Telegram Web Link
በዓለ ጥምቀት

እንኳን አደረሳችሁ!

ጥምቀት ሥርዓቱ ከብሉይ ኪዳን ይጀምራል፡፡ አንድ አይሁድነትን ያልተቀበለ አዲስ ሰው ወደ ይሁዲነት ሲመጣ ከማኅበረ አይሁድ ከመቀላቀሉ አስቀድሞ ግዝረትን እና በውኃ  መታጠብን (መጠመቅ) እንዲፈጽም ይደረጋል፡፡ ይህም ለመንጻት ሥርዓት በዘሌዋውያን ካህናት  አማካኝነት  ይፈፀም ነበር፡፡ ውኃ መንጽኢ ነውና ማንም ሰው በተለያየ ምክንያት ቢረክስ  የሚነጻበት  (የኅፅበት) ሥርዓት ለእያንዳንዱ  ምክንያት ነበረው፡፡  (ዘሌ. ፲፬፥፲፭-፳፪) ይህንንም ተዘርዝሮ እናገኘዋለን፡፡ ይህም በእውነት በውኃ ላይ የእግዚአብሔር  መንፈስ እንዳደረበት  ያስረዳል፡፡ (ዘፍ.፫፥፪) ተያይዞ እስከ ዘካርያስ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ ደርሷል፡፡

በመልአኩ  ቅዱስ ገብርኤል  ብሥራት የተወለደው  ጻድቅ፣ ቅዱስ ሐዋርያ ሰማዕት፣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የዮሐንስ በረሃ በሚባለው እና ከሕፃናቱ ጀምሮ ባደገበትምድረ በዳ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ በብሕትውና ተወስኖ ሲኖር ቆይቶ ለክርስቶስ  መንፈቅ ሲቀረው  በ፴  ዘመኑ የዮርዳኖስ  አውራጃ  በምትሆን በይሁዳ  ‹‹ነስሑ  እስመቀርበት መንግሥተ ሰማያት፤ መንግሥተ ሰማያት በልጅነት፣  ልጅነት  በሃይማኖት ልትሰጥ ቀርባለችና በወንጌል አምናችሁ ንስሐ እያለ ሰበከ፤ በነቢይ ‹‹የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤  ጥርጊያውንም አቅኑ  እያለ  በምድረ በዳ  የሚጮህ  ሰው ድምፅ›› እንደ  ተባለለት፡፡ (ኢሳ.፵፥፫፣ማቴ.፫፥፫)

ቃሉን የተቀበሉም ስለ ኃጢአት ስርየት ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ በፈለገ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ይጠመቁ ነበር፡፡ ይህም አማኞችን  ለክርስቶስ  ጥምቀት የሚያዘጋጅና በእግዚአብሔር  መንግሥት ውስጥ ለመሆን የሚያበቃ ነበር፡፡ ‹‹እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸክም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይበረታል፤  እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል›› (ማቴ.፫፥፲፩) ክርስቶስም ናዝራዊ ከተባለበት (ማቴ. ፥፳፫) ከናዝሬት  ወደ ዮርዳኖስ  ጥር ፲፩   ቀን  ወረደ፤  ቅዱስ  ዮሐንስም  ስለ  እርሱ  መሰከረ  ‹‹ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር  ዘያአትት ወያሴስል ኃጢአተ ዓለም፤ እነሆ  የዓለምን ኃጢአት  የሚያስወግድ የእግዚአብሔር  በግ፡፡›› (ዮሐ.፩፥፳፱)

ዮሐንስም ክርስቶስ በእርሱ እንዲጠመቅ መምጣቱን ባየ ጊዜ ወትሮ ባሪያ ወደ ጌታው ይሄዳል  እንጂ እንዴት ይህ ይሆናል?  አለው፤ ትሕትናን ከእናቱ ተምሯልና፤  ‹‹የጌታዬ  እናት ወደ  እኔ ትመጣ ዘንድ  እንዴት  ይሆንልኛል?››  እንዳለች ቅድስት ኤልሳቤጥ፡፡ (ሉቃ.፩፥፵፫)  ደግሞስ ሌላውን ሁሉ በስምህ አጠምቃለሁ፤  አንተን  በማን ስም አጠምቃለሁ?  ቢለው  ‹‹ወልዱ  ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሃለነ››፤ ‹‹አንተ  ካህኑ ለዓለም በከመ  ሢመቱ  ለመልከ  ጼዴቅ››  ብለህ  አጥምቀኝ ብሎታል፤  ብርሃንን  የምትገልጥ የቡሩክ  አብ የባሕርይው  ልጅ ይቅር  በለን፤  እንደ  መልከ  ጼዴቅ  የዓለም ሁሉ ካህን  አንተ  ነህ››  እያልክ  አጥምቀኝ ብሎታል፤  ከዚያም ዮሐንስ ሊያጠምቀው ወደ ዮርዳኖስ ገብቷል፡፡

ዮርዳኖስ  የጥምቀቱ ቦታ  እንዲሆን  ጌታ የፈቀደው  አስቀድሞ  ትንቢት  አናግሮ  ምሳሌ መስሎ ‹‹ባሕርኒ ርእየት ወጎየት ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ ርእዩከ ማያት እግዚኦ  ርእዩከ ማያት ወፈርሁ፤ አቤቱ ውኆች አዩህ፤ ውኆችም አይተውህ ፈሩህ፤ ጥልቆችም ተነዋወጡ፤ ውኆችም ጮሁ፡፡›› (መዝ. ፸፮፥፲፮) ‹‹ባሕር  አየች፤  ሸሸችም፤  ዮርዳኖስም  ወደ ኋላ  ተመለሰ፤››  (መዝ.፻፲፫፥፫) ዮርዳኖስ መነሻው ከላይ ነቁ፤ አንድ ነው፤ ዝቅ ብሎ በደሴት ይከፈላል፤  ከታች ወርዶ ይገናኛል፡፡ የሰውም ልጅ አባቱ አንዱ አዳም ሲሆን እስራኤልና  አሕዛብ በግዝረት በቁልፈት  ተለያይተዋልና፡፡ ከታች ወርዶ እንደገና በወደብ እንዲገናኝ ሕዝብ እና አሕዛብ  በክርስቶስ  ጥምቀት አንድ  ሆነዋል፤  ከዚህም  የተነሣ  ጌታ የሁለቱ  ወንዝ  መጋጠሚያ  ላይ  በመጠመቅ አንድነታችንን  መልሶልናል፡፡  ይህንን  ውለታ በማሰብ (ይህን  የነጻነት  በዓል)  እናከብራለን፡፡

ከዚህም በላይ  የሥላሴ  ምሥጢር እኛ በምንረዳው መልኩ ያየንበትን በዓል የዕዳ ደብዳቤያችን የተፋቀበትን ቀን፣ ነጻነታችንን ያወጅንበትን፣ የእግዚአብሔር  ልጆች የሆንበትን  ዕለት  ከበዓልም  የሚበልጥ  ዐቢይ  በዓል  አድርገን  አናከብረዋለን፡፡  ይህንንም  ቀን  ቀድሶ  የሰጠን  ቅዱስ አምላክ ምስጋና ይድረሰው፤ አሜን፡፡
ከበዓሉ በረከት ረድኤት ያሳትፈን!
ማኅበረ ቅዱሳን በወልዲያ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በማኅበረሰብ ክፍሎች፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ችግር ለማቅለል ሁለገብ ማኅበራዊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
በዚህ መሠረት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ላለፉት ዓመታት በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማና ዙሪያው በሚገኙ ተፈናቃይ ጣቢያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በከፋ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። 

ማኅበረ ቅዱሳንም ይህን ማኅበራዊ ቀውስ ለማቃለል ባለፉት ሳምንታት በወልዲያ ከተማ በሚገኙ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች በመገኘት ከ614,000 (ከስድስት መቶ አሥራ አራት) ሺህ ብር በላይ ወጭ የሆነበት የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዚህ የድጋፍ ርክክብ ወቅትም የማኅበረ ቅዱሳን ወልዲያ ማእከል ልዑካን እና የተፈናቃይ አስተባባሪዎች ተወካዮች በመገኘት ድጋፉን ለተጎጅዎች አስረክበዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት
የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስከበር እና የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየተሰራ ነው።

ጥንታዊት፣ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስፋፋት በምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎችን መብትና ጥቅም ባለመንካት በትዕግሥትና በማስተዋል የምትጓዝ አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማት ሰላምን አብዝታ የምትሰብክ መንፈሳዊት ተቋም መሆኗ ይታወቃል።

ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮቷን ለማስፋፋት በተጓዘችባቸው አያሌ ዓመታት አገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ፊደላትና የራሷ የቀን አቆጣጠር ባለቤት እንድትሆን ያስቻለች፣በሊቃውንቶቿ የመጠቀ እውቀት አማካኝነት የሥነ ጥበብ፣የሥነ ስዕል፣የዕጽዋትና የጠፈር ምርምርና ጥናቶችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ለዓለም ያበረከተች ጥንታዊት ተቋም ስለመሆኗም አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ይሁን እንጂ ይህች ለአገረ መንግስት መመስረትና መጽናት፣ለእውቀት መስፋፋት፣ ለአብሮነት መጎልበት፣ ትውልድን በሥነ ምግባር ቀርጻ ፍቅርና አንድነትን በተግባር የሰበከች እናት ቤተክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ፣በአስተምህሮቿ፣በዕምነቷ፣በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል።
ስለሆነም በተደጋጋሚ እየተፈጸሙባት የሚገኙትን እነዚህን እኩይ ተግባራት ከዚህ በላይ በዝምታና በትዕግስት ማለፍ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ መብቷን በእጅጉ የሚጋፋ፣ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

ስለሆነም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ማጥናት፣መከታተልና ሕግን መሰረት ያደረገ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድግ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘችው ወቅታዊ ሁኔታውን በዝርዝር በማጥናት ተቋማዊ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ያደረገች ሲሆን የቤተ ክርስቲያናችን የሕግ አገልግሎት መምሪያም በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ፍትሕ ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት ክስ መመስረት የሚያስችለውን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ተግባር ለመለወጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከዚህ ጎን ለጎንም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በጠቅላይ ቤተክህነት ከሚገኙ መምሪያዎች መካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን መምሪያዎች በማካተት የተቋቋመው ኮሚቴም ዝርዝር ጥናቶችን በሚገባ በማጥናትና ችግሮቹን ለይቶ ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ በቤተክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር አማካኝነት ተቋማዊ አቋም የሚወሰድበትና በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የማያዳግም መፍትሔ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን እየገለጸች በሁለቱም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በተከታታይ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገለጽ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወቀች በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምዕመናንና ምዕመናት በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት የሚደረግላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለቤተክርስቲያናችን መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እናት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ጥር ፲፯ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
''ቦሩ ሜዳ'' የፊት ለፊት የጥያቄና መልስ መድረክ

''ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለምን የአዋልድ መጻሕፍትን ትጠቀማለች ?''

“ቦሩ ሜዳ” በማኅበረ ቅዱሳን ወርኃዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ላይ

ቀን፡- ጥር 25/2017 ዓ/ም
ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ

በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ

እርስዎም ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በመገኘት ከአዋልድ ማጻሕፍት ጋር ተያይዞ ያለዎትን ጥያቄ በማንሳት ምላሽ ያገኙ ዘንድ ተጋብዘዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የግቢ ጉባኤያት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራን በተመለከተ  ምክክር አካሄደ።

የማእከሉ የግቢ ጉባኤያት አማካሪ ቦርድ፣ የግቢ ጉባኤያት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ኮሚቴ እና የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እና በማእከሉ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው መርሐ ግብር በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ መምህራን እና በማኅበሩ አገልግሎት ረዥም ልምድ ያላቸው አባላት የታደሙ ሲሆን በማእከሉ የሚገኙ ግቢ ጉባኤያት ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው በሚል ርእስ ጽሑፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም የጉባኤው ታዳሚዎች በቀረቡት የግቢ ጉባኤያት ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ ለመስጠት በ አምስት ቡድን ተከፍለው እንዲሠሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
2025/07/13 11:56:17
Back to Top
HTML Embed Code: