Telegram Web Link
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#መጻጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሣምንት)

በዐቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት መካከል አራተኛው እሑድ መጻጉዕ ይባላል፡፡ መጻጉዕ የተባለበት ምክንያት በዚሁ ሰንበት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሣ በመሆኑ ነው፡፡ «38 ዓመት የታመመውን መጻጉዕን ኢየሱስ አዳነው» እንዲሁም ልጁ የታመመበት የመቶ አለቃው "ጌታዬ በቃልህ እዘዝ ልጄ ይድናል፡፡ በቤቴ ጣርያ ሥር አንተ ልትገባ አይገባህም" አለው። "ጌታ በሚያልፍበት መንገድ አንድ ዕውር ፈውሰኝ" ብሎ ጮኸ የሚመሩት ሰዎች ዝም በል አሉት፡፡ ዕውሩ ግን እምቢ ብሎ "የዳዊት ልጅ ጌታ ይቅር በለኝ ዕርዳኝ" እያለ ጩኸቱን ቀጠለ፡፡ "በሰንበት ኢየሱስ መጻጉዕን ተነሥ አልጋህን ተሸከም ባለው ጊዜ ቀኑ ሰንበት ነበረ፡፡ መጻጉዕም አልጋውን ተሸክሞ ወደ ቤቱ ገባ የእግዚአብሔር ልጅ በሰንበት ፈውሷልና "በሰንበት ድውያንን ፈወሰ የዕውራንንም ዓይኖች አበራ" እያለ 38 ዓመት በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዞ ሲማቅቅ የኖረውን መጻጉዕንና ሌሎቹን በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙትን ሕሙማን መፈወሱን በጠቅላላው ለምፅ ማንጻቱን፣ ዕውር ማብራቱን፣ አንካሶችን ማርታቱን፣ ልምሾዎችን ማዳኑን፣ አጋንንትን ማውጣቱን፣ ወዘተ እየጠቃቀሰና እያነሣሣ ስለሚዘምር ዕለቱና ሳምንቱ መጻጉዕ ተብሏል፡፡

ስለዚህም ይህ ሰንበት የሕሙማን ፈውስ መታሰቢያ ዕለት ነው ማለት ይቻላል፡፡ በነዚህ ሁሉ ታሪኮች የመጻጉዕንና የሌሎቹን ሕሙማን ሁሉ ደኅንነት ታሪክ እንረዳለን፡፡ የሰንበቱም ስያሜ ልብ ወለድ አጠራር ሳይሆን የቅዱሳት መጻሕፍትን ምሥጢርና የጾመ ድጓውን ይትበሀል ተከትሎ የተሰየመ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

#የዕለቱ_ምንባቦች
1ኛ. የቅ.ጳውሎስ መልእክት ወደ ገላ. 5÷1-26
2ኛ. የቅ. ያዕቆብ መልእክት 5÷14-20
3ኛ. የሐዋርያት ሥራ 3÷1-12

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ 4ዐ(41)÷3
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቤሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ።

(እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ላይ ሳለ ይረዳዋል፡፡ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል እኔስ አቤቱ ማረኝ፡፡) መዝ 4ዐ÷3  የሚለው ይሆናል፡፡

#የዕለቱ_የወንጌል
በዮሐንስ ወንጌል 5፥1-25 ድረስ ያለው ነው፡፡

ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታች ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፡፡
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
🔹 ✥● ከሚከተሉት ውስጥ ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ከሚለው መጠርያ ስሟ ሌላ በየትኛው ትጠራ ነበር?? ✥●
Forwarded from ዘ-ተዋሕዶ ቦት
🔴✞ የህግ ሁሉ ፍፃሜ ምንድን ነው ✞

    
Audio
🔴ከትምህርቱ መካከል መልእክት አዳምጡ!!
"" ሥርዓተ ጸሎት "" (ክፍል ፫/3)

"ጸሎት ዘሰብዓቱ ጊዜያት" (ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

(መጋቢት 20 - 2016)

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Audio
"" ሚስት አግብቻለሁ "" (ሉቃ. ፲፬:፳)

(መጋቢት 22 - 2016)

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Audio
"" ስንክሳር - መጋቢት ፳፱ ""

"ርዕሰ በዓላት"

(መጋቢት ፳፰ - ፳፻፲፮)

https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

https://youtu.be/1LiAwF8_6Qw?si=WApphOkNC3xo0jrD
Audio
"" ሕማማተ ክርስቶስ ""

"በዓለ ስቅለት"

(መጋቢት 27 - 2016)



https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Audio
"" የመጨረሻዋ ሰዓት "" (፩ዮሐ. ፪:፲፰)

"ነገረ ምጽአት"

(መጋቢት 29 - 2016)

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ራሴን መሸፈኛ ክንፍ የለኝም እኔ
ይታያል ኃጢያቴ የበደል ዕርቃኔ

#ፈራሁ

ቀኑ ከረፈደ ከመሸብኝ መጣሁ
ደጃፍህ ላይ ቆምኩኝ እንዳልገባ ፈራሁ
በደሌን ሳትመዝን ግቢ ብትለኝም
ኃጢያቴ ከበደኝ አላራመደኝም

  የሰው ዕድሜው እኮ አጭር ነው ጥቂት ነው
  እንዴት ነው ሳላውቅህ ዘመኔ ያለቀው?
  ጉብዝናዬን ዓለም ስቃ ተጫውታበት
እንዴት ብዬ ልርገጥ ደጅህን በድፍረት?
  ፈራሁ ልግባ ወይ አልግባ
   እንዴት ይመዘናል የአንተ ደም በእኔ እንባ ?

እኔ ፈራሁ እንጂ አንተ እኮ አታስፈራም
መምጣቴ ነው ደስታህ ፍቅርህ አይታማም
ሽምቅቅ አለች ነፍሴ መስቀልህን ሳየው
በደሌን አሰብኩት ደምህን እያየሁ
   ፈራሁ ልግባ ወይ አልግባ
   እንዴት ይመዘናል የአንተ ደም በእኔ እንባ ?

በንጽህናህ ፊት እንዴት እቆማለሁ
እንደ መላዕክቱ በምን እጋረዳለሁ
ራሴን መሸፈኛ ክንፍ የለኝም እኔ
ይታያል ኃጢያቴ የበደል ዕርቃኔ
   ፈራሁ ልግባ ወይ አልግባ
   እንዴት ይመዘናል የአንተ ደም በእኔ እንባ ?

ጠዋት እና ማታ ለመጣው አንድ ነህ
አምሽቶ ለገባም እኩል ትከፍላለህ
አብርሃም ወይስሐቅ በድንኳንህ ቢያድሩም
በአንተ መንግሥት ግን ከወንበዴ አይቀድሙም
   ፈራሁ ልግባ ወይ አልግባ
   እንዴት ይመዘናል የአንተ ደም በእኔ እንባ ?


#ውስጥ #መሆናችን በድፍረት ልባችንን ላደነደነው አይነት ሰዎች #ፍርሀቱን #ይስጠን



https://youtu.be/yZRhhLT74rY?si=TplnxdckbmIF7GG2
የእመቤታችን ድንግል ማርያም የወላጆቿ መቃብር።
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ክፍል_ሁለት
ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 14 ቁጥር 27 ያለውን አነበበው እንደዚህ አለ
ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም
ቁራአን ግን ሰለ ፍቅር አንድም አላስተማረኝም
ክርስቲያን ጓደኛ አትያዙ ይላል
ከክርስቲያን አንድም ነገር አትቀበሉ
ጥላቻ ነው ያስተማረኝ
መፅሐፍ ቅዱስ ግን ከሰው ጋር በፍቅር እንዴት እንደምኖር አስተማረኝ
ኢየሱስም፡— እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ሲል ሰማሁት ይች ቃል በውስጤ ተቀመጠች ከቤተክርስትያን ወጥቼ እቤት እስከምደርስ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ እንዴት በሎ እያልኩ ጥያቄ ሆንብኝ ማታ ጓደኞቼ ለፀሎት እየተዘጋጁ አሚናት ነይ እንፀልይ አሉኝ ኡፍፍፍፍ ጀምራችሁ እንግዲህ አልኳቸው እና ውጭ ወጣሁ አንዲት ሙስሊም ጓደኛ አለችኝ እሷ ከክርስቲያኖች ጋር ጓደኛ እንድሆነ አትፈልግም ነበር እኔ ግን እወዳቸዋለሁ ግን መፅሐፍ ቅዱስ ሲያንቡ እና ፀሎት ላይ ሲሆኑ በጣም ያናድደኛል አንድ ቀን በጣም አመመኝ እና ፈቃደኛ ክሆነሽ እንፀልይ አሉኝ በእናንተ ፀሎት እኔ አልድንም ቀልደኛ ናችሁ አልኳቸው
እኔ ሳላውቅ ውሃ ሰጡኝ እና ጠጪ አሉኝ እኔ ግን ምንም አልመሰለኝም ነበር ውሃውን ስጠጣው አስመለሰኝ እና ወጣ በጣም ደስ አላቸው እኔ አልገባኝም ምን ሆናችሁ አልኳቸው ለምን እንደዚህ አደርገኝ ሰል የእግዚአብሔር ታምራት ነው አሉኝ በቃ ከዛ ወደዚህ ውሃ እነሱ ሲሰጡኝ አልጠጣም በጣም ፈራሁ ግን ከዛ ወደዚህ በጣም ስላም ተሰማኝ ዝም በሎ ደስ እያልኝ መጣ ናቲ ያነበበው ትዝ አለኝ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ያለው ቃል ኢየሱስ የሚባለው እውነትም ሰላም ይስጣል ማለት ነው እያልኩ ብቻየን ማሰብ ጀመርኩ መዝሙር መስማት ጀመርኩ ግን ጓደኞቼ እንዲያውቁ አልፈልግም ነበር መዝሙር ስስማ ከየት መጣ ሳልል እንባዬ ይፈሳል ዝም በዬ አለቅሳለሁ ግን ምን እንደሆንኩ አላውቅም ግን ሰላም ይሰማኛል
ማታ ተኝቼ በህልሜ አሜን አሜን እላለሁ ጓደኞቼ ይስቃሉ ጧት ስንሳ ይነገሩኛል እኔ በህልሜ አይቼ የማላውቀው ነገር ማየት ጀመርኩ እስከዛሬ በህልሜ የሚመጣው እባብ ስይጣን አወሬ ጋር ነበር የማደርው የመጨረሻ ህልም ደስ የሚል ነበር በህይወቴ አይቼ የማላውቀው 3 ቀን መንታ መንገድ ላይ ቁሜ በቀኝ ያለው ብርሃን በግራ ያለው መንገድ ጨለማ ነበር ማሀል ላይ የሆነ ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ዝም በሎ ያየኛል ኡፍፍፍ ያረቢ የአላህ ምንድነው ሶስት ቀን ተከታታይ አንድ አይነት ህልም እያልኩ ጥያቄ ሆነብኝ
እኔ በጣም ደስተኛ ሆኛለሁ ግን የቤተሰቦቼ ነገር ሀሳብ ሆኖብኛል እናቴ እና አባቴ ከተለያዩ ሶስት አመት አስቆጥርዋል የእነሱ አንድ መሆን ናፍቆኛል ለአንዷ ጓደኛዬ እንደዚህ አልኳት የእናንተ ጌታ እውነትም ስላምን ይስጣል ባሁኑ ሰአት እኔ ደስተኛ ሆኜ በሽታው ከኔ እርቆ መኖር ጀምሪያለሁ ግን የቤተሰብ ነገር ሀሳብ ሆኖአል አልኳት እና ምን ችግር አለው ማታ እንፀልያለን አለችኝ ማታ ፀልይን ከሶስት ቀን በኋላ ቤተሰብ ጋር ድውዪ አወራሁ እናቴ ደስ አላት አባትሽ አለ እኔጋ ነው አለች ኡፍፍፍ አቤት ደስታ ከምርሽ ነው አልኳት አናገሪው አለች እና ስልኩን ሰጠቸው አባቴም በጣም ደስ አለው በቃ በአንድ ሆናችሁ አልኩ እና እኔም ደስ አለኝ በቃ ህይወት እንደገና መኖር ተጀመረ
እኔ በቃ ይህን ጌታ ምን ልብለው ገራ ገባኝ እኮ ካሆነ በኋላ ልጁ በሆነስ አልኩ እረ ክርስቲያን ለሆነው ከራሴ ጋር ሙግት ጀመርኩ
በልጅነቴ ቤተክርስቲያን ላይ ደንጋይ እየጣለኩ ስርበሽ የነበረው ትዝ አለኝ
ክዚህ በላይ ምን ደስታ አለ ኡፍፍፍ አደስ ስው ሆንኩ ለበዙ አመት የናፈቀኝ ነገር ገና ክርስትያን ሳልሆን ተሳካልኝ
ክርስቶስ መሞቱን መነሳቱን ማረጉንም አመንኩ  ተጠመኩም ክርስትያን ሆንኩ አሁን ከማንም በላይ ደስተኛ ነኝ

share👇join👇share
https://www.tg-me.com/dmse_tewado
እውነት ለሁሉ ይድረስ
#ድምፀ_ተዋህዶ
2024/05/16 14:44:41
Back to Top
HTML Embed Code: