Telegram Web Link
በቀጥታ ስርጭት ግድያ - በሜክሲኮ አንዲት የ23 ዓመት ወጣት ጦማሪ በምታስተላልፈው የስርጭት ፕሮግራም ላይ ተገደለች

የውበት ሳሎን ባለቤት እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነችው ቫሌሪያ ማርኬዝ በኢንተርኔት ላይ ቀጥታ ስርጭት ላይ እያለች አንድ የሞተር ሳይክል የያዘ ሰው ወደ ሳሎኗ ቀረበ።

በጭካኔም ደረቷ ላይ ተኩሶ ገደላት። ተጨማሪ ተኩስ አከታተለባት።

ተጠርጣሪው ተይዟል፣ ምርመራም እየተደረገበት ነው ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
😭25👍12
በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና በተከታታይ ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች በሚያስመዘግቡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚፈቅደው መመሪያ ቅሬታ ቀረበበት፡፡

መመሪያው ግልፅ እና ያልተብራራ ነው ሲል የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማኅበር ቅሬታውን አሰምቷል፡፡

የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ገበየሁ፣ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ገቢራዊ የሆነው የቅድመ-ምረቃ እጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና አወጣጥ በትክክለኛ መንገድ ግምገማ ሳይደረግበት ዕርምጃ የሚያስወስድ መመሪያ ማውጣት አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡

በተለይ ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ትምህርት ጥራቱ ምን ይመስላል የሚለው መሠረታዊ ጉዳይ ሳይፈተሽ ወደ ዕርምጃ መገባቱ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከማቀጨጭና ከዘርፉ ከማስወጣት የዘለለ ምንም ዓይነት ሚና እንደማይኖረው ዋና ሥራ አስኪያጁ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

መመሪያው የተብራራ ስላልሆነ በድጋሚ እንዲታይ ማኅበሩ ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን ገልፀዋል፡፡

መመሪያውን በተመለከተም ሆነ ለሌሎች ጥያቄዎች ማኅበሩ ለትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢያቀርብም ምላሽ አለማግኘቱን ዋና ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል፡፡

"በተከታታይ ሦስት ጊዜ በመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ ዕርምጃ ይወሰዳል" የሚለው በተቋም ደረጃ ነው ወይስ በፕሮግራም (በዲፓርትመንት) ያስመዘገቡ ናቸው ለሚለው ጥያቄ መመሪያው ውስጥ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

"የከፍተኛ ትምህርት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፈቃድና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ" የሚል ስያሜ የተሰጠው መመሪያው፣ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ፈቃድ እንዲታደስለት ትምህርት ካጠናቀቁት ውስጥ የወቅቱ ተመራቂዎች ቢያንስ 25 በመቶ የሚሆኑት የመውጫ ምዘናን ፈተና ማሳለፍ ይኖርባቸዋል ይላል፡፡

በኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ቅበላ በተደረገላቸው ተማሪዎች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን በመመሪያው ተካቷል፡፡  #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
👍345👎3
በወቅታዊ የጤና አገልግሎት ዙሪያ ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መረጃ

የጤና ሚኒስቴር ለማኅበረሰባችን ጥራቱን የጠበቀ እና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመቅረጽ የኅብረተሰቡን ባለቤትነት ባረጋገጠ መልኩ ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑ የዐደባባይ ሐቅ ነው።

ምክንያቱም መቼምና በምንም ሁኔታ መቋረጥ ከሌለባቸው ማኅበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የጤና አገልግሎት በመሆኑ፤ ስለዚህም ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት በመላ ሀገራችን በሚገኙ የጤና ተቋማት እንደ ወትሮው ሁሉ መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ለማኅበረሰባችን ያለምንም መቆራረጥና መስተጓጎል እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡

ይሄንን የተረዳው የጤና ባለሞያ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ጫና ሳይገፋ የገባውን የሞያ ቃል ኪዳን እና መሐላ ጠብቆ ማኅበረሰቡን እያገለገለ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል፡፡

ይሁን እንጂ በጥቂት የማስተማሪያ የጤና ኮሌጆች/ተቋማት በመደበኛ የሥራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የተወሰኑ ባለሞያዎች እንዳሉ መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ ከእነዚህ የጤና ባለሞያዎች መካከል ብዙዎቹ በሐሰተኛ መረጃ የተወናበዱ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ ጥፋትን ዓላማቸው ያደረጉ ናቸው።

ድርጊቱ የራስን ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወገን እና መላውን ማኅበረሰብ ከመጉዳት ባለፈ ከሞያ ሥነ ምግባር፣ ከሰብአዊነት አኳያ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

ከሕግ አኳያም የጤና ሞያ የሥራ ማቆም አድማ ከማይደረጉባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑ በግልጽ ተደንግጓል። የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ እንኳን ቢኖራቸው በሥራ ገበታቸው ተገኝተው መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ ጉዳያቸውን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በመሆኑም እነዚህ የጤና ባለሞያዎች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው ማኅበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ በየተቋማቸው ጥሪ ተደርጓል።

መንግሥት የጤና ባለሞያውን ዘላቂ ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ለመስጠት ቀደም ብሎ የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1362 /2017 አጸድቆ ደንብና መመሪያዎችን በማውጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል።

በጎ ኅሊና ያላቸው የጤና ባለሞያዎች ይህንን በመገንዘብ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ያቀርባል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኅብረተሰቡ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በሚሠራጩ የሐሰት መረጃዎች ሳይረበሽ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት በተለመደው መልኩ በጤና ተቋማት ማግኘት እንደሚችል እናሳውቃለን ።

መንግሥት በሆደ ሰፊነት ችግሩን ለመፍታት ያሳየውን ትዕግሥት ወደጎን በመተው በሥራ ገበታቸው ላይ ባልተገኙ እንዲሁም በጤና ተቋሙም ሆነ ከጤና ተቋሙ ውጭ ሆነው ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩት ላይ አስፈላጊ የሆነ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ቀድመን እናሳውቃለን፡፡

የጤና ሚኒስቴር

@YeneTube @FikerAssefa
👎167👍46😁97
🛒 BUYING OLD GROUPS 🛒

ድሮ የከፈታችሁት Group Chat ነበር? Owner ከሆናችሁ ፣ History Visible ከሆነ እና Chat Clear ካልተደረገ እንገዛችኋለን!

👥2023 - 🇪🇹 200 ETB

👥2022 - 🇪🇹400 ETB

👥2021 - 🇪🇹450 ETB

👥2020 & 2019 - 🇪🇹500 ETB

👥2018 & 2017 - 🇪🇹600 ETB

Payment Methods:
🇪🇹Telebirr, Bank
Proofs - https://www.tg-me.com/OLDGPPROOF

ሜምበር ለውጥ አያመጣም 1ሺ ሜምበርም ሆነ 10 ዋጋው አንድ ነው.. የተከፈተበት አመት ላይ ብቻ Chat ይኑረው።

ለመሸጥ: @OldGroupBuyer_APX
👍31
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍5
🟢 SAMSUNG M16 5G 🟢 (NEW)

✔️storage 128gb
✔️Ram 6gb
✔️Dual

💵Price 25,000 Birr

🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺

😀 0942405669
✈️@Endalk4240

Join channel https://www.tg-me.com/phonestore_22
👍4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
900,000 ብር ምን መግዛት ይችላል?

መኪና? ቤት?

በዚህ ጊዜ 900,000 ብር ምንም መግዛት አይችልም ።

እኛ ጋር ግን በ900,000 ብር ሱቅ መግዛት ትችላላችሁ ።

ያውም እስከ 200,000 ብር መከራየት የሚችል ሱቅ።

ፒያሳ አድዋ ዜሮ ዜሮ አጠገብ 20 ካሬ ሱቅ አየሸጥን ነው።

ከግራውንድ እስከ 5ኛ ፎቅ።

ለሁለት ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው።

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ  (Direct/ Whatsapp) ፦ በ
0909253426 / 0940407294 ይደውሉ
👍31
በሩሲያ፣ ዩክሬን እና ቱርክ መካከል የሚደረገው የሶስትዮሽ ስብሰባ 3:30 ላይ በኢስታንቡል እንደሚካሄድ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልፅዋል።

@Yenetube
7👍7
አንድ ኮርያዊ ሰው ከአንዲት ፊሊፒንሳዊት እናት የጡት ወተት በመግዛት ሲጠጣ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ቁጣን ቀስቅሷል

በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች የተጋራው ቪድዮው ግለሰቡ በመንገድ ላይ የነበሩ እናቶች ጋር በመሄድ 500 ፔሶ ወይንም ዘጠኝ ዶላር ገደማ በመክፈል የጡት ወተታቸውን እንዲሸጡለት ሲጠይቅ ይታያል።

ነዋሪነቱ በፊሊፒንስ የሆነው ደቡብ ኮርያዊው የማህበራዊ ሚድያ አንቂ በከፍተኛ ሁኔታ በሚታወቅባቸው ትስስር ገፆች ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ይህ የሆነውም የእናት ጡት ወተት በመግዛቱና በመጠጣቱ ምክንያት ነው ተብሏል። ጉዳዩ የተከሰተው እኤአ ሜይ 9 ምሽት ላይ ሲሆን በሰዓቱም JTBC የተሰኘ አንድ መገናኛ በዙሀን ከ4.5 ሚልየን በላይ ተከታዮች ባሉት የማህበራዊ ትስስር ገፁ የግለሰቡን ድርጊት ማጋለጡን ተከትሎ ነው።

ከ4ሺ በላይ የተለያየ ይዘት ያላቸው ቪድዮዎችን በመስራት ለተመልካቾች በማቅረብ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው ግለሰቡ ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም በቀረፃቸውና በለጠፋቸወሸ ከ30 በላይ ቪድዮዎቹ የእናት ጡት ወተት ሲገዛና ሲጠጣ የሚታይ ቢሆንም ብዙም ትኩረት ሰጥቶ የተመለከተው ሰው አልነበረም። አሁን ግን JTBC የተሰኘው ጣብያ በሰራው የምርመራ ዘገባ የግለሰቡን ድርጊት ለማጋለጥ ቢቻልም ማንነቱ ግን እስካሁን ይፋ አለመደረጉ ተገልፆል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍174👎1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አደጋ ውስጥ ነው

የፕሪቶሪያ ስምምነት “አደጋ” ውስጥ ነው ሲሉ የዩኤስ የፖሊሲ ኤክስፐርት ለሴኔቱ አባላት ገለፁ።


May 13/2025 በሴኔቱ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ በምስራቅ አፍሪካ ላይ ያተኮረ ችሎትን በተመለከተ ንግግር ያደረጉት የውጭ ግንኙነት ምክር ቤት ባልደረባ ሚሼል ጋቪን በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ያለውን ደካማ የሰላም ሁኔታ አስጠንቅቀዋል።  ይህም የፕሪቶሪያ ስምምነት አተገባበር ላይ እንቅፋት ነው ብለዋል።
ዩኤስ አሜሪካ ምን “ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ አለባት” በሚል ለሴናተር ቫን ሆለን ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት ከሞላ ጎደል እየከረረ ያለውን ሁኔታ ለመቅረፍ” ሲሉ ሚሼል ከዚህ ቀደም በሃድሰን ኢንስቲትዩት ባልደረባ ጆሹዋ መሰርቪ የተነሱትን ስጋቶች አስተጋብተዋል። እንደዋነኛ ስጋት የተነሳው የኤርትራ መንግሥት ስምምነቱን በመጣስ  በትግራይ ክልል ውስጥ የኤርትራ ጦር መስፈሩን አንስተዋል።

በትግራይ ክልል ለሁለት አመታት የቆየውን አስከፊ ጦርነት ያበቃው የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጫና ማድረግ እንደሚያስፈልግ ሁለቱም ባለሙያዎች ገልፀዋል።

ሚሼል "ይህ የፕርቶሪያ ስምምነት ሁለቱም ተፋላሚ ኃይሎች  የተስማሙበት ቢሆንም ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አልተተገበረም ብለዋል።

አሁን ላይ ስምምነቱ አዲስ አደጋ ገጥሞታል ያሉት" ሚሼል የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ተሳትፎ እንዲጨምር" ጠይቀዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍343👎1
በወላይታ ሶዶ ከተማ በተከሰተ የመኪና አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ!

መነሻውን ከሐዋሳ ያደረገ አይሩፍ መኪና የድንጋይ ከሰል ከጫነው መኪና ጋር በመጋጨቱ ምክንያት አደጋው ሊከሰት የቻለ ሲሆን የአደጋው መንስዔ እየተጣራ ይገኛል።

መነሻውን ሀዋሳ ከተማ ያደረገ ዶልፍን የሕዝብ ማመለሻ መኪና ኮድ ሲ.ዳ/S.D/ ታርጋ ቁጥር 04178 እና ተሳቢ የጭነት መኪና ኮድ /ET/ ኢት/ ታርጋ ቁጥር 36646 የሆነ የድንጋይ ክስል በመጫን ወላይታ ሶዶን በማቋረጥ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ መኪና ጋር በመጋጨት በሰውና በንብረት ላይ የሞትና ከባድ የትራፊክ አደጋ ከጥዋቱ 1:00 አከባቢ የተከሰተ ስሆን እስካሁን የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ ታውቀዋል።በአደጋው የተጎዱት በከተማዋ በሚገኙ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
😭34👍82
ሀዋሳ ኢንተርን ሀኪሞች እና ሬዚደንቶች እንዲወጡ በታዘዙት መሠረት ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ ይገኛሉ!

የዩኒቨርስቲ ነባር ጤና ባለሙያዎች ይሁን ኢንተርን ተማሪዎች፤ ከአቋማችን ፊንክች አንልም ብሎአል። በዚህ በአቋማቸው ምክንያት አገዛዙ ግቢውን ለቆ እንዲወጡ ባዘዘው መሰረት ለቆ ወደቤታቸው እየሄዱ ይገኛሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
🔥53😭26👍155👀3
🎁 Shamo of 500 ETB Airtime! 🎁

On May 16, 2025 at 18:00 (UTC), 🤖 HuluPay will randomly choose 10 winners who will will share 500 ETB in Airtime! 💰

To take part in this shamo:
Join all 2 channels
1. @yenetube
2. @hulujackpot
Click the "Join Shamo" button below

Don't miss your chance to win!
6👍6
📒 ውድ የ International Student Community እና Refocus Africa ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ 🎉

International Student Community ከ Refocus Afrika ጋር በመተባበር የፊታችን 🗓 May 24 እና 25 ( ግንቦት 16 እና 17) ልዩ የ Cultural Exchange እንዲሁም የ Scholarship Process Guidance 🎆ይዞላችሁ መቷል !!!

🗺️ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 kilo Alamudin ህንፃ አዳራሽ 🏚️
ከ ጠዋቱ 2:00 እስከ 11:00 ሰአት

ትምህርታቹን ውጭ ሀገር ሄዶ የመማር ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችሁአል።

፨ በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ በማስተርስ እንዲሁም በዶክተሬት ዲግሪ👨🏾‍🎓

በዕለቱ ሲገኙ ፦
📕ፓስፖርት/ የልደት ሰርተፍኬት
📝ትራንስክሪፕት ይዘው መምጣት እንዳይረሱ

🌍የዚህ እድል ተሳታፊ በመሆን የወደፊት የትምህርት ጉዞዎን ይጀምሩ✈️

ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ ፧‼️

ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ #ይጫኑ 👇👇
https://forms.gle/SJ6nzXdNAixTptGv5

Join our telegram channel
➡️ https://www.tg-me.com/isc_italy
👍51
YeneTube
Photo
እስካሁን 78 ሃኪሞች ታስረዋል

ዛሬ አራተኛ ቀኑን የያዘውን የጤና ባለሞያዎች ከፊል የስራ ማቆም አድማን ተከትሎ የታሰሩ ባለሞያዎች ብዛት 78 መድረሱ እንዲሁም በባለሞያዎቹ ላይ እየደረሰ ያለው እስር እና እንግልት ተጠናክሮ መቀጠሉን ታውቋል። 

መሠረት ሚድያ ዛሬ በደረሰው መረጃ በተለይም ትላንት ለሊት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የጸጥታ ሃይሎች ወደሃኪሞች መኖሪያ በመግባት የህጻናትና የካንሰር ስፔሻሊስትን ጨምሮ 25 ሬዝደንትና ስፔሻሊስት ሃኪሞችን አፍነው መውሰዳቸው ታውቋል፣ እስካሁንም የደረሱበት አልታወቀም።

ይህንና ተመሳሳይ አፈናና እንግልትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች ንቅናቄ አባላት ሙሉ ለሙሉ ስራ ለማቆም በመወሰናቸው አሁን ላይ በህክምና ላይ ያሉ ታካሚዎች በማይንገላቱበት መንገድ እስከ ነገ ቅዳሜ ድረስ ሙሉ ለሙሉ ስራ የማቆም አድማውን ተፈጻሚ የሚያረግ ፕሮግራም አውጥተው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ታውቋል።
ሆኖም እስካሁን አፈናና እንግልት በደረሰባቸው እንደ ጥቁር አንበሳና ዘውዲቱ የመሳሰሉ ሆስፒታሎች ውስጥ የሚሰሩ ባለሞያዎች ሙሉ ለሙሉ ሰራ ማቆማቸው ተሰምቷል።

በተመሳሳይ በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል በአስተዳደር ሃኪሞች ወደስራ ገበታቸው ካልተመለሱ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የተሰጠውን ማስታወቂያ ተከትሎ የሆስፒታሉ ሬዝደንትና ኢንተርን ሃኪሞች ከግቢው የተቀበሉትን ንብረት በማስረከብ ለቀው እየወጡ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ጤና ባለሞያዎች በዚህ ንቅናቄ ጊዜውን ያማከለ እና ለመኖር የሚያስችል የደመወዝ ጭማሪ፣ የሪስከና የመሳሰሉት ከፍያዎች መፈጸም፣ የትራንስፖርት እገዛ፣ ጊዜውን የጠበቀ እና ያልተቆራረጠ የduty ክፍያ፣ ባለሞያውን ለአደጋና እንግልት የማያጋልጥ የስራ ቦታ፣ የጤና መድህን፣ የመኖሪያ ቤት ወይም ቦታ እንዲሁም ለትምህርት የሚመችና በደንብ የተደራጀ የመማሪያ ስፍራ እና በአጠቃላይ 12 የሆኑ ጥያቄዎቻቸው እንዲመለሱላቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።

የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ ትናንት ባወጣው መግለጫ ከሰሞኑ የስራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የጤና ባለመያዎች 'በሐሰተኛ መረጃ የተወናበዱ' እና 'ጥፋትን ዓላማቸው ያደረጉ' ናቸው ማለቱ ይታዋሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
👍58👎117😁7
🎉 Shamo Results! 🎉

The shamo in @yenetube has ended, and 10 winners have been selected to share 500 ETB in airtime!

Winners:
1. @abe1812 - 50 ETB
2. Rich - 50 ETB
3. @Wenda1627 - 50 ETB
4. @tadesse12345678 - 50 ETB
5. @Rcboy321 - 50 ETB
6. @shumkine - 50 ETB
7. Berket🐾🌱SEED - 50 ETB
8. @Sudi_5 - 50 ETB
9. @TARETYT - 50 ETB
10. @Wizkale - 50 ETB

Congratulations to all winners! 🎊 Winners will be contacted to claim their prizes.
👍20👎43👀1
በ490,000 ቅድመ ክፍያ  በመሀል ካዛንቺስ  የቤት ባለቤት ይሁኑ ‼️

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አያት ካዛንቺስ መንደር

እጅግ ውብ ዕይታ ያላቸው ቤቶች

ከ 1 መኝታ እስከ ባለ 4 መኝታ
👉ባለ አንድ መኝታ 45, 55 ,60 ካ.ሜ
👉ባለ ሁለት መኝታ  80,ካ.ሜ
👉ባለ ሶስት መኝታ  95,105,115 ካ.ሜ
👉ባለ አራት መኝታ  140  ,160 ካ.ሜ

✍️ ቅድመ ክፍያ 10%
📹 (ከ490,000ብር ቅድመ ክፍያ  ጀምሮ)

❇️  በ 18 ወራት የሚረከቡት ቤት💁

      

       📍በግቢው ዙሪያ

   ➾ፓርኮች ና የወንዝ ዳር ልማት
    ➾አለማቀፍ ት/ቤትና ሆስፒታል
    ➾የእምነት ተቋማ

       📍የቤቶቹ እይታ

    ➤ ወደ ቤተ መንግስት ( ጊቢ ገብርኤል )
    ➤ ወደ ያካ ተራራ ጫካ
    ➤ ወደ ወንዝ ዳር ልማት
    ➤ ወደ ወዳጅነት ፓርክ

👉 ቀድሞ ለመጣ ቅድሚያ ይስተናገዳል

❇️  ከሀገር ውጭ ያላችሁ ደንበኞች በወኪል መግዛት እንደምትችሉ እናሳውቃለን ።

ለምዝገባ 📲 0950123353 ወይም
በ whatsapp :-https://wa.me/251950123353
አሁኑ ይደውሉ
👍10
2025/07/09 11:27:05
Back to Top
HTML Embed Code: