Telegram Web Link
#viral | ደቡብ ምስራቅ ሜክሲኮ ታሪካዊ በተባለለት ከባድ ጎርፍ ተጥለቀለቀ

የወሃው ሙላት አራት ሜትር ደርሷል፡፡

ከሞቃታማ ዝቅተኛ ግፊት የተነሳው ከባድ ዝናብ በቬራክሩዝ ከተማ የሚገኙ ወንዞች እንዲያጥለቀልቁ በማድረግ ጎዳናዎችን፣ ቤቶችን እና ንግዶችን በውሃ እንደሞላ የአካባቢው ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ነዋሪዎች ወደ ጣሪያዎቻቸው የሸሹ ሲሆን፣ የዝርፊያ እና የአገልግሎት መቆራረጦች ቀውሱን አባብሰውታል።

የቬራክሩዝ ገዥ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል። የአደጋ ጊዜ ዕቅዶች እንደተጀመሩ፣ የነፍስ አድን ጀልባዎች እንደተሰማሩ እና ጊዜያዊ መጠለያዎች እንደተከፈቱ ተዘግቧል።

ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7
🌍 አፍሪካ ፣ ልዩ ምርጫ ይህን የመልዕክት መለዋወጫ 'ፎልደር' ከአህጉሪቱ አዳዲስ ዜናዎች ከሚገኙበት ቻናሎች ላይ ይጨምሩት ⤵️

👉👉 https://www.tg-me.com/addlist/lwYcxR-tjCBiODBi 👈👈

#social
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
4
🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሀዲያና ስልጤ ዞኖች የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮችን አስረከቡ

"ረቡዕ ዕለት በሀላባና በከምባታ ዞኖች የነበረው ሞዴል የገጠር መንደሮች ርክክብ ሥነ-ሥርዓት ቀጥሎ፣ በዛሬው ዕለት በሀዲያና ስልጤ ዞኖች የተገነቡ ቤቶችን አስረክበናል፡፡" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

የተገነቡት መንደሮች፦

◻️ ባለሦስት መኝታ መኖሪያ ቤቶች፣

◻️ የማብሰል ባዮጋዝ፣

◻️ የፀኃይ ኃይል ማመንጫ፣

◻️ የዶሮና የንብ ማርቢያ እና

◻️ የእንስሳት በረት የተሟላላቸው ናቸው፡፡

"መርሐ - ግብሩ በተመጣጣኝና አነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ከማስገኘት አንፃር ለገጠሩ ማኅበረሰብ ብልጽግና ያለንን ሕልም የሚያሳይ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።


🏡 በአራቱ ዞኖች የተሠራው ሥራ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች መደገም እንዳለበት አሳስበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
13👍4👎2
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
“ልክ ዳግም እንደ መወለድ ነው” ስትል ፍልስጤማዊቷ የጋዛ ነዋሪ ወደ መኖሪያ ቤቷ መመለሷን አመሰገነች ፍልስጤማዊቷ ላማ ክፋርኔህ ከስፑትኒክ ጋር ባደረገችው ቆይታ፣ በተኩስ አቁም ስምምነቱ አማካኝነት በፍልስጤማውያን ሕጻናት፣ አዛውንቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች ላይ የሚሰነዘሩት ጥቃቶች እንደሚያበቁ ያላትን ተስፋ ገልጻለች። “ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱና እንደበፊቱ እንደገና መማር እንደምንችል ተስፋ አደርጋለሁ”…
'ጦርነቱን በማስቆም ረገድ የሚደረግ ማንኛውም መዘግየት ተቀባይነት የለውም' ሲል የፍልስጤም አመራር የጋዛን የተኩስ አቁም በደስታ ተቀበለ

የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማሕሙድ አባስ አማካሪ መሕሙድ አል-ሀባሽ ለስፑትኒክ  እንደተናገሩት፣ የፍልስጤም አመራር “በጋዛ ሰርጥ ላይ የተካሄደውን የእስራኤል ጥቃት ማቆም በአዎንታዊ መልኩ ገምግሟል።”

“የዚህ ጦርነት ሙሉ በሙሉ እና በዘላቂነት ማብቃት ሁልጊዜም ፍፁም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።


🎯  ዋናው ዓላማ “የፍልስጤማውያንን ሕይወት መታደግ” እና “እስራኤል ለሁለት ዓመታት ሙሉ ያካሄደችውን አውዳሚ ጦርነትና ጭፍጨፋ ማቆም” መሆኑን አስምረውበታል።

➡️ ስለ ጋዛ የወደፊት አስተዳደር እና የሃማስ ትጥቅ መፍታት በተመለከተ፣ አል-ሀባሽ እነዚህ ዝርዝሮች “ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ ሊነጋገሩባቸው ይችላሉ” ብለዋል፡፡ ሆኖም “ጦርነቱን በመቋጨት ውስጥ የሚፈጠር የትኛውም መዘግየት ተጨማሪ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ተቀባይነት የለውም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😁54👎1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
“ከዛሬ ጀምሮ ነዳጅ የሚጠቀሙ ማንኛውም ከባድ መኪና ማስገባት የተከለከለ ነው” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 🇪🇹 የኢትዮጵያው መሪ ትናንት በኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ ባደረጉትና በማኅበራዊ ሚዲያቸው ላይ ባሰራጨት ንግግራቸው ውሳኔውን ይፋ አድርገዋል። “በአንጻሩ ማንኛውም ባለሃብት ጋዝ የሚጠቀሙ "ቦቴዎች" (የፈሳሽ ጨነት ከባድ መኪኖች)፣ “ትራኮች” (የደረቅ ጭነት ከባድ…
🇪🇹 በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ እንዲገቡ መወሰኑን ገንዘብ ሚኒስትር አስታወቀ

🛢 ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ የማምረት ሥራ በይፋ መጀመሯን ለአዲሱን መመሪያ መውጣት እንደምክንያት ጠቅሷል።

ሚኒስቴሩ ውሳኔውን አስመልክቶ ለጉምሩክ ኮሚሽን ባስተላለፈው መመሪያ “ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ማናቸውም አይነት የደረቅ እና የፈሳሽ ችነት ተሽከርካሪዎች እና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ አገር እንዲገቡ መፈቀዱን እንገልጻለን፡፡” ብሏል፡፡


“ለነዳጅ ግዥ የምናወጣውን የውጭ ምንዛሪ የሚያስቀር በመሆኑ መንግሥት የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀምን ለማበረታታት ወስኗል” ሲል ነው ገንዘብ ሚኒስቴር የገለፀው፡፡ ፡

🚚 ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን በፊት ወደ አገር እንዲገቡ ከተፈቀደላቸው እንዲሁም በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ አገር ከሚገቡት በስተቀር በቤንዚን እና ናፍታ የሚሠሩ የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግም አሳስቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
11😁1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
የአውሮፓ ሕብረት እና ኦባማ የኖቤል የሰላም መውሰዳቸው ሽልማቱ በብቃት ላይ የተመሠረተ አለመሆኑን ያሳያል - ጉናር ቤክ የፖለቲካ ተንታኝ እና የቀድሞ የጀርመን አማራጭ ፓርቲ የአውሮፓ ፓርላማ አባል ጉናር ቤክ ለስፑትኒክ በሰጡት አሰተያየት፣ የቬንዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ለሆኑት ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የኖቤል የሰላም ሽልማት መሰጠቱን አስመልክቶ፣ ሽልማቱ ለፖለቲካ አክቲቪስቶች መሰጠት የለበትም ሲሉ ይሞግታሉ። “በርካታ…
'የወንጀለል እና ፋሺስታዊ ቅስቀሳ ነው:' ሲሉ የስፔን ፖለቲካኛው የማቻዶ የኖቤል ሽልማት ለሰላም የሚሰጥ ስድብ ነው አሉ

የቬንዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የኖቤል የሰላም ሽልማት መሰጠቱ፣ “የተከበረ፣ የታመነና ጀግና የሆነውን የቬንዙዌላን ሕዝብ” ላይ ያነጣጠረ “የወንጀልና ፋሺስታዊ ቅስቀሳ” ነው፤ ሲሉ የአንዳሉሲያ ፓርላማ ምክትልና የስፔን ኮሚኒስት ፓርቲ አባል የሆኑት ኢስማኤል ሳንቼዝ ካስቲሎ ተናግረዋል።

ለሳንቼዝ ካስቲሎ፣ ይህ ውሳኔ የሰላምን ትርጉም የሚያዛባ ሲሆን፣ የዓለም አንድነት ምልክት የሆነውን ሽልማት ወደ የፖለቲካ መጠቀሚያነት የሚቀይር ነው።

ማቻዶ “የጎዳና ላይ ዓመፅን ያበረታቱ፣ በገዛ አገራቸው ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን እንዲጣል የጠየቁ እንዲሁም በይፋ የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንዲኖር ጥያቄ ያቀረቡ” ናቸው፤ ለሳቸው ክብር መስጠት የመሰል መዘዞች ዳፋ ሲቋቋም ለኖረው የቬንዙዌላ ሕዝብ ቀጥተኛ ንቀት ነው ሲሉ ይሞግታሉ።

“እሳቸው የመደብ ጥላቻን፣ ለድሆች ንቀትን፣ ለአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ሲባል ብሔራዊ ሉዓላዊነትን መካድን እና የልሂቃንና አግላይ የሆነውን አሰራርን ማስቀጠልን ይወክላሉ” ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።


ሳንቼዝ ካስቲሎ፣ የቬንዙዌላ ሕዝብ አሁንም መድኃኒት፣ አስፈላጊ ሸቀጦች እና ምግብ የማግኘት ዕድሉን ገድበውበት በነበሩ ማዕቀቦች ትዝታ ውስጥ እየኖረ እንደሆነ ጠቁመዋል።

“እነዚህ የተከሰቱት በተፈጥሮ አደጋ ወይም  በአስተዳደር ስህተት ምክንያት አይደለም፤ ይልቁንስ ለአገራቸው በሕዝቡ የተመረጠውን ሉዓላዊ መንገድ ከመቀበል ይልቅ እንድትሽመደመድ በመረጡት እንደ ማቻዶ ባሉ ግለሰቦች የተቀየሱ ስትራቴጂ ውጤት ናቸው” ብለዋል።


🌎 ሳንቼዝ ካስቲሎ፣ ማቻዶን እንደ “የሰላም ሴት” አድርጎ ማሳየቱ “በላቲን አሜሪካ ባሉ የነፃነት ሂደቶች ላይ የሚካሄድ የምልክትና የባህል ጦርነት” አካል መሆኑን አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህም ወግ አጥባቂ ልሂቃንን ለማፅዳትና ሉዓላዊነታቸውን የሚከላከሉ አገራትን ወንጀለኛ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረግ ጥረት ነው ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
7👍1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
'ጦርነቱን በማስቆም ረገድ የሚደረግ ማንኛውም መዘግየት ተቀባይነት የለውም' ሲል የፍልስጤም አመራር የጋዛን የተኩስ አቁም በደስታ ተቀበለ የፍልስጤም ፕሬዝዳንት ማሕሙድ አባስ አማካሪ መሕሙድ አል-ሀባሽ ለስፑትኒክ  እንደተናገሩት፣ የፍልስጤም አመራር “በጋዛ ሰርጥ ላይ የተካሄደውን የእስራኤል ጥቃት ማቆም በአዎንታዊ መልኩ ገምግሟል።” “የዚህ ጦርነት ሙሉ በሙሉ እና በዘላቂነት ማብቃት ሁልጊዜም ፍፁም ቅድሚያ…
🇺🇸🇵🇸🇮🇱 የጋዛ ስምምነት ግጭቱ እንደገና እንዲቀጥል የሚያደርግ ጊዜ ቆጣሪ ቦምብ ሊሆን ይችላል ተባለ

🗣  የጋዛ የሰላም እቅድ ቁልፍ ጥያቄዎችን ሳይመልስ በመቅረቱ፣ ውጊያ እንደገና እንዲቀጥል በር ሊከፍት ይችላል ሲሉ የሊባኖስ አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ጆሴፍ ሄሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ባለ 20 ነጥቡ ዕቅድ ሃማስ “መሣሪያውን እንዲያስረክብ" እንዲሁም “ወደ ሰላማዊ አብሮ መኖር” ፊቱን እንዲመለስ እና የፍልስጤምን መንግሥት የመመሥረት ዕድል የሚያስረዳው ነጥብ ግልጽ የሆነ ተቃርኖ ይፈጥራል።

1️⃣ ሄሉ እንዳሉት፣ “መሣሪያቸውን ከሰጡ፣ አሁንም የትግል ንቅናቄዎች  ናቸው? መሣሪያ የሌለው የትግል ንቅናቄ ምንድነው?” ሲሉ ጠይቀዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የእስራኤልን ግድያ የተመለከቱ ወጣት ጋዛውያን አድገው ለመበቀል መፈለጋቸው አይቀሬ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

2️⃣ ፕሮፌሰሩ እንዳብራሩት፤ ሃማስ መሣሪያውን ለመተው ፈቃደኛ ካልሆነ፣ እስራኤል “እሺ ወይ ወደ ጦርነት እንመለሳለን ወይም ይህን በራሳችን ውሎች እናስፈጽማለን ማለትም በማንኛውም ጊዜ የሃማስን ባለስልጣን፣ መሪ ወይም ፖለቲከኛ ኢላማ ማድረግ እንችላለን” ልትል ትችላለች።

ሄሉ ሁኔታውን በሊባኖስ ውስጥ ሂዝቦላህ ትጥቅ እንዲፈታ ከቀረበው ጥያቄ ጋር ያነጻጽሩታል፤ ቡድኑ በቆራጥነት እምቢ ስላለ፣ ግጭቱ ሳይፈታ ቀርቷል።

በአጠቃላይ የሰላም ዕቅዱ በቋንቋውና በዓላማዎቹ “የመፈፀም ፍላጎት ያለው” እንደሆነ ይገመግሙታል፤ ነገር ግን “ወደ ዘላቂ ስምምነት የሚያመራ ተቋማዊ መንገድ” የለውም ሲሉ ሄሉ ያጠቃልላሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
10👏2😁2🤪1
🇲🇦 የሞሮኮ ንጉስ በወጣቶች የሚመራውን ተቃውሞ ተከትሎ ፈጣን ማኅበራዊ ማሻሻያ እንዲደረግ አሳሰቡ

ንጉሥ መሐመድ ስድስተኛ ለፓርላማው የመክፈቻ ስብሰባ ባደረጉት ዓመታዊ ንግግር፤ "ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ እንዲሁም የትምህርትና የጤና ዘርፎችን በተጨባጭ ማሻሻል ቀዳሚ ተግባራት አድርገናል" ብለዋል።


ንጉሡ "ቀጣዮቹ የአገር ውስጥ ልማት ፕሮግራሞች በፍጥነት እንዲተገበሩና ጠንካራ ተፅዕኖ እንዲኖራቸው" አሳስበዋል።

"በትላልቅ ብሔራዊ ፕሮጀክቶች እና በማህበራዊ ፕሮግራሞች መካከል ምንም ዓይነት ግጭት ወይም ፉክክር ሊኖር አይገባም" ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።


መስከረም 17 ሞሮኮ ውስጥ የተጀመረውና ለአንድ ሳምንት በቆየው ሕዝባዊ አመጽ፣ ተቃዋሚዎች የትምህርት ስርዓት እና የጤና አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ ሲጠይቁ ቆይተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
5👍2
2025/10/24 14:03:41
Back to Top
HTML Embed Code: