Telegram Web Link
ፒኤስጂ ከፍተኛ ገቢ አስገብተዋል !

ስኬታማ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ በዚህ አመት ከፍተኛ ገቢ ማግኘቱ ተገልጿል።

ፒኤስጂ በ 2024/25 የውድድር ዘመን 850 ሚልዮን ዩሮ የሚገመት ገቢ ማግኘታቸው ተነግሯል።

ክለቡ ነገ የክለቦች አለም ዋንጫን የሚያሸንፍ ከሆነ ገቢው ከዚህም ከፍ እንደሚል ተዘግቧል።

ፒኤስጂዎች በውድድር አመቱ እስካሁን የፈረንሳይ ሊግ እና ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ አራት ዋንጫዎችን አሳክተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
👍20689👏21😱7🔥3🤔3
2️⃣ ቢልዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል “ ኢንፋንቲኖ

የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር በአለም ትልቅ ዋጋ ያለው ውድድር መሆኑን ገልጸዋል።

የክለቦች አለም ዋንጫ ውድድር ትልቅ ስኬት ማስመዝገቡን የገለፁት ኢንፋንቲኖ “ ከውድድሩ 2️⃣ ቢልዮን ዶላር ተገኝቷል " ብለዋል።

የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ይፋ ባደረጉት መረጃም :-

- 2.5 ሚልዮን በላይ ሰዎች ጨዋታውን ተከታትለዋል።

- የጨዋታው አማካይ ተመልካች ቁጥር 40,000 ነው።

- ጨዋታዎቹን በቴሌቪዥን በነፃ ከ 20 ቢልዮን በላይ ተመልካቾች ተከታትለዋቸዋል።

- የጨዋታ ትኬቶች ለ 168 ሀገራት ደጋፊዎች ተሸጠዋል

- ፊፋ ከትኬት ሽያጭ ከአንድ ጨዋታ 31 ሚልዮን ዶላር አግኝቷል ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
249😁74👍23😱9👏4😢3👎2
NUR TECHNOLOGIES

አዳዲስ እና ዱባይ ዩዝድ የሆኑ
HP
Lenovo
Dell
Microsoft Surface
Macbook
እና ሌሎችም ላፕቶፓችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከሙሉ ዋስትና ጋር ከኛ ያገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ ከስር የሚገኘውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://www.tg-me.com/NurTechnologies
📞0911646359
አድራሻ - ቦሌ መድኃኒለም ሰላም ሲቲ ሞል ፊት ለፊት ለአሚር ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
31🔥2👍1
ባርሴሎና የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹ ፍራንክ ዲዮንግን ኮንትራት ለማራዘም በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ባርሴሎና የተጫዋቹን ውል ለማራዘም የሚያደርገው ንግግር ለስምምነት መቃረቡ ተነግሯል።

በአሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ የሚመራው ባርሴሎና ተጫዋቹ በቡድኑ ለማቆይት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
183👏32😁10👍1👎1🥰1
ማድሪድ የመጀመሪያ ጨዋታው ይራዘምለታል ?

የክለቦች አለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚው ሪያል ማድሪድ የመጀመሪያው የላሊጋ ጨዋታ እንዲራዘምለት ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ይሁን እንጂ የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ሪያል ማድሪድ ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉን አስታውቀዋል።

ሪያል ማድሪድ በክለቦች አለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ በመድረሱ ምክንያት ለዝግጅት ጊዜ ያጥረኛል በሚል ነበር ከኦሳሱና ጋር የሚያደርገው የመጀመሪያ ጨዋታ እንዲራዘም የጠየቀው።

የላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ በበኩላቸው " ጨዋታው አይተላለፍም " ያሉ ሲሆን ቼልሲ እና ፒኤስጂ እንኳን ይህንን አልጠየቁም ብለዋል።

" ሪያል ማድሪድ እየጠየቀ ያለው ሀያ ሳይሆን ሀያ አንድ እረፍት ይኑረኝ ነው በዚህ ምክንያት የማዛወር ጨዋታ የለም " ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

" ሪያል ማድሪድ አንድ ቀን ስላላረፈ በኦሳሱና ይሸነፋል የሚል እምነት የለኝም " ዣቪየር ቴባስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁261118👍27👎9👏8
TIKVAH-SPORT
ቪክቶር ዮኬሬሽ ወደ ልምምድ አይመለስም ! ስዊድናዊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ ወደ ስፖርቲንግ ሊዝበን ልምምድ ተመልሶ ሪፖርት ለማድረግ እንዳላሰበ ተገልጿል። ተጨዋቹ በነገው ዕለት ወደ ልምምድ መመለስ የሚጠበቅበት ቢሆንም በድጋሜ የክለቡን ማልያ መልበስ እንደማይፈልግ ለክለቡ ማሳወቁ ተነግሯል። ተጨዋቹ አርሰናልን ለመቀላቀል በንግግር ላይ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን መድፈኞቹ ለማስፈረም…
" ከልምምድ መቅረቱ የባሰ አወሳስቦታል "

የስፖርቲንግ ሊዝበኑ ፕሬዝዳንት ቫራንዳዝ ቪክቶር ዮኬሬሽ ልምምድ ላይ አለመገኘቱ ነገሩን አባብሶታል ሲሉ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

“ የዮኬሬሽን ትክክለኛ የገበያ ዋጋ መክፈል የማይፈልጉ ከሆነ በሚቀጥለው ሶስት አመት እንደዚህ እንቀጥላለን “ ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግሯል።

ተጨዋቹ ልምምድ አልገኝም ስለማለቱ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ “ እቅዱ ክለቡን የሚለቅበትን መንገድ የባሰ አወሳስቦታል “ ብለዋል።

አክለውም " ማንም ቢሆን ከክለቡ ጥቅም በላይ አይደለም እኛ የተረጋጋን ነን " ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋለል።

" ልምምድ ስለቀረ በመቅጣት እና ቡድኑን ይቅርታ በማስጠየቅ የዝውውር መስኮቱ ከተዘጋ በኋላ መፍታት እንችላለን።" ፕሬዝዳንቱ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
259😁166👎58👍43🤬12🤔3😢2👏1
TIKVAH-SPORT
ሳንቲ ካዞርላን በላሊጋው እንመለከተዋለን ? ስፔናዊው አማካይ ሳንቲ ካዞርላ በልጅነት ክለቡ ሪያል ኦቬዶ ያለውን ኮንትራት ሊያራዝም እንደሚችል ተገልጿል። የ 40ዓመቱ ሳንቲ ካዞርላ ቡድኑን ከሁለት አመታት በፊት በመቀላቀል ከ 24 አመታት በኋላ ለላሊጋው ማብቃቱ አይዘነጋም። አሁን ላይ ክለቡ ሳንቲ ካዞርላ ውሉን በማራዘም በሚቀጥለው የውድድር አመት በስፔን ላሊጋ እንደሚጫወት እርግጠኛ መሆናቸው ተነግሯል።…
ሳንቲ ካዞርላ ውሉን አራዘመ !

ስፔናዊው አማካይ ሳንቲ ካዞርላ በልጅነት ክለቡ ሪያል ኦቬዶ ቤት ያለውን ኮንትራት ማራዘሙ ይፋ ተደርጓል።

የ 40ዓመቱ ሳንቲ ካዞርላ ቡድኑን በአምበልነት እየመራ ከ 24 አመታት በኋላ ለላሊጋው ማብቃቱ አይዘነጋም።

አሁን ላይ ሳንቲ ካዞርላ በሪያል ኦቬዶ ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት ውሉን እንዳራዘመ ይፋ ሆኗል።

የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ሳንቲ ካዞርላ ከ 24ዓመታት በኋላ ወደ ላሊጋ የተመለሰውን የልጅነት ክለቡን እየመራ በስፔን ላሊጋ የምንመለከተው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
231👏44👍19🔥1😁1
“ የማሸነፍ እድሉ እኩል ነው “ ኩኩሬላ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ተከላካይ ማርክ ኩኩሬላ የፍፃሜ ጨዋታውን የማሸነፍ እድሉ ለሁለቱም ክለቦች እኩል መሆኑን ተናግሯል።

“ ፍፃሜ ሁልጊዜም ፍፃሜ ነው “ የሚለው ኩኩሬላ “ የማሸነፍ እድሉ ለሁለታችንም እኩል ነው 50/50 ይሆናል “ ሲል ተደምጧል።

አክሎም “ ከረጅም የውድድር አመት በኋላ እዚህ አሁን ያለንበት ደረጃ ይገባናል " በማለት ተናግሯል።

“ ለጨዋታው ዝግጁ ነን እነሱ ምርጥ ተጨዋቾች አሏቸው እኛም ምርጥ ተጨዋቾች አሉን ጨዋታው ከባድ ይሆናል።" ማርክ ኩኩሬላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥235😁193102👍44👎12😢4🙏1
ክረምትን በምን ሊያሳልፋ አስበዋል?

Can PlayStation 🎮  መፍትሄ ይዞ ብቅ ብሎሎታል🫴

-Sony
  PlayStation 2
  PlayStation 3
  PlayStation 4
  PlayStation 5

-Microsoft
   Xbox 360
   Xbox one
   Xbox one s
   Xbox Series

ምርቶችን አዘጋጅቶ እናንተን በመጠበቅ ላይ ነን
እንግዲያውስ እርሶ በተመቻቹ ሰአት ብቅ በማለት ሱቃችን መጎብኘት ይችላሉ

እቃዎቻችን 6 ወር ዋስትና ስላለው የለ ሀሳብ ይዝናኑ

ለልጅም  ለአዋቂ የሚሆኑ PlayStation Cidi Game ስላሉን ይደውሉልን

Tv በተለያየ Brand እና Size እኛ ዘንድ ያገኛሉ

ባሎት ማንኛውም እቃ መቀያየር ይቻላል

ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ

🤝Tanks for choice

ስልክ፦ 0904658609 ወይም     
0977349492  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life

    Can PlayStation እና Tv Market
24🔥5👏3👍1🥰1
ቀመረኛው!!
ዛሬም የሚያሸንፉባቸው የእለቱ የውርርድ ጥቆማዎች እነሆ!
አሁን ነው ማሸነፍ እድሜ ለቀመረኛው!!
ቀመረኛው - በቤቲካ ብቻ!
10
ሊዮኔል ሜሲ የራሱን ሪከርድ አሻሻለ !

አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ሚያሚ ሌሊት ናሽቪሌን 2ለ1 ሲያሸንፍ ሁለቱን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥሯል።

ሊዮኔል ሜሲ በአምስት ተከታታይ የሜጀር ሊግ ሶከር ጨዋታዎች ከአንድ በላይ ግቦችን በማስቆጠር የራሱን ሪከርድ አሻሽሏል።

ሜሲ ከቀናት በፊት በአራት ተከታታይ የሜጀር ሊግ ሶከር መደበኛ ውድድር ጨዋታዎች ከአንድ በላይ ግቦችን ያስቆጠረ በታሪክ የመጀመሪያው ተጨዋች መሆን ችሎ ነበር።

ሊዮኔል ሜሲ ባለፉት አምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መመረጥ ችሏል።

የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ሪከርድ ባሻሻለባቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች 10 ጎሎችን አስቆጥሯል።

በተጨማሪም በውድድር አመቱ ሊዮኔል ሜሲ 16 ግቦችን አስቆጥሮ ሰባት አመቻችቶ አቀብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
484😁51🔥49👎21👍14🥰9🙏5🎉3
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ንዋኔሪን ለማስፈረም እየተመለከተ ነው ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የአርሰናሉን የፊት የመስመር ተጨዋች ኢታን ንዋኔሪ ለማስፈረም የኮንትራት ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል። ቼልሲ ተጨዋቹ ከዚህ በፊት በአርሰናል ውሉን ከማራዘሙ በፊት ሊያስፈርሙት ከፍተኛ ጥረት አድርገው እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ ኢታን ንዋኔሪ በአርሰናል ቤት ያለው ኮንትራት አንድ አመት የሚቀረው…
አርሰናል የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፊት መስመር ተጨዋቹን ኢታን ንዋኔሪ ኮንትራት ለማራዘም የሚያደርገው ንግግር ለስምምነት መቃረቡ ተገልጿል።

መድፈኞቹ የተጫዋቹን ውል በማራዘም በቡድናቸው እንደሚያቆዩት እርግጠኞች መሆናቸው ተዘግቧል።

አርሰናል የተጫዋቹን ወኪል እና ቤተሰቦች አግኝተው የሚኬል አርቴታን እቅዶች በማሳየት የአሰልጣኝ ቡድኑ በተጨዋቹ ላይ እምነት እንዳለው ማስረዳታቸው ተነግሯል።

አርሰናል የተጫዋቹን ኮንትራት በተቻላቸው ፍጥነት በማራዘም ቆይታውን ማረጋገጥ እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ተጫዋቹን ከአርሰናል ለማስፈረም ጣልቃ ለመግባት መሞከራቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
274👍39😁18🤬6🔥5🥰2🤔1😢1
አርሰናል ለቪክቶር ዮኬሬሽ ስንት አቅርቦ ነበር ?

አርሰናሎች ቪክቶር ዮኬሬሽን ለማስፈረም ለስፖርቲንግ ሊዝበን 65 ሚልዮን ዩሮ አቅርበው እንደነበር ተገልጿል።

መድፈኞቹ ተጨዋቹ ከክለቡ ጋር ከነበራቸው ስምምነት በላይ ጨምረው ቢያቀርቡም ስፖርቲንግ ሊዝበን ውድቅ በማድረግ ተጨማሪ መጠየቁ ተነግሯል።

አርሰናል አሁን ላይ የተጫዋቹን ዝውውር እውን ለማድረግ በውስጥ በመስራት ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።

“ ልምምድ አልገኝም “በማለት ለክለቡ ያሳወቀው ቪክቶር ዮኬሬሽ በበኩሉ በስፖርቲንግ ሊዝበን እንደተከዳ እንደሚሰማው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
👍25891😁60👎12🤔4
" ሻምፒየንስ ሊጉን እናመጣዋለን “ ላሚን ያማል

ስፔናዊው የባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል ቡድናቸው በሚቀጥለው የውድድር አመት ተፎካካሪ እንደሚሆን ገልጿል።

" በሚቀጥለው የውድድር አመት በትልቅ ደረጃ እንፋለማለን " ሲል ላሚን ያማል ለክለቡ ደጋፊዎች ቃል ገብቷል።

አክሎም " በሚቀጥለው አመት በእርግጠኝነት የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን ወደ ቤቱ እንመልሰዋለን " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
😁395233👎31👍23🔥23👏14🤔2🤬2😢1
" ጆታ ከችግር እንዲያወጣህ የምትጠይቀው ተጨዋች ነበር “ አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከዲያጎ ጆታ ህልፈት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

“ ዲያጎ ጆታ ጀግናችን ነበር “ ያሉት አርኔ ስሎት እሱ በአካል ባይኖርም በሄድንበት ቦታ ሁሉ ሁልጊዜም በልባችን ውስጥ አብሮን ይሆናል ብለዋል።

“ የእሱን ማልያ ቁጥር መስቀል ማድረግ ያለብን እና ልናደርግለት የሚገባ ብቸኛው ነገር ነው “ ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

“ ጆታ ነገሮች ሲወሳሰቡ ከችግር ውስጥ እንዲያወጣህ ሄደህ የተለየ ነገር አድርግልኝ ብለህ የምትጠይቀው አይነት ተጨዋች ነው “ አርኔ ስሎት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
469😢81👍28🙏15👏8💯2😁1
🔥⚽️ ትኩስ የስፖርት ዜና በስልካችን! 💬

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30001 SMS በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2ብር ብቻ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
13😁2
#Wanawsportswear✔️

ሙሉ ትጥቁን ከተጨማሪ ስጦታ ጋር መሸመት እየቸሉ የምን ተጨማሪ ወጪ ነው?

አቅምን ባገናዘበ ዋጋ ከከፍተኛ ጥራት እና ተጨማሪ ስጦታዎች ጋር በአንድ ላይ አድርጎ አዲስ ለገበያ የቀረበውን የዋናው ስፖርት ማሊያ በቁምጣ ከነጻ ቦርሳ ጋር በ1000 ብር ሲሸምቱ ስጦታዎትን መውሰድዎትን አይዘንጉ!

🛒ብዛት ከ20 ጀምሮ ሲያዙ = 1 ነጻ ፖሎ
🛒ብዛት ከ50 ጀምሮ ሲያዙ= 2 ነጻ ፖሎ
🛒ብዛት ከ100 ጀምሮ ሲያዙ = 2 ነጻ ፖሎ + 2 የቡድን ባንዲራ

💰 በ1000ብር | ማሊያ • ቁምጣ • ቦርሳ
ለቡድንዎት ትክክለኛው ምርጫ!

📞ለማዘዝ
8️⃣2️⃣8️⃣9️⃣
➡️+251901138283
➡️+251910851535
➡️+251913586742

🔗 ማህበራዊ ገጾቻችን🔗
Instagram|Facebook |TikTok |X|Youtube
🔥🔥🔥🔥በኢትዩጵያ የተመረተ🔥🔥🔥🔥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14
ሊቨርፑል ተጨዋቾቹ ስንት ቁጥር ይለብሳሉ ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዚህ ክረምት ቡድኑን የተቀላቀሉ አዳዲስ ተጨዋቾች በጊዜያዊነት የሚለብሱትን የማልያ ቁጥር ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት :-

- ፍሎሪያን ቨርትዝ :- 5️⃣8️⃣ ቁጥር ማልያ

- ሚሎስ ኪርኬዝ :- 5️⃣7️⃣ ቁጥር ማልያ

- ጄርሚ ፍሪምፖንግ :- 5️⃣9️⃣ ቁጥር ማልያ

- ማማርዳሽቪሊ :- 5️⃣5️⃣ ቁጥር ማልያ እንደሚለብሱ ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ የውድድር ዘመኑ ከመጀመሩ በፊት ቋሚ የማልያ ቁጥር እንደሚሰጣቸው ክለቡ አስታውቋል።

ሊቨርፑል ዛሬ ከቀኑ 11:00 ከፕሪስተን ጋር የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
163😁63🤔20👍4
" ዋንጫውን ለጆታ ማሸነፍ እፈልጋለሁ " ፔድሮ ኔቶ

ፖርቹጋላዊው የቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ፔድሮ ኔቶ የክለቦች አለም ዋንጫን ለዲያጎ ጆታ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ተናግሯል።

“ ዛሬ ዋንጫውን ለዲያጎ ጆታ ስል ማሸነፍ እፈልጋለሁ እሱ ሁልጊዜም አብሮኝ ይሆናል “ ሲል ፔድሮ ኔቶ ተናግሯል።

“ ጨዋታው ከቼልሲ ጋር የማደርገው ሁለተኛ ፍፃሜ ጨዋታዬ ነው የአለም ሻምፒዮን መሆን እንችላለን ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን አላማችን እሱ ነው።“ ፔድሮ ኔቶ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
296😁48👍26🔥8
“ ዋንጫውን ለመውሰድ ያለንን እንሰጣለን “ ዴምቤሌ

የፒኤስጂው ወሳኝ የፊት መስመር ተጨዋች ኡስማን ዴምቤሌ ቡድናቸው ዛሬ ለዋንጫው ያለውን እንደሚሰጥ ተናግሯል።

“ ዋንጫውን ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን “ ሲል ኡስማን ዴምቤሌ ከጨዋታው በፊት ተናግሯል።

የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በበኩላቸው “ ይህንን ታሪካዊ የውድድር አመት በጥሩ ሁኔታ መፈፀም እንፈልጋለን “ ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
👏20375😁17👍13👎12
2025/07/14 15:32:26
Back to Top
HTML Embed Code: