ሦስቱ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ መግባታቸው ተገለጸ።
ግንቦት ፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ
ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባሕርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ብፁዕ አቡነሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የተንገላታችበትን እዩና በቃ በሉ፤ሁሉን የሚያግባባ ነገር ፈልጉና ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት ፍቱ፤ በዚህ ኣማራጭ እናት ሀገር እፎይታ እንድታገኝ ኣድርጉ፤ ይህንም ለውድ እናት የሚደረግ ካሣ ኣድርጋችሁ ውሰዱት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መልእክትና ጥሪም ይህ ነው፤
በመጨረሻም የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኣስተዳደራዊ ኣፈጻጸማችን በመገምገም ለቀጣዩ ጊዜ የስራ ኣቅጣጫን የሚያስቀምጠው የረክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖናዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተጀመረ መሆኑን ለኦርቶዶክሳውያን ሕዝበ ክርስቲያን እናበስራለን፤
እግዚአብሔር የተባረከና የተቀደሰ ጉባኤ ያድርግልን!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣
ግንቦት ፮ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
©የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

ማኅበረ ቅዱሳን በአገራችን ያለውን ማኅበራዊ ቀውስ ለማርገብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ
ግንቦት ፲፭/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን በአገሪቱ የሚታየውን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለመቅረፍ እንዲሁም ሥነ ልቦናዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ እየሠራ እንደሚገኝ የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ክፍል ገልጿል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ዲያቆን ንጉሤ ባለው ጊዜ እንደገለጹት በኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ላይ ከጋብቻ፣ ከማኅበራዊ ቀውስ ጋር ተያይዞ የወጣቶች ሕይወት ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸው ካህናት ንስሐ ልጆቻቸውን በትክክል እንዲይዙ፣ ቤተሰብን የሚያማክሩ ፣ ወጣቶችን በትክክል የሚመክሩ እንዲሆኑ ለማድረግና በተጨማሪም በዘርፉ ያሉ የጤና ባለሙያዎች የሳይኮሎጂና የሳይካትሪስት ባለሙያዎችን ጨምሮ እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት ስድስት ወራት በ 11 ማእከላት 483 አመካካሪዎችን ያሠለጠነ ሲሆን እነዚህ ማኅበራዊ ቀውስ እንዳይኖር በመሥራት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሆነ ለአገር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ማድረግ እንደሚቻል ዲያቆን ንጉሤ አክለው ገልጸዋል።
በመጨረሻም እስካሁን በተከናወኑ ሥልጠናዎች አጋር ለነበሩ አካላት ምስጋናቸውን የገለጹት ም/ ዳይሬክተሩ ሥልጠናውን ለማስቀጠል የሎጅስቲክ፣ የቁሳቁስ፣ የሥልጠና ስፍራ፣ የካህናትና የባለሙያዎች ማረፊያ የሚያስፈልግ ቢሆንም የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማግኘት ተግዳሮት ሆኖብናል ብለዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ ማስተላለፉ ተገለጸ
1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።
ምንጭ የኢኦተቤክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ