Telegram Web Link
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️ሶሪያ ከሩሲያ ጋር ግንኙነቷን ማደስ ትፈልጋለች - የሶሪያ የሽግግር ፕሬዝዳንት የሀገሪቱ መረጋጋትና የቀጣናው ሰላም ለደማስቆ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ሩሲያ እና ሶሪያ በትብብር ድልድይ የተሳሰሩ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
በፕሬዝዳንት ፑቲን እና አል-ሻራ ውይይት የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦

🟠 በአልሻራ የሚመሩት ኃይሎች በሶሪያ ድል መቀዳጀት መቻላቸው ትልቅ ስኬት እና ማህበረሰቡን ለማጠናከር የተወሰደ እርምጃ ነው ሲሉ ፑቲን ገልፀዋል፡፡

🟠 ፑቲን በሶሪያ እና ሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት ሁልጊዜም ወዳጃዊ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

🟠 የሶሪያ የሽግግር ፕሬዝዳንት ፑቲን ላደረጉላቸው አቀባባለ አመስግነዋል፡፡

🟠 አዲሱ የሶሪያ መንግሥት ከሩሲያ ጋር ያላውን ግንኙነት እንደ አዲስ ማስጀመር እንደሚፈልግ የሽግግር ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

🟠 በአዲሷ ሶሪያ ልማት ላይ ሩሲያ ወሳኝ ሚና እንደሚኖራት አል-ሻራ አንስተዋል፡፡

🟠 ሩሲያ እና ሶሪያ በታሪካዊ ግንኙነት የተሳሰሩ ናቸው ሲሉም አል-ሻራ ገልፀዋል፡፡

🟠 ሶሪያ ሩሲያ በተለያዩ መስኮች እንድታሳካ ባስቻለቻቸው በርካታ ስኬቶች ላይ አሁንም ትተማመናለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
11👍4
🇧🇯 የቤኒን የምርጫ ኮሚሽን በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚሳተፉ የመጨረሻ አምስት እጩዎችን አጸደቀ

❗️ሀገሪቱን እየመሩ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ታሎን በሕገ-መንግሥቱ የሥልጣን ዘመን ገደብ ምክንያት መወዳደር እንደማይችሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የወቅቱ የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስትር ሮሙአልድ ዋዳኝ ሀገሪቱን በጥመረት የሚያስተዳድሩት ፓርቲዎች እጩ ሆነው ቀርበዋል። በቤኒን ቀዳሚ ተቃዋሚ ፓርቲ የሆኑት ዲሞክራቶች ደግሞ በጠበቃው ሬናውድ ቪግኒሌ አግቦድጆ ይወከላሉ።

👉 የምርጫ ኮሚሽኑ የእጩዎቹን ዝርዝር ለሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በሚመጣው ህዳር ወር በምርጫ ወረቀቱ ላይ ስለመካተታቸው ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በሰው ሠራሽ አሰተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8👍3
አዲሱ የማዳጋስካር አስተዳደር ቁልፍ ሰዎች እነማን ናቸው?

ሚካኤል ራንድሪያኒሪና፣ ጊዜያዊ መሪ፦

🔸 በአንትሲራቤ ወታደራዊ አካዳሚ የሰለጠኑት ኮሎኔሉ፤ ልዩ የተቋማዊ ጥበቃ ድጋፍ ሰጪ ወታደራዊ ክፍል (ካፕሳት) አዛዥ ነበሩ፤
🔸 ትልቋ የደቡባዊ ማዳጋስካር ከተማ በሆነችው በቶሊያራ የቀድሞ የእግረኛ ጦር አዛዥ የነበሩ ሲሆን በርካታ ጦር ሰፈሮችንም በአዛዥነር መርተዋል፤
🔸 ለመንግሥት ባላቸው ትችታዊ አቋም ይታወቃሉ፤
🔸 በዓመፅ ቀስቃሽነት ክስ ከህዳር 2023 - የካቲት 2024 ታስረው ወደ ሥራቸው ተመልሰዋል፤
🔸 መነሻቸው በሆነው አንድሮ ክልል ከ2016 እስከ 2018 ገዥ ሆነው አገልግለዋል።

ዴሞስቴኔ ፒኩላስ፣ የጦር ኃይሎች አዲሱ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም፦

🔸 እስከ 2021 ድረስ በአምቦአሳሪ አትሲሞ የባለብዙ ተልዕኮ ሻለቃን በአዛዥነት ያገለገሉ ሲሆን የድርቅና ረሃብ እርዳታ የኦፕሬሽን ማስተባበሪያ ማዕከልን መርተዋል፤
🔸 ከ2019 እስከ 2023 በአንትሲራቤ ወታደራዊ አካዳሚን መርተዋል፣ በተለይም ከቻይና እና ከፈረንሳይ ጋር በወታደራዊ ትብብር ፕሮግራሞች ላይ ተሳትፈዋል፤
🔸 የካፕሳት ወታደራዊ ክፍል በማዳጋስካር ፕሬዝዳንት ላይ በተነሱ ተቃውሞዎች ምክንያት ሥልጣን ከያዘ በኋላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሆነው ተሹመዋል፤
🔸 በሜላኪ ክልል ማይንቲራኖ የተወለዱት ግለሰቡ የግሪክ እና የማዳጋስካር የዘር-ግንድ አላቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7👍1🫡1
🔨 የኖቤል ሽልማት የፖለቲካ መዶሻ ወደ መሆን አመዝኗል – የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

የኖቤል ሽልማት ባለፉት አስርት ዓመታት ወደ ስውር የፖለቲካ መሳሪያነት ወርዷል ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

👀 ዛካሮቫ አክለውም የኖቤል ሽልማት ለፖለቲካ እንቅስቃሴ እውቅና መስጠት ቢችልም፤ ግልጽነት በጎደላቸው የአሠራር ሂደቶች እና ግልጽ ባልሆኑ የምርጫ መስፈርቶች እንደ መሳሪያ ሆኖ ማገልገል እንደሌለበት ገልፀዋል።

የውጭ ጣልቃ ገብነትን አጥብቀው የሚደግፉት እና የሀገሪቱ የኃይል ሀብት ለሽያጭ እንዲቀርብ የሚሞግቱት የቬንዙዌላዋ ‘የተቃዋሚ መሪ’ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7👍2🔥1
❗️የማዳጋስካር ወታደርዊ ኮለኔል ሚካኤል ራንድሪያኒሪና በቀጣይ ቀናት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መኃላ ይፈፅማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍4😁42
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️ፑቲን እና አል-ሻራ ሲያደርጉት የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ የመሪዎቹ ውይይት ሁለት ሰዓት ከግማሽ በላይ የፈጀ እንደነበር የስፑትኒክ ባልደረባ ዘግቧል፡፡ በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❗️ሩሲያ የሶሪያን የመሠረተ ልማት ዳግም ግንባታ ለመደገፍ ዝግጁ ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኖቫክ ተናገሩ

ባለሥልጣኑ ይህን ያሉት ፑቲን እና የሶሪያ ግዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አህመድ አል-ሻራ ካደረጉት ውይይት በኋላ ነው፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍62
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የባሕር ሳይንስን ለመማር ከሀገር መውጣት ግዴታ አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ዘመናዊ የሥልጠና ሥርዓት መዘርጋት ይገባል - ካፒቴን ሳሙኤል ሲሳይ

🇪🇹 የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፓርት እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ካፒቴኑ፤ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የባሕር ኢንዱስትሪው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለበትን የሰው ኃይል እጥረት ለመቅረፍ ጉልህ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ይገልጻሉ።

"እዚህ ጉባኤ ላይ የተገኙት ግዙፍ የመርከብ እና የሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት አለባቸው። የወጣቶች ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ ይህን ክፍተት የመሙላት እምቅ አቅም አላት" ብለዋል።


📌 ካፒቴኑ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ ኢትዮጵያ ከዘርፉ ዓለም አቀፍ ተዋንያን ጋር በትብብር ሥልጠናዋን ማላቅዋ የሚፈጥረውን ዕድልም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
6🙏4
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️የማዳጋስካር ወታደርዊ ኮለኔል ሚካኤል ራንድሪያኒሪና በቀጣይ ቀናት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መኃላ ይፈፅማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ ነው፡፡ በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
❗️የማዳጋስካር መፈንቀለ መንግሥት መሪ ሚካኤል ራንድሪያኒሪና ራሳቸውን ገዜያዊ ፕሬዝዳንት አድርገው ሾሙ

የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ከሥልጣን ለማውረድ የተደረገውን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት የመሩት ኮሎኔል ሚካኤል ራንድሪያኒሪና፤ አንድሪ ራጆሊና ከሀገር መሸሻቸውን ተከትሎ በሕገ-መንግሥቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥያቄ መሠረት የመንግሥትን ሥልጣን እንደሚረከቡ አስታውቀዋል።

የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በወታደራዊው ልዩ ኃይል (ካፕሳት) የተወሰደውን የሀገሪቱን ሕገ-መንግስት የማገድ ተግባር "ሕገ-ወጥ እርምጃ" ሲል ማክሰኞ ዕለት አውግዟል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5😁5
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት የማስፋት ቁርጠኝነት አብነት ማድረግ ይገባል - የአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ጥምረት

📌 ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ሥርዓት ለመሸጋገር መሠረተ ልማት ሥራ ላይ በትኩረት እየሠራች እንደምትገኝ የጥምረቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዋረን ኦንዳንጄ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

"የኢትዮ ቴሌኮምን የሕዝብ የመኪና መሙያ ማዕከላት ተመልክቻለሁ። በሥፍራዎቹ ቻርጅ ለማድረግ የተሰለፉ ተሸከርካሪዎችም ሽግግሩ በሂደት ላይ መሆኑን ይናገራሉ። መሠረተ ልማቱን በመላ ሀገሪቱ ለማዳረስ ይበልጥ መሥራት ይገባል" ብለዋል።


ኢትዮጵያ በዘርፉ እያሳየችው ያለው ቁርጠኝነት ኢንቨስትመንትን ከመሳብ አንጻር ያለውን አንደምታም አንስተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አትሙቺ ያላት ነፍስበመዘናጋት በባቡር ልትገጭ ጫፍ የደረሰች ሴት የጥበቃ ሠራተኛ በወሰደው ቅጽበታዊ ምላሽ ህይወቷ ሊተርፍ ችሏል፡፡

📍ካይሰሪ ግዛት፣ ቱርክ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
17😱7
🇪🇹 ኢትዮጵያ የንጋት ሐይቅን በፍኖተ ካርታ ለመምራት ሂደት ላይ መሆኗ ተገለፀ

በግድቡ ላይ የተፈጠረውና ከአፍሪካ 4ኛው ግዙፍ ሀይቅ የሆነው የንጋት ሰው ሠራሽ ሀይቅን የዘላቂ ልማት ማዕከል የሚያደረግ ስትራቴጂክ እቅድ ወደ ተግባር ለማስገባት ያለመ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ፍኖተ ካርታውን ከባለድርሻ አካላት ጋር ከሚደረጉ ውይይቶች በሚገኙ ግብዓቶች በማዳበር ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፣ ውሃውን በቋሚነት ለማስተዳደርና ቅንጅታዊ አሠራርን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠራ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በመድረኩ ባደረጉት “የንጋት ሀይቅ ለቀጣዩ ትውልድ በቅብብሎሽ የምናስረክበው ትልቅ በረከት ነው” ብለዋል።


ለሐይቁ የተዘጋጀው ማስተር ፕላን በውስጡ ምን ይዟል፦

🌿 የኢኮ ቱሪዝም አገልግሎት፣
🐟 የዓሣ ንግድ ማስፋት፣
🚜 ለግብርና ዘመናዊ መስኖ አቅም መፈጠር፣
🚤 አዳዲስ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን የሚያጎለብትበት ቀጣይ ስራዎችን ያመላክታል፡፡

🔎 የአፈፃፀም ስትራቴጂውን ለማጠናቀቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሚደረግ ውይይት ረቂቅ ዕቅዱ አሁንም ክፍት እንደሆነ መናገራቸውን የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
11👀2
የኮንጎ ሪፐብሊክ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ በ2029 መጨረሻ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የፖይንት-ኖየር–ሉቴቴ–ማሉኩ-ትሬቾት የነዳጅ ምርት ማስተላለፊያ መስመር ለ30-40 ዓመታት ለማዕከላዊ አፍሪካዊቷ ሀገር አስተማማኝ የነዳጅ ምርት አቅርቦት ያረጋግጣል ሲሉ የሚኒስቴሩ የአፍሪካ የትብብር ዘርፍ ኃላፊ ታቲያና ዶቭጋሌንኮ ተናግረዋል።

የግንባታ ስምምነቱ በዚህ ዓመት ሰኔ ወር በሁለቱ ሀገራት መንግሥታት መጽደቁን በሩሲያ የኃይል ሳምንት ላይ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6😁1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የባሕርተኞች ሥልጠናን ወደ ቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ተቋማት ለማስፋት እየሠራን ነው - የኢትዮጵያ ማሪታይም ማሠልጠኛ ተቋም

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍራንስ ጁበርት፤ ኢትዮጵያ ለሌሎች ወደብ አልባ የዓለም ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ጠንካራ የባሕርተኞች ሥልጠና አደረጃጀት ባለቤት መሆኗን ተናግረዋል።

📌 ኃላፊው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ተቋሙ ከ29 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ተቀብሎ በማሠልጠን ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

"ከ7 ሺህ በላይ ባሕርተኞች አሉን። ከ2 ሺህ 600 በላይ መኮንኖችን ያሠለጠንን ሲሆን፤ በዓመት የምናሠለጥናቸውን የመሐንዲሶች ቁጥርም 1ሺህ ለማድረስ እየሠራን ነው" ብለዋል።


ፍራንስ ጁበርት የአፍሪካ የማሪታይም ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱ በሀገሪቱ ዘርፉን ይበልጥ ለማስፋት ያለውን አስተዋጽኦሞ አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
10
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️ሱዳን እና ሩሲያ በሥልጠና እና ፈጠራ የፋይናንስ ትብብራቸውን አጠናክረዋል - የፋይናንስ ሚኒስትሩ

ከሩሲያ ጋር የተደረገው አዲስ የጋራ ስምምነት በሁለቱ ማዕከላዊ ባንኮች መካከል ለሚኖር ጥልቅ ትብብር መሠረት የሚጥል መሆኑን የሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር ጅብሪል ኢብራሂም መሐመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ ይህ አጋርነት ከሥልጠና አልፎ በዲጂታል ክፍያ ስርዓቶች ውስጥ ያሉ የወደፊት ፈጠራዎችን ያካትታል ብለዋል።

“ይህ በሁለቱ ማዕከላዊ ባንኮች መካከል ለሚደረግ ተጨማሪ ትብብር አንድ እርምጃ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ወደፊት ክፍያዎች ወደ ስዊፍት አልያም ወደሌላ ከመሄድ ይልቅ ወደ ዲጂታል ክፍያዎች ሊሸጋገሩ ይችላሉ” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2👍1
አዲስ አሸባሪ ቡድን ከናይጄሪያው ቦኮ ሃራም እንደተገነጠለ ተነገረ

"ይህ አዲስ የዉሉዉሉ ቡድን ከቦኮ ሃራም በመገንጠል በሰሜን ማዕከላዊ ዞን ብቅ ማለት ጀምሯል፡፡ የላኩራዋ ቡድን አሁን በኳራ ትልቅ ችግር ሆኗል" ሲሉ የናሳራዋ ግዛት ገዥ አብዱላሂ ሱሌን ጠቅሶ የአካባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።


የግዛቱ አስተዳዳሪ፤ ከአዲሱ አሸባሪ ቡድን የተውጣጡ ታጣቂዎች በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ መኖራቸውን የደህንነት መረጃዎችን በመጥቀስ ገልጸዋል፡፡ ይህ ክልል የቤኑዌ፣ ኮጊ፣ ኳራ፣ ናሳራዋ፣ ኒጀር፣ ፕላቶ ግዛቶችን እና የናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃን ጨምሮ የፌደራል ዋና ከተማ ግዛትን ያካትታል።

👉 ቡድኑ ወደ ግዛታቸው ሰርጎ እንዳይገባ የደህንነት ባለሥልጣናት እንዲከላከሉ አብዱላሂ ሱሌ ጥሪ አቅርበዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
2😁2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#viral| በሰሜን ሩሲያ አውራ ጉዳና ላይ ለጥቂት ከአደጋ ያመለጠው አጋዘን

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
8👍6🤣2🙏1🙉1
🇷🇺🇺🇸 ትራምፕ ስለ ቶማሃውክ ሚሳኤል የሰጡት አስተያየት በአላስካ የተደረገው ውይይት ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም - ላቭሮቭ

💬 “ስለ ቶማሃውክ የተናገሩት አንዳችም ነገር በአላስካ በሃሳብ ደረጃ የተወያየነው ጉዳይ ላይ ተጽዕኖ የለውም፤ በሃሳብም በተግባርም ደረጃ ብል ይቀላል” ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለሩሲያ ሚዲያ ተናግረዋል።


ሌሎች ያነሷቸው ሀሳቦች፦

▪️ ሩሲያ ለአላስካው ውይይት ውጤት የአሜሪካን ተጨባጭ ምላሽ አሁንም እየጠበቀች ነው።

▪️ ሞስኮ በአላስካው ጉባኤ ላይ በተገኘው ስምምነት ላይ በመመስረት በተለያዩ ደረጃዎች ከዋሽንግተን ጋር ተግባራዊ ጉዳዮችን በማንኛውም ጊዜ ለመወያየት ዝግጁ ነች።

▪️ ለዩክሬን የሚደረጉ የቶማሃውክ አቅርቦቶች የሩሲያ-አሜሪካ ግንኙነትን መደበኛ ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ከፍተኛ ስጋት ይደቅናሉ።

▪️ ኪዬቭ በሩሲያ ግዛት ላይ ለሰነዘረቻቸው ጥቃቶች አሜሪካ መረጃ እንዳቀረበች የሚገልጹ የፋይናንሻል ታይምስ ዘገባዎችን ሩሲያ ተመልክታለች፤ በዚህም ሞስኮ ከዋሽንግተን ማብራሪያ ጠይቃለች።

▪️ በሩሲያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የሥራ ግንኙነት በተለያዩ መንገዶች ቀጥሏል፤ ነገር ግን እስካሁን ምንም ከፍተኛ ደረጃ ስብሰባዎች አልታቀዱም።

▪️ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ኪዝ ኬሎግ በዩክሬን ያለው ግጭት “እንዲያበቃ” ጥሪ አቅርበዋል።

▪️ የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ምክንያታዊ ሰው ናቸው፤ በመካከለኛው ምስራቅ ያሳዩትን አቅም በዩክሬን ቢደግሙት ሞስኮ በደስታ ትቀበላለች።

▪️ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባለቤት በዩክሬን ግጭት ውስጥ በተለይም ልጆችን ከመመለስ ጋር በተያያዘ ጠቃሚ ሚና ይጫወታሉ።

▪️ ሩሲያ በዩክሬን የኢስታንቡል ሂደት ላይ ባቀረበችው ማሻሻያ ሀሳብ ዙሪያ ምላሽ እየጠበቀች ነው፤ እስካሁን ከዝምታ ውጪ ምንም የለም።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
25👏1
2025/10/20 07:22:37
Back to Top
HTML Embed Code: