┄┉✽̶🌺✿ምኞትና ፍቅር✿🌺̶̥✽̶┉┄
▬▬▬❁ ክፍል አንድ ❁▬▬▬
✍... ረድኤት ከረፋዱ አራት ሰዓት አከባቢ የቤታቸዉን በረንዳ በማፅዳት ላይ ሳለች የግቢያቸዉ
በር ተንኳኳ፡፡ ማን ሊሆን ይችላል? ብላ እያሰበች ወደ በሩ ተጠጋች "አባዬና እማዬ ዛሬ የስራ
ቀን ስላልሆነ ቤት ዉስጥ ናቸዉ፡፡" እና ማን ነዉ? እያለች የግቢዉን በር ጠጋ አለችና "ማን
ነዉ?" አለች "እኔ ነኝ" የሚል ለስላሳ ድምፅ ከዉጭ የተሰጣት መልስ ነበር፡፡ ድምፁን
ከዚህ በፊት ባታዉቀዉም ሰላም ያለ ሰዉ እንደሆነ በድምፁ ስለተረዳች በሩን ከፈተችለት፡፡
በጣም ቆንጅዬ ወጣት ነበር፡፡ "ደህና ነሽ" አላት፡፡ እሷም "ደህና ነኝ" ብላ
ስትመልስለት "የሚከራይ ቤት አለ ብለዉኝ ነበር... አለ እንዴ?" ሲላት የረድኤት አባት
ለረዢም ሰዓት በር ላይ እንደቆመች ስላዬ
"ማን ነዉ?" እያሉ ወደ በሩ ተጠጉ፡፡ ወጣቱንም ባዩ ጊዜ ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ
ወጣቱ ልጅ ለረድኤት የጠየቃትን ጥያቄ ለአባቷ ለጋሽ ሀብታሙ ደገመላቸዉ፡፡ ጋሽ ሀብታሙም አለ ወደውስጥ ግባ ልጄ፡፡ አሉት እሺ ብሎ ገባ የሚከራየውን ቤት ገብቶ አየ ስንት እንደሚከራይ ጠየቃቸውና ተስማምተው ቢኒያም ወደ ቤት ተመለሰ ፡፡ ... ከዚህ ጊዜ በኃላ ነበር ረድኤት ቢንያምን ያወቀችዉ፡፡ ቢንያም እጅግ በጣም ዉብና
ማራኪ ልጅ ነዉ፡፡ ሚስቱ ደግሞ ኤደን ትባላለች፡፡ እጅግ ሲበዛ ዝምተኛና ቆንጂዬ ናት፡፡ ቤት
ስለምትዉልና ረድኤትም የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ብትሆንም ሰመርን ከቤተሰቦቿ ጋር ስለምታሳልፍ ሁሌም አብረዉ ይዉሉ ነበር፡፡
ኤዲ ምንም ያክል ዝምተኛ ብትሆንም ለባሏ ግን ፍቅርን መስጠት የምትችል፤ በተለይ
ሲጫወቱና ሰዉነቱ ላይ እየተንከባለለች ቅብጥብጥ ቅብጥ፤ ሽፍድ ስትልበት... ረድኤት "እኔ በሆንኩ" ብላ ትቀናባታለች፡፡ .
.
..... ቢኒያም ከስራ ሊመጣ አከባቢ ኤዲ እጅግ በጣም ተዉባ ከወትሮዉ በተለዬ ይበልጥ
አምራ የግቢዉን በር ለመክፈት ከቤቷ ወጥታ በሯ አጠገብ ትቀመጣለች፡፡ ልክ በሩ
እንደተንኳኳ ሩጣ ትሄድና ቶሎ ትከፍታለች፡፡ ቢኒያምም እቅፉ ዉስጥ አስገብቶ ሲስማት
ለተወሰነ ሰዓታት የተለያዩ ሳይሆን ለአመታት ተራርቀዉ ተነፋፍቀዉ የተገናኙ ይመስላሉ፡፡
ቢኒያም ፍቅር መስጠት ተክኖበታል፡፡
ሲያፈቅራትና ሲወዳት ምድር ላይ ሌላ ሴቶች እስከመፈጠራቸዉም ረስቶ ነዉ፡፡ ለሱ ሴት
ማለት እሷ ብቻ ናት፡፡ እንደ እናት ያከብራታል፤ ያፈቅራታል በጣም ይሳሳላታል፡፡ ፍቅራቸዉ
እንኳን አብሯቸዉ ለሚኖር ሰዉ ለአንድ ቀን በመንገድ ላይ ያያቸዉ ራሱ ይቀናባቸዋል፡፡
.
....ከግቢዉ ነዋሪም ጋር በጣም ተግባብቷል፡፡ ጋሽ ሀብታሙ ለብቻቸዉ ባገኛቸዉ ሰዓት "አባባ
ገና ወጣት ነህ አረጁ የሚል ሰዉ ተሳስቷል፡፡ አሁን እኔ እና አንቱ ሩጫ ብንሽቀዳደም
አዝነውልኝ ካልተዉልኝ በስተቀር ትበልጡኝ የለ እንዴ! አንቱኮ ሀይሌ ገ/ስላሴን ያስንቃሉ፡፡" እያለ
ይቀልዳቸዋል፡፡ እሳቸዉም የወጣትነት ጊዜያቸዉ ታዉሷቸዉ በጨዋታዉ ከሳቁ በኃላ "አይ
ልጄ..." ብለዉ ትረካቸዉን ይጀምራሉ፡፡ ለወሬያቸዉ አክብሮ ጆሮ ስለሰጣቸዉ ከስራ
የሚመለስበትን ሰዓት እንደ ኤዲ እርሳቸዉም ይጠባበቃሉ፡፡ በተለይ ደሞ ረድኤት...!
#ይቀጥላል ክፍል ሁለት
💕🍃🌹🍃.......
😘JOIN & SHARE 😘
@zahkyu
Any comments
@nahom20
💕.......🍃🌹🍃.......... 💞

▬▬▬❁ ክፍል ሁለት ❁▬▬▬
✍....የፍቅርን ሸማ ለብሶ ለኤዲ መዉደድን አጉርሶ በመኖር የተካነዉ ቢኒያም ይሄ ፍቅር
አሰጣጡ ረድኤት እንድትወደዉ አድርጓታል፡፡
ሁሌም ስለሱ ታስባለች ከቤት የሚወጣበትን ሰዓት እየጠበቀች ታየዋለች... ወደ ስራ ሲሄድ
እሷም እንደ ኤዲ ከአይኗ እስኪጠፋ ድረስ በአይኗ ትሸኘዋለች!፡፡
... ቀኑ እሁድ ቀን ነበር ረፋድ አከባቢ የረድኤት እናትና አባት ከቤታቸዉ በረንዳ ላይ በልጃቸዉ
ፍላጎት ቡና እየጠጡ ነዉ፡፡ ጨዋታዉ ደምቋል፡፡ የረድኤት እናት (እማማ በለጡ) የልጅነት
ቁንጅናቸዉ ዛሬም አለ፡፡ ፊታቸዉ ላይ ፈገግታቸዉ ያሳብቅባቸዋል፡፡ እሳቸዉን አይቶ ረድኤትን
"ልጃችሁ ናት?" ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ረድኤትን በካርቦን አስደግፈዉ የሳሏት እንጂ
አምጠዉ የወለዷት ብቻ አትመስልም፡፡
... ኤዲ አስከዛሬ ብቻዋን የምሰራዉን ስራ ዛሬ በቢኒ አጋዥነት ቤታቸዉ በረንዳ ላይ እቃ
ያጥባሉ፡፡ የነ ረድኤት ቤትና የነ ቢኒ ቤት ፊት ለፊት ስለሆነ ከቤት ዉጭ የሚደረጉ ነገሮች
እያንዳንዳቸዉ ይተያያሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር ረድኤት ቡና ማፍላቷን ረስታ በነሱ ፍቅር ተስባ
በመተዛዘናቸዉ ተደምማ ዛሬም 'ኧረ የኔ በሆነ" አይነት ስሜት ታያቸዋለች፡፡
... ቢኒ በስራቸዉ መካከል ሚስቱን ዉሃ ረጨት እያረገ ይቀልዳታል፤ በመሃል ደሞ
ስራቸዉን ረስተዉ ይተያያሉ፡፡ በስስት ያያታል ሳያወሩ በአይን ይግባባሉ፡፡ እሷን ሲመለከት
ልቡ ቦታዉን ለቆ አይኑ ላይ የመጣ ይመስላል፤ የአይኖቹ ብሌን ልብ ቅርፅ ይሰራሉ ምንም
አይነጋገሩም ግን በአይኖቻቸዉ ፍቅርን ያዜማሉ፡፡
... የሚገርመዉ ግን ሶስተኛ አይንም ነበረ፡፡ ረድኤት! ... ረድኤትም በኤዲ ቦታ ራሷን ተክታ
ቢኒን ታየዋለች የራሷ ባል አስኪመስላት በስስት ታየዋለች፡፡ በሃሳብ ተጉዛ ራሷን ከቢኒ
ጋር አርጋ ነዉ የምታስበዉ፡፡ እናቷ ሲጠሯት እንኳ አሰማም፡፡ እማማ በለጡ ተጣሩ "ረድኤት"
ዝም መልስ የለም እሷ ክንፍ አዉጥታ በራለች ዘመናትን ተሻግራ ከቢኒ ጋር ተጋብታ፤
ቆንጅዬ ልጆችን ወልዳ........... በሀሳብ ጭ.... ልጥ ብላች፡፡
እናቷ እየተጣሩ ነዉ፡፡ "ረድኤት" "ኧረ ረድኤት" ብለዉ ሲጮሁ ደንግጣ ከሃሳቧ ብትት
ከእንቅልፏ ንቅት አለች፡፡ ነገሩ የእማማ በለጡ አጠራር የልጃቸዉን ብቻ ሳይሆን
ጥንዶቹንም አስደንግጧቸዋል፡፡
ቢኒ በስስት ኤዲን እየተመለከታት "አንቺ ባትኖሪኮ ምን እንደምሆን ሳስበዉ..." ብሎ
ሳይጨርሰዉ ኤዲም "ከእኔ የተሻለች ፈጣሪ ይሰጥህ ነበር" አለችዉ፡፡
ቢኒ ሁሌም ቢሆን "ከኔ የተሻለች..." ስትል አይወድም፡፡ ምክንያቱ ደሞ ከእሷ የተሻለች
ሴት አለ ብሎ ማሰብ ስለማይፈልግ፡፡
..."ፈቲዬ አንቺ ደሞ በዚች ቃል ሁሌ ታናጅኛለሻ?" እሷም ወሬ ለማስቀየር... "የኔ ማር..."
ስትለዉ "እንደዉም ካንቺ የተሻለች አገባለሁ" ሲላት ንዴቱ ወደራሷ ዞረና "ሂድ" ብላ ዉሃ
ረጨችበትና አኮረፈች፡፡
ኤዲ ስትስቅም ስታኮርፍም በጣም ዉብ ናት፡፡ ካኮረፈች ደግሞ እንደ ህፃን ልጅ ያረጋታል ፡፡
ቢኒም ማባበል ጀመረ ቶሎ እንደማትስቅ ስለገባዉ ልመናዉን ተወና ለቅጣቱ ተዘጋጀ፡፡....
እሷ አታወራም አኩርፋለች "ዛሬ ራሴን ራሴ ነኝና የምቀጣዉ፡፡ ተመልከቺኝ ..." ብሎ እንደ
ህፃን ልጅ ተንበረከከ እጁንም ወደላይ አርገበገበ፡፡ አሁንም እንዳኮረፈች ናት ከዚያ
አጎበደደና ጆሮዉን ሲይዝ ኤዲ በሳቅ ፍርስ አለች፡፡
... ረድኤትና ቤተሰቦቿም "ምንድነዉ ያሳቃት?" ብለዉ ሲመለከቱ...
#ይቀጥላል ክፍል ሦስት
💕🍃🌹🍃.......
😘JOIN & SHARE 😘
@Zahkyu

#bexi🎵
what's up you all.👋 this is our channel and you will be watching cute pics music and other things stay tuned
@kalsa
https://www.tg-me.com/bexina

Telegram
Bez
🎻📚