አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ክብሩ ከፍ ያለውና የላቀው ጌታችን አላህ የለሊቱ መገባደጃ 1/3ኛ ሲቀር ወደ ምድራዊ ሰማይ ይወርዳል፡፡ ከዛም፡- ‹‹ማነው የሚማጸነኝ እኔም የምቀበለው? ማነው የሚጠይቀኝ እኔም የምሰጠው? ማነው ማረኝ የሚል እኔም የምምረው?›› ይላል" (ቡኻሪይ 1145፣ ሙስሊም 758)፡፡
• የሶላቱ-ለይል አስጋገድ ሁኔታ ሁለት ሁለት ረከዓህ ነው፡- ዐብደላህ ኢብኑ-ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ አሉ፡- "የለሊት ሶላት ሁለት ሁለት (ረከዓህ) ነው" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
• የሶላቱ-ለይል አሰጋገድ መጠን የተገደበ ነገር የለውም፡፡ ሰውየው አቅሙ የፈቀደውን ያህል መስገድ ይችላል፡፡ የአላህ መልክተኛ የለይል ሶላትን ዊትርን ጨምሮ ከ11-13 ረከዓህ ይሰግዱ ነበር፡፡ ከዛ ጨምረው አያውቁም፡፡ ስለዚህ ከፊል ዑለማዎች ይህን መሠረት በማድረግ የሶላቱ መጠን ከዚህ ቁጥር መብለጥ የለበትም ይላሉ፡፡ አላህ ወፍቆት ለይል ተነስቶ ከዛ በላይ ለመስገድ የሚፈልግ ሰው ካለ በአቅራቢያው ያሉ ዑለማዎችን መጠየቅና መረዳት ይችላል፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
• የለይል ሶላትን ልምዱ ያደረገ መልካም የአላህ ባሪያ፡ የሆነ ቀን በእንቅልፍ ወይም በሌላ ምክንያት ለሊቱን ሳይሰግድበት ቢያመልጠው በቀኑ ክፍል ቀዷውን ሊያወጣና ሊሰግደው ይችላል፡- እናታችን አዒሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ ነቢይ(ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) በእንቅልፍ ምክንያት ለይልን ተነስተው ባይሰግዱ፡ በቀኑ ክፍል አስራ ሁለት ረከዓህ ይሰግዱ ነበር" (ሶሒሑ-ቲርሚዚይ 365)፡፡
ኢማሙ ሙስሊም በዘገቡት ሌላ ዘገባም እናታችን አዒሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) በድጋሚ እንዲህ አለች፡- "የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) በእንቅልፍ ምክንያት ወይም በህመም ለይልን ባይሰግዱ በቀኑ ክፍል አስራ ሁለት ረከዓህ ይሰግዱ ነበር" (ሙስሊም 746)፡፡
• የለይል ሶላትን የሚሰግድ የአላህ ባሪያ በአጠገቡ የተኛ ሰው ከሌለ ወይንም ሌላውን ሰው እስካልረበሸ ድረስ ድምጹን ከፍ አድርጎ መስገድ ይችላል፡፡ በተለይ ከፍ ባለ ድምጽ መቅራቱ ለሱ ነሻጣ አጋዥ ከሆነ ይወደድለታል፡- ዐብዱላህ ኢብኑ-አቢ ቀይስ፡- "እናታችን አዒሻን (ረዲየላሁ ዐንሃ) ስለ-መልክተኛው የቂርኣት ሁኔታ እንዴት እንደነበር ጠየቅኋት፡፡ እሷም፡- ‹‹አንዳንድ ጊዜ በሚስጥር (ድምጽ ዝቅ በማድረግ)፡ አንዳንዴ ደግሞ ከፍ በማድረግ ይቀሩ ነበር›› አለችኝ፡፡ እኔም፡- ‹‹ጉዳዩን በሁሉም መንገድ ሰፋ ላረገልን አላህ ምስጋና ይድረሰው አልኩኝ›› ይላል" (ሶሒሕ አቢ ዳዉድ 1291፣ ሶሒሑ-ቲርሚዚይ 369)፡፡ አላህ ይወፍቀን!
ሶላቱል ዊትር፡-
• ሶላቱል ዊትር ማለት ነጠላ (አንድ ረከዓህ) ሆኖ የሚሰገድ ሶላት ማለት ነው፡፡
• ሶላቱል ዊትር ጠንካራ ከሆኑ የሱና ሶላቶች ውስጥ የሚመደብ የሶላት አይነት ነው፡- ዐሊይ ኢብኒ-አቢ ጧሊብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "ዊትር እንደ ፈርድ ሶላታችሁ ግዳጅ አይደለም፡፡ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ያሳዩን ሱና ነው፡፡ እንዲህም አሉ፡- ‹‹እናንተ የቁርኣን ሰዎች ሆይ! አላህ ዊትር(አንድ) ነውና ዊትርንም ይወዳል፡ ስለዚህ ዊትርን ስገዱ››" (ሶሒሒ-ቲርሚዚይ 374)፡፡
• የሶላቱል ዊትር ወቅት፡- ከዒሻእ በኋላ እስከ ፈጅር ወቅት መግባት ባለው መሐከል ነው፡- ኻሪጀተ ኢብኑ-ሑዛፈተል ዐደዊይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡- "የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) ወደኛ ብቅ አሉና፡- ‹‹አላህ ሶላትን ጨመረላችሁ፡፡ እሷም ከቀያይ ግመሎች (ሰደቃ) የምትበልጥላችሁ ነች፡፡ በዒሻእና በፈጅር መካከል ያለችዋ ዊትር ነች›› ብለው ነገሩን" (ሶሒሑ-ቲርሚዚይ 373)፡፡
• የዊትር ሶላት የመጨረሻ ሶላታችን መሆን አለበት፡፡ ሶላቱ-ለይልን ተነስቶ የሚሰግድ ሰው ካለ ከሶላቱ ቀጥሎ የመጨረሻውን በዊትር መዝጋት አለበት፡፡ ለይል የማይነሳ ከሆነ ደግሞ ከዒሻእ በኋላ ከመተኛቱ በፊት በዊትር መዝጋቱ የተወደደ ተግባር ነው፡- ዐብዱላሁ ኢብኑ-ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከለሊቱ ክፍል የመጨረሻ ሶላታችሁን ዊትር አድርጉ" (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
• ሶላቱል ዊትርን መስገድ የፈለገ ሰው በአንድ ረከዓህ ብቻ መስገድ ይችላል፡፡ ከፈለገም በሶስት፣በአምስት፣በሰባት፣በዘጠኝ መስገድ ይችላል፡፡ ዋናው መጨረሻ ላይ በአንድ ረከዓህ ዊትር ሆኖ መጠናቀቁ ነው፡- ዐብዱላሁ ኢብኑ-ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ዊትር በመጨረሻው ለሊት የሚሰገድ አንድ ረከዓህ ነው" (ሙስሊም 752)፡፡
አቢ አዩበል አንሷሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ዊትር በሁሉም ሙስሊም ላይ (ሊሰግደው) የተገባ ነገር ነው፡፡ የፈለገ ሰው በዘጠኝ፣ የፈለገ ሰው በሰባት፣ የፈለገ ሰው በአምስት፣ የፈለገ ሰው በሶስት፣ የፈለገ ሰው በአንድ ረከዓህ መስገድ ይችላል" (አቡ-ዳዉድ 1421)፡፡
• ሶላቱል ዊትርን በሶስት ረከዓህ አያይዞ መስገድ ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከመግሪብ ሶላት ጋር እንዳይመሳሰል በመጨረሻው እንጂ በመሐል ተሸሁድ መቀመጥ የለበትም (ሐኪም አል-ሙስተድረክ 1/314)፡፡
• በአንድ ለሊት ሁለት ዊትር የለምና፡ ለይል የሚነሳ ሰው ከዒሻእ በኋላ ዊትርን አይስገድ፡፡ ወይንም ለይል ላልነሳ እችላለሁ ያለ ሰው ቀድሞ ዊትሩን ሰግዶ ይተኛ፡፡ ከዛም አላህ ወፍቆት ለይል ከተነሳ፡ የለይል ሶላቱን ሁለት ሁለት ረከዓህ አድርጎ በዛው ያለ ዊትር ያጠናቅቀዋል፡፡ ድጋሚ ዊትር የለምና!
• በሶላቱል ዊትር ላይ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ረከዓህ ላይ ‹‹ሱረቱል-አዕላ›› እና ‹‹ሱረቱል ካፊሩን›› መቅራቱ የተወደደ ነው፡፡ በሶስተኛው ላይ ደግሞ ‹‹ሱረቱል ኢኽላስ›› አንዳንዴም ‹‹ሱረቱል ፈለቅ››ንና ‹‹ሱረቱ-ናስ››ን አብሮ ጨምሮ መቅራት ይወደዳል፡፡ ከዛ ውጪም ሰጋጁ የገራለትን የቁርኣን ክፍል መቅራት ይችላል፡፡- ኡበይ ኢብኑ-ከዕብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ በሶስት ረከዓህ ዊትር ይሰግዱ ነበር፡፡ በመጀመሪያው ረከዓህ ‹‹ሱረቱል አዕላ››ን በሁለተኛው ደግሞ ‹‹ሱረቱል ካፊሩን››ን፡ በሶስተኛው ‹‹ሱረቱል ኢኽላስ››ን ይቀሩ ነበር፡፡" (ሶሒሑ-ነሳኢይ 1/371-372)፡፡
• ሶላቱል ዊትር ላይ ቁኑት ማድረግ ሱና ነው፡፡ ግዳጅ አይደለም፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አንዳንዴ ይተዉ ስለነበር፡፡ የቁኑት አደራረጉ በሁለት መልኩ ነው፡-
1. ከሩኩዕ በፊት እዛው ቂያም ላይ እያለን የምናደርገው፡- ኡበይ ኢብኑ-ከዕብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ ዊትርን ይሰግዱ ነበር፡፡ ከሩኩዕ በፊትም ቁኑት ያደርጉ ነበር" (ኢብኑ ማጀህ 1182፣ አልባኒይ፡ አል-ኢርዋእ 2/167)፡፡
2. ከሩኩዕ መልስ ሱጁድ ከመውረድ በፊት የሚደረግ ነው፡፡ (ቡኻሪይ 2010፣ አልባኒይ ሶላቱ-ተራዊሕ 41-42)፡፡ - ቁኑት ላይ ከሚደረጉ ዱዓዎች መካከል፡-
#ቀሪውን_ኮሜንት_ላይ
@yasin_nuru @yasin_nuru

የረመዿን የመጨረሻዎቹ 10 ቀኖች‼️
============================
✔️ የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት «ዐሽረል አዋኺር» ይሰኛሉ።
የረመዿን ቀናቶች ከሌሎቹ የአመቱ ቀናቶች የተለዩና የተባረኩ ናቸው።
የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ደግሞ ከሌሎቹ የረመዿን ቀናት የተለዩና ድንቅ ናቸው።
*
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከምንጊዜውም በላይ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ለየት ያሉ እንደነበሩ ከእናታችን ዐኢሻህ ረዲየልሏሁ ዐንሃ የተገኘ ሐዲሥ ይጠቁመናል።
👉ዐኢሻህ ረዲየልሏሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች፥
"كان النبي - صلى الله عليه وسلم - إذا دخل العشر أحيا الليل وأيقظ أهله، وجدَّ وشدَّ المئزر"
"(የረመዿን የመጨረሻዎቹ) አስር (ቀኖች) በገቡ ጊዜ፣
ሌሊቱን ያነጉ (ሕያው ያደርጉ) ነበር፣ ቤተሰባቸውን ያነቁ ነበር፣ የሚጠነክሩና ሽርጣቸውን ያጠብቁ ነበር።"
[ቡኻሪ፥ 2014
ሙስሊም፥ 1174]
"ሽርጣቸውን ያጠብቁ ነበር!" የሚለው ገለጻ በዒባዳ ላይ ይታገሉና ይተጉ ነበር ለማለት ነው ተብሏል።
አንዳንድ ዑለሞች ደግሞ ሚስቶቻቸውን ይርቁ ነበር ለማለት የተፈለገበት የአሽሙር አገላለጽ ነው ብለዋል።
*
👉 አሁን ከርሷው በተገኘ ሌላ ሐዲሥ ላይ እንዲህ ትለናለች፥
"كان رسول الله - صلى الله عليه وسلم - يجتهد في العشر الأواخر ما لا يجتهد في غيره"
"(በረመዿን) የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ውስጥ ነብዩ ﷺ በሌሎች (ቀናት) የማይታገሉትን ይታገሉ ነበር። (በዒባዳ ይበልጥ ይበረቱ ነበር።)"
[ሙስሊም፥ 1175]
||
ከነዚህ ሁለት ሐዲሦች የምንረዳው፤
ነብያችን ﷺ በመጨረሻዎቹ የረመዿን ቀኖች ከምንግዜውም በላይ በዒባዳ ይተጉ እንደነበር ነው።
*
እነዚህን የረመዿን የመጨረሻ አስር ቀናት ይበልጥ ልዩ ከሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል አንዱና ዋናው፣
የመወሰኛዋ ሌሊት (ለይለተል ቀድር) በነዚህ አስርት ቀናት ውስጥ የምትገኝ መሆኗ ነው።
በዚህች የተባረከች ሌሊት የሚሰራ መልካም ስራ ከሰማኒያ ሶስት አመት በላይ ከሚደረግ ስራ በላይ ይበልጣል።
||
ስለዚህ በእነዚህ የተባረኩ ቀናት ውስጥ፣
ከምንጊዜውም በላይ ራሳችንንና ቤተሰባችንን በዒባዳ ልክ እንደ ነብያችን ﷺ ልንነቃና ልናነቃ ይገባል።
||
በነዚህ ቀናት ውስጥ ነቅተን መስራት ካሉብን ስራዎች ውስጥ
የሚከተሉትን ነው።
✔️ ለይለተል ቀድርን መጠባበቅ፣
✔️ኢዕቲካፍ መውጣት፣
✔️ቁርኣን ይበልጥ ማብዛት፣
✔️በአላህ መንገድ ላይ ሶደቃ ማውጣት፣
✔️ሌሊቱን በዒባዳ ማሳለፍ (ሐይ ማድረግ)፣
✔️ቤተሰባችንን ማንቃት፣
✔️ተሀጁድና ሌሎች ትርፍ ሶላቶችንም ጠንቅቆ መስገድ፣
እንዲሁም ሌላም ተጨማሪ ማንኛውንም መልካም የሚባል ተግባር ከወትሮው ይልቅ ይበልጥ ማብዛት።

#ዛሬ_ማታ_እኮ_ረመዳን_21_ነው_መተኛት_የለም_ኢንሻአላህ!
*""(በለይለተል ቀድር)""የሚደረግ ዱዓ_*
አኢሻ ረድየላሃ አንሃ የአላህ መልእክተኛን ሠለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም *ለይለቱል ቀድርን ካወኩኝ ምን ብዬ ዱዓ ላድርግ?*
ብዬ ጠየኩኝ(አለች)። እርሳቸውም
_*اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني*_
_አላሁመ ኢንነከ ዐፉውን ቱሒቡል_ዐፍወ ፈአዕፉ አን_ኒይ በይ" አሉኝ። (ቲርሚዚይ ዘግበውታል )
ትርጉሙ....
*""‘አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ። ይቅርታንም ትወዳለህ። ይቅር በለኝ!፤""* ማለት ነው

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሽረል አዋኺር የረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርቱ ቀናት!
ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በነዚህ ምርጥ ቀናትን እንዴት ማሳለፍ እንዳለበን በአጭሩ ያስታውሰናል ይከታተሉ።
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
☪ JOIN: @yasin_nuru ☪
☪ JOIN: @yasin_nuru ☪ ╚════════════

Audio
ኡስታዝ ያሲን ኑሩ - “አጫጭር ቀላል የሆኑ ለጭንቅ ግዜ መፍትሔ የሆኑ ዚክሮች”
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
☪ JOIN: @yasin_nuru ☪
☪ JOIN: @yasin_nuru ☪ ╚════════════╝
🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
☪ JOIN: @yasin_nuru ☪
☪ JOIN: @yasin_nuru ☪ ╚════════════╝
💐🌹አላህ ሆይ💐🌹
የልዕቅናም፣የንግስናም ፣የፍርዱ ቀን ባለቤትም ነህ፣
ካንተ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም፤ለስልጣንህ ተጋሪ የለህም፣ የሰማይ እና የምድር ብቸኛ አስተናባሪ ነህ:: የፍርዱ ቀን ባለቤትህም ነህ::
💐🌹አላህ ሆይ 💐🌹
የምንወደውን የምስራች እንለምንሃለን ደስታን የምናገኝበትን ዘመን አምጣልን፣ ልባችን ባንተ ላይ የሚፀናበትን ኢማን ለግሰን
💐🌹ያ ረቢ💐🌹
ላንተ የገቡትን ቃል ከሚፈፅሙ ባሮችህ መካከል መድበን፣ ቃልኪዳህን አምነው ቃላቸውን ከሚጠብቁ፣ ለትዕዛዝህ አድረው ከሚታዘዙህ፣ ካንተ ዘንድ ያለውን ምህረት እና እዝነት ሁሌም ከሚከጅሉ ባሮችህ መካከል አድርገን
💐🌹 ኢላሂ💐🌹
ሁሌም አክብረን አታዋርደን፣ አንተ በጣም መሐሪ እና ይቅር ባይ ነህና ይቅር በለን
💐🌹ኢላሂ💐🌹
አንተ ወንጀል መሐሪ ፣ የሠው ልጆች ፈጣሪ ፣የውስጥ አዋቂ የሆንክ ጌታ ሆይ ደስታን እና ጤናን ለግሰን፣ አይኖቻችንን እና አካላችንን በመልካም የምንገለግልበት አድርገን፣
መልካም ስራዎቻችንን ተቀበለን፣ መጨረሻችንንም አሳምርልን
ጌታችን አላህ ሆይ💐🌹
💐🌹ኢላሂ💐🌹
የፆምነውን ፆም ተቀበለን፣ ያጓደልነውን በእዝነትህ ሸፍንልን፣ መልካም ስራዎቻችን ሁሉ ተቀበለን
💐🌹ሃያሉ ጌታችን ሆይ💐
💐🌹አዛኙ ጌታችን ሆይ 💐🌹
በህይወት ላሉት እና ለሌሉት ምዕመናን በሙሉ ምህረትህን ለግስ፣ ከዚህች አለም እና ከቀጣዩ አለም ፈተናም ጠብቀን
💐🌹አላህ ሆይ💐🌹
ለምኑኝ እሰጣቹኃለው ባልከው መሰረት ጉዳዮቻችንን ሁሉ ወዳንተ አቅርበናል:: የጠየቅንህን ሁሉ ለግሰን:: ነገራችንን ሁሉ ገር አድርግልን፣
💐🌹«ኢላሂ! 💐🌹
በፍቃድህ ታዘዝንህ ውለታው ያንተ ነው። በዕውቀትህም አመፅንህ ማስረጃው ያንተ ነው፤ ፈርደህብን የሰራነውን አመፅ ይቅር በለን።
💐🌹ኢላሂ! 💐🌹
በባይተዋርነታችን በድህነታችን፣ በአቅመ ቢስነታችን በሰፊው ማርታህ እና በመብቃቃትህ ይሁንብህ እዘንልም ይቅርታህንም ለግሰን።
💐🌹 ኢላሂ!💐🌹
ካንተ ሌላ አምላክ እንደሌለ በመመስከር አንተ ጋ ውድ በሆነው ነገር ይኸው ታዘንሀል።
የምትጠላውን ሽርክ ርቀንም በብቸኝነት አምልከንሀል፤ እባክህ በመሀከሉ ያሉ አመፆችን ይቅር በለን።»
💐🌹ጌትዬ 💐🌹
ወዳንተ አልቀሰን ተመልሰናል እና ከሰፊው ምህረትህ አቋድሰን:: በወንጀላችን ብዛት ካመጣህብን በላዕ ነጅ አውጣን
💐🌹አላህ ሆይ💐🌹
🌹በትክክለኛ እና በመልካም ነገራቶች ላይ ሁሉ አነሳሳን:: ለእያንዳንዱ ለምንጠየቀው ጥያቄ መልሱን ቀላል አድርግልን:: ከሁሉም ኣይነት ቅጣትህ ታደገን::ምርመራህ በበረታበት ወቅት ፊታቸው ከሚያበሩት አድርገን::
🌹ለኸይር መቀማመጣችን በመልካሞች እና በምርጥ ወዳጆችህ አስጊጥልንን ዱዓችንን ሁሉ ተቀባይነት ያላቸው አድርግልን
💐🌹አላህ ሆይ💐🌹
አንተ በጣም ይቅር ባይ ነህ፣ይቅርባይነትን ትወዳለህና ይቅር በለን
💐🌹ኢላሂ 💐🌹
አስታዋሾች ባስታወሱህ፣ አመስጋኞች ባመቀሰገኑህ ብዛት ቁጥር ልክ ምህረትህን እንለምንሀለን
ሰጋጆች በሰገዱት፣ አንተን የሚያልቁህ ባላቁህ ቁጥር ልክ ምህረትህን እንጠይቅሀለን
በወንጀላችን ብዛት ልክ ምህረትህን እስክናገኝ ድረስ ምህረትህን እንጠይቅሀለን
💐🌹 አላህ ሆይ ማረን💐🌹
ምሽታችን ምህረትህን የምናገኝበት አድርግልን
💐🌹 አላህ ሆይ💐🌹
በዲናችን ላይ የመጣብንን ፈተና አንሳልን:: የምዕመናንን ልቦናዎች አስማማ:: በሃቅ ላይ አንድነታችን የሚጠናከር አድርገው:: ዲናችንን ከፍ ለማድረግ እየለፉ ያሉትን ሁሉ ከፍ አድርጋቸው:: ዲናችንን ለማዋረድ የሚጥሩትን ሁሉ አዋርዳቸው:: በማንችለው ፈተና አትፈትነን
💐🌹ኢላሂ 💐🌹
ሙስሊሞች አድርገህ እንደፈጠርከን ሙስሊሞች እንደሆንን በተውሂድ ላይ ግደለን::መጨረሻችንን አሳምርልን:: ከመጥፎ አሟሟትም ጠብቀን
💐🌹ለጋሹ ጌታዬ ሆይ💐🌹
በልጅ ናፍቆት የሚሰቃዩ ባለትዳሮችን ሷሊህ ልጆችን ወፍቃቸው:: ትዳር ለሚመኙት ሁሉ መልካም ትዳርን ለግሳቸው
💐🌹አላህ ሆይ💐🌹
በህይወት ያሉ ወላጆቻችንን ረጅም እድሜ ከአፊያ ጋር ለግሳቸው:: ሃቃቸውንም ከማጉደል ጠብቀን::
በህይወት የሌሉ ወላጅቻችንንም በሰፊው እዝነትህ አካባቸው:: በልጅነታችን ኖሯቸው ምንም አልከለከሉንም ኣንተም ጀነትህን አትከልክላቸው
💐🌹አምላኬ ሆይ 💐🌹
በዚህች ሰዓት በሃገራችን እና በመላው አለም በጭንቀት ላይ ያሉ ባሮችህን ፈርጃቸው:: ሃገራችንን ሰላም አድርግልን:: ለዲናችን ጠላት የሆኑትን ሁሉ አንተ መክትልን::
በዚህች አለም መልካሙን በመጪው አለምም ስኬትን ለግሰን
አሚን
@yasin_nuru. @yasin_nuru

🍇 “ሐይድ” መስጂድ መግባት
አይከለክልም!
📌 ጥያቄ:- "ሐይድ" ላይ ለሆኑ ሴቶች መስጂድ መግባት ይቻልላቸዋልን?
✅ መልስ:- አዎ ! ይህን ማድረጋቸው ለነሱ ይቻላል። ምክንያቱም ፦
ሴት ልጅ መስጂድም ውስጥም ቢሆን ዕውቀት የሚሰጥበት ከሆነ ስፍራ ከመገኘት የሚከለክላት ነገር የለም !!!
👉 ምክንያቱም ያ ሴት ልጅን መስጂድ መግባቷን የሚከለክላት የሆነው ወቅት መረጃ አይገኝለትም !!!
✅ እዚህ ጋር ከዚህ በተቃራኒው የሚፈቀድ በመሆኑ ላይ የሚያመላክት ነገር (መረጃ) አለ።
ከነዚህም መረጃዎች ውስጥ
ሁለቱ "የሰይደቱ ዐይሻ"
(ረዲየላሁ ዐንሃ) ሐዲሶች (ተጠቃሽ ናቸው።)
1ኛው. ከነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጋር ሐጅ ያደረገች ጊዜ ከመካ ቅርብ እርቀት በሚገኘው "ሰሪፍ" የሚባል ቦታ ላይ ባረፈችበት የወር አበባ ደሟ በድንገት መጣባት ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምም) በርሷ ላይ
ገቡ። እርሷም የምታለቅስ ሆና አገኟት።
እርሳቸውም እንዲህ አሏት ፦
"ምን ሆንሽ ?" "ሐይድ" ሆነሽ ነውን ?"
እርሷም እንዲህ አለች ፦
" አዎ ! አንቱ የአላህ መልዕክተኛ (ኦኜአለው !)
እርሳቸውም እንዲህ አሏት ፦
" ይህ አሸናፊና የላቀው አላህ በአደም ሴት ልጆች ላይ የደነገገው ውሳኔ ነው።"
(በከዓባ ዙሪያ ጠዋፍ ከማድረግ ውጪና ሶላት ከመስገድ ውጪ ሐጅ ላይ የሚሰራውን ስራ ሁሉ ስሪ ! "
✅ ከዚህ ሐዲስ የሚያመሳክርልን (መረጃ የሚሆንልን) ነገር ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከመስጂዶች ሁላ ታላቅ የሆነውን መስጂድ እንድትገባ አልከለከሏትም !!! ይህም ቦታ "መስጂደ አል-ሐረም" ነው። የከለከሏት ደሞ ጠዋፍ እንዳታረግና ሶላት እንዳትሰግድ ነው !!!
👉 ይህ መሆኑ ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለዐይሻ ወደ "መስጂደ አል-ሐረም" እንድትገባ የፈቀዱላት ለመሆኑ መረጃ ነው። ነገር ግን ጠዋፍ ከማድረግና ሶላት ከመስገድ ከለከሏት !!!
👉 እንግዲህ ይህ የመጀመሪያው ሐዲስ የሚያመላክተው ነገር አንዲት "ሐይድ" ላይ ያለች ሴት መስጂድ መግባት የሚቻልላት መሆኑን ነው።
✅ የትኛውም መስጂድ ቢሆን (መግባት) ይቻላል።
በእርግጥም ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለ"ሰይደቱ ዐይሻ" (ረዲየላሁ ዐንሃ) "ሐይድ" ላይ ሆና ወደ "መስጂደ አል-ሐረም" እንድትገባ ፈቅደውላታል።
ሶላት መስገድና ጠዋፍ ማድረግን እንጂ አልከለከሏትም !!!
👉 መስጂድ የመግባቱ (የመቻሉ) "ሑክም" ድንጋጌ ከ"መስጂደ አል-ሐረም" ውጪ ባሉ መስጂዶች ላይ የበለጠ ይሆናል።
2ኛው. ሐዲስ በድጋሚ ሰይደቱ ዐይሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ያወራችው ሲሆን... የመጀመሪያው ሐዲስ ሰሒሕ "ቡኻሪ" ውስጥ የተዘገበ ሲሆን ይህ ሁለተኛው ሐዲስ ደግሞ "ሙስሊም" ውስጥ ተዘግቧል።
እርሷም እንዲህ አለች ፦
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አንድ ቀን እንዲህ አሏት። « መስገጃ (ጨርቅ ነገር) ከመስጂድ አቀቢኝ (ስጪኝ) » አሏት።
እርሷም እንዲህ አለች ፦
" አንቱ የአላህ መልዕክተኛ እኔ ሐይድ ሆኜአለሁ። "
እሳቸውም እንዲህ አሏት ፦
« ታዲያ እኮ ሐይድሽ በእጅሽ ላይ አይደለም ! »
👉 (በዚህ አባባላቸው) የተፈለገበት የወረ አበባ ደም ነው። የሐይድ ደም ደግሞ ያለጥርጥር "ነጃሳ" ነው !!!
👉 ይህ ሲባል ግን እራሷ (አካሏ) የተነጀሰ ነው ማለት አይደለም !!!
❌ ከአንድ ግለሰብ ላይ "ነጃሳ" ከሰውነቱ ውስጥ መውጣቱ ሙሉ አካሉ ተነጅሷል የሚለውን ነገር አያሲዝም !!!
✅ ይህ የሆነ ጊዜ ከሴቶች ውስጥ "ሐይድ" የሆኑ ዕንስቶች ሸሪዓዊ ዕውቀት የሚሰጥበት ቦታ መገኘት ይቻልላቸዋል። ቦታው ከፍ ካለውና የተቀደሰ ከሆነው አላህ ቤቶች ውስጥ ወደሆነ ቤት (መስጂድ) ውስጥም ቢሆን (መግባት ይቻላል።)
👉 (ሐይድ ላይ የሆነችው ዕንስት መስጂድ የመግባቷ) ሸሪዓዊ ፍርድ ከነዚህ ሁለት ትክክለኛ ሐዲሶች በመነሳት ድንጋጌው የፀና ይሆናል።
📚 ሲልሲለቱ አል-ሁዳ ወል-ኑር (623)
🖍️ ታላቁ ኢማም መሐመድ ነስረዲን አልባኒ
✍️ ትርጉም በኢስማኤል ወርቁ

ዘካተል ፊጥርን የሚመለከቱ ነጥቦች
~
1- ምንነቱ፦ ሙስሊሞች ከዒደል ፊጥር በፊት ለችግረኞች የሚሰጡት የእህል / የምግብ ሶደቃ ነው።
2- ሑክሙ፦ በሚችል ሰው ላይ ግዴታ ነው። [አልቡኻሪይ፡ 1503] [ሙስሊም፡ 984]
3- በማን ላይ ነው ግዴታው?
3.1. በትንሽ በትልቁ፣ በሴት በወንዱ፣ በሁሉም ሙስሊም በሆኑ የቤተሰብ አባላት ቁጥር የሚወጣ ሶደቃ ነው።
3.2. ገና ያልተወለደ ፅንስ እዚህ ግዴታ ውስጥ አይገባም።
3.3. አንድ ሰው የሌሎችን ዘካተል ፊጥር (ለምሳሌ ከሱ ጋር ያልሆኑ ቤተሰቦቹን ወይም የአገልጋዮችን) ማውጣት ይችላል። ግን እንደሚያወጣላቸው ማሳወቅ ይገባል።
4- ምን ያህል አቅም ባለው ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው? ለራሱም ለቤተሰቡም ለዒድ ሌሊትና ቀን የሚበቃ ቀለብ ባለው ላይ ግዴታ ነው።
5- ለማን ነው የሚሰጠው? የእለት ጉርስ ለሌለው ድሃ።
5.1. ዘካ እና ዘካተል ፊጥር የሚስሰጠው ለሙስሊም ብቻ ነው። ሌሎች ሶደቃዎችን ሙስሊም ላልሆኑ አካላት መስጠት ይቻላል።
5.2. ሑክሙን ባለማወቅ ወይም የሚግገባው አካል ስለማያገኙ ለሰራተኞቻቸው ዘካተል ፊጥር የሚሰጡ ሰዎች አሉ። ሰራተኞቻቸው የማይገባቸው ከሆኑ የተሰጣቸውን ለሚግገባቸው አሳልፈው መስጠት ይኖርባቸዋል።
6- የሚሰጡ የእህል / የምግብ አይነቶች፦ ተምር፣ ዘቢብ፣ አይቤ እንዲሁም በሃገር በአካባቢው ለቀለብነት የሚውሉ፣ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይበላሹ መቆየት የሚችሉ እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍ፣ ወዘተ. ያሉ የእህል / የምግብ አይነቶች ሁሉ ይገባሉ። ምክንያቱም "ከምግብ አንድ ቁና" የሚል ሐዲሥ አለና። [አልቡኻሪይ፡ 1508] [ሙስሊም፡ 985] በዒዱ እለት መመገብ የሚችሉት አይነት ቢሆን ተመራጭ ነው።
7- መጠኑ፦ አንድ ቁና (ሷዕ) ነው። በአራቱ ኸሊፋዎች ዘመን በዚህ መልኩ ነው ሲፈፀም የኖረው።
7.1. በራስ ፈቃደኝነት ጨምሮ መስጠት ይቻላል።
7.2. የሚስሰጠው መጠን በኪሎ ግራም:- በሐዲሥ የመጣው በስፍር ስለሆነ የክብደት መለኪያ ስንጠቀም እንደ እህሉ አይነት መጠኑ ይለያያል። ወደ ኪሎ ሲቀየር ዱቄት ላይ 2.5 ኪሎ አቅራቢያ ይመጣል። ይሄ የአንድ ሰው መጠን ነው። 10 ቤተሰብ ያለው ሰው 25 ኪሎ ማለት ነው።
8- ጊዜው፦ ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻ እለት ተጠናቆ የዒዱ ሌሊት ሲገባ ነው። ልብ በሉ! በኢስላማዊው አቆጣጠር የአንድ እለት ቀዳሚው ክፍል ቀኑ ሳይሆን ሌሊቱ ነው።
8.1. ከዒድ ሶላት ማሳለፍ አይፈቀድም። ረስቶ በጊዜው ያላወጣ ሰው ሲያስታውስ ቢሰጥ ወንጀል አይኖርበትም። አውቆ ወይም ችላ ብሎ ወቅት ካሳለፈ ግን ወንጀል ላይ ወድቋል። ቢሆንም ግን የድሃ ሐቅ ስለሆነ ወቅቱ ቢያልፍም ሊያወጣ ይገባል።
8.2. ተቀባዩ በመራቁ የተነሳ በእለቱ ለማድረስ የሚቸገር ሰው "የት ላድርግልህ?" ብሎ ይጠይቅና ከወከለበት ቦታ ያደርግለታል። በዚህን ጊዜ በእለቱ ባይወስድም ችግር የለውም።
8.3. አስቀድሞ መስጠት ይቻላል? ለሚሰበስቡ አካላት አንድ ቀን ሁለት ቀን ቀድሞ መስጠት ይቻላል። ከዚህ ውጭ በጊዜው መስጠት እየተቻለ ቀደም ብሎ መስጠት አይገባም። ነገር ግን በእለቱ ለመስጠት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲኖሩ ትንሽ ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል። እንዲሁም በውጭ ሃገራት ያሉ ሰዎች ለሚሰጥላቸው አካል ቀደም ብለው ገንዘቡን በመላክ እህሉን ማስገዛት ይችላሉ። ወኪሉ ግን በተቻለ መጠን ወቅቱን መጠበቅ አለበት።
9. ከቤተሰብ ርቃችሁ ለምትገኙ ተማሪዎች ወላጆቻችሁ ዘካተል ፊጥር የማያወጡላችሁ ከሆነና የማውጣት አቅሙ ካላችሁ ዘካተል ፊጥር ማውጣት እንዳትረሱ።
10. አስገዳጅ ወይም አንገብጋቢ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር በገንዘብ ማውጣት አይቻልም።

#በዚህ_በተከበረ_ወር_ካልተስተካከልን_መቼ_ነው...
🔷🔷 #መቼ_ነዉ ❓❓❓
🔺መቼ ነው ☞ እውነተኛ ሙስሊሞች የምንሆነው?
🔻መቼ ነው ☞ አላህ በፈጠራቸው ነግሮች የምንማረከው?
🔺መቼ ነው ☞ አሏህ ለምን እንደፈጠርን የምንረዳው?
🔻መቼ ነው☞ አሏህ እንደሚፈልገው መኖር የምንጀምረው?
🔺መቼ ነው☞ ስለ ሀይማኖታችን በሙሉ ልብ እምንናገረው?
🔻መቼ ነው☞ እማይጠቅም ንግግር ከመናገር የምንቆጠበው?
🔺መቼ ነው☞ ሀዲስና ቁርአን ስንሰማ የምንደነግጠው?
🔻መቼ ነው☞ ለመልካም ስራ ሰበብ የምንሆነው?
🔺መቼ ነው☞ በሰላታችን የምንጠቀመው?
🔻መቼ ነው☞ ዱአችን ተሰሚነት የሚያገኝው?
🔺መቼ ነው☞ ዲናችንን የምንረዳው?
🔻መቼ ነው☞ ውሎና አዳራችን በሱና የሚሆነው?
🔺መቼ ነው☞ ሙሉ በሙሉ በአሏህ ላይ የምንመካው?
🔻መቼ ነው☞ የዱንያን ትልቅነት ከልባችን የምናወጣው?
🔺መቼ ነው☞ ቤታችን ውስጥ ያለው የተበላሸ ሂዎት የሚስተካከለው?
🔻መቼ ነው☞ ቤታችን ውስጥ ቁርአንና ሀዲስ የሚቀራው የሚወራው?
🔺መቼ ነው☞ ውሽት እምናቆመው?
🔻መቼ ነው☞ የአሏህን ውሳኔ መቃውም እምናቆመው?
🔺መቼ ነው☞ እኔ እኔ ማለት ትተን ውንደሜ እህቴ ማለት እምንጀምረው?
🔻መቼ ነው☞ ለሰዎች ከአላህ ውጪ ጌታ እንደሌለ እምንናገረው?
🔺መቼ ነው☞ በኛ ዘመን በዲናችን የበላይነት ምናገኝው?
🔻መቼ ነው☞ የኢስላም ዘቦች የምንሆነው?
🔺መቼ ነው☞ ኢስላምን የምናስተዋውቀው?
🔻መቼ ነው☞ ለድሃ እምናዝነው?.
🔺መቼ ነው☞ ትዳራችን ስላም ሚያገኝው?
🔻መቼ ነው☞ የጋብቻን ጥቅም ተገንዝበት ለትዳር የምንቻኮለው?
🔺መቼ ነው☞ ዱአቶቻችን ለገጠሩ የሚጨነቁት?
🔻መቼ ነው☞ ከሀሜት : ሰውን ከመበድል: ክማስቀየምና ከማማት እምንላቀቀው?
🔺መቼ ነው☞ ወላጆቻችንን እምናስደስተውና እምንታዝዝው?
🔻መቼ ነው☞ ያልተጣራ ውሬ ካማውራት እምንቆጠበው?
🔺መቼ ነው☞ ለአሏህ ብለን እምንዋደደው?
🔻መቼ ነው☞ አሏህ በወሰነልን ነገር ደስተኞች የምንሆነው?
🔺መቼ ነው☞ የሌሊት ሰላትንና ዚክርን የምንላመደው?
🔻መቼ ነው☞ የበድለንን ይቅር የመንለው?
🔺መቼ ነው☞ ከራስ ወዳድነት እምንላቀቀው?
🔻መቼ ነዉ ☞ ከሞት ቡኃላ ላለው ሂወት ስንቅ እምናዘጋጀው?
🔺መቼ ነው☞ ኡለማዎቻችንን እምናከብረው?
🔻መቼ ነው☞ ለእውቅት ጊዜ የምንሰጠው?
🔺መቼ ነው☞ ባወቅነው የምንሰራው?
🔻መቼ ነው☞ የምንሞትበትን ቀንም ይሁን ስፍራ እንደማናውቅ ተገንዝበን በተጠንቀቅ የምንቆመው?
🔺መቼ እረ መቼ ነው☞ ኢስላምን የምንኖረው?
🔻መቼ ነው ☞ ለእነዚህ ተግባራዊ መልስ የምንመልሰው?
🤲አሏህ ያግራልን🤲
ለጓደኞቻችሁ ላኩላቸው
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል" ረሱል (ﷺ)
@yasin_nuru <> @yasin_nuru

#ዛሬ_ማታ_እኮ_ረመዳን_27_ነው_መተኛት_የለም_ኢንሻአላህ!
~
🌟🌟 ስለ ለይለተል ቀድር የትኛውም ቁጥር ቢገመት የ27ኛዋ ግን ይለያል🔥🔥 ከየትኛውም ሌሊት በተለየ ከፍ ያለ ግምት ይሰጣታል።💥💥
💫💫 ይቺን ሌሊት ፈፅሞ ዘንግቶና ቸልተኛ ሆኖ ማሳለፍ አይገባም።
✨✨ ስለዚህ ለክብደቷ የሚመጥን ትጋት ይኖረን ዘንድ እንዘጋጅ። ሶላት፣ ቁርኣን መቅራት፣ አዝካር፣ ድምፅን ዝቅ፣ ቀልብን ስብር አድርጎ ደግሞ ደጋግሞ በዱዓእ የሙጥኝ ማለት ያስፈልጋል።🌙🌙
*""(በለይለተል ቀድር)""የሚደረግ ዱዓ_*
አዒሻ (ረዐ) ባስተላለፉት ሐዲስ መሰረት #የአላህ_መልእክተኛ_ሆይ🥰! ለይለቱል ቀድር ቢገጥመኝ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ስላቸው፣
_*اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني*_
_አላሁመ ኢንነከ ዐፉውን ቱሒቡል_ዐፍወ ፈአዕፉ አኒ በይ" አሉኝ። (ቲርሚዚይ ዘግበውታል )🤲🥺
#ትርጉሙ....
*""‘አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ። ይቅርታንም ትወዳለህ። ይቅር በለኝ!፤""* ማለት ነው🤲🤲

ረመዳን አላለቀም። በቀሩት ጥቂት ቀናት ውስጥ በኸይር ስራ መሽቀዳደም ይገባል።
ለዋጂቡ ቅድሚያ ይስጡ። የገንዘብዎን ዘካ ችላ አይበሉ። የሶላት ጉዳይ አደራ። ዘካተል ፊጥር ባግባቡ ያውጡ።
የኛን እጅ የሚጠብቁ ቤተሰቦቻችንን ሐቅ አላህ ባገራልን እናሟላ። ችላ ያሉት እዳ ካለ በጊዜ ያወራርዱ።
ከዚያ ባሻገር የወሩ ትሩፋት እንዳያልፈዎት በሌሎችም ኸይር ስራዎች ይቻኮሉ።
የታመመን ማሳከም፣ የተራበን ማብላት፣ የታረዘን ማልበስ፣ ፆመኛን ማስፈጠር፣ የመስጂድ ግንባታ ላይ መረባረብ፣ ወዘተ.
ከወትሮው በተለየ ረመዳን ላይ የእርዳታ ውትወታው የሚበረታው የአማኞች ልብ ይረጥባል ተብሎ ስለሚጠበቅ ነው።
ስለዚህ የታማኝነት ጥርጣሬ እስከሌለ ድረስ ለተማፅኖዎች ቦታ በመስጠት የራስን አስተዋፅኦ ማበርከት ለቻለ ሰው ትልቅ መታደል ነው።
#ችግረኛን_እንደመርዳት_ግን_ምን_የሚያስደስት_ነገር_አለ?
አላህ ሃብት ሰጥቶን ኸይር የተባለ ነገር ላይ የምንሳተፍ ያድርገን🤲🤲 ያረብ🥰🥰 #አሚንንን

የነብዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ታሪክ ✍
❶) ጥያቄ፦የነብያችን (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስም ማን ይባላል ?
መልስ፦ ሙሃመድ ኢብኑ ዐብደላህ ኢብኑ ዐብደል ሙጠሊብ ኢብኑ ሀሺም ፡ሀሺም (ከቁረይሽ ጎሳ ሲሆኑ)፡ ቁረይሾች ደግሞ ከአረብ ናቸዉ አረቦች ደግሞ ከነብዩላህ ኢስማዒል(አለይሂ ሰላም) ዝርያ ናቸዉ።
❷), ጥያቄ፦ነብያችን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) መቼ ቀን ነዉ የተወለዱት ?
መልስ፦ ሰኞ ቀን ተወለዱ።
➌), ጥያቄ፦ ነብያችን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) የተወለዱት የት ሀገር ነዉ ?
መልስ፦የተወለዱት ሀገር(መካ) ነዉ።
➍),ጥያቄ፦ የነብያችን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) አባት የሞተዉ መቼ ነበር ?
መልስ፦ አባታቸዉ የሞተዉ በእናታቸዉ መህፀን ዉስጥ ሳሉ ነዉ።
➎), ጥያቄ፦ የነብያችን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቀልብ (ልብ)የተቀደደዉ መቼ ነበር ?
መልስ፥ ልባቸዉ የተቀደደዉ የአራት አመት ህፀን ሳሉ ነበር።
❻), ጥያቄ፦የነብያችን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) እናት የሞተችዉ መቼ ነበር ?
መልስ፦እናታቸዉ የሞተችዉ(የስድስት)አመት ህፀን ሳሉ ነበር)።
❼),ጥያቄ፦የነብያችኝ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እናት ከሞተች ቡሃላ አሳዳጊያቸዉ ማን ነበረ ?
መልስ፦አያታቸዉ(ዐብደል ሙጠሊብ)ከዚያ ኡሱ ከሞተ ቡሃላ አጎታቸዉ (አቡ ጧሊብ)።
➑),ጥያቄ፦ነብያችንን(ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) አላህ ነብይ አድርጎ የላካቸዉ መቼ ነበር ?
መልስ፥ በአርባ አመታቸዉ።
❾) ጥያቄ፦የነብያች(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ልጆች ስንት ናቸዉ ? ስማቸዉስ ?
መልስ፦ ሰባት ናቸዉ። ስማቸዉም፦
❶.ቃሲም
❷.አብደላህ
➌.እብራሂም
➍.ዘይነብ
❺.ሩቂያ
❻.ፋጢማ
❼.ኡሙ ኩልሱም...ይባላሉ

29
#ለይለቱል_ቀድር
#የመጨረሻዋ_የረመዳን_ወር_ጎዶሎ_ቁጥር_ዛሬ_ምሽት።
ከዛሬ ምሽት ቡኋላ መቼም ላናገኛት እንችላለን ወጥረን በኢባዳ እናሳልፍ!
አዒሻ (ረዐ) ባስተላለፉት ሐዲስ መሰረት #የአላህ_መልእክተኛ_ሆይ🥰! ለይለቱል ቀድር ቢገጥመኝ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ስላቸው፣
_*اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني*_
_አላሁመ ኢንነከ ዐፉውን ቱሒቡል_ዐፍወ ፈአዕፉ አኒ በይ" አሉኝ። (ቲርሚዚይ ዘግበውታል )🤲🥺
#ትርጉሙ....
*""‘አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ። ይቅርታንም ትወዳለህ። ይቅር በለኝ!፤""* ማለት ነው🤲🤲
@yasin_nuru @yasin_nuru
#ለይለቱል_ቀድር
#የመጨረሻዋ_የረመዳን_ወር_ጎዶሎ_ቁጥር_ዛሬ_ምሽት።
ከዛሬ ምሽት ቡኋላ መቼም ላናገኛት እንችላለን ወጥረን በኢባዳ እናሳልፍ!
አዒሻ (ረዐ) ባስተላለፉት ሐዲስ መሰረት #የአላህ_መልእክተኛ_ሆይ🥰! ለይለቱል ቀድር ቢገጥመኝ ምን ብዬ ዱዓእ ላድርግ? ስላቸው፣
_*اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني*_
_አላሁመ ኢንነከ ዐፉውን ቱሒቡል_ዐፍወ ፈአዕፉ አኒ በይ" አሉኝ። (ቲርሚዚይ ዘግበውታል )🤲🥺
#ትርጉሙ....
*""‘አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ። ይቅርታንም ትወዳለህ። ይቅር በለኝ!፤""* ማለት ነው🤲🤲
@yasin_nuru @yasin_nuru
🌙ማሌዥያ 🇲🇾🇲🇾🇲🇾
🌙 የዒድ አልፊጥር በዓል የምታከብረው ሰኞ መጋቢት 22/2017 እንደሚሆን ይፋ አድርጋለች።
🌙አውስትራሊያ🇦🇺🇦🇺🇦🇺
የሸዋል ወር የመጀመሪያ ቀን ሰኞ መጋቢት 22/2017 ነው ብላለች
🌙ኢንዶኔዥያ🇮🇩🇮🇩🇮🇩
ሰኞ መጋቢት 22 ብላለች