“መከራ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እና ለእኛ ለልጆቿ አዲስ አይደለም!!”፡- ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
ጥር ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማእከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ለብፁዕ አቡነ ቄርሎስን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጥር 17 ቀን 2017 ዓ.ም የገና እና የጥምቀት በዓላትን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደርሰዎ መርሐ ግብር አከናውነዋል።
ብፁዕነታቸው እንደተናገሩት “መከራ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ለእኛ ለልጆቿ አዲስ አይደለም” ስለዚህ ሁላችሁም በመከራው ተስፋ ሳትቆርጡ በመጽናት የምትችሉትን ሥራ ሥሩ በማለት የተናገሩ ሲሆን እንደ ማኅበርም አንድነታችሁን አጽኑ በማለት አባታዊ መመሪያ እና ቡራኬ ሰጥተው ስለጠየቃችሁኝ አመሠግናለሁ ብለዋል።
በተጨማሪነትም በመርሐ ግብሩ ላይ በማእከሉ መዘምራን መዝሙር የቀረበ ሲሆን አጠቃላይ የማኅበሩን የሥራ እንቅስቃሴ እና የአባላትን ሁኔታ ጠይቀዋል፡፡

በሲዳማ ሀገረ ስብከት በሀዋሳ ከተማ የታነጸው የሀዋሳ አየር ማረፊያ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተመረቀ።
ጥር ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም
በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ማኀበረሰብ፣በCAPAT ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የበረራ ሠራተኞች መንፈሳዊ ጉባኤ እና በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት የታነጸው የሀዋሳ አየር ማረፊያ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ጥር 18 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ቅዳሴ ቤቱ ተከብሮ ውሏል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በክልል ትግራይ ደቡባዊ ዞን ማይጨው የደቡባዊ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት እና በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ የማኅበራት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ፣መጋቤ ጥበባት ቀሲስ ሞላልኝ መርጊያ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሀገረ ስብከቱ የመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች፣መ/ፀ/መ/ር/ቆ/አባ ኪዳነማርያም የሀዋሳ ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪን ጨምሮ የሌሎች ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንደተናገሩት ይህ ቤተክርስቲያን የተሰራው የእግዚአብሔር ስም እንዲጠራበት እንዲሁም ምእመናን እንዲባረኩበት ነው ያሉ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜም ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በዓለ ንግሡም ተከብሯል፡፡
በተጨማሪም በቦታው በርካታ ቁጥር ያላቸው ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ውጭ የሆኑ ምእመናን በታደሙበት ለተግባሩ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀትና ስጦታዎች ተበርክቷል።
የተመረቀው ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በሚያዝያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም መሠረት ድንጋይ መቀመጡ ይታወሳል።

በጾመ ፍልሰታ ስብሐተ ነግህ የሚባሉ የምእራፍ ዜማዎች
በመሪ ዘምስለ ተመሪ ከነንባቡ ጋር እነሆ ብለናል
ምዕራፍ መጽሐፍ ስብሐተ ነግህ ዘዘወትር ገፅ 207-219
1)አምላኪየ አምላኪየ
2)ምቅናይ እገይሥ ኀቤከ
በመሪ ዘምስለ ተመሪ ከነንባቡ ጋር እነሆ ብለናል
ምዕራፍ መጽሐፍ ስብሐተ ነግህ ዘዘወትር ገፅ 207-219
1)አምላኪየ አምላኪየ
2)ምቅናይ እገይሥ ኀቤከ