ ይዘንላቸውና)
ከ10 በላይ የተከበሩ የአላህ ቤቶች (መሳጂድ) ወድመዋል፤
እልፍ ቅዱስ ቁርኣኖች ተቀዳደዋል፤
ሙስሊም ሴቶች ከነ ፆመኝነታቸው ክብረ—ንጽሕናቸው ተደፍሯል፤
ለቁጥር የሚታክቱ መኖሪያ ቤቶች ፈራርሰዋል፤
ለጎንደርን ኢኮኖሚያዊ አቅም ዋርካ የሆኑ የንግድ ማዕከላት ተዘርፈው
ወድመዋል፤
ከ 500 በላይ ሙስሊሞች ያለ ወንጀላቸው ብቻ ሳይሆን ተበዳይ ሆነው ሳለ
ለእስር ተዳርገዋል፤
ሙስሊም ጎንደሬዎች መፈጠራቸውን እስኪጠሉ በማያገግም የሞራል
ስብራት ተጎድተዋል።
… ይሄ ሁሉ አስነዋሪና የክ/ዘመኑ ጭካኔ ተፈፅሞ ሲያበቃ መንግስት ጉዳዩን
በፕሮፖጋንዳ ለመሸፋፈን በእጥፍ እየተጋ ይገኛል።
ፍትህ በፅን*ፈኞች የጥላቻ ስብከት ውድ ህይወታቸውን ላጡ ነፍሶች!! ፍትህ
በአክ*ራሪ ብሄርተኞችና የሞት ነጋዴዎች ትብብር ለተቀጠፉ ንፁሃን!!
“justice delayed is justice denied” # GondarMassacre
#የጎንደርጭፍጨፋ
#የደባርቅጥቃት
#IslamoPhobiaInEthiopia



#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
አሳዛኝ ታሪክ.. ስታነቡ በትክክል አንብቡ!!

አስገራሚ ክስተት ከሳዑዲዋ ሪያድ ከተማ! የዱባይ ከተማ ፖሊሶች አዲስ መኪናውን እያፀዳ ያለን አንድ ሰው በቁጥጥር ስር አዋሉ!! ነገሩ እንዲህ ነው.. ይህ ሰውዬ መኪናውን እያፀዳ በነበረበት ወቅት የሁለት አመት ህፃን ልጁ አጠገቡ ያለውን መዶሻ አንስቶ መኪናውን በመዶሻ እና በሚስማር እየመታ መኪናው ላይ ቅርፅ እያወጣ ነበር ይህ ክስተት በሰዓቱ አባትየውን በጣም አስገርሞት ነበር! ይህ አባት መኪናውን ሲያየው በጣም ተበላሽቷል።

እሱ እንደዛ ደክሞ ያፀዳውን መኪና ልጁ በመዶሻ ቀጥቅጦ መሰባበሩ አባትን ክፉኛ አበሳጨና | በንዴት ልጁን መምታት ጀመረ !!!በቁጣ የታወረው ይህ አባት የልጁን ጣት በመዶሻ እየቀጠቀጠ መሆኑን ከብዙ ቆይታ በኋላ ነበር ያስተዋለው። ወዲያውኑ ተደናግ ልጁን ወደ ሆስፒታል ይዞ ከነፈ። ሆኖም የልጁ ጣት ከመቆረጥ አልተረፈችም ነበር የሆነው ሆኖ አባት ልጁ ወዳለበት ክፍል ሊያየው ሄደ። ይህ ህፃን ልጅ ገና አባቱን እንዳየ "አባዬ ጣቴ መቼ ነው የሚበቅለው? " ብሎ ጠየቀው።

የዚህ ልጅ ንግግር አባትየው ላይ እንደመብረቅ ነበር የወረደው!! ወዲያውኑ ከሆስፒታሉ ወጣና መኪናዋ ወዳለችበት ቦታ ሄዶ ቀጥቅጦ ሰባበራትና ፊት ለፊቷ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። በሰራው ነገር ቁጭት ይዞት እያነባ እያለ ልጁ መኪናዋን ሲቀጠቅጥ ወደ ነበረበት ቦታ አስተዋለ። " አባቴ እወድሃለሁ" ይላል ፅሁፉ!! ይህን ሁሉ ከባድ የሀዘን ስሜት መሸከም ያልቻለው አባት በቀጣዩ ቀን ራሱን አጠፋ። እስቲ ቂሳውን ከመጀመሪያው ጀምረን እንገምግመው!
- እንዴት አንድ ሰው መኪናውን በመዶሻ ያፀዳል??
- ሲጀመር መዶሻ እና መኪናን ምን አገናኛቸው??
- እንዴት ብሎ ነው የሁለት አመት ህፃን ልጅ አባቴ እወድሃለሁ" ብሎ የሚፅፈው??
- የዱባይ ከተማ ፖሊሶች ሪያድ ላይ ስለተፈጠረው ነገር ምናባታቸው አገባቸው?
- ሲቀጥል ሰውዬው ራሱን አጥፍቶ ከሆነ የዱባይ ፖሊሶች እንዴት በቁጥጥር ስር አዋሉት??.. ኧረ ወገን እያስተዋልን እናንብብ ቡዙዎቻችን ሰዓታችንን የምናባክነው እንደዚህ በማይረቡ ነገሮች በመጠመድ ነው። ዝም ብለን የምንነዳ ከሆነ ማንም ሰው በቀላሉ ትኩረታችንን መስረቅ ይችላል። ኧረ እባካችሁን ሰዎች የማንም መጫወቻ አትሁኑ! የዛሬ ትምህርታችን ይሄው ነው !!
የፕሮፋይል ምስል በማድረግ አጋርነታችን እናሳይ!
ይህን ምስል በጎንደር በፅንፈኞች የተጨፈጨፉትን ሙስሊም ወንድሞቻችን
እና እህቶቻችን የደረሰባቸውን ግፍ የምንገልፅበት ምስል ነው::
ሁላችንም ለትንሽ ቀናትም ቢሆን ይህን ምስል የፕሮፋይላችን ምስል
በማድረግ ለጎንደር ሙስሊም ወገኖቻችን አጋርነታችንን እናሳይ!
#ፍትህ_ለጎንደር_ሙስሊሞች
#gondarMuslimsmassacre #የጎንደርጭፍጨፋ
#gondermassacre
በማንም ላይ ቢሆን ድንበር ከማለፍ ተቆጠብ!
በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
በማንም ላይ ቢሆን ድንበር ከማለፍ ተቆጠብ!!

🎙Audio

🔗 Telegram Link
https://www.tg-me.com/ustazilyas/661

🔗 YouTube Link
https://youtu.be/U4mwMiPOVa8

🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

____
🏳️ የኡስታዝ ኢልያስ አህመድ የትምህርት መድረክ

https://www.facebook.com/ustathilyas

@ustazilyas
ሰለዋት እናብዛ‼️
🌴🌴🌴

ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዓ ተጠባብቀን በረሱል [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ላይ ሰለዋት የምናወርደው
ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ የምንዘናጋው

📚እስኪ አላህና መልዕክተኛውን ምን እንደ ሚሉን እንመልከት
👇👇👇

🌴💥🕋🌴💥🕋

قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾
[الأحزاب: ٥٦]
አላህ እንዲህ ይላል፦
{አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ; እናንተ ያመናችሁ ሆይ በእሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ}


📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇

"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا "
و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407
{ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል}

"من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات"
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩)
{በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል}

" من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات "
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠)
{ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል}

" من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا "
رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠)
وصححه الألباني رحمه الله
{በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል}

🌴🌱🌴🌱🌴🌱
"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"


"ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው"
#share
#Join
@smithhk
ሰዎችን ሊፈትን በሚችል ሁኔታ በእውነትም ቢሆን አታሞካሻቸው። ጭራሽ
ያልደረሱበት ደረጃ ላይ ከሰቀልካቸው ደግሞ ድርብ ጥፋት ውስጥ ወድቀሃል።
በአንፃሩም ስለጠላሃቸውም ብቻ መልካም ጎናቸውን አትካድ። እነርሱን
ለማጠልሸት ብለህ የስነምግባር እሴቶችን አትናድ።
ስለማንም በሚኖርህ አቋም ላይ በጭፍን አትነዳ፤ በመፈክርም አትሸንገል።
በጥቅሉ አንተነትህን በግለሰቦች ማንነት ላይ አታንጠልጥል።
በማይመለከትህ ጉዳይ ውስጥም ዘው አትበል፤ ስለ ሁሉም ነገር አስተያየት
መስጠት አይጠበቅብህም። በሚከሰቱ ውዝግቦች ላይ ሁሉ ለአንዱ ለመወገን
አትቻኮል፤ በጥልቀት ባልተረዳኸው ሀሳብ ላይ የፍርድ ቃላትን ከመሰንዘር
ተቆጠብ።
እውነተኝነት መቼም ቢሆን አይለይህ፤ ፍትኸኝነት እስትንፋስህ ይሁን፤
መረጋጋት ከደምህ ጋር ይዋሃድ!
ይህን ሁሉ መተግበር የምትችለው የአላህ ፍራቻ በልብህ ሲሰርፅና
ንግግርህ በመዝገብ ሰፍሮ በታላቁ የፍርድ እለት እንደምትጠየቅበት ዘውትር
ስታስታውስ ብቻ ነው።
©ሸይኽ ኢልያስ አህመድ
ከቀናቶች ሁሉ በላጭ በሆነችው ጁምዓ ቀን ላይ ደረስን::
የጀምዓን ሱናዎች፣ሱረቱል ካህፍን መቅራት ፣ዱዓ ማድረግ እና በብዛት
ሰለዋት ማውረድን አንዘንጋ!


#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ነገ በአኼራ አንገታቸው ከፍ ብለው የሚታዩት አዛን አድራጊወች ሙአዚኖች ናቸው......

ብዙ ሰው በዚች ምድር ላይ ሲኖር ህልም ይኖረዋል ህልሙን ለማሳካት በሚችለው ሁሉ ለማሳካት ይለፍል።

የሰወች ህልም ለማሳካት ግን የሚለፍት ጥቂቶች ናቸው ። ዛሬ አንድን የሰወችን ህልም ለማሳካት የሚለፉ ሸይኽ ላስተዋውቃቹህ

ሸይኽ እንድሪስ ይባላሉ የኻሊድ መስጊድ ሙአዚን ሲሆኑ እድሜ ልካቸውን ቁርዓን በማቅራትና መስጊዱን በሙአዚንነት እያገለገሉ ይገኛሉ። እኒህ ሸይኽ በርካታ ህፃናትን ቁርዓን በማቅራት ለብዙ ሰወች ባለ ውለታ ናቸው።

እኒህ ሸይኽ ትዳር የላቸውም ሀያታቸውን ቁርዓን በማቅራት ነው የኖሩት የሚገርመው ቁርዓን የሚያቀሩት ነፃ በሚያስብል መልኩ ነው ። ለአንድ ልጅ 3 ብር ነበር በቅርብ ወደ 10 ብር አድጎል ። እኒህ ሸይኽ ለዱንያ ምንም ቦታ የላቸውም ።

እኒህ ሸይኽ አንድ ህልም አላቸው ለብዙ አመታት የለፉበት በይቱላህን መዘየር ሀጅ የማድረግ ህልም አላቸው ። ሸይኹ ዘንድሮ ሀጅ ለማድረግ ለብዙ አመታት ያጠራቀሙት ገንዘብ አለ ይህም 120,000 ብር ነው ። ዘንድሮ የሀጅ ወጪ በጣም ስለጨመረ እኒህ ሸይኽ ልባቸው ተሰብሮል የኒህ ሸይኽ ነግቶም መሽቶም የአላህን ቤት መዘየር ነው ፍላጎታቸው እናም የቀረውን ቀሪ ብሮች በምንችለው እንገዛቸው እና ህልማቸውን እውን እናርገው

በእጃቸው 120,000 (አንድ መቶ ሀያ ሺ)
ብር አከባቢ አላቸው ይሄን ብር በቀን ሁለቴ ጧትና ማታ ብቻ እየተመገቡ ነው
ለዓመታት በይቱላህን በመናፈቅ ያጠራቀሙት ነው።

ንግድ ባንክ ተከፍቷል

1000478280487 ሸህ እንድሪስ አብደላ አህመድ

ለመሳተፍ አናግሩኝ @Faysul
#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
🎉ውብ ጁምአን ከነሱናው ተመኘሁላችሁ!

የጁምዐ ሱናዎች👇
👉ገላን መታጠብ
👉ሱረቱል ካህፍ ን መቅራት
👉በረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ ሰለዋት ማውረድ
👉ሰደቃ መስጠት
👉ንፁህ ልብስ መልበስ
👉 ሲዋክ (ጥርስን ማፅዳት)
👉መስጂድ በጊዜ መገኘት
👉ዳዓ እና ኢስቲግፋር ማድረግ
👉የጁሙዓ ኩጥባን ማዳመጥ

﷽ {إنّ اللهَ وملائكتَهُ يُصَـلُّونَ على النبي يا أيها الذين آمنوا صَلُّوا عليه وسلِّمُوا تسليما} اللهم صلِ و سلم على نبينا محمد ﷺ

•✿•˚•❀•˚•✿•˚•❀•˚•✿•┈
🕋 የተባረከ ጁምዓ 🕋

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
#ጁምዐ_ነው‼️
➝➝➝➝➝➝
ሰለዋት የታዘዝንበት ነው!!!
================>
ሰለዋት በማለታችን የምናገኛቸው
ጥቅሞች

➠➠➠➠➠➠➠➠➠
አላህ እንዲህ ይላል፦

↩️ قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾
[الأحزاب: ٥٦]
አላህ እንዲህ ይላል፦
{አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ፤ እናንተ ያመናችሁ ሆይ በሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ}

↪️ የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል

⬅️ "أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا "
و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407
{ጁምዐ ቀንና ጁምዐ ሌሊትን በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል}
~===~===~~~===>
"من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات"
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩)
{በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል}
=~~~~>
" من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات "
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠)

➡️{ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፤ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፤ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፤ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል።}
=====================>

" من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا "
رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠)
وصححه الألباني رحمه الله

🔷{በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል}

📝 "اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"

#share #ሼር
#Join
Https://www.tg-me.com/smithhk
╭─┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅─╮
አቡልወሊድ ሰዒድ ቢን ዐሊ ዐል-ጋሚዲ
╰─┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅┅─╯

Mahi mahisho

በአረቢያ ባሕረ ገብ መሬት ውስጥ ከሚገኙት እጅግ ዝነኛና ጥንታዊ ጎሳዎች አንዱ በሆነው በሱዑድ ዐረቢያ ደቡብ ግዛት የጋሚድ ጎሳ በአቅራቢያቸው ይገኛል። ውልደቱ እ.አ.አ. በ1970 በባልጁርሺ አስተዳዳሪ በሆነው አል-ሐል መንደር ነው፡፡
የአስራ ሰባት ዓመት ታዳጊ ሳለ አንድ አመሻሽ ላይ አቅራቢያቸው ወዳለ መስጂድ አቀና። የመስጂዱ ኢማም ስለ መምሉኩ ወጣት ስለ ሠይፍዲን ቁጡዝ ጀግንነት እየተናገሩ ነበር፡፡ ተታሮችን በዓይን ጃሉት ስላሸነፈው ሠይፈዲን ታሪክ እያወሱ ነው። ስለኩርዱ ጀግና! ከሰሜን ኢራቅ በይተል መቅዲስን ከመስቀል ጦረኞች ነፃ ስላወጣው ሰላሐዲነል አዩቢ ገድልም ይተርኩት ይዘዋል።
ወጣቱ አቡልወሊድ በሐሳብ ነጎደ። ሰላሐዲን ስላደረገው ተጋድሎ፣ ስለፈፀመው ጀግንነት ማሰብ ጀመረ። ያለፈውን እውነታ በብሩህ አዕምሮው መስሎ ታሪኩን ከመከራው ዘመን ጋር በዓይነ ህሊናው እያነፃፀረ ንግግራቸውን ይከታተላል። ጊዜው ጊዜ ነው ክስተቱም አሳዛኝ ነው። "አሁን ኢየሩሳሌምን በጽዮናዊነቷ እስራኤል ተነጥጥቀናል" አለ ለራሱ በሹክሹክታ፡፡ በዓለም ያሉ ሙስሊሞች ክብራቸው ተዋርዷል። አፍጋኒስታን በሩሲያውያን ቅኝ ግዛት ተይዛለች .. ፈጣን ውሳኔ ወሰነ “ጂሃድ” ነበር፡፡
ለራሱ እንዲህ አለ:- "ጅማሮው እየሩሳሌም ሊሆን ይገባል ከተቀደሰው ስፍራ! ከኢስራእ ጉዞ መነሻ ይሁን" ጉዳዩ ቀላል እንዳልሆነ ስላወቀ ወደ አፍጋኒስታን ምድር ለመሄድ ወሰነ።
በወጣትነት ዘመኑ በጎችን በመጠበቅ በረሱል (صلى الله عليه وسلم) ዘመን የተደረጉ የጂሃድ ውሎዎችን፣ የሰሐቦችን የሕይወት ታሪክ ማንበብ ያዘወትር ነበር።
ከቀናቶች በአንደኛው ቀን ታሪኮችን ያስተምረው የነበረው ኡስታዙ "በሀገረ አፍጋኒስታን የሰሐቦችን ህይወት በዕለት ተዕለታቸው የሚከውኑ ጭፍሮች አሉ። በጂሃድ መስክ ላይ የተሰማሩ። እነሱን ማየት ከፈለክ አባትህን አስፈቅድና ህይወታቸውን ለማየት አብረን እንሄዳለን። ከዚያም ወደ ቤተሰብህ ትመለሳለህ" አለው። አባቱ ለአላህ አደራ ሰጥቼሀለሁ በማለት ወደ አፍጋኒስታን እንዲሄድ ወዶ ፈቅዶ ሸኘው፡፡
ወደ ጂሃዱ ምድር ሲደርስ . . . ታሪኩንን ለእርሱ እተውለታለሁ በአንደበቱ እንዲህ ይተርክልናል "ወደ ጂሃድ ምድር ስደርስ ቦታው ላይ የተገኘ እንጂ ሌላ ሰው የማይሰማው አይነት ስሜት ሰውነቴን ወረረው። መንፈሴ ሲታደስ ተሰማኝ። ሕይወቴ ተቀየረ። ይህ አላህ በእኔ ላይ ከዋለው ፀጋ መካከል አንዱ ነው በማለት አሰብኩ። ወታደራዊ ስልጠናውን ብካፈልም በጂሃድ መስክ መዝመት ግን አልተፈቀደልኝም። ወደ ቤተሰቤ የምመለስበት ጊዜ ሲደርስ በጂሃድ ምድር መቆየት ወይስ ወደ ቤተሰቦቼ መመለስ? መምረጥ ነበረብኝ። ወደ ጂሃዱ መስክ የተጓዙ ሁሉ ሙጃሂዶቹን ሲቀላቀሉ የሚመለሱበትን ቀን የሚገልጽ ካርድ ይሰጣቸዋል። ካርዱን ተመለከትኩት። አፍጥጬ አየሁት። የሆነ ነገር ወደዚህች ምድር እየጎተተኝ እንዳትሄድ የወዲያኛው ዓለም የአኺራህ ጅማሮ መቀበርያህ ይህ ምድር ነው የሚለኝ መሰለኝ። .. ወሰንኩ .. የመመለሻዬ ቀን የተከተበበትን ወረቀት ቀድጄ በአፍጋኒስታን ምድር ለመቆየት ወሰንኩ"
በአፍጋኒስታን ጃላላባድ፣ በሎጋሪ፣ በከስት እና በሌሎችም ክልሎች ስለኢስላም ተዋግቷል .. አስቸጋሪ ሁኔታዎች፣ የመንገዱ መርዘም፣ በረዶና ሙቀቱ፣ ርቀቱና ዳገቱ ሳይበግረው በላኢላሀ ኢለላህ ጥላ ሥር ለዓመታት ተፋልሟል። ጋራ ሸንተረሩን፣ ገደል አቀበቱን ለወራት ተጉዞ ሸሂድነትን ፍለጋ ኳትኗል። ብዙ ጊዜ ሸሚዙ በጥይት ተበሳስቶ ወደ አካሉ ሳይደርስ ከሸሂድነት ናፍቆቱ ገትቶታል። በአፍጋኒስታን መስጂድ ውስጥ ከፍተኛ በሆነ የቦንብ ፍንዳታ መስጂዱ ቢናወጥም ግድግዳው ቢናድም ሰውነቱ ቢቆሳስልም በአላህ መንገድ የሚደርስበትን ችግር መከራና ጉዳት ለማንም ሳይናገር ጉዳቱን ዋጥ አድርጎ ከመስጂዱ ጥግ ይቀመጣል ..
እሱ ቁም ነገር እንጂ አይናገርም። በበዙ ዒባዳዎቹ እንጂ ጊዜውን አያባክንም። ልበ ሩህሩህ አዛኝና ደግ ነበር። የልጆችን የሴቶችን ጩኸትና የሙስሊሞችን የስቃይና የመከራ ዜናዎችን ሲሰማ ልቡ ይረበሻል። ዓይኑ የእንባ ዘለላዎችን ያረግፋል። ግና በጠላቶች ላይ ደንዳና ልብ ነበረው። አስደናቂ ግርማ ሞገስን አላህ የቸረው ድንቅ ሙጃሂድ። በዕለት ተዕለት ህይወቱ የሚያውቀው በውጊያ ሜዳ ላይ ደፋርና አንበሳ ሆኖ ሲያገኘው ያየውን ማመን ይከብደዋል። ... ያ የተረጋጋ እና ዝምተኛው ሰው? በማለት በአግራሞት ይጠይቃል።
አፍጋኒስታን ብቻም ሳይሆን ታጃኪስታን በሚገባ ታውቀዋለች። በበረዶ በተሸፈኑ ተራራዎች ላይ ሆኖ ሩሲያውያንን ለሁለት ዓመታት ሲዋጉ መቆየቱን ትመሰክራለች፡፡ ሁለት ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደረሰባቸው። ከሁለት ዓመታት የጂሃድ ትግል በኋላ በህዳሴው ፓርቲና በሙጃሂዶቹ መካከል እርቅ ተደረገ፡፡
ወጣቱ አቡል-ወሊድ እ.አ.አ. በ1995 መጀመሪያ ወደ አፍጋኒስታ ተመለሰ ..
አንድ ምሽት ላይ ከጓደኛው ከኸጣብ ጋር ተቀምጦ ቴሌቪዥን እየተመለከተ ሳለ “ከአላህ በቀር ሌላ አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ ናቸው” የሚል ጽሑፍ ግንባራቸው ላይ የለጠፉ ወጣቶችን ተመለከቱ፡፡
የሸይኹን ንግግር አስታወሰ። የበይተል መቅዲስን ነፃ አውጪ የኩርዱን ሰላሐዲን አልአዩቢንና የተታር ሠራዊትን ድል ያደረገውን ቁጡዝን አስታወሰ .. ወደ ቺቺኒያ ምድር ለመሄድ ወሰነ።
በአፍጋኒስታንና በታጂኪስታን ለተከታታይ 17 ዓመታት ሲዋጋ ኖሮ በቺቺኒያ ምድር ከጌታው ጋር ተገናኘ። የጂሃድን ጥሪ ተቀብሎ በአላህ መንገድ ሲፋለም የኖረው ሙጃሂድ ሩሑ ከጀሰዱ ተላቀቀች፡፡

══════════════
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ በእናንተ ሰበብ አንድ ሰው ወደ መልካም ነገር ቢመራ እኩል አጅርን ይጎናፀፋሉ
#ሼር #share
#join
Https://www.tg-me.com/smithhk
ከሰባቱ ባህሪያት የትኛውን ተላብሰናል?

እነዚህ ሰባት ድንቅ ባህሪያት ቀጥለን ከምናየው የአቡ ሁረይራ ሀዲስ ውስጥ ይገኛሉ። አቡ ሁረይራ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላሉ ይለናል፡-

سبعة يظلهم الله في ظله يوم لا ظل إلا ظله: إمام عادل، وشاب نشأ في عبادة الله، ورجل قلبه معلق بالمساجد، ورجلان تحابا في الله اجتمعا عليه وتفرقا عليه، ورجل دعته امرأة ذات منصب وجمال فقال إني أخاف الله، ورجل تصدق بصدقة فأخفاها حتى لا تعلم شماله ما تنفق يمينه، ورجل ذكر الله خاليًا ففاضت عيناه
“በዚያ ከአርሹ ጥላ በስተቀር ምንም ጥላ በሌለበት ቀን (የፍርዱ ቀን)፤ አላህ ሰባት ሰዎችን በአርሽ ጥላ ስር ያኖራቸዋል። እነሱም፡- ፍትሃዊ መሪን፣ አላህን በመገዛት ወጣትነቱን ያሳለፈ፣ ልቡ ከመስጅድ ጋር የተቆራኘን ሰው፣ ለአላህ ብቻ ብለው በአላህ መንገድ ላይ የተዋደዱንና በርሱም መንገድ ላይ የተለያዩ (ሲለያይም ለአላህ ብለው)፣ አንዲት ቆንጆ ሴት ራሷን ለዝሙት አዘጋጅታለት ‘አላህን እፈራለሁ’ በማለት እምቢ ያለ፣ በድብቅ ምጽዋት የሚሠጥ ሰው፣ ብቻውን ሆኖ አላህን ሲያስታውስ አላህን ፈርቶ አይኖቹ በእንባ የሚሞላና ጉንጮቹ የሚርሱ ሰው” (አል-ቡኻሪ 620)

በእርግጥ በዚያ ቀን ጥላ ያሻናል። የማንም ሳይሆን የአላህ ጥበቃ ያስፈልገናል፤ ከዚያን ያህል ርቀት በቃጠሎዋ የምናውቃት ፀሐይ በአንድ ስንዝር ልዩነት ስትቀርበን ሁላችን በላባችን ስንጠመቅ ሞልቶም እስከ አንገታችን ሲደርስ ያኔ በእርግጥ ጥላ ያስፈልገናል። ምንስ ጥላ ይኖራል ከአላህ ሁሉን ከሚችለው ጌታ ጥላ በስተቀር። በዚያን ወቅት ከነዚህ ሰባት ሰዎች መካከል ከሆንን የአላህን ጥበቃና ጥላ እናገኛለን። ኢንሻአላህ! እስቲ ስለ ሰባቱ ሰዎች ባህሪ ጥቂት እንበል።

ፍትሃዊ መሪ፡- ይህ የትልቅ ስልጣን ባለቤትን ብቻ አይመለከትም። ማንኛውም የትንሽም ሆነ ትልቅ ስልጣን ባለቤት ኃላፊነት የሚሰማው መሪ መሆን አለበት። አላህ ሁሉንም የሰው ልጅ ፍትሃዊ ይሆኑ ዘንድ ያዛል። ፍትሃዊነት የስልጣን ባለቤትነት ሲረጋገጥ ከባድ ይሆናል። ይሄኔ ነው የፍትሃዊነት ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባው። በጣም ከባዱ ደግሞ ከሚጠሉህ ሰዎች ጋር የአንተን መውደቅ ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር በፍትሃዊነት መኖር ነው። ምንም እንኳ ስልጣንና ኃይል በእጅህ ቢሆን እንኳን! ይህ በእርግጥ ታላቅ ትዕግስተኝነትንና ታማኝነትን ይሻል። ጉዳዩ ግለሰባዊ ሳይሆን ማህበረሰባዊ ነው። ለዚህም ይመስላል ከሰባቱ ሰዎች የመጀመሪያ በመሆን የተጠቀሰው።
አላህን በማምለክ ላይ ወጣትነቱን ያሳለፈ፡- አላህን መገዛት በሁሉም ሰብዐዊ ፍጡር ላይ ግዴታ ነው። ጉዳዩ ግን ወጣትነት ስሜታዊነት የሚንፀባረቅበት እድሜ በመሆኑ ነው። ዓለም ያረገዘችውን ሁሉ የምትወልድበት ወቅት በወጣትነት አይን የተመለከትናት ወቅት ነው። ተቃራኒ ፆታ፣ ገንዘብና ስሜት በወጣት ላይ ያበረታሉ። እነዚህን መጋፈጥ ደግሞ በእርግጥ ትልቅ ችሎታን፣ ትዕግስተኝነትንና ቆራጥነትን ይጠይቃል። ለእነዚህ ሁሉ ስሜቶች ከተሸነፉ በኋላ በእርጅና ወቅት ለኢስላማዊው መንፈስ ራስን መስጠት የሚገርም አይሆንም። የሚገርመው የሚደንቀውም በፍርዱ ቀን የአላህን ጥላ የሚያጋነውም እነዚህን ፈተናዎች በሚገባ ተቋቁሞ አላህ በመገዛት ያሳለፈ ወጣት ነው።
ልቡ ከመስጅድ የተቆራኘ ሰው፡- በዚህ ገለፃ ወቅት ነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ የተጠቀሙት የአረብኛ ቃል (ሙአለቅ) የሚለውን ነው። በቀጥታ ሲተረጎምም የተንጠለጠለ ማለት ነው። ይህን ኢማም ማሊክ የተባሉ የኢስላም አዋቂ ሲያብራሩ እንዲህ ይላሉ:- “ይህ ሰው ወደ መስጅድ ይመጣል፤ ከመስጅድ ሲወጣ ግን በፍጥነት የሚመለስበትን ጊዜ እየናፈቀ ነው።” በእርግጥ የሰዎች ልብ ከስራቸው፤ ከቤተሰቦቻቸውና ከንግዳቸው ላይ የተንጠለጠለ ነው። መስጅድ የቅድሚያ ፍላጎታቸው አይደለም። ነገር ግን አላህን በእውነት ለሚወዱ ሰዎች በምድር ካለ ቦታ ሁሉ መስጅድ ለነርሱ ተወዳጅ ስፍራ ነው። የቅድሚያ ፍላጎታቸውም የአላህን ቤት መጠበቅና በውስጡም ዘውታሪ መሆን ነው። ታዲያ ለነዚህስ የአላህን ጥላ አይገባቸውምን? አላህም በእርግጥ በነገሮች ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው።
ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሁለት ሰዎች፡- ፍቅር የማህበረሰባችን ቋሚ ነው። ያለውዴታ የተሟላ ማህበረሰብን መገንባት የማይታሰብ ነው። ኢስላም ከሁሉም ሰዎች ጋር በፍቅርና በርህራሄ እንድንኗኗር ያዛል። ነገር ግን ውዴታው የአላህን ውዴታ በመሻት ለአላህ ብቻ ተብሎ ሲሆን ደግሞ የልቅናን ማማ ይቆናጠጣል። ውዴታውም የተባረከ ይሆናል። ጉዳያቸው ሁሉ አላህን በማስደሰት ላይ ስለሚገነባም ለራሳቸውም ሆነ በዙሪያቸው ላሉት ሁሉ መልካምን ይለግሳል። ይህን አይነቱ ውዴታ እውነትን፣ ታማኝነትን፣ የተላበሰ ውዴታም በመሆኑ የአላህን በረከት ይቸራል፣ ዘለዓለምም የእዝነት መሠረት ይሆናል። እነኚህስ አይገቡምን? የአላህ ጥበብ በእርግጥ ሰፊ ናት!!
ቁርጠኝነት የተላበሰ የመልካም ባህሪ ባለቤት፡- ነቢዩ /ሰ.ዐ.ወ/ ስለዚህ ሰው ድንቅ ባህሪ ሲያወሱ የተጠቀሙት የአረብኛ ቃል “መንሰብ” የሚለውን ሲሆን ይህ ማለት ሁሉንም ያሟላች ሴት (ቁንጅና፣ ሀብት፣ ጥሩ ዘርና የተከበረ ቤተሰብ) ማለት ነው። ይህን ሁሉ ያላት ሴት ማንም ሰው በሌለበት ይህንን ከባድ የስሜት ጥያቄ ስታቀርብ እምቢ፣ አሻፈረኝ ማለት ድንቅ የአላህን ፍራቻ ያመላክታል። ታላቁ የኢስላም አዋቂ ኢብን ሀጀር አል አስቀላኒ ሐዲሱ በተከበረ፣ መልከ መልካምና ሀብታም ወንድ ጥያቄ ያልተሸነፈችን ሴትንም ያመላክታል ይላሉ። በእርግጥም ይህንን ጥያቄ አሻፈረኝ ማለት ጠንካራ ስብዕናን ይሻል። በአላህ ፍራቻ ልባቸው የተሞላ ግን ይህን አማላይ ጥያቄ አሻፈረኝ ለማለት አያንገራግሩም። ታዲያ የአላህ ጥላ አይገባቸውምን? የአላህ ራህመት ምንኛ ሰፋች!
ለዝና ብሎ የማይለግስ ቸር፡- የዚህ ሰው ባለቤት የራሱ ግራ እጅ በማይመለከትበት ሁኔታ ቀኝ እጁ ይሰጣል ማለት ለመስጠቱ ምላሽን ከሰዎችም ሆነ ከራሱ አይሻም። ይልቁንም የሥራውን ምስጋና ከአላህ ብቻ ይጠብቃል። የሰዎች ምስጋና ፍላጎት ፈፅሞ አይቀይረውም። ፍላጎቱ አላህን ማስደሰት ብቻ ነው። ይህ ከስጦታዎች ሁሉ የላቀው አሰጣጥ ነው ሽልማቱም አርሽ ጥላ ስር መቀመጥ ነው።
አላህን ብቻውን ባስታወሰው ጊዜ ጉንጮቹ በእንባ የሚርሱ ሰው፡- አላህን ብቻ በማሰብ፣ ድንቅ ባህሪያትን እና ስሞቹን በማስታወስ፣ እርሱንም በማመስገንና በማወደስ የምታልፍ ሰዓት ከሰዓቶች ሁሉ እጅግ የተዋበችዋ ሰዓት ነች። አላህን ማስታወስ በማንኛውም ወቅት የሚተገበር የአምልኮ አይነት ሲሆን ስሙም “ዚክር” ይባላል። ማንም በማይመለከትህ ሰዓት፣ ልብህ ከአላህ ጋር ሲገናኝ፣ ውለታዎች ስታስታውስና አይኖችህ በእንባ ጎርፍ ሲሞሉ ጉንጮችህ በዚህ የተቅዋ (አላህን ፍራቻና ጠንቃቃነት) ዶፍ ሲናጡ በእርግጥም ለአላህ ያለህን ውዴታና ተቅዋ ያመላክታል። የአላህን ፊት መሻትህን ያስገነዝባል። አላህን በእውነት የወደዱ ደግሞ በእርግጥ ስኬትን ይጎናፀፋሉ። በዚያች የጭንቅ ቀንም የአርሽ ጥላ ስር ይጠለላሉ።
እነዚህ ሰባት ድንቅ ባህሪያት እውነተኛ እምነትን፣ ቁርጠኛ አቋምን መለኪያ ሚዛን ናቸው። ስሜት፣ መንፈስን፣ አስተሳሰብንና ተግባርን ባማከለ ሁኔታ ለአላህ ያለንን ውዴታ ያሳያሉ። እነዚህ የምርጥ አማኞች ባህሪያት ናቸው። አላህ እነዚህን ባህሪያት በእውነት ከሚጎናፀፉት ሰዎች ያድርገን። ሁላችንንም በጭንቁ ቀን በእርሱ አርሽ ጥላ ስር ያኑረን። አሚን🤲
عن عبدالله بن عمرو رضي الله عنهما ،
عن النبي ﷺ قال :

((يُقَالُ لِصَاحِبِ القُرْآنِ :
اقْرَأ وَارْتَقِ وَرَتِّلْ كَمَا كُنْتَ تُرَتِّلُ فِي الدُّنْيَا ؛ فَإنَّ مَنْزِلَتَكَ عِنْدَ آخِرِ آيَةٍ تَقْرَأُ بِهَا))

رواه الترمذي.🍂
عن ابن عباس رضي الله عنهما قال :
قال رسول الله ﷺ :

((إنَّ هَذَا يَوْمُ عِيدٍ جَعَلَهُ اللهُ لِلمُسْلِمِينَ ، فَمَنْ جَاءَ إلَى الجُمُعَةِ فَلْيَغْتَسِلْ ، وَإنْ كَانَ طِيبٌ فَلْيَمَسَّ مِنْهُ ، وَعَلَيْكُمْ بِالسِّوَاكِ))

رواه ابن ماجه.🍂
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ

«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)


فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ ۖ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ

የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡

وَمَن يَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ لَا بُرْهَانَ لَهُ بِهِ فَإِنَّمَا حِسَابُهُ عِندَ رَبِّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الْكَافِرُونَ

ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡

وَقُل رَّبِّ اغْفِرْ وَارْحَمْ وَأَنتَ خَيْرُ الرَّاحِمِينَ

በልም «ጌታዬ ሆይ ማር፤ እዘንም፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ በላጭ ነህ፡፡»
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال :
سمعت رسول الله ﷺ يقول :

((كُلُّ أُمَّتِي مُعَافًى إلَّا المُجَاهِرِينَ ، وَإنَّ مِنَ المُجَاهَرَةِ أنْ يَعْمَلَ الرَّجُلُ بِاللَّيْلِ عَمَلًا ، ثُمَّ يُصْبِحَ وَقَدْ سَتَرَهُ اللهُ عَلَيْهِ ، فَيَقُولَ : يَا فُلَانُ ، عَمِلْتُ البَارِحَةَ كَذَا وَكَذَا ،
وَقَدْ بَاتَ يَسْتُرُهُ رَبُّهُ وَيُصْبِحُ يَكْشِفُ سِتْرَ اللهِ عَنْهُ))

رواه البخاري.🥀
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጁሙዓ ሱናዎች‼️
============
1) ሲዊክ መጠቀም፣
2) የተሻለ ልብስ መልበስ፣
3) ገላን መታጠብ፣
4) መስጅድ ቶሎ መግባት፣
5) ሱረቱል ከህፍን መቅራት፣
6) ሺቶ መቀባት (ለወንድ)፣
7) ሰለዎት ማብዛት፣
8) ዱዓ ተቀባይነት ያላቸውን ወቅቶች መከታተል።
መቼ ለመሞት አስበሃል?

ምናልባት በዚህ ሰዓት የዩኒቨርስቲ ትምህርትህን አጠናቀህ ከተማሪነት ዓለም ወደ ሰራተኛው መደብ ልትቀላቀል የአንድ ሴሚስተር እድሜ ብቻ ቀርቶህ ይሆናል፤ አሊያ ደግሞ ከእጮኛህ ጋር ልትሞሸርና የአባወራነትን ማእረግ ከነሙሉ ጥቅሙና ክብሩ ልትጎናጸፍ ሁለት ሳምንታትን ብቻ እየጠበቅህ ይሆናል፤ ወይ ደግሞ ከዱባይ ያስጫንከው ውድ ዕቃ በወሳኝ ሰዓት ወደብ ደርሶ ገበያውን ልትቆጣጠረውና በሕይወት ዘመንህ አግኝተህ የማታውቀውን ትርፍ ልታጋብስና ተፎካካሪዎችህን ድባቅ ልትመታ ሁሉም ነገር ተሰካክቷል – ልክ እንደተቀባበለ ክላሽንኮቭ፤ . . . በዚህ ሁሉ መሃል ታዲያ አንተ መቼ ለመሞት አስበሃል?

ሚስትህ አይንህን ባይንህ ልታሳይህ ቀናትን እንድትጠብቅ ነግራሃለች፤ እቁብህ ሊወጣ ሰዓታት ቀርተውታል፤ ወይም ደግሞ ለዘመናት የደከምክለትን መጽሐፍ አጠናቀህ ለህትመት ልታበቃ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ያሉ ጥቂት ገጾች ብቻ ቀርተውታል፤ . . . እጅግ ሲበዛ የምትወደው የልጅነት ጓደኛህ፣ ክፉ ደግ አብራችሁ ያሳለፋችሁ፣ እንደውም ከበርካታ ችግሮች የታደገህ ከዘመናት በኋላ ከሚኖርበት አሜሪካን አገር አንተን ለመጠየቅ ከነ ቤተሰቡ አውሮፕላን ላይ መሳፈሩን “ሰርፕራይዝ“ ብሎ ነግሮሃል፤ . . . እኔ እምልህ . . . ታዲያ አንተ መቼ ለመሞት አስበሃል?

ያንተን ሃሳብ እንጃ እንጂ እኔ መቸም አሁኑኑ ሙት እልሃለሁ። ሙት! የምሬን ነው። አሁኑኑ ሙት – አሁኑኑ። ምንም እንኳ አስቸኳይ ጉዳይ ቢኖርህ፤ ምንም አንኳ አሳሳቢ ነገር ቢገጥምህ፤ ምንም እንኳ ጅምር ጉዳይህን ማሳካት ቢኖርብህም ሙት ግዴለህም።

መቼም የዘንድሮው አዝመራ ለጉድ ነው። ያንተ ደግሞ ለብቻው ነው። ሰው ሁሉ ጉድ ተሰኝቶበታል። አንተም አምላክህን በምን አስደስተህ ለዚህ ታላቅ ውለታ እንደበቃህ ማስታወስ ተስኖሃል። የሱ ችሮታ እንጂ የዚህ ዓይነት አዝመራ እንዴት ሆኖ ሊበቅል! እንዴት ሆኖስ ሊያፈራ? ለማንኛውም ይህን የመሰለ አዝመራ አሳጭደህ ወደ ጎተራህ ልታስገባ ቀን ቆርጠህ አጨዳው ላይ የሚሳተፉትን ዘመድ አዝማድ፣ ጎረቤት ጓደኛ እድር፣ አገር ሽማግሌ ወዘተ… ነግረሃል፤ . . . የመጀመሪያ ሴት ልጅህን ድል ባለ ሰርግ ልትድርና ወግ ማዕረግህን ልታይ፣ ብድርህን ልትመልስ፣ ምን የመሰለ ሰርግ ሰርገሃል። አገር ሁሉ ጉድ የተሰኘበት ሰርግህ “ሰርግ ማለት የእገሌ ነው እንጂ” እየተባለ ገና እለቱ ሳይደርስ መተረት ጀምሯል፤ . . . ዋናው ነገር ታዲያ አንተ መቼ ለመሞት አስበሃል? የሚለው ነው።

ለዘመናት የለፋህበት የምርምርና የጥናት ውጤትህ (አዲሱ ግኝትህ) ለህዝብ ሊቀርብ በዚያም ሐገርና ህዝብን ልትጠቅም ያንተም ስምና ዝና በዓለም ላይ ሊናኝ ሰዓታት ቀርተውታል፤ . . . ከዘመናት ጥረት ግረት በኋላ ባፈራኸው ጥሪት ቤተ መንግስትን የሚያስንቅ ማለፊያ ቤት ገንብተሃል። የእልፍኙ ስፋት፣ የመኝታ ቤቱ ግርማ፣ የመስኩ ውበት (በግቢው ውሥጥ ያለው)፣ መዋኛ ገንዳው ሁሉ ሳይቀር ልዩ ነው። ግንባታው የተከናወነው በውድ ቁሳቁሶች ሲሆን ባለሙያዎቹ ደግሞ በመስኩ አንቱ የተባሉ ናቸው። በውድ ቁሳቁስና በጥሩ ባለ ሙያ የተሰራ ቤት ማማር ሲያንሰው ነው። ጥንካሬም ጌጡ ነው። ታዲያ ይህን የመሰለ ቤት አስመርቀህ ልትገባበት ምን ቀረህ? ምንም! . . . ታዲያ አንተስ! መቼ ለመሞት አስበሃል?

የእህል ውሃ ነገር አያስገባው የለ፤ ራስህን ችለህ ቤተሰብህን ከችግር ለመታደግ ስደት ጀምረሃል። መቼም የስደት ነገር መሃሉ አይነገርምና የሰማኸውና አንተን የገጠመህ አይገናኝም። ’’ሰው ሁሉ ይህን መሰል ከባድ ፈተናና ችግር ተቋቁሞ ነው ያለፈለት ወይስ የኔ የብቻው ነው?’’ ብለህ መቆዘምህ አልቀረም። ቁርና ሀሩር ተፈራርቀውብሃል። በተለይ በተለይ በበረሃ ላይ ያደረከውን ጉዞ ያክል አስቸጋሪና ፈታኝ ነገር ገጥሞህ እንደማያውቅ ልብ ብለሃል። የዉሃ ጥሙ ኃይለኝነት የሰዓታት ሳይሆን ከተፈጠርክ ጀምሮ የተጠራቀመ የውሃ ፍላጎት ውጤት መስሎሃል። የሰውነትህ ፈሳሽ ሁሉ ተሟጦ አልቆ ግንባርህ የጨው ግግር ማምረት ጀምሯል። ይህን ሁሉ መከራና ስቃይ አልፈህ ደስ የሚል ጥላ ያለው ዛፍ ስር ደርሰሃል። አየሩ ብቻ ምግብ ነው። ከስሩ ኩልል ያለ የምንጭ ውሃ ሲኖር ድምጹ መንፈስን ይማርካል። አምስት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ያ ሁሉ ድካምና ስቃይ ብን ብሎ ጠፍቶ በምትኩ ትልቅ እፎይታና እርካታ ተጎናጽፈሃል። . . . ታዲያ መቼ ለመሞት አስበሃል?

የፊታችን እሁድ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የሙሐደራ ፕሮግራም በከተማይቱ እምብርት ላይ በሚገኘው ሰፊ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ይከናወናል። በዚያ ፕሮግራም ላይ ብቻ ከሃምሳ ሽህ ሰዎች በላይ በአካል እንደሚገኙበት ተተንብዮአል። ፕሮግራሙ በከተማይቱ በሚገኙ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎች ላይ በተሰቀሉት ታላላቅ ዲስፕሌዮች ከመታየቱ በተጨማሪ በተለያዩ የቴሌቪዢን ጣቢያዎች ጭምር በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። የዚህ ፕሮግራም ቁልፍ ሰው ደግሞ አንተ ነህ። ህብረተሰቡ ያንተን ንግግር ለማድመጥ ካለው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ ከሩቅ የክፍለ ሃገር ከተሞች ሳይቀር ከፕሮግራሙ መጀመር ሳምንታት አስቀድሞ ወደ ከተማው ተምሟል። ታላላቅ ሰዎች ሳይቀሩ ፕሮግራሞቻቸውንና የውጭ ጉዟቸውን ጭምር በመሰረዝ ያንተ ፕሮግራም ላይ ለመገኘት ወስነዋል። አንተም ብትሆን የዋዛ አይደለህምና ፕሮግራሙን ለማድመቅና ህብረተሰቡ ከጠበቀው በላይ ተጠቃሚ እንዲሆን ለወራት በከባዱ ተዘጋጅተሃል። ይሁንና ታዲያ አንተ መቼ ለመሞት አስበሃል?

. . . . . . . . . .

ያንተን ሃሳብ እንጃ እንጂ እኔ መቸም አሁኑኑ ሙት እልሃለሁ። ሙት! የምሬን ነው። አሁኑኑ ሙት – አሁኑኑ። ምንም እንኳ አስቸኳይ ጉዳይ ቢኖርህ፤ ምንም አንኳ አሳሳቢ ነገር ቢገጥምህ፤ ምንም እንኳ ጅምር ጉዳይህን ማሳካት ቢኖርብህም ሙት ግዴለህም። የሚሻለው እሱ ነው – ለሞት ቀጠሮ መስጠት ምን ይሉት ፈሊጥ ነው? ከስንት ልፋትና መከራ በኋላ ያፈራኸውን ሀብትና ንብረት ተረጋግተህ በሰከነ አኗኗር ማጣጣም አልጀመርክ ይሆናል። ይሁና! ሙት ከተባልክ መሞት ነው። በስንት ጾምና ጸሎት የተወለደውን ልጅህን አቅፈህ መሳም አምሮህም ይሆናል፤ ቢሆንም ሞት ነውና ሙት። . . . ወንድሜ ሆይ ምነው ግራ የተጋባህ ትመስላለህ። ነገሩ ጠናህ እንዴ? . . . “አይዞህ ሊገባህ ነው” አሉ ሸኽዬ።

እስቲ አንዳንድ ጉዳዮችን እንጨዋወት። መቼም የነጋዴ ዓላማ ነግዶ ማትረፍ ነው። ጠቀም ያለ ትርፍ ያለውን ነገር አነፍንፎ በጥሩ ዋጋ መሸጥ ደግሞ ከጉብዝና ይቆጠራል። ትርፍን የእጥፍ እጥፍ የሚያሳድግ አጋጣሚ ሲገኝ ደግሞ “ዋው” ያስብላል። ስለዚህ ከትርፋማው እቃ ላይ አንዳንድ ነገሮች ቢታከሉበት ትርፉ ትርፍርፍ ይላል። ተጠቃሚም “ጥሩ” ዕቃ በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛል። ከነገዱ አይቀር በደንብ ማትረፍ ነው እንጂ ቁጥ ቁጥ ምን ያደርጋል። አንዴ ዘጋ አድርጎ ራስን መለወጥ እያለ የምን መትነፍነፍ ነው። የገበያውን ሁኔታ አጢኖ ከዚህ ቀደም ተወዳጅ የሆነችውን ዕቃ በሆነ ነገር ቀይጦ ብቻ ጉዳት የማያስከትል ይሁን እንጂ (ቢያስከትልስ አበሻን መች ጀርም ይገድለውና) ቸብ ቸብ አድርጎ ዘወር ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ሌላ የተሻለ ዝግ ያለውን ፈልጎ መሰማራት። ያኔ ደንበኞች በዚህኛው የስራ መስክ በደንብ ይካሳሉ። አሪፍ አይደል ታዲያ! በጣም እንጂ!! . . . ግን የቅድሙን ምክሬን አስታውስ – ሙት ያልኩህን። አሁኑኑ ሙት ያልኩህን። ስራውን ጀምረኸውም ሊሆን ይችላል ወይም መሀል ላይ ብቻ መሞትህን አትዘንጋ – ሙት። . . .
2025/07/05 16:42:04
Back to Top
HTML Embed Code: