Telegram Web Link
" እኛም ምርጥ ቡድን ነን " ኢንዞ ፈርናንዴዝ

የሰማያዊዎቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ቡድናቸው በራሱ እንደሚተማመን ከፍፃሜው ጨዋታ በፊት ተናግሯል።

“ ጠንካራ ቡድን እንደምንገጥም እናውቃለን “ ያለው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ለጨዋታው በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅተናል ብሏል።

አክሎም “ እኛ በራሳችን እንተማመናለን እኛም እንደ እነሱ ምርጥ ቡድን ነን " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🥰132😁8753👍22👎10
" ጨዋታው አያስፈራንም ለማሸነፍ እንጥራለን "

የሰማያዊዎቹ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማሎ ጉስቶ ቡድናቸው ጨዋታውን ለማሸነፍ መጣር እንዳለበት አሳስቧል።

" እኛ ቼልሲዎች ነን " የሚለው ተጨዋቹ እዚህ ያለነው ስለሚገባን ነው ጨዋታው ምንም አያስፈራንም በማለት ተናግሯል።

“ ለእኛ ጥሩ ፈተና ይሆናል አስፈላጊው ነገር ከዚህ ቡድን ጋር መፎከር እንደምንችል ማሳየት ነው “ ሲል ማሎ ጉስቶ ገልጿል።

" ለፍፃሜ መድረስ ብቻ በቂ አይደለም የፍፃሜ ጨዋታውን ለማሸነፍ መጣር አለብን “ ማሎ ጉስቶ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
140😁65👍9👏9🥰4🤩4🤬1
#ClubWorldCupFinal 🇺🇸

ቼልሲ በምሽቱ የክለቦች አለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ በጉዳት ምክንያት በግማሽ ፍፃሜው ያጣውን ሞይሰስ ካይሴዶ ግልጋሎት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

ሞይሰስ ካይሴዶ ከጉዳቱ በማገገም ወደ ልምምድ የተመለሰ ሲሆን በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘቱ ለሰማያዊዎቹ ጥሩ ዜና ሆኗል።

በተጨማሪም አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የአንድ ጨዋታ ቅጣታቸውን የጨረሱት ሊያም ዴላፕ እና ሌቪ ኮልዊል ወደ አሰላለፍ ይመለሱላቸዋል።

በሌላ በኩል አርሰናልን ለመቀላቀል የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው ኖኒ ማዱኬ በጨዋታው አይሳተፍም።

ኖኒ ማዱኬ በአሁኑ ሰዓት አርሰናልን ለመቀላቀል የሚያስችለውን የጤና ምርመራ ለማድረግ ለንደን ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
142👍21🔥8😁3
TIKVAH-SPORT
#ClubWorldCupFinal 🇺🇸 ቼልሲ በምሽቱ የክለቦች አለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ በጉዳት ምክንያት በግማሽ ፍፃሜው ያጣውን ሞይሰስ ካይሴዶ ግልጋሎት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ሞይሰስ ካይሴዶ ከጉዳቱ በማገገም ወደ ልምምድ የተመለሰ ሲሆን በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘቱ ለሰማያዊዎቹ ጥሩ ዜና ሆኗል። በተጨማሪም አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የአንድ ጨዋታ ቅጣታቸውን የጨረሱት ሊያም ዴላፕ እና ሌቪ ኮልዊል ወደ…
#ClubWorldCupFinal 🇺🇸

ፒኤስጂም ልክ እንደ ቼልሲ ሁሉ ሁለት ተጨዋቾቹን በቅጣት አጥቶ ነበር የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታውን ያደረገው።

ይሁን እንጂ ፒኤስጂ በቅጣት ያጣቸውን ዊሊያን ፓቾ እና ሉካስ ሄርናንዴዝ ግልጋሎት በዛሬው ፍፃሜ ጨዋታም አያገኝም።

ዊሊያን ፓቾ እና ሉካስ ሄርናንዴዝ በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በተመለከቱት ቀይ ካርድ ምክንያት ሁለት ጨዋታዎች መቀጣታቸው የሚታወስ ነው።

በግማሽ ፍፃሜው ለፒኤስጂ ጥሩ ዜና የነበረው ጉዳት ላይ የነበረው ኡስማን ዴምቤሌ ወደ ቋሚ አሰላለፍ መመለሱ ነበር።

ኡስማን ዴምቤሌ በዛሬው የፍፃሜ ጨዋታም በቋሚነት ለመጀመር ዝግጁ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
162👍13👎6🤔4👏1
በጨዋታው እረፍት ሰዓት ምን እንመለከታለን ?

በምሽቱ የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታ እረፍት ሰዓት የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚኖር የውድድሩ አዘጋጅ ፊፋ አሳውቋል።

በአለም እግርኳስ ታሪክ በእረፍት ሰዓት የሙዚቃ ድግስ እና ትዕይንት ሲቀርብ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚሆን ተገልጿል።

የሙዚቃ ትዕይንቱ በእረፍት ሰዓት ለዚሁ አላማ ተብሎ በሚዘጋጅ መድረክ ላይ እንደሚቀርብ ተነግሯል።

የስታዲየሙ መጫወቻ ሜዳ ለሁለተኛው አጋማሽ አደጋ እንዳይገጥመው በመስጋት ዝግጅቱ ሜዳው ላይ ላይሆን እንደሚችል ተነግሯል።

በጨዋታው ኮሎምቢያዊው ጄ ባልቪን ፣ አሜሪካዊቷ ዶዣ ካት ፣ ናይጄሪያዊቷ ቴምስ እና አውስትራሊያዊው ኢማኑኤል ኬሊ መድረኩን ያደምቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአሜሪካ ስፖርት ውስጥ የእረፍት ሰዓት ትዕይንት ማቅረብ የተለመደ ሲሆን ታዋቂው ሱፐር ቦውል የዚህ አንዱ ማሳያ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
👎9588😁16👏9👍6🤬2😱1
NUR TECHNOLOGIES

አዳዲስ እና ዱባይ ዩዝድ የሆኑ
HP
Lenovo
Dell
Microsoft Surface
Macbook
እና ሌሎችም ላፕቶፓችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከሙሉ ዋስትና ጋር ከኛ ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ ከስር የሚገኘውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/NurTechnologies
📞0911646359
አድራሻ - ቦሌ መድኃኒለም ሰላም ሲቲ ሞል ፊት ለፊት ለአሚር ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
16
ሊቨርፑል የወዳጅነት ጨዋታውን አሸነፈ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከፕሪስተን ጋር የቅድመ ውድድር ዝግጅት የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታውን አድርጎ 3ለ1 አሸንፏል።

ለሊቨርፑል የማሸነፊያ ግቦችን ብራድሌይ ፣ ዳርዊን ኑኔዝ እና ኮዲ ጋክፖ አስቆጥረዋል።

በጨዋታው በቅርቡ ህይወቱ ላለፈው የሊቨርፑል ተጨዋች ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ መታሰቢያ ተካሄዷል።

ሊቨርፑል ከአስር ቀናት በኋላ ከኤሲ ሚላን ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
237🥰12😁8👍7🔥6👎3🙏1
የውድድሩን የወርቅ ጫማ ማን ሊያሸንፍ ይችላል ?

በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ደረጃ ለብቻው ወጥቶ መምራት የቻለ ተጨዋች አልታየም።

አሁን ላይ አራት ተጨዋቾች በውድድሩ ባስቆጠሯቸው አራት ጎሎች የወርቅ ጫማውን ለማሸነፍ ፉክክሩን እየመሩ ይገኛሉ።

ይሁን አንጂ በዛሬው ፍፃሜ ጨዋታም የወርቅ ጫማውን ለማሸነፍ እድል ያላቸው ተጨዋቾች አሉ።

የፒኤስጂው ፋብያን ሩይዝ እና የቼልሲው ፔድሮ ኔቶ በፍፃሜው ግብ አስቆጥረው የወርቅ ጫማውን የማሸነፍ የተሻለ እድል ይኖራቸዋል።

ፉክክሩን እነማን ይመራሉ ?

4️⃣ ጎል :- ጎንዛሎ ጋርሺያ ፣ ማርኮስ ሊዮናርዶ ፣ ሴርሁ ጉራሲ እና አንሄል ዲማርያ

3️⃣ ጎል :- ፋብያን ሩይዝ እና ፔድሮ ኔቶ

2️⃣ ኡስማን ዴምቤሌ ፣ አሽራፍ ሀኪሚ ፣ ጇ ፔድሮ እና ጇ ኔቬዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
169👍7
#ClubWorldCupFinal 🇺🇸

በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ካየናቸው ፈጣሪ ተጨዋቾች መካከል ብዙዎቹ በሁለቱ የፍፃሜ ተፋላሚ ክለቦች ውስጥ ይገኛሉ።

በውድድሩ ጥሩ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ከየትኛውም ተጨዋች በበለጠ ሶስት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

አርጀንቲናዊው ኢንዞ ፈርናንዴዝ በውድድሩ ከአንድ በላይ ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ያቀበለ ብቸኛው የቼልሲ ተጨዋች ነው።

በፒኤስጂ በኩል አራት ተጨዋቾች በውድድሩ ሁለት ለግብ የሆነ ኳስ በማመቻቸት ቀጣዩን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥11255😁4👏1
ዩኤፋ በፊፋ ስራ ደስተኛ አለመሆኑ ተገለጸ !

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ለመገኘት አለመፈለጋቸው ተገልጿል።

በውድድሩ የሁሉም አህጉራት ፌዴሬሽኖች በፕሬዝዳንታቸው ቢወከሉም የዩኤፋው ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን ከውድድሩ መራቃቸው ተነግሯል።

ከፊፋ ጋር አለመግባባት ውስጥ መሆኑ ሲገለፅ የነበረ ዩኤፋ ፊፋ በክለቦች ውድድር ውስጥ ጣልቃ መግባቱ እንዳላስደሰታቸው ተገልጿል።

የዩኤፋ ሀላፊዎች ፊፋ የክለቦች አለም ዋንጫ ላይ እያደረገ ያለው ነገር በአለም የሚወደደውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ያደበዝዘዋል በሚል መስጋታቸው ተዘግቧል።

ፊፋ የክለቦች አለም ዋንጫን በሁለት አመት የማድረግ ሀሳብ ሊያመጣ እንደሚችል ሲገለፅ ነበር።

በተጨማሪም የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ በውድድሩ ሊቨርፑል ፣ ባርሴሎና ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ፣ አርሰናል እና ኤሲ ሚላን የመሳሰሉ ትልቅ ቡድኖችን መመልከት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
187😁37👍9👎5🔥2
አርሰናል የዮኬሬሽን ዝውውር ሊያጠናቅቅ ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የቪክቶር ዮኬሬሽን ዝውውር በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

መድፈኞቹ ከስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር የመጨረሻ ድርድር ካደረጉ በኋላ ዝውውሩን ወደ ማጠናቀቅ እየተቃረቡ መሆኑ ተነግሯል።

አርሰናል ለተጨዋቹ ያቀረበው የዝውውር ሒሳብ 70 ሚልዮን ዩሮ እና ተጨማሪ 10 ሚልዮን ዩሮ እንደሚጠጋ ተዘግቧል።

ተጨዋቹ በቀጣይ በአርሰናል የሚያቆየውን የአምስት አመት ኮንትራት እንደሚፈርም ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
491👍71😁35🔥21👎19👏12
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ቼልሲ ከ ፒኤስጂ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
124👍27🔥9🙏8
#ClubWorldCupFinal 🇺🇸

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ከሬስ ጄምስ እና ማሎ ጉስቶ አንዳቸውን ይመርጣሉ ተብለው ቢጠበቁም ሁለቱንም አሰልፈዋል።

በጨዋታው ማሎ ጉስቶ በቀኝ መስመር ተጨዋነት እንደሚያገለግል ሲጠበቅ ሬስ ጄምስ በመሐል ክፍሉ ከሞይሰስ ካይሴዶ ጋር ይጣመራል ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በጨዋታው በመሐል ክፍሉ ተጨማሪ ተጨዋች ማየት መፈለጋቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ አሰልጣኙ ሬስ ጄምስን ከወቅቱ ምርጥ ሶስት አማካዮች ጥምረት ፊት ማሰለፋቸው ለአደጋ ሊያጋልጣቸው እንደሚችል ተሰግቷል።

በግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ቋሚ አስራ አንድ ስብስብ ውስጥ የነበረው ክርስቶፈር ንኩንኩ ከምሽቱ ጨዋታ ውጪ ነው።

ይህንንም ተከትሎ ኮል ፓልመር በጨዋታው ወደ ቀኝ የፊት መስመር ቦታ ተስቦ እንዲጫወት ሚና ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
103😁15👍9🔥3
ፒኤስጂ የቼልሲን ሪከርድ ይገታ ይሆን ?

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች አምስት ግቦች ተቆጥረውበታል።

ይሁን እንጁ ቼልሲ በየትኛውም ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ግብ አልተቆጠረበትም።

ፒኤሴጂ በበኩሉ በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር በመጀመሪያው አጋማሽ ስምንት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

በውድድሩ ከፒኤስጂ በላይ ብዙ የመጀመሪያ አጋማሽ ግብ ( 11 ) ያስቆጠረው አነስተኛውን ክለብ ኡክላንድ ሲቲ የገጠመው ባየር ሙኒክ ብቻ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
121👍15🤔3😁2🥰1
TIKVAH-SPORT
🇺🇸 ዶናልድ ትራምፕ በፍፃሜው ይታደማሉ ! የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክለቦች አለም ዋንጫ ፍፃሜን በስታዲም በመገኘት እንደሚታደሙ ተገልጿል። በትላንትናው ዕለት በነበራቸው ስብሰባ በሜት ላይፍ በሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ እንደሚገኙ አሳውቀዋል። “ በስታዲየም እገኛለሁ “ በማለት ሁለት ሰዓት ከቆየው ስብሰባቸው በኃላ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። የአለም የክለቦች ፍፃሜ በቼልሲ እና ሪያል ማድሪድ…
#CWCFinal 🇺🇸

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፍፃሜ ጨዋታውን ለመታደም ስታዲየም ተገኝተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ሲገኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጨዋታው በኋላ ለዋንጫው አሸናፊ ዋንጫውን ያስረክባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በውድድሩ ምክንያት ከፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ጋር በተደጋጋሚ የተገናኙት ትራምፕ ሀገራቸው ቀጣዩን አለም ዋንጫ እንደምታዘጋጅ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
130👍20😁14👎7🙏5🤬2
ተጀመረ

ቼልሲ 0 - 0 ፒኤስጂ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
40🔥9👍6🤩2
9 '

ቼልሲ 0 - 0 ፒኤስጂ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
54👍8🔥4👏4
2025/07/14 21:39:57
Back to Top
HTML Embed Code: