#Oromia: በኦሮሚያ ክልል በአዲስ መልክ ለተደራጁ የቀበሌ መዋቅሮች 6 ሺህ 800 የሞተር ብስክሌቶች ተከፋፍሏል።
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ የሞተር ብስክሌቶቹ በቀበሌ መዋቅር የመንግሥት አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚሰራውን ሥራ የሚያግዙ በመሆኑ በአግባቡ ለተፈለገው ዓላማ እንዲውሉ አስገንዝበዋል። [OBN]
@TikvahethMagazine

👎67👍66❤18🤔11
#እንድታውቁት
ከዚህ ቀደም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሳይኖራችሁ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላችሁ ግብር ከፋዮች ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራችሁን ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በአካል መሔድ ሳይጠበቅባችሁ https://mor-migration.fayda.et በመጠቀም ማያያዝ የሚቻል መሆኑን የብሔራዊ መታወቂያ አስታውቋል።
እስካሁን በኢትዮጵያ ከ25 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በፋይዳ አገልግሎት መመዝገብ ተችሏል ሲባል ከ91 በላይ ተቋማት ጋርም ትስስር ተፈጥሯል።

❤24👎12👍3😢1
ባለ 15 ወለል የሲኒማ ኮምፕሌክስ በመዲናዋ በዛሬው ዕለት ሥራ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
በ24,000 ካ.ሜ ላይ ያረፈው "አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ" ባለ አራት ወለል የመኪና ማቆሚያ 592 ህፃናትንና 887 አዋቂዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት የሲኒማ አዳራሾችን ከሙሉ መገልገያዎች ጋር የያዘ ነው ተብሏል።
ከተማ አስተዳደሩ በቅርብ ጊዜ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስን አስመርቆ እንደነበር ይታወሳል።

❤114👍27👎14🤔14😢3
🤙 ኑሮዎን ፒያሳ ላይ ያድርጉ
➣ ውብ አፓርትመንቶቻችን ለኑሮ ምቹ በሆነችው አዲሲቷ ፒያሳ ላይ እርሰዎን ይጠብቃል
66 ካሬ ባለ 1 መኝታ
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ 6,072,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
➣ 100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 5,313,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
2 መኝታ 75 ካሬ
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ
6,900,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
➣ 100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 6,037,500 ብር ጠቅላላ ዋጋ
3 መኝታ 106 ካሬ
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ 9,752,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
➣100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 8,533,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
❗️ልብ ይበሉ ከላይ የተፃፉት አነስተኛ ካሬዎች ለ ምሳሌ ሲሆኑ ከፍ ያለ ካሬ ማግኜት ትችላላችሁ
ለበለጠ መረጃ
👇
☎️+251986687513
WhatsApp:- +251986687513
Email:- [email protected]

❤18👍1
ፓኪስታንን በአዲስ አበባ
ከ 100 በላይ የፓኪስታን ካምፓኒዎችን በአንድ ቦታ ሊያገኟቸው ነው!
5ኛው የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤ እና ኤግዚቢሽን ከጥቅምት 6-8 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል::
የመድኃኒት ምርቶች እና የህክምና መሣሪያዎች፣ የውበት እና የቆዳ እንክብካቤ ውጤቶች፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ የምግብ እና የግብርና ምርቶች (ሩዝ, ቅመማ ቅመሞች) ፣ የአውቶሞቲቭ መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የቤት እቃዎች
እና ሌሎችንም ን ምርቶች የሚያስመጡ ወይም የሚያከፋፍሉ ከሆነ ይህ እድል በፍፁም እንዳያመልጥዎት!!
ቀኑን ያስታውሱ ከጥቅምት 6-8 በሚሊኒየም አዳራሽ!!
ለበለጠ መረጃ www.pakafricaconnect.com ድህረገፃችንን ይጎብኙ

❤15👍2
በአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከ2 ሚሊዮን 500 ሺህ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባል በማድረግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን ገልጿል።
የዘንድሮው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን የአባልነት ምዝገባ የገቢ መጠንን መሰረት ያደረገ የአከፋፈል ሥርዓት እንደሚከተል ተነስቷል።
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በዓመት አንድ ጊዜ በሚዋጣ ገቢን መሰረት ያደረገ መዋጮ ራስን እና ቤተሰብን ከድንገተኛ እና ካልታሰብ ወጪ በመታደግ መታከም የሚቻልበት ሥርዓት ነው።
ነዋሪዎች በተተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በሚቀርባቸው ጤና ጣቢያ ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ ቀርቧል።
በ2017 ዓ.ም ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ ባሉ የመንግስት ጤና ተቋማት ተጠቃሚ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በዚህም ማህበረሰብ ከሚሰበሰበው መዋጮ በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም ብቻ ለአገልግሎቱ 1.3 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል ተብሏል፡፡
ምንጭ : ጤና ቢሮ ፤ ሸገር ኤፍ ኤም

❤43👍10🙏3🤯1
ፔንታጎን አዲስ አዲስ የፕረስ ፖሊሲ ቢያወጣም ከ30 በላይ የዜና ተቋማት ውድቅ አድርገውታል።
ሮይተርስ፣ ኤፒ፣ ሲኤንኤን እና ዘ ኒውዮርክ ታይምስን ጨምሮ ከ30 በላይ የአሜሪካ የሚዲያ ድርጅቶች የፕሬስ ነፃነትን ይገድባል ያሉትን አዲስ የፔንታጎን የፕሬስ ፖሊሲ ውድቅ አድርገዋል።
ፖሊሲው ሚስጥራዊ የተደረጉ እንዲሁም አንዳንድ ሚሥጥራዊ ያልሆኑ መረጃዎች ጭምር ላይ ገደቦችን ያስቀመጠ ነው።
በዚህም ጋዜጠኞች በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ መጠየቅም ሪፖርት መስራትም አይፈቀድላቸውም፤ ምሥጢራዊ ባይሆንም የደኅንነት ችግር አለው የተባለን ጉዳይ መዘገብ አይችሉም፤ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ መጠየቅ ጭምር ይከለክላል።
ጋዜጠኞች የፔንታጎን ጋዜጣዊ መግለጫ ለመታደም በተዘጋጀው የስምምነት ፎርም ላይ እንዲፈርሙ ይጠየቃሉ። ይህንን የጣሱ ጋዜጠኞች እንደ "ደኅንነት ሥጋት" ይቆጠራሉ፤ መግቢያቸው ይቀማል፤ የሚዲያ ተቋማቸውም ቀጣይ ይህንን መብት ሊነጠቅ ይችላል።
ፔንታጎን ህጎቹ የብሄራዊ ደኅንነትን ይከላከላሉ ሲል እና የሚዲያ ባለሞያዎች ይህ አዲሱ የሳንሱር መንገድ ነው፤ የሚዲያ ነጻነትንም የሚጋፋ እና የሚገድብ ነው አልፎም ግልፅነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

3❤54🤣11👍4🤔2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ መጀመሩን መጀመሩን ገልጿል።
አየር መንገዱ ከዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ጀምሮ በየቀኑ ወደ ፖርት ሱዳን (PZU) በረራ እንደሚያደርግ ነው ያስታወቀው።
ይህንን በረራ ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ጀምሮ የቀን የበረራ መጠኑን በእጥፍ እንደሚያሳድግም ነው የገለጸው።

❤37🤔9
#ጥቆማ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለ50 አዲስ ተመራቂዎች የሥራና የሥራ እድል አቅርቧል።
ኩባንያው ግራጁዌት ማኔጅመንት ትሬኒ (Graduate Management Trainee) በተሰኘው ፕሮግራምሙ ባለፉት 12 ወራት ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ባላቸው የትምሀርት መስኮች ያጠናቀቁ ተማሪዎችን አወዳድሮ በቴሌኮም ዘርፍ የፕሮፌሽናል እውቀትና እድገት እድል እንዲያገኙ እንደሚያግዝ ገልጿል።
ለምዝገባ ብቁ የሚሆኑ ተማሪዎች ውጤታቸው 3.5 እና ከዚያ በላይ መሆን እንደሚጠበቅበት አስታውቆ አስፈላጊው ማጣራትና ሌሎች ግልጽ የመለያ ሂደቶችን ያለፉ 50 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እድሉን ያገኛሉ ብሏል።
እድሉ ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ምዝገባው የሚቆየው እስከ ጥቅምት 07/ 2018 ዓ.ም ወይም (17/10/2025, 11:55 PM) ብቻ ይሆናል።
ለመመዝገብ https://egjd.fa.us6.oraclecloud.com/hcmUI/CandidateExperience/en/sites/STEP/job/932

❤58🤔3👎2