Telegram Web Link
የእስልምና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ ወገኖቻችን በጠቅላላ እንኳን ለ1442ኛው የረመዳን ፆም በሰላም አደረሳችሁ! ፆሙ ለአገራችን እና ለህዝባችን የበረከት ፆም ይሆንልን ዘንድ እንመኛለን!

"በሉ እናንተ ሂዱ የኛም ወደዛው ነው
ወትሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው
እስላም ክርስቲያኑ ገጠመ ጦማቸው
እስላም ክርስቲያኑ ባንድ ውሎ ጦማቸው
ወደ አምላክ ለመሄድ ቀጠሮ እንዳላቸው
ምነው ይኼን አይቶ አምላክ በረዳቸው..."
@
ቴዲ አፍሮን ሊሸልም የሚችል ድርጅት አልያም ተቋም ምን መስፈርቶች ያስፈልጉታል? የሚለው ጥያቄ ለኔ መሰረታዊ ጥያቄ ነው።
ታታዬ አንተስ ምን ትላለኽ..?

ከላይ በመግቢያዬ ያስቀመጥኩት አንዲት እንስት ደስ ከሚያሰኝ ሰላምታ በኋላ የጠየቀችኝን ጥያቄ ነው። እኔማ ዝም ብል መልካም ነው። ምክኒያቱም.... አይ ብዬ ብናገር ግን የምሰብራቸው ጩኸቶች አሉ ብዬ ዝም አልኩ ብላት "..ኧረ የሆነ ነገርማ በል.." አለችኝ። ሴት የላከው አይሁንብኝና ከስሜታዊነት ወጥቼ በ20ዎቹ አጋማሽ እንዳለ ወጣት አንድ ነገር ልበላችሁ። አንድ ነገር ላይ ያተኮረ ግን ዕልፍ ኃሳብ...! አትርሱ ደግሞ ነገ /ሚያዝያ 6/2004 ዓ.ም/ ከቴዲ አፍሮ የተረከብነው ድንቅ ነገር አለ! እሱን ነገ አወጋችኋለሁ! ዛሬ ወደ ጉዳዬ ልመለስ...

ቴዲ አፍሮን ሊሸልም የሚችል ድርጅት አልያም ተቋም ምን መስፈርቶች ያስፈልጉታል? የሚለው ጥያቄ ለኔ መሰረታዊ ጥያቄ ነው። በኢትዮጵያ ለቴዲ አፍሮ የሚመጥን መንግስታዊም ሆነ የግለሰብ ተቋም የለም ብል ማጋነን አይሆንብኝም። እነ እገሌ ሽልማት በሚወስዱበት መድረክ ላይ ቆሞ ቴዲ አፍሮ ሲሸለም አይታቹ ሊሆን ይችላል። እውነታው ግን ቴዲ አፍሮ ያንን ድርጅት እየሸለመው እንጂ ያ ተቋም ቴዲ አፍሮን ለመሸለም ብቁ ሆኖ አይደለም። ምክኒያቱም ቴዲ አፍሮ በካናዳ እና በአሜሪካን አገር እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት የዋሽንግተን ቢሮ አንተ የትውልዱ ኮከብ አርቲስት እንዲሁም የዘመኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ ነህ ሲሉ ሁሉም በህብረት በአንድ ሀሳብ ተስማምተው ሸልመውታል። ልብ በሉልኝ የዘመኑ ማለት የአመቱ አይደለም! ዘመን የሚለካው በ100 አመታቶች ነው። የአፍሪካ ህብረት ደግሞ ለአፍሪካ ወጣቶች ተምሳሌታቸው ነህ ሲል ሸልሞታል። ሙሉ መረጃውን ከታች በዝርዝር አስቀምጣለሁኝ።

ዓለማችን የቴዲ አፍሮን ግዙፍነት ተረድታ ብቻውን ሸልማዋለች። ይኼ ለአርቲስቱ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿም ኩራት ነው። ለምን ሰሞኑን ተጠርቶ አልተሸለመም አልያም እንኳን አልተጠራ የሚለው ለኔ ተራ ወሬ ነው። ቴዲ አፍሮ ሚሊኒየም ደግሰ ስትጠራው ድኃዬጋ ጣራ በሌለው ሜዳ ላይ ይሻለኛል ብሎ ዳንኪራ የሚረግጥ ጥበበኛ ነው! ለድኃ እንጂ ለቱጃር የማይታገል ለጥበብ እንጂ ለመጥበብ የማይሰራ ለአገር እንጂ ለጎጥ የማይጮኽ ግዙፍ የኪነጥበብ ሰው ነው።

ይኼንን ካልኩ በቂ ነውና ለሌሎች ሽልማቶች /ሌሎችን ለመሸለም/ ጊዜ ስለሌለው ውስንነት ባለባቸው ስፍራዎች የመገኘት ፍላጎቱ እምብዛም ነው። በዚህ ሁኔታ የሚነደው የቴዲ አፍሮ አድናቂ መኖር የለበትም። ምክኒያቱም ቴዲ አፍሮ ወሰን የተበጀለት አርቲስት ሳይሆን መዳረሻውን በዓለም ጫፍ ያደረገ ግዙፍ አርቲስት ነው። ለዓለማችን የዋለውን ውለታ ከዓለም ህዝብ እንጂ ከ____ አይቀበልም።

እኔ ሁሌም በኩራት ሆኜ ስለዚህ ግለሰብ በፍጹም ነፃነት የምጽፍ ✎#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/ ነኝ!

✔️የአፍሪካ ሕብረት ለአፍሪካ ወጣቶች አርአያ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ በማለት የሕብረቱን የክብር ሽልማት አበርክቶለታል። በዕለቱ የአፍሪካ ሕብረት ሽልማት ስነስርዓት ላይ ከዲሲ ከንቲባ የእውቅና ሽልማትም ተሰቶታል።

✔️2014 Kora Award በፕላቲንየም ደረጃ የክብር የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል። ከኢትዮጵያ ሌላ አርቲስት የተቀበለ ያለ አይመስለኝም።

✔️East African Theater Institute :- በምስራቅ አፍሪካ በጥበብ ሰውን በመፍጠር (Human Development through Performing Arts in East African Region) በሚል በባጎሞዮ ታንዛንያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር Nov 8, 2006 የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

✔️Winnipeg Multi Cultural Form - የትውልዱ ኮከብ (Star of the Generation) በማለት በኪነ ጥበባዊ ሙያው ላበለከተው ዘርፈ ብዙ አስተዋፆ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል።

✔️Ethio - Canada Heritage Centre የትውልዱ ድልድይ (Bridge of the Generation) በማለት ኪነጥበባዊ ሙያውን በብቃት ስለተወጣ የእውቅና ሽልማት ሰቶታል።

✔️ለሰላም እና ለአንድነት ላበረከተው አስተዋጾ በካናዳ ፖርላመንት ስም የፖርላመንት አባል በሆኑት አሌክስ ኑታል (Alex Nuttall) በኩል የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል።

✔️East African Arts and Cultural Associations - የጊዜው ተፅዕኖ ፈጣሪ አርቲስት በሚል እውቅና አበርክቶለታል።

✔️Society of Ethiopians Established in Diaspora (SEED) (ማኅበረ ግዩራን ዘረ ኢትዮጵያ) - ታሪክና ባህልን በጥበብ ስራዎቹ ለማጉላት ላደረገው የላቀ ጥረት እንዲሁም ለበጎ አድራጎት አስተዋፆዎቹ እውቅና የሲድ አዋርድ ሸልሞታል።

ሌሎችም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሽልማቶችን ብቻውን ተቀብሏል። የሆነው ሆኖ በሰራው ልክ ዓለማችን የምድሯን ድንቅ እና ልዩ ሰው አቅሟ በፈቀደ መጠን አመስግናዋለች።

በድጋሚ ✎#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/ ነኝ!
@
#ሚያዝያ_6_2004 ለውድ የጥበብ አፍቃሪያን ታላቅ የምስራችን ጥበብ ከተሞላበት ዜማ ጋር ይዞ ብቅ ያለበት ቀን ነው።
#ሚያዝያ_6_2004 ለውድ የጥበብ አፍቃሪያን ታላቅ የምስራችን ጥበብ ከተሞላበት ዜማ ጋር ይዞ ብቅ ያለበት ቀን ነው።

ቴዲ አፍሮ #ጥቁር_ሰው የተሰኘ አልበሙን ቀደም ብሎ የጨረሰው ቢሆንም በአንዳንድ ምክኒያቶች ግን ዘግየት ብሎ ሚያዝያ 6/2004 ዓ.ም ገበያ ላይ ሊውል ችሏል። አልበሙ ገበያ ላይ በዋለበት ግዜም በፍጥነት ከተማው ላይ በተለያዩ ድርጅቶች እና አትርፎ ሻጮች ምክኒያት ተዳርሷል። በተለያዩ ክልሎችም እንዲሁ! /አሳታሚው ድርጅት ካቀደው በላይ በፍጥነት ተሸጦ ነበር። 300,000 CD 'ና ከ120,000 ካሴት በላይ ተባዝቶ ነበር ገበያ ላይ የዋለው!/ በሳምን ውስጥም ከአስር ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ ተችሏል። ዋናው የውል ተፈራራሚው አዲካ ሲሆን ካሴቱን በ 17.50 ሳንቲም ለአከፋፋይ ድርጅቶች አስረክቦ ተረካቢዎችም በ25 ብር ገበያ ላይ አውለውታል... አዲካም በሳምንት ውስጥ ድርሻውን 6.3 ሚሊየን ብር ወስዶ ቀሪው በጋራ ለሰሩ ለአከፋፋይ የሙዚቃ ድርጅቶች ገቢ ሆኗል።

ይህ አልበም በወጣበት ግዜ የኢትዮጲያ የሙዚቃ ገበያ ደረጃው በጣም ከፍ ብሏል /ከዚህ ቀደም ማንኛውም ሙዚቀኛ ባልሸጠበት ዋጋ ሊሸጥ ችሏል።/ የማንም አርቲስት በሳምንት ውስጥ ይህን ያህል እትም አልተሸጠለትም ነበር #ጥቁር_ሰው ግን በወጣ የመጀመሪያው ሳምንት ውስጥ በፍጥነት ይህን ያህል ሔደ......የዕልፍ ሚዲያዎችም መነጋገሪያም ሆኗል። ይኼንን ወሰን ዳግም መስበር የቻለው የራሱ የቴዲ አፍሮ #ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበሙ ሲሆን ኢትዮጵያ አልበም በመጀመሪያ ዙር እትም ከ500 ሺህ በላይ ሲዲዎች በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ከገበያ ላይ አልቀው ነበር።

#ጥቁር_ሰው የተሰኘው አልበም ቀድሞ ተሰይሞለት የነበረው ሌላ ስም ቢሆንም በአንዳንድ ምክኒያቶች ከተቀነሱ ሙዚቃዎች ጋር ተያይዞ ስሙ አሁን ወዳላበት ሊፀና ችሏል። አልበሙ ውስጥ የተካተቱት ሙዚቃዎች ከሃያ ሙዚቃዎች መሃል ተመርጠው የወጡ ሙዚቃዎች ናቸው። /ሞልተው ከተረፉ ስራዎች መሃል/ ይህ ደግሞ ቴዲ አፍሮ ሁሌም በስራው ዝግጁ መሆኑን ያሳያል።

ስለ #ያስተሰርያል እና ስለ #ጥቁር_ሰው አልበም አርቲስት መስፍን አበበ ሲመሰክር "ቴዲ ካንድም ሁሌቴ ገበያውን ተቆጣጥሮታል" ብሏል.... ይህ አልበም በወጣበት ወቅት ቴዲ አፍሮ እንደ አንድ አድማጭ ሆኖ የሰውን የልብ ትርታ መስማት እንዳሻውም ተናግሮ ነበር ቢሆንም ግን ያሰበውን ያህል ግዜ አድማጭ ሆኖ መቆየትን አልቻለም። ብዙ ድርጅቶች የኮንሰርት ውል ይዘው ባጨናነቁት ግዜ አፍሪካ ላይ ተሰርቶ የአፍሪካ ምድር የተናወጠችበትን ስራውን ይዞ ዓለምን በኃይል ሊያናውጣት ታሪክና ፍቅርን ህብረት እና ተስፋን በአንድ ያመቀውን አልበሙን ይዞ ወደ መድረክ ብቅ አለ! እውነት ወዳጆቹ ተደሰትን ሙዚቃውንም እየሰማን ተማረክን እስከ ዛሬም ስናደምጣቸው ቆይተናል! ግን አሁንም ለኛ አዲስ ናቸው።

#ጥቁር_ሰው አልበም ለተከታታይ ዘጠኝ /፱/ አመታቶች የኛንም ስሜት መቆጣጠር ችሏል። በከፍተኛ በጀት ወደ ህዝቡ የደረሰው አልበም ሚያዝያ 6/2013 ዓ.ም ዘጠነኛ አመቱን ይይዛል። መልካሙንም ክፉውንም ነገር አልፎ ለዚህ የበቃው #ጥቁር_ሰው አልበም ለኛ ለሁላችን ኩራታችን ነውና መልካም የዘጠነኛ ዓመት በዓሉን አስበን ልንውል ስለወደድን ይህችን ጦማር አዘጋጀን።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
@
ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የተሰኘው ነጠላ ዜማ በቴዲ አፍሮ ህጋዊ የዩትዩብ ቻናል ከተለቀቀ ዛሬ አራተኛ አመቱን ደፈነ። ይኼ ሙዚቃ ሚያዝያ 7/2009 ዓ.ም ምሽት ላይ ነበር የተለቀቀው። በተለቀቀ በሰዓታት ውስጥ ግን ድፍን አዲስ አበባ በዚህ ሙዚቃ ዳንኪራ ስትረግጥ አምሽታለች። ከተማይቱ አዲስ ዘመንን የምታከብር ያህል በየ ስፍራው እንደ ብሔራዊ መዝሙር ይኼ ሙዚቃ ብቻ ሲደመጥ አነጋ... በዕለቱ በተለያዩ ስፍራዎች እየተዘዋወርኩ ለሊቱን ሙሉ ስሜቱን ለማጣጣም የሞከርኩ ሲሆን በየ ቦታው የሚታየው የህዝቡ ስሜት እጅግ ልዩ ነበር። ዘፈነ ከተለቀቀ በአራት አመታት ውስጥ በዩትዩብ ብቻ 20 ሚልየን አድማጭን አግኝቷል። ይኼ ደግሞ በኢትዮጵያ ያለ ተንቀሳቃሽ ምስል ብዙ ተመልካቾችን ያገኘ የመጀመሪያው ነጠላ ዜማ ነው። ሊንኩን ተጭነው ኢትዮጵያ የተሰኘውን ዜማ ያድምጡ ሌሎችም ዕለቱን በድምቀት እንዲያሳልፉ ሼር ያድርጉላቸው!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

https://youtu.be/VsrL9Rz-A5A
ቴዲ አፍሮን የቅርብ ጎደኞቹ ሊጋባው እንደሚሉት ያውቃሉ..? ሊጋባው ማናቸው..? ለምንስ ጓደኞቹ ቴዲ አፍሮን ሊጋባው ይሉታል..?
"እንደኮራ ሞተ እንደተጀነነ
ጠጅ ጠጣ ቢሉት ውሃ እየለመነ
የጎንደሩ ባላባት ሊጋባው በየነ.."

እንግዲህ ሊጋባው በየነ የቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ሹም ሲሆኑ ከንጉሡ ጋ በተደጋጋሚ በመጋጨታቸው በተደጋጋሚ በግርፋት የተቀጡ ሲሆን ለእስር ተዳርገው ነበር። ከእስር በምህረት በተፈቱ ጊዜ ጎንደርን ያስተዳድሩ ተብለው ጎንደርን ቢሰጧቸው ላሰረኝ መንግስት አላገለግልም በማለት ሹመታቸውን ገፉት። ጮማ እየቆረጡ ጠጅ እየተጎነጩ እንደ ሹመኛ መኖር አላጓጓ አላቸው። ክብር በለጠባቸው። በስተመጨረሻ ግን ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ በኢጣሊያ ስትወረር አገሬን ብለው ተነሱ። በጦር ሜዳም እየተዋጉ ሞቱ። ያኔ ነው ህዝቡ ይህን ግጥም የገጠመላቸው...

"እንደኮራ ሞተ እንደተጀነነ
ጠጅ ጠጣ ቢሉት ውሃ እየለመነ
የጎንደሩ ባላባት ሊጋባው በየነ.."

ታዲያ ቴዲ አፍሮ ለምን ሊጋባው ተባለ..? የሚል አካል ቢመጣ በውስጡ ያለው ፅናት እስከሞት መሆኑን በማስመስከሩ ነው። ሊጋባው በየነ ሹመታቸውን ተቀብለው መንግስት የማዳከም እድላቸውን መጠቀም ይችሉ ነበር... በተንኮል የሚደርሳቸውም አልነበረም። ዳሩ ግን ክብራቸውን አስቀደሙ... ቴዲ አፍሮም እንዲያው አደረገ..! የደላቸው በሚሊኒየም አዳራሽ ዳስ ጥለው ውስኪ ደርድረው ሲጠብቁት ብርድ ሳያሰጋቸው በአዲስ አበባ ስታዲየም እሱን ወደሚጠብቁት አመራ። መድረካቸው ደምቆ የኮንሰርት ክልከላ ከማያጋጥማቸው ሰዎች ጋ ተቀላቅሎ ሳንቲም ከመልቀም ይልቅ በግፍ ለምትታመሰው ኢትዮጵያ መጮኽን መረጠ።

ቴዲ አፍሮ እንደ ሊጋባው ኮርቶና ተጀንኖ ያልፋል እንጂ እራሱን አስገምቶ ኪሱን ለመሙላት አይዳዳውም። በመንግስት የግንብ ቅጥር ውስጥ ሳይሆን በድኃ ህዝብ ዳስ ውስጥ ይሞቀኛል ብሎ ያምናል። አካል ከሚያስር መንግስት ይልቅ ልብን በፍቅር የሚያስር ህዝብ ያስፈራኛል። ሚሊየኖችን አፍስሶ ንዋይ ከሚቸረኝ መንግስት በላይ የኛ ነህ ብሎ የሚኮራብኝ ድኃ ህዝቤ ይልቅብኛል በማለት ህዝቡን አብልጦ ከህዝብ ወግኖ ይኖራል።

#ሊጋባው /#ቴዲ_አፍሮ/

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
እረፍት አጣሁና ያንቺን ሰላም በመራቤ
ባየሽኝ ሰሞኑን ታሞልሻል ልቤ....!
እረፍት አጣሁ እኔ፤ ያንቺን ስቃይ በመስማቴ
ባየሽኝ ሰሞኑን አቃተኝ እናቴ!
💔 💔 💔

#ታሞልሻል_ልቤ

በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ስላለው ማብቂያ የሌለው መከራ ከልብ እናዝናለን! አሁንም በአገራችን ጉዳይ ስሙ ቅዱስ የሆነ አባታችን እግዚአብሔር ጣልቃ ይገባበት ዘንድ ጩኸታችን ሁሉ ወደ እርሱ ነው። #ቀላል_ይሆናል! ህዝበ እስራኤልን ከፈርኦን እጅ ነፃ ያወጣ የከነዓን ምድር ያወረሰ ያ ሀያል አምላክ ዛሬም በዝፋኑ አለ። እኛም የህልማችንን ከንዓን እንወርሳለን። ምክኒያቱም ያ አምላክ ዛሬም ይፈርዳል! ዛሬም ይሰራል። በፊቱ ኃይለኛ የለም። በፊቱ ትልቅ ወይም ግዙፍ የለም። አይኖርምም። የሚሳነውና የሚያቅተው አንዳችም የለም። ዘመኑ የእርሱ ነው።

"...ኢትዮጵያ ታበጽሕ እደዊሃ ኀበ እግዚአብሔር..."

@Teddyafronet

💚💛❤️
Teddyafro
«...ከምንም ያልተናነሰ ሃጥያት ለሰው በጎ አለማሰብና ምቀኝነት ነው። ያለን የሚበረክትልን ጥሩ ለማያስብልን ጥሩ ስናስብለት ነው።» #ቴዲአፍሮ®

💚💛❤️
Ťâťä Ä£ŕø
ደራሲ እና ተዋናይ መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን።

የአርቲስት መስፍን ጌታቸውን ነፍስ ከጻድቃን ጋ እንዲያሳርፍልን እንመኛለን!

ነፍሥ ይማር!
Ťâťä Ä£ŕø
ስቅለት
እንኳን ለጌታችንና አምላካችን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ከስቅለት ቀኑ ቀድሞ ባለው ቀን ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት። ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና፥ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት፥ አስረው ሲደበድቡት አድረዋል።

ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት። ምራቃቸውን ተፉበት። ዘበቱበት። ራሱንም በዘንግ መቱት። እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ።

በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት። በሠለስት (ሦስት ሰዓት ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት። ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት።

ስድስት ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች አምስት ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት። ሰባት ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ።
ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ሰባት ቃላትን ተናገረ።

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባሕርይ ሥልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ። አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት።

በዚያች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ። ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ። ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ። (ማቴ. 27:1, ማር. 15:1, ሉቃ. 23:1, ዮሐ. 19:1)

ጌታችን በመስቀል ላይ የተናገራቸው ፯ቱ /7/ የመስቀል ቃላት

፩. "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" (ሉቃስ ፳፬፥፴፬ /24፥34)/
፪. "እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከኔ ጋር በገት ትኖራለህ" (ሉቃ ፳፫፥፬ / 23፦4/)
፫. "እነሆ ልጅሽ እነኋት እናትህ" (ዮሐ. ፲፱፥፳፩-፳፮ /19፥21-26)
፬. "አምላኬ አምላኬ ስለምን ተውከኝ?" (ማቴ. ፲፯፥ ፵፮ /17፦46/)
፭. "ተጠማሁ" ዮሐ ፲፱፥፳፰ ( 19፦28)
፮. "ሁሉ ተፈጸመ" ዮሐ. ፲፱፥፴ /19፦ 30/)
፯. "አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ" (ሉቃ.፳፫፥፵፮ /23፦ 46/)

ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ የታዩ ተአምራት የሚከተሉት ናቸው።

በሰማይ
፩ . ፀሐይ ጨለመች
፪. ጨረቃ ደም ሆነች
፫. ከዋክብት ረገፉ

በምድር ደግሞ ማቴ. 27፦51_53/

፩. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀደደ
፪. ምድር ተናወጠች
፫. መቃብሮች ተከፈቱ
፬. ሙታን ተነሱ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በስቅላት በሞት ከፈረዱበት በኋላ ብዙ ጊዜ የሚከተሉት ነገሮች ይፈጸሙበት ነበር።

፩፦ ከመሰቀሉ በፊት ይገረፋል (ማቴ 27፤26
፪፦ መስቀሉን ወይም የመስቀሉን ግንድ ተሸክሞ ከከተማ ወደ ውጭ ወዳለው መስቀያ ቦታ ይወሰዳል (ዮሐ 19፤17
፫፦ በምሳሌ 31፤6 የተጻፈውን በማሰብ በኢየሩሳሌም የነበረ የሴቶች ማህበር የስቃይ ማደንዘዣ መጠጥ ለሚሰቀሉት ይሰጣል (ማቴ 27፤34
፬፦ በመስቀል ላይ ይቸነከራል ወይም በገመድ ይታሰራል (ዮሐ 20፤25
፭፦ ከበደለኛው ራስ በላይ የሟቹ ወንጀል ተጽፎ ይለጠፋል (ዮሐ 19፤19
፮፦ የተሰቀለውን ሰው ልብስ ወታደሮች እንዲካፈሉት ያደርጋል (ዮሐ 19፤23
፯፦ የተሰቀለው ሰው የሚሞተው ደሙን በማፍሰስ ሳይሆን በልቡ ድካም ነው። የሚሰቀለው ሰው ብዙ ጊዜ በሁለተኛው ወይም ሦስተኛው ቀን ይሞታል (ማር 15፤44) ወዳጆች እንዳያወርዱት መስቀሉ በወታደሮች ይጠበቃል። ተሎ እንዲሞት ሲፈልጉ እግሮቹን ይሰብሩ ነበር። ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ግን ጎኑን ወጉት (ዮሐ 19፤31 ይቆየን….በሰማይ፤ /ማቴ 24፦29 እና 27፦45/

ቸሩ እግዚአብሔር ከጾሙ በረከትን ያሳድርብን። ጾሙ የሐጥያት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ ያድርግልን አሜን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ለእኛ ለኀጥአን ፍጡሮቹ ሲል ይህንን ሁሉ መከራ የታገሰ አምላክ ስለ አሥራ ሦስቱ ኅማማቱ፥ አምስቱ ቅንዋቱ፥ ስለ ቅዱስ መስቀሉ፥ ስለ ድንግል እናቱ ለቅሶና ስለ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስ ብሎ ይማረን።

መድኃኔዓለም ከወዳጆቹም ጸጋ ክብርን ያድለን።

"የተጠራችሁለት ለዚህ ነው። ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏልና። እርሱም ኃጢአት አላደረገም። ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም። ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም። መከራንም ሲቀበል አልዛተም. . . እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ::"
(፩ጴጥ. ፪፥፳፩-፳፭)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
2025/07/04 15:29:06
Back to Top
HTML Embed Code: