Telegram Web Link
በደቡብ አፍሪካ-ዚምባብዌ ድንበር ላይ በደረሰ አስከፊ የአውቶቡስ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን የክልል ባለሥልጣናትን ጠቅሰው እንደዘገቡት፤ እሁድ ምሽት ከመካዶ አቅራቢያ በኤን አንድ አውራ ጎዳና ላይ አንድ አውቶቡስ ተገልብጦ የሞት እና የአካል ጉዳት አስከትሏል።

አደጋው የደረሰው ከዚምባብዌ ድንበር 90 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ ሲሆን፤ የአውቶቡሱ ሹፌር መሪውን መቆጣጠር ባለመቻሉ ተሽከርካሪው ገደል ውስጥ መግባቱ ተጠቅሷል።

የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት 38 የተረፉ ሰዎችን በአቅራቢያው ወደሚገኙ ሆስፒታሎች ሲያጓጉዙ የነፍስ አድን ቡድኖች ተጨማሪ ተጎጂዎችን መፈለግ መቀጠላቸውን ዘገባው አክሏል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
😢83🕊2
❗️ሩሲያ የጋዛ ቀውስ ዳግም ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት አላት - ሰርጌ ላቭሮቭ

ሞስኮ በሻርም ኤል-ሼክ የሚካሄደው የጋዛ የሰላም ጉባኤ ስኬታማ እንዲሆን ከልብ ትመኛለች ሲሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከዓረብ ሀገራት ለተወጣጡ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ሰርጌ ላቭሮቭ ያነሷቸው ተጨማሪ ነጥቦች፦

◻️ ሩሲያ ሁሉም የሚመለከታቸው ሀገራት የጋዛ ቀውስ ዳግም እንዳይከሰት እንዲከላከሉ ጥሪ ታቀርባለች፡፡

◻️ የትራምፕ የጋዛ እቅድ በጠረጴዛው ላይ ያለ የተሻለው እቅድ ቢሆንም የፍልስጤምን ችግር አይፈታም።

◻️ የፍልስጤም ግዛት ሳይፈጠር የመካከለኛውን ምስራቅ ግጭት በዘላቂነት መፍታት አይቻልም፡፡

◻️ በጋዛ ዙሪያ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት የሩሲያ-አረብ ስብሰባ ተላልፏል፤ በአዲስ ቀን ዙሪያ ስምምነት ሲደረስ ይከናወናል፡፡

◻️ የትራምፕ የሰላም እቅድ የጋዛን ብቻ ሳይሆን የዌስት ባንክን እጣ ፈንታ መግለጽ አለበት።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5👍4😁2👎1
🇪🇹 ኢትዮጵያውያን በክንዳችሁ ብርታት፤ ሠንደቅ ዓላማችሁን እና ሀገራችሁን መጠበቅ ይኖርባችኋል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‘ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሃሳብ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል፡፡

"ኢትዮጵያውያን በአዕምሮአችሁ ሰላምን ማፅናት በልባችሁ የተስፋን ወጋገን አጥብቆ መያዝ፣ በክንዳችሁ ብርታት ደግም ሠንደቅ ዓላምችሁን እና ሀገራችሁን መጠበቅ ይኖርባችኋል” ሲሉ ርዕስ ብሔር ታዬ አፅቀሥላሴ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በተከናወነው 18ኛው የሠንደቅ ዓላማ ቀን አከባበር ላይ ተናግረዋል፡፡


የሠንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ክብርና ቃልኪዳን በልቡ የሚያድስበት፣ የጋራ ማንነነቱን የሚያጎላበትና የነገ ተስፋውን የሚያጸናበት ታላቅ ብሔራዊ ዕለት ነው ብለዋል፡፡

⚖️ ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በአዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሰኞ ይከበራል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍10👎73
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️ሩሲያ በምዕራብ ሰሃራ ያላት አቋም በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች የሚመራ ነው - ላቭሮቭ

ለረጅም ጊዜ መሠረታዊ መርህ የነበረው ለምዕራብ ሰሃራ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ሲሆን ይህም በሕዝበ ውሳኔ እንዲሆን የታሰበ ነበር ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ሩሲያ የሞሮኮን የራስ ገዝ አስተዳደር እቅድ ሁሉም ተሳታፊ ወገኖች ከተስማሙበት ብቻ እንደሆነ የምትቀበለው አክለዋል።

አሜሪካ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የመጀመሪያ የሥልጣን ዘመን ምዕራባዊ ሰሃራን የሞሮኮ አካል አድርጋ የአንድ ወገን እውቅና በመስጠት ጉዳዩ ተዘግቷል ብትልም፤ ሩሲያ ሁሉንም የሚያስማማ ዘላቂ መፍትሄ እንዲመጣ አጥብቃ ታስገነዝባለች ሲሉ ላቭሮቭ ገልጸዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች አሁን ያሉት ብቸኛና ትክክለኛ ማዕቀፍ ናቸው ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ ሩሲያ አዳዲስ ውሳኔዎችን ለመቀበል ዝግጁ የምትሆነው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቀረቡት የመግባቢያ መርሆዎች ላይ ከተስማሙ ብቻ ነው ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
6👏1
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️ሩሲያ በምዕራብ ሰሃራ ያላት አቋም በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎች የሚመራ ነው - ላቭሮቭ ለረጅም ጊዜ መሠረታዊ መርህ የነበረው ለምዕራብ ሰሃራ ሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ሲሆን ይህም በሕዝበ ውሳኔ እንዲሆን የታሰበ ነበር ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ሩሲያ የሞሮኮን የራስ ገዝ አስተዳደር እቅድ ሁሉም ተሳታፊ ወገኖች ከተስማሙበት ብቻ እንደሆነ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት ሥር መሠረቱ አህጉሪቱ በማሥሠሪያ ትከፈል የነበረበት የቅኝ ግዛት ዘመን ነው  - ላቭሮቭ

ይህ በማሊ እና በአልጄሪያ መካከል ያለውን ውጥረት እንዲሁም በሩዋንዳ፣ በቡሩንዲ እና በሌሎች ሀገራት ያሉ የጎሳ ግጭቶችን ይመለከታል ብለዋል።

“የአፍሪካን ካርታ ብትመለከቱ በእነዚህ ሀገራት መካከል ብዙ ሰው ሠራሽ ድንበሮችን ማግኘት ትችላላችሁ” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
💯8
ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤቶች የተፈቱ ዘመዶቻቸውን እየተቀበሉ ነው

በራማላህ ፍልስጤም የደስታ የአደባባይ አቀባበሎች በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ታይተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
17👍3🙏3😁1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❗️ለአዲሱ መካከለኛው ምስራቅ ታሪካዊ ጎህ ቀዷል - ትራምፕ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በእስራኤል ፓርላማ ክኔሴት ንግግር ሲያደርጉ የጦርነት ዘመን አብቅቶ የእምነትና የተስፋ ዘመን ጀምሯል ብለዋል፡፡

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍8🤪3
በአፍሪካ የእድገት ትርክት ውስጥ የክህሎት ሙያ ዳግም ክብር ሊያገኝ ይግባል - የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ በአፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስርዓቶች ላይ ጉልህ ለውጥ እንዲደረግ፤ የአፍሪካ ክህሎት ሳምንት 2025 በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

“ራዕያችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ በጋራ ከተረባረብን አፍሪካ ክህሎትን የተላበሱ፣ ብቁና የበለፀጉ ወጣቶች አህጉር የምትሆንበት ወቅት ሩቅ አይሆንም” ብለዋል፡፡


ዘላቂ መረጋጋትና የጋራ ብልፅግና የሚሰፍነው በአምራች ዘርፉ ላይ እሴት በመጨመር፣ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠትና የሥራ እድል በመፍጠር እንደሆነም በንግግራቸው አስምረዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
3👍2
❗️የማዳጋስካር ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊና በፈረንሳይ ወታደራዊ አውሮፕላን ከሀገሪቱ መውጣታቸው ተሰማ

ፕሬዝዳንቱ የመጨረሻ መድረሻቸው ባይታወቅም በሞሪሺየስ አድርገው ዱባይ ሊገቡ ይችላል ሲሉ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ሀገሪቱን ለቅቆ የመውጣት ውሳኔ የመጣው በራጆሊና እና በፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን መካከል በተደረገ ቀጥተኛ የፕሬዝዳንታዊ ስምምነት እንደሆነ ተዘግቧል።

ዛሬ ሰኞ ማለዳውን ፕሬዝዳንቱ በአካባቢው አቆጣጠር 1፡00 ሰዓት ለመላው ሀገሪቱ ንግግር እንደሚያደርጉ ፅ/ቤታቸው አስታውቆ ነበር፡፡ በማዳጋስካር ሥልጣናቸውን እንዲለቁ የሚጠይቅ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲሰማ ቆይቷል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍63
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
❗️የትራምፕ የምክር ቤት ንግግር በግራ ዘመም የእስራኤል ፓርላማ አባል መስተጓጎል ገጥሞት ነበር ሆኖም ፕሬዝዳንቱ ብዙም ሳይቆይ ንግግራቸውን ቀጥለዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ትራምፕ ለእስራኤል ፓርላማ ባደረጉት ንግግር የተናገሯቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

🟠 በመካከለኛው ምስራቅ የሽብርና የሞት ዘመን አብቅቷል፣ ቀጣናውም “አዲስና ታሪካዊ ዘመን” እያየ ነው።

🟠 ያለ ልዩ ተደራዳሪው ዊትኮፍ፤ “ዓለም ሦስተኛ የዓለም ጦርነት ሊገጥማት ይችል ነበር።”

🟠 ዊትኮፍ ሞስኮን ከጎበኘ በኋላ ከፑቲን ጋር “ብዙ አስደሳች ነገሮችን” እንደተወያየ ሪፖርት አድርጓል።

🟠 በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ከማምጣት የዩክሬንን ግጭት መፍታት ቀላል ነው።

🟠 ራሳቸውን ተፈጥሯዊ ሰላም ፈጣሪ ሲሉ በመግለፅ፤ ጦርነቶችን በማስቆም እንደሚሳካላቸው አንስተዋል።

🟠 አሜሪካ ጦርነቶችን ለመጀመር ፍላጎት የላትም፤ ነገር ግን አስፈላጊ ከሆነ “ማንም አሸንፎ በማያውቀው ልክ” ታሸንፋለች።

🟠 የጋዛ ግጭት መቆም፤ “የፍልስጤማውያን የረዥም ጊዜ ቅዠት” እንዲያበቃ አድርጓል።

🟠 የኢራን የዩራኒየም ማበልጸጊያ ተቋማት ሳይወድሙ የጋዛ የሰላም ስምምነት እውን አይሆንም ነበር፡፡

🟠 ኢራን ከአሜሪካ ጋር “ስምምነት ላይ በመድረስ” ግንኙነቷን መደበኛ ለማድረግ ፈቃደኛነት እያሳየች ነው።

🟠 ከጋዛ ስምምነት በኋላ በዩክሬን ግጭት አፈታት ዙሪያ ትኩረት ለማድረግ አቅደዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
🙏109😁7👍2👏1
🇪🇹 ኢትዮጵያዊቷ ሃዊ ፈይሳ በታሪክ አምስተኛዋ ፈጣን ሴት አትሌት መሆን ቻለች

የ2025 የቺካጎ ማራቶን የሴቶች ውድድርን በአስደናቂ ብቃት 2:14:56 በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ የምንግዜም አምስተኛዋ ፈጣን ሴት ሯጭ በመሆን አዲስ ታሪክ ማስመዝገብ መቻሏን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ሃዊ ውድድሩን ተቆጣጥራ የመራችበት መንገድ፣ ከ30 ኪሎ ሜትር በኋላ በብቸኘነትና በበለጠ ፍጥነት መምራቷ ርቀቱን ከጨረሱ ሴቶች ሁሉ ፈጣኗ እንድትሆን አድርጓታል።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት መገርቱ አለሙ በ2:17:18 በመግባት 2ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

በወንዶች ኢትዮጵያዊያኑ አትሌቶች አትሌት ሁሰዲን መሀመድ እና አትሌት ሰይፉ ቱራ 5ኛ እና 6ኛ ደረጃን በቅደም ተከተል ይዘዋል። ኡጋንዳዊው አትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞ በ2:02:23 ውድድሩን አሸንፏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
👍109😁1
2025/10/21 11:07:46
Back to Top
HTML Embed Code: