Telegram Web Link
በሀረሪ ክልል በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ - የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ

ባለፈው ዓመት እንደ ሀገር ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በሀረሪ ክልል የተሻለ ውጤት ተመዝግቦ እንደነበር - የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ አስታውሰዋል፡፡

ዘንድሮ ከአምናው የተሻለ ውጤት በክልሉ ለማስመዝገብ ዝግጅት መደረጉን የገለፁት ኃላፊው፤ ተማሪዎቹን ለማብቃት ከፍተኛ ባለሙያዎችን በመመደብ የማጠናከሪያ ትምህርትና የስነ-ልቦና ዝግጅት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

በአጠቃላይ 2292 ተማሪዎች በክልሉ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ሲሆን፤ 1931 ተማሪዎች በኦንላይን እና ቀሪዎቹ 361 በወረቀት በስድስት የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚፈተኑ ተገልጿል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
በአፋር ክልል 4893 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ - የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ

በክልሉ በ2017 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሚቀመጡ ተማሪዎች መካከል፥ 4099 ተማሪዎች በወረቀት እና 794 ተማሪዎች ደግሞ በኦንላይን ፈተናቸውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሁመድ አብደላ ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ ከ44 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን ፈተና እንደሚወስዱ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ለስነ-ልቦና የሚያዘጋጁ ተከታታይ ሞዴል ፈተናዎች በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
በማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ

ከቀናት በኋላ መሠጠት የሚጀምረውን ፈተና በክልሉ በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፍቃዱ ተናግረዋል።

በክልሉ 35246 ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን፤ 28035 ተማሪዎች በወረቀት እና 7211 ተማሪዎች በበየነ መረብ ፈተናውን እንደሚወስዱ ኃላፊው ገልፀዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
🌐 ቅመም ማይፋይ በአዲስ ዋጋ መጥቷል 🙌

💨⚡️ እስከ 7 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😊

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️

#SafaricomEthiopia
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በአራት መስኮች ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው የባለሙያ ክፍተት በሚታይባቸው አራት የህክምና መስኮች በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዋቆ ገዳ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት አካባቢ በሚነገሩ ሦስት ቋንቋዎች ማለትም በቤንች ኖን፣ በሸኪኖኖ እና በሸኮ ኢድ ቋንቋዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች እያስተማረ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በ54 የቅድመ-ምረቃ እና በ42 የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመማር ማስተማር ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ #SRTA

@tikvahuniversity
#AAU

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ የተማሪዎች ምርቃት ስነ-ስርዓት እና የተቋሙን የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ያከብራል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን 75ኛ ባች ተማሪዎች ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት በትምህርት ልህቀት፣ በአመራር ልማት እንዲሁም በሀገር ግንባታ ያደረገው ዘላቂ እና ዘርፈ ብዙ አበርክቶ ይዘከራል ተብሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከ75 ዓመታት በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመባል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤ የፈጠራ፣ ምርምር እና የዕውቀት መፍለቂያ በመሆን በርካታ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራንን አፍርቷል፡፡

@tikvahuniversity
የሁለት ወር የልጆች የክረምት ስልጠና!
25% ቅናሽ እስከ ነገ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም.

👉 ስልጠናው ዕድሜያቸው ከ 7-18  ዓመት ላሉ ልጆች የሚሰጥ ነው።
👉 ልጆች ፕሮጀክቶች እየሠሩ የሚሰለጥኑበት
👉 ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

የሚሰጡ ስልጠናዎች
👉 Computer Programming and Website Development
👉 AI and Robotics
👉 Graphic Design, Video Editing and Animation
👉 Art (Film Acting, Writing and Modeling)
👉 Painting, Drawing and Sculpture
👉 Language and Basic Computer

☎️  0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
በአማራ ክልል ከ41 ሺህ በላይ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ የክረምት ስልጠና ይወስዳሉ። - የክልሉ ትምህርት ቢሮ

ስልጠናው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ አቅም ለመገንባትና የተማሪዎችን ውጤት ለማሳደግ አላማ አድርጎ የሚሰጥ መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ደምስ እንድሪስ ገልፀዋል።

ከ27 ሺህ በላይ የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የክረምት ስልጠና ተጠቃሚ በመሆን በዩኒቨርሲቲዎች ገብተው እንደሚሰለጥኑ ኃላፊው ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከ7ኛ-8ኛ ክፍል የሚያስተምሩ 11,200 መምህራን እና 2,300 የትምህርት ቤት አመራሮች አዳዲስ በተጨመሩ የሙያ ትምህርቶች ላይ በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች አማካኝነት ይሰለጥናሉ ብለዋል።

በተጨማሪ 1,500 ለሚጠጉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ56 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ

በክልሉ በ2017 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሚቀመጡ ተማሪዎች መካከል፥ 49,032 ተማሪዎች በወረቀት እና ከ7 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በኦንላይን ፈተናቸውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ፀሐይ ወራሳ ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ በክልሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የሚረዱ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ኃላፊዋ ገልፀዋል።

በቀጣይ ሳምንት መሰጠት የሚጀመረው የመልቀቂያ ፈተና፤ በክልሉ በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል ተብሏል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በነዳጅ እጥረት ምክንያት በክልሉ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን ወደ ፈተና ማዕከላት ማጓጓዝ መቸገሩን አሳወቀ፡፡

ቢሮው ትናንት ሰኔ 19/2017 ዓ.ም ለትምህርት ሚኒስቴር እና ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በጻፈው ደብዳቤ እንዳለው፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች በሚገኙ 247 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ከ36 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከቀናት በኋላ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ገልጿል፡፡

ተፈታኞቹን ወደ ሰባት የፈተና ማዕከላት ለማጓጓዝ እና ከፈተናው በኃላ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ የትራንስፖርት ወጪ ባለው መደበኛ ታሪፍ ተሰልቶ ወደ እያንዳንዱ ወረዳ የተላከ ቢሆንም፤ አሁን በክልሉ ባለው የነዳጅ እጥረት ምክንያት ተማሪዎቹን ወደ ፈተና ማዕከላት ማጓጓዝ አለመቻሉን ቢሮ አስረድቷል፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ያወጣው መርሐግብር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲዎች (የፈተና ማዕከላት) እንደሚገቡ ያሳያል፡፡

"ተማሪዎቹ በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናቸውን ወስድው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ፥ ትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከሚመለከታቸው የፌዴራል አካላት ጋር በመሆን ነዳጅ ወደ ትግራይ እንዲገባ በማድረግ ችግሩን እንዲፈታልን" ሲል ቢሮው ጠይቋል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
ፊልም በኩፖን! 📽

ወደ *777# በመደወል ወይሞ በM-PESA ልዩ ልዩ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ ጥቅሎችን እንግዛ! አባይ ወይስ ቬጋስ የተሰኘውን የአማርኛ ፊልም የምናይበትን ኩፖን እናግኝ!

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit #Furtheraheadtogether
ዩኒቨርሲቲዎች ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞችን ዛሬ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም መቀበል ጀምረዋል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል። በወጣው መርሐግብር መሰረት ሰኞ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ይጀምራል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

ምስል፦ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ፣ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት/ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ሀገር አቀፍ ፈተናው ሰኞ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሚሰጡ ፈተናዎች ይጀመራል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቹን እየተቀበሉ ሲሆን፤ በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠውን ፈተና በብቃት ለመስጠት ዝግጁ እንደሆኑ ገልፀዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ምስል፦ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እና ቦረና ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniveristy
2025/06/28 20:44:07
Back to Top
HTML Embed Code: