Warning: mkdir(): Permission denied in /var/www/bootg/function.php on line 101

Warning: file_put_contents(aCache/detail/y/e/t/b/yetbeb.txt): Failed to open stream: Permission denied in /var/www/bootg/function.php on line 103
ከጥበብ የተመረጠ ጥበብ - Telegram Web
ራሳችንን ለማሻሻል የሚረዱን መጽሀፍ ናቸው የተጻፈ ሁሉ እውነት አይደለም እየለየን በጥበብ እየመረመርን እናንብብ መልካም ንባብ @yetbeb
ከሞት ያልተናነሰ ሕይወት!

• እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስ የምንከተለው ዓላማ ሳይኖረን መኖር!

• ራሳችንን፣ ዓላማችንንና ስራችንን በማሻሻል ላይ ከማተኮር ይልቅ ስለሰዎች ስናስብና ስናወራ መኖር!

• ቢያንስ በአንድ ሰው ላይ መልካም ተጽእኖ ሳያሳድሩ መኖር!

• በየእለቱ ሳይለወጡ ሁልጊዜ በአንድ አይነት አመለካከት፣ ስፍራና ልምምድ እየረገጡ መኖር!

• መንቀሳቀስ እስከማንችን ድረስ በፍርሃት ታስሮ መኖር!

• በሰዎች ላይ ቂም ይዘን እነሱን ካልተበቀልን በስተቀር ውስጣችን አላርፍ እያለንና እየነደደ መኖር!

• አንድ ሰው ስለገፋንና ትቶን ስለሄደ ብቻ ነገን ማየት እስከማንችል ድረስ የወደቀ ስሜት ይዞ መኖር!

• እንደዚህ አይነት አነቃቂ መልእክት ከሰሙና ካነበቡ በኋላ ከመፈክር ባላለፈ ሁኔታ ለውጥን ሳናመጣ ራሳችንን እዚያው ነገር ላይ እያገኙ መኖር!

@yetbeb
እይታ-እዮብ ማሞ.pdf
8.5 MB
ሰው በአመለካከቱ ወደ መሆን ያመጣውን ሁኔታ ለማጥፋት ሲታገል የሚኖር ፍጡር ነው። "ሁኔታዬ መለወጥ አለበት" የሚል የማያቋርጥ ትግል ሲታገል ይታያል። ያንን ሁኔታ ወደ መሆን ያመጣውን አመለካከቱን እና ዕይታውን ግን መለወጥ አይፈልግም። ይህ ሁኔታውን ወደ መኖር ያመጣው አመለካከቱ በውስጡ እንዳለ ላያስተውለው እራሱ ይችላል።
አለማወቅ ግን ከውጤቱ እንዲያመልጥ ሊያደርገው አይችልም።
አመለካከቱን ሳይለውጥ ሁኔታውን ለመለወጥ የሚያደርገው ጥረት ከንቱ ስለሆነ በሁኔታው እንደታሰረ ይኖራል።

ዶ/ር እዮብ ማሞ
"ዕይታ"
ከተሰኘው መፅሃፍአቸው የተወሰደ @yetbeb
#አልተዘዋወረችም

አንዳንዴ፣ ያለፍኩበትን ከንቱነት ገና ሊጀምሩት የሚራኮቱ ጀማሪ ጅሎችን ስመለከት የሆነ የግሌ ሬዲዮ ጣቢያ መክፈትና ከጧቱ አስራ ሁለት ሰዓት ላይ በጎርናና ድምፅ "ይህ የጅሎች ድምፅ ነው! እንደምን አደራችሁ ጅሎች?" ማለት ያምረኛል።

ሁሉም ከእኔ ወዲያ ብልጥ ላሳር የሚባልባት አገር ዜጋ ነኝና ማንም መልስ አይሰጥም፤ ይኼንን ዝምታ ከብልጠት ይቆጥሩታል።

እኔም "ዝምተኛ ነኝ" ስልና "ዝምተኛ ነው" ስባል ነበር የኖርኩት።

ጅልነት የተደላደለ መኖሪያው የዝምታ ባህር ውስጥ መሆኑ የገባኝ ቆይቶ ነው "ጅል ዝም ቢል ብልህ ይመስላል!" ይባል የለ።

በጊዜ ፈውስ እንዳናገኝ ቂል ነፍሳችንን በዝምታ ብልህ ስናስመስል መኖርን በተረት፣ በአሽሙር እና በዘፈን አስተማሩን (ተማማርን ማለት ይሻላል!) ዝምታና ማድበስበሱ ብልህ ያስመሰለው የጅል አገር ዜጋ ነኝ።

ከአሌክስ አብርሀም

@yetbeb
የሀብት መንገድ .pdf
15.5 MB
የሀብት መንገድ / Rich Dad Poor Dad በሮበርት ኪዮላኪ

ሀብታሞች ለልጆቻቸው ስለገንዘብ የሚያስተምሯቸው ድሆችና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የማያውቁት ምስጢር!!

ትርጉም :- ብርሃኑ በላቸው

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩት
Best Amharic books PDF

@yetbeb
አስተውል ይሄ እውነታ ነው ‼️

• ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም !ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ ።

• ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ! ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ ።

• ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም ! በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ ።

• አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም !ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ ።

• ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም ! በሆድ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ ።

• ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም !ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ ።

• ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ! ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ ።

• ስራህን ወደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ! ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ወደድ ማለት እንጂ ::
የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ .pdf
16.8 MB
📚ርዕስ:- የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ
📝ደራሲ:- ዶ/ር እዮብ ማሞ
📜ዘውግ:- ሳይኮሎጆ
📅ዓ.ም:- 2012
📖የገፅ ብዛት:- 152
@yetbeb
አልኬሚስቱ..pdf
27.8 MB
ልቦለድ በሚመስል ታሪክ ውስጥ የሰውን ንጹህ ፍላጎት እጣ ፋንታና ለስኬትና ለህልሙ የሚያደርገውን ጉዞ ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ብዙዎች ይሄንን አንብበው እንደተተቀየሩ የመሰከሩለት ጥሩ መጽሀፍ ነው ይነበብ
💥ፅናት💥

💫በስንፍና ወይም በፍርሃት ፣በተፈጥሯዊ ተግዳሮት ወይም በሰው ሰራሽ ፈተና ሳንበገር በእውቀታችን መሠረት ተግባራችንን የመምራት ፅናት ማዳበር ይገባል።

💫ለእውነታ ታማኝ የመሆን አስተዋይነት ያስፈልገናል።

💫እውነታ ላይ ተመስርተህ እውቀት መገንባት ፣ በእውቀት ላይ ተመስርተህ መምረጥና መወሰን፣ በውሳኔህ ላይ ተመስርተህ መፈፀም ከተጨባጭ ተግባር አንፃር ለእውነታ ታማኝ መሆን ነው ።

💫ድርጊትና ተግባር የእውነታ ውጤት ነው።


ሰላም ዋሉ

"መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
@yetbeb
#ታንኮራፊያለሽ!

አንድ ሰው  የሚስቱ ማንኮራፋት ይረብሻቸዋል። እና ሁሌ "በጣም ስለምታንኮራፊ ልተኛ አልቻልኩም " ይላታል። እሷም አታምነውም ነበር ። ከዛም አንድ ቀን ስታንኮራፋ  ሪከርድ አረጋት ። በማግስቱ ግን ድጋሜ  ከእንቅልፏ አልተነሳችም።

እና ከዛን ቀን ጀምሮ እንቅልፍ እንቢ ሲለው ያንን ሪከርድ ደጋግሞ ይሰማዋል ። አንዳንዴ የሚያስጠሉን ወይም የሰለቹን ነገሮች ሊናፍቁን ይችላሉ።

እናንተ የምትሰሩበት ቢሮ ዛሬ ብትሞቱ ከሶስት ቀን በኋላ የስራ ማስታወቂያ ይለጠፋል። የሚወዷችሁ ሰዎች ግን በህይወት እስካሉ እናተን ያስታውሳሉ ።

እስኪ ዛሬ ከሚወዷችሁ ሰዎች ጋር  ግዜያችሁን አሳልፉ ። ደውሉላቸው ፍቅር ስጧቸው 
@yetbeb
2024/04/29 18:38:03
Back to Top
HTML Embed Code: