ባለ 15 ወለል የሲኒማ ኮምፕሌክስ በመዲናዋ በዛሬው ዕለት ሥራ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
በ24,000 ካ.ሜ ላይ ያረፈው "አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ" ባለ አራት ወለል የመኪና ማቆሚያ 592 ህፃናትንና 887 አዋቂዎችን የመያዝ አቅም ያላቸው ሁለት የሲኒማ አዳራሾችን ከሙሉ መገልገያዎች ጋር የያዘ ነው ተብሏል።
ከተማ አስተዳደሩ በቅርብ ጊዜ የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርና ሲኒማ ኮምፕሌክስን አስመርቆ እንደነበር ይታወሳል።
@TikvahethMagazine

❤113👍26👎14🤔14😢3
🤙 ኑሮዎን ፒያሳ ላይ ያድርጉ
➣ ውብ አፓርትመንቶቻችን ለኑሮ ምቹ በሆነችው አዲሲቷ ፒያሳ ላይ እርሰዎን ይጠብቃል
66 ካሬ ባለ 1 መኝታ
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ 6,072,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
➣ 100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 5,313,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
2 መኝታ 75 ካሬ
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ
6,900,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
➣ 100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 6,037,500 ብር ጠቅላላ ዋጋ
3 መኝታ 106 ካሬ
➣ 40% ሲከፍሉ 20% ቅናሽ 9,752,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
➣100% ለከፈለ 30% ቅናሽ 8,533,000 ብር ጠቅላላ ዋጋ
❗️ልብ ይበሉ ከላይ የተፃፉት አነስተኛ ካሬዎች ለ ምሳሌ ሲሆኑ ከፍ ያለ ካሬ ማግኜት ትችላላችሁ
ለበለጠ መረጃ
👇
☎️+251986687513
WhatsApp:- +251986687513
Email:- [email protected]

❤18👍1
ፓኪስታንን በአዲስ አበባ
ከ 100 በላይ የፓኪስታን ካምፓኒዎችን በአንድ ቦታ ሊያገኟቸው ነው!
5ኛው የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤ እና ኤግዚቢሽን ከጥቅምት 6-8 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል::
የመድኃኒት ምርቶች እና የህክምና መሣሪያዎች፣ የውበት እና የቆዳ እንክብካቤ ውጤቶች፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ የምግብ እና የግብርና ምርቶች (ሩዝ, ቅመማ ቅመሞች) ፣ የአውቶሞቲቭ መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የቤት እቃዎች
እና ሌሎችንም ን ምርቶች የሚያስመጡ ወይም የሚያከፋፍሉ ከሆነ ይህ እድል በፍፁም እንዳያመልጥዎት!!
ቀኑን ያስታውሱ ከጥቅምት 6-8 በሚሊኒየም አዳራሽ!!
ለበለጠ መረጃ www.pakafricaconnect.com ድህረገፃችንን ይጎብኙ

❤15
በአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከ2 ሚሊዮን 500 ሺህ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባል በማድረግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻሉን ገልጿል።
የዘንድሮው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን የአባልነት ምዝገባ የገቢ መጠንን መሰረት ያደረገ የአከፋፈል ሥርዓት እንደሚከተል ተነስቷል።
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን በዓመት አንድ ጊዜ በሚዋጣ ገቢን መሰረት ያደረገ መዋጮ ራስን እና ቤተሰብን ከድንገተኛ እና ካልታሰብ ወጪ በመታደግ መታከም የሚቻልበት ሥርዓት ነው።
ነዋሪዎች በተተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በሚቀርባቸው ጤና ጣቢያ ከጥቅምት 1 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ ቀርቧል።
በ2017 ዓ.ም ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ ባሉ የመንግስት ጤና ተቋማት ተጠቃሚ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በዚህም ማህበረሰብ ከሚሰበሰበው መዋጮ በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም ብቻ ለአገልግሎቱ 1.3 ቢሊዮን ብር ድጎማ አድርጓል ተብሏል፡፡
ምንጭ : ጤና ቢሮ ፤ ሸገር ኤፍ ኤም

❤42👍10🙏3🤯1
ፔንታጎን አዲስ አዲስ የፕረስ ፖሊሲ ቢያወጣም ከ30 በላይ የዜና ተቋማት ውድቅ አድርገውታል።
ሮይተርስ፣ ኤፒ፣ ሲኤንኤን እና ዘ ኒውዮርክ ታይምስን ጨምሮ ከ30 በላይ የአሜሪካ የሚዲያ ድርጅቶች የፕሬስ ነፃነትን ይገድባል ያሉትን አዲስ የፔንታጎን የፕሬስ ፖሊሲ ውድቅ አድርገዋል።
ፖሊሲው ሚስጥራዊ የተደረጉ እንዲሁም አንዳንድ ሚሥጥራዊ ያልሆኑ መረጃዎች ጭምር ላይ ገደቦችን ያስቀመጠ ነው።
በዚህም ጋዜጠኞች በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ መጠየቅም ሪፖርት መስራትም አይፈቀድላቸውም፤ ምሥጢራዊ ባይሆንም የደኅንነት ችግር አለው የተባለን ጉዳይ መዘገብ አይችሉም፤ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ መጠየቅ ጭምር ይከለክላል።
ጋዜጠኞች የፔንታጎን ጋዜጣዊ መግለጫ ለመታደም በተዘጋጀው የስምምነት ፎርም ላይ እንዲፈርሙ ይጠየቃሉ። ይህንን የጣሱ ጋዜጠኞች እንደ "ደኅንነት ሥጋት" ይቆጠራሉ፤ መግቢያቸው ይቀማል፤ የሚዲያ ተቋማቸውም ቀጣይ ይህንን መብት ሊነጠቅ ይችላል።
ፔንታጎን ህጎቹ የብሄራዊ ደኅንነትን ይከላከላሉ ሲል እና የሚዲያ ባለሞያዎች ይህ አዲሱ የሳንሱር መንገድ ነው፤ የሚዲያ ነጻነትንም የሚጋፋ እና የሚገድብ ነው አልፎም ግልፅነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲሉ ገልጸዋል።

3❤52🤣11👍4🤔2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ መጀመሩን መጀመሩን ገልጿል።
አየር መንገዱ ከዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ጀምሮ በየቀኑ ወደ ፖርት ሱዳን (PZU) በረራ እንደሚያደርግ ነው ያስታወቀው።
ይህንን በረራ ከጥቅምት 22 ቀን 2018 ጀምሮ የቀን የበረራ መጠኑን በእጥፍ እንደሚያሳድግም ነው የገለጸው።

❤35🤔9
#ጥቆማ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለ50 አዲስ ተመራቂዎች የሥራና የሥራ እድል አቅርቧል።
ኩባንያው ግራጁዌት ማኔጅመንት ትሬኒ (Graduate Management Trainee) በተሰኘው ፕሮግራምሙ ባለፉት 12 ወራት ከዘርፉ ጋር ግንኙነት ባላቸው የትምሀርት መስኮች ያጠናቀቁ ተማሪዎችን አወዳድሮ በቴሌኮም ዘርፍ የፕሮፌሽናል እውቀትና እድገት እድል እንዲያገኙ እንደሚያግዝ ገልጿል።
ለምዝገባ ብቁ የሚሆኑ ተማሪዎች ውጤታቸው 3.5 እና ከዚያ በላይ መሆን እንደሚጠበቅበት አስታውቆ አስፈላጊው ማጣራትና ሌሎች ግልጽ የመለያ ሂደቶችን ያለፉ 50 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች እድሉን ያገኛሉ ብሏል።
እድሉ ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ምዝገባው የሚቆየው እስከ ጥቅምት 07/ 2018 ዓ.ም ወይም (17/10/2025, 11:55 PM) ብቻ ይሆናል።
ለመመዝገብ https://egjd.fa.us6.oraclecloud.com/hcmUI/CandidateExperience/en/sites/STEP/job/932

❤56🤔3👎2
#AksumUniversity
በአክሱም ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት ዛሬ ቀን 5/2/2018 ዓ/ም ከሰዓት 7:30 ገደማ አከባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
በእሳት አደጋው በሆስፓታሉ የሚገኝ ዋና መድኃኒት መጋዘን /Main Pharmacy Store የነበሩ በሚልዮኖች የሚገመቱ የህክምና መሳርያዎችና ግብዓቶች ወድሟል ተብሏል።
እስት አደጋዉ በየዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችና ፣ የጤና ሳይነስ ተማራዎች፣ የአክሱም ከተማ ፀጥታ አበለት፣ የአክሱም ከተማ ማዛጋጃ ቤት፣ የአክሱም ከተማ ወጣቶች፣ ፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እሳት አደጋ ሰራተኞች በመሆን አደጋውን ተቆጣጥረዋል።
የአደጋዉ መንሰኤ በመጣራት ላይ ይገኛል ተብሏል።

😢112❤56🤣9👍3🕊2
አዲሷን ጀንበር
በአዲሷ ካዛንቺስ መንደር ‼️
የሚመኙት ያማረ ነገዎ
እውን ይሆን ዘንድ‼️
እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች
ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ 80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ 95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ 140 ,160 ካ.ሜ
✍ ቅድመ ክፍያ 10%
❇️ በ 24 ወራት የሚረከቡት ቤት💁
📍በግቢው ውስጥ
➾ ት/ቤት እና የጤና ማዕከል
➾ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ መጫወቻ
➾መዋኛ ገንዳ
➾የሳይክል እና የእግር ሽርሽር ስፍራዎች
➾ሰፊ የመኪና መቆሚያ ከ24/7 ጥበቃ ጋር
➾የመኪና ቻርጀር ስፍራዎች
SHARE" @tegegnemelak
SHARE" @tegegne9752
Contact us:@tegegne123
📞09 44 85 67 35
09 67 76 97 52
በአዲሷ ካዛንቺስ መንደር ‼️
የሚመኙት ያማረ ነገዎ
እውን ይሆን ዘንድ‼️
እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች
ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ 80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ 95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ 140 ,160 ካ.ሜ
✍ ቅድመ ክፍያ 10%
❇️ በ 24 ወራት የሚረከቡት ቤት💁
📍በግቢው ውስጥ
➾ ት/ቤት እና የጤና ማዕከል
➾ እግር ኳስና ቅርጫት ኳስ መጫወቻ
➾መዋኛ ገንዳ
➾የሳይክል እና የእግር ሽርሽር ስፍራዎች
➾ሰፊ የመኪና መቆሚያ ከ24/7 ጥበቃ ጋር
➾የመኪና ቻርጀር ስፍራዎች
SHARE" @tegegnemelak
SHARE" @tegegne9752
Contact us:@tegegne123
📞09 44 85 67 35
09 67 76 97 52
❤15
ተከፈተ!!!
ከ120 በላይ የፓኪስታን ካምፓኒዎች ሚሊኒየም አዳራሽ ገብተዋል።በርካቶችም በቦታው በመገኘት የንግድ ትስስር ፈጥረዋል። ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን የመድኃኒት ምርቶች እና የህክምና መሣሪያዎችን፣ የውበት እና የቆዳ እንክብካቤ ውጤቶችን፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ የምግብ እና የግብርና ምርቶችን (ሩዝ, ቅመማ ቅመሞች) ፣ የአውቶሞቲቭ መለዋወጫዎችን፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን፣ የቤት እቃዎች እና ሌሎችንም ምርቶች የሚያመርቱ ካምፓኒዮች ይገኛሉ!! ይምጡ በነፃ ይሳተፉ!!
ለመሳተፍ በ https://pakafricaconnect.com/ ይመዝገቡ

❤9👍2
#ኢትዮኢስታንቡል
ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆነውና በህንድ አገር ከሚገኘው አፖሎ ሆስፒታል ጋር በትብብር መሥራት የሚያስችለውን ስምምነት ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረመ።
ስምምነቱ ከኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ዓላማዎች አንዱ የሆነውን ወደ ውጪ አገር የሚያስኬዱ ሕመሞችን ሕክምና በአገር ውስጥ መስጠትን መሰረት በማድረግ እንደ ካንሰር ያሉ ከፍተኛ ሕመሞች ያሉባቸውን ሕሙማን ወደ ህንድ አገር መላክ የመሰሉትን ያካተተ ነው።
እንዲሁም ሐኪሞች ከአፖሎ ሆስፒታል እየመጡ በኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ሕክምና መስጠት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ የተደረገና በውጪ አገር ታክመው የሚመጡትን ሕሙማን ቀጣይ የሕክምና ክትትልም በኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የገለፁት የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃን ተድላ ከአፖሎ ሆስፒታል ጋር በትብብር መስራቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግና ሐኪሞች የሥራ ላይ ሥልጠና እና የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙ ዕድል እንደሚሰጥም ጨምረው አመልክተዋል።
የአፖሎ ሆስፒታል ተወካዮችም በበኩላቸው
ስምምነቱ የሜዲካል ቱሪዝምን በኢትዮጵያ በሰፊው ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚን እንደሚፈጥርና በስምምነቱም ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ስምምነቱን የፈረሙት በኢትዮ ኢስታንቡል ጠ/ሆስፒታል በኩል ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ብርሃን ተድላ ሲሆኑ በአፖሎ ሆስፒታል በኩል ዶ/ር ፕራሳድ ናማኒ የኢንተርናሽናል ቢዝነስ ዴቬሎፕመንት ማኔጀር እና ዶ/ር አጂሽ ራጅ ከፍተኛ የቀዶ ጥገና ሐኪም ናቸው።

❤44👍8
እንግሊዝ ወደ ሀገሯ ለሥራ የሚገቡ የሌላ ሀገር ዜጎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ መስፈርቶችን ከፍ አደረገች።
እንግሊዝ ከአዲሱ የፈረንጆቹ 2026 ዓመት ጀምሮ ለአብዛኛዎቹ የስራ ቪዛዎች ብቁ ለመሆን ስደተኞች B2 ደረጃ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ወይም የተሻለ የመካከለኛ ደረጃ (Upper Intermediate ) ጋር ሊኖራቸው እንደሚገባ አስታውቃለች።
አዲሱ ህግ አሁን ያለውን የB1 ደረጃ የሚተካ ሲሆን ይህም ማለት አመልካቾች በመናገር፣ በማንበብ፣ በመፃፍ እና በማዳመጥ ጠንካራ የእንግሊዝኛ ችሎታዎችን ማሳየት አለባቸው።
ለውጡ በዋናነት በሰለጠነ ሰራተኛ እና በሌሎች የፕሮፌሽናል ቪዛ አማራጮች የሚያመለክቱ ሰዎችን ይመለከታል።
በዚህ መሰረት ከላይ የተጠቀሱትን ቪዛዎች ለማግኘት እንደ IELTS ባሉ ፈተናዎች 5.5–6.5 ማምጣት ይጠበቃል።
በመላው አፍሪካ ፖሊሲው ወደ እንግሊዝ የሚሰደዱ ሰራተኞችን ቁጥር እንደሚቀንስ እና ሀገራት የእንግሊዘኛ ትምህርት እና ስልጠናን እንዲያሻሽሉ ያበረታታል ተብሎ ታምኖበታል።

❤68👎26👍6🤔2🕊2
የኢትዮጵያ_የውጭ_ሀገር_ሥራ_ስምሪት_አፈጻጸምን_ለመደንገግ_የወጣ_መመሪያ.pdf
434.7 KB
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ማስፈፀሚያ ረቂቅ መመሪያ ላይ አስተያየት ተጠየቀ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 1389/2017 አንቀፅ 84(2) መሠረት የማስፈፀሚያ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ተሰጥቶታል።
በዚህ መሠረት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱን ማስተግበሪያ ረቂቅ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማንኛውም ዜጋ ወይም ድርጅት በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ ይህ ማስታወቂያ ከተወጣ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት አስተያየት እንዲቀርብ ጠይቋል።
ረቂቅ መመሪያውን ከላይ ተያይዟል።
አስተያየት ለመስጠትም የሚከተሉትን አድራሻዎች መጠቀም ይችላሉ ብሏል።
- [email protected] ወይም
- [email protected]

❤38🤔4👎1