መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
፩ኛ #ዘመነ_ዮሐንስ ዘመነ ዮሐንስ የሚለው የዮሐንስ ድጓ #ከመስከረም ፩ ጀምሮ እስከ ኅዳር ፴ ሰማዕት ድጓ ድረስ ባለው ዘመን የሚዘመረው ቀለም (ቃለ እግዚአብሔር ) ሲሆን በዘመናት አከፋፈልም ዘመነ መጸው ይባላል። ፩.፩ #ወርኃ_መስከረም ወርኃ መስከረም በድጓው አቀማመጥ እነዚህን በዓላት ይይዛል፦ #ዘዮሐንስ ፣ #ዘተከዚ ፣ #ዘኤልሳቤጥ _ዘሰንበት ፣#ኤልሳቤጥ_ዘዘወትር ፣ #ዘዘካርያስ ፣ #ዘፍሬ_ሰንበት…
፪ኛ #ወርኃ_ጥቅምት
ወርኃ ጥቅምት እነዚህን በዓላት ይይዛል። ዘአብርሃ ወአጽብሃ፣ ዘጰንጠሌዎን ፣ ዘጽጌ ሰናብት ፣ ዘጽጌ ዘወትር ፣ ዘማቴዎስ ፣ ዘሚካኤል ፣ ዘአረጋዊ ፣ ዘእስጢፋኖስ ፣ ዘእግዝእትነ ማርያም ፣ ዘሉቃስ ሐዋርያ ፣ ዘአባ ይምዓታ ፣ ዘዕንባቆም ናቸው።
@zemariian

፫ኛ #ወርኃ_ኅዳር
ወርኃ ኅዳር እነዚህን በዓላት ይይዛል። ዘአባ አበይዶ ፣ ዘአባ ዮሐኒ ፣ ዘቊስቋም ፣ ዘአርባዕቱ እንስሳት ፣ ዘቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ፣ ዘአእላፍ መላእክት ፣ ዘአእላፍ ዘወትር ፣ ዘሚናስ ፣ ዘእግዝእትነ ማርያም ጽዮን ፣ ዘቆዝሞስ ወድምያኖስ ፣ ዘካህናተ ሠማይ ፣ ዘሙታኔ ፣ ዘቅዱስ መርቆሬዎስ ፣ ዘናግራን ፣ ዘቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማእት ፣ ዘጳጳሳት ፣ ዘጻድቃን ፣ ዘሰማእታት ሲሆኑ በነዚህ መካከልም ንዑሳት ክፍላት /አዝማናት/ አሉ። እነሱም፦ ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ መስቀልና ዘመነ ጽጌ .....ናቸው።
#ዘመነ_ዮሐንስ ፦ የተባለበት ምክንያት የዮሐንስን መንገድ ጠራጊነት እና የሐዲስ ኪዳን መሸጋገሪያነት እየገለበጠ በመዝሙር መጀመሪያ ስለዘመረው ነው።
እሱም እንዲህ ይላል፦ "ብፁዕ አንተ ዮሐንስ ዘሀለወከ ታእምር ወተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ጸሊ በእንቲአነ ውስተ ጥረት እሰ ዓውድ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ"
ትርጉም፦ ዮሐንስ አንተ ብፁዕ ነህ ታውቅ ዘንድ ያለህ በእግዚአብሔርም ፊት የምትሔድበት ስለኛ ፀልይልን በዓውድ አመቱ መጀመሪያ መታሰቢያህ ተጻፈ በረከትህን አገኝ ዘንድ ባርከኝ ማለት ነው።
የዚህ ዘመን መጨረሻው ደግሞ የሰማዕት ሰላም ሲሆን እሱም እንዲህ ይላል፦
ሰማዕተ ባልሐ አስቦሙ አንጽሐ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ በፍስሐ ወበሰላም ጸውዖሙ ውስተ ርስቱ ዘለዓለም።
ትርጉም፦ የሰማእታትን አዳነ ዋጋቸውንም ከፈለ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርን እናመሰግነው በደስታና በሰላም ወደ ዘለዓለም ርስቱ ጠራቸው ማለት ነው። በዝ ተፈጸመ ዘመነ ዮሐንስ ፤ ዘመነ ዮሐንስ እዚህ ላይ ያበቃል።

፬ኛ #ወርኃ_ታኅሣሥ
ወርኃ ታኅሣሥ እነዚህን በዓላት ይይዛል።
ዘኤልያስ፣ ዘ፫ቱ ደቂቅ ፣ ዘምህላ ስብከት ፣ ዘስብከት ፣ ዘዘወትር ፣ ዘጎርጎርዮስ ፣ ዘዝክረ ቅዱሳን ፣ ዘአባ ሰላማ ፣ ዘቅዱስ ገብርኤል ፣ ዘቅዱስ ገብርኤል ወዘቅዱስ ደቅስዮስ ፣ ዘብርሃን ፣ ዘብርሃን ዘዘወትር ፣ ዘክብረ ቅዱሳን ፣ ዘኖላዊ ፣ ዘኖላዊ ዘዘወትር ፣ ዘክብረ ቅዱሳን ፣ ዘመርዓዊ ፣ ዘጌና ፣ ዘልደት ፣ ዘሕፃናት ናቸው።

፭ኛ #ዘወርኃ_ጥር
ወርኃ ጥር እነዚህን በዓላት ይይዛል።
ዘሕፃናት፣ ዘዮሐንስ ፣ ዘግዝረት ፣ ዘናዝሬት ፣ ዘገሃድ ፣ ዘጥምቀት ፣ ዘቃና ዘገሊላ ፣ ዘሣልሲት ፣ ዘሰናብስት ፣ ዘመርዓዊ ፣ ዘዘወትር ፣ ዘክብረ ቅዱሳን ፣ ዘቂርቆስ ፣ ዘእግዝእትነ ማርያም እና ዘማኅበር ናቸው።

፮ኛ #ወርኃ_የካቲት
ወርኃ የካቲት እነዚህን በዓላት ይይዛል።
ዘማርያም እኖተ እፍረት ፣ ዘስምዖን ፣ ዘያዕቆብ ሐዋርያ ናቸው።
በነዚህ ዘመናት ውስጥ ንዑሳት ክፍላት አሉ እነርሱም፦
፩ ስብከት
፪ ኖላዊ
፫ ብርሃን
፬ መርአዊ
፭ ልደት
፮ ጥምቀት
፰ አስተርእዮ ..... ናቸው።
#አስተምህሮ ፦ የተባለበት ምክንያት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለአስተማረው ትምህርት ፣ ስላደረገው ተአምራት በሰፊው ስለሚያነሳና ለቅዱስ ያሬድም ትምህርቱ የተገለጠለት በዚህ ዘመን ስለሆነነው።
እሱም እንዲህ በማለት ይጀምራል፦
" መሐሪ ዘአልቦ መዓት ንጹሕ ዘአልቦ ርስሐት ጻድቅ ውእቱ ዘአልቦ ኃጢአት መኰንን ውእቱ ዘኢያደሉ ለገጽ ሠርዓ ሰንበት ለሰብእ ዕረፍተ ወብውህ ሎቱ ይኅድግ ኃጢአተ።"
ትርጓሜውም፦ ቁጣ የሌለበት ይቅር ባይ ፣ ይቅርታው የበዛ መዓቱም የራቀ ፣ ነውር የሌለበት ንጹሐ ባህርይ ኃጢአት የሌለበት እውነተኛ ነው ለሰው ልጆች እረፍት ሰንበትን ሠራ ኃጢአትን ያሥተሰርይ ዘንድ ይቻለዋል። የሚል ነው።
መጨረሻው፦ ፬ት ዘመ ..ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት በመስቀሉ አርኀወ ገነት ተሞዓ ኃይለ ሥልጣኑ ለሞት በመስቀሉ ገብረ መድኃኒተ። ትርጓሜውም ሰንበትን ለዕረፍት ሠራ በመስቀሉ ገነትን ከፈተ የሞት የሥልጣኑ ኃይል ተሻረ በመስቀሉ ድኅነትን አደረገ ማለት ነው።
የአስተምህሮ ቀለም (ዘመን) እዚህ ላይ ተፈፀመ።

#ፋሲካ
ፋሲካ የሚባለው ዘመን ከትንሣኤ እሰከ ከ ጳጉሜ መጨረሻ ያለው ወቅት ነው።
በዚህ ዘመን ውስጥም ንዑሳን ክፍላት አሉ። እነዚህም ትንሣኤ፣ ዕርገት ፣ ጰራቅሊጦስ ፣ ክረምት ናቸው።
#ፋሲካ፦ ማለት ማለፍ ፣ መሻገር ማለት ነው።
ይህ ዘመን ፋሲካ የተባለው የሰው ልጅ ከግብርናተ ዲያቢሎስ ነፃ የወጣበትን ፣ ከሲኦል ወደ ገነት የተሸጋገረበትን፣ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያገኘበትን ....ክፍል ስለያዘ ነው።
እሱም እንዲህ በማለት ይጀመራል፦
'' ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚ ዜማ በዓለ በትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ። ''
ትርጉም፦ ለአብ ምስጋና ይገባዋል ለወልድም ምስጋና ይገባዋል ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባዋል ጥንታዊ (መጀመሪያ ) ዜማ በደስታ በዓልን አድርጉ በመሠዊያው እሰከ ከሚሰማ ድረስ ይቺ ፋሲካ የቀደመች ህግ ናትና ማለት ነው።
መጨረሻው፦ ምልጣን ዘዮሐንስ ሲሆን እሱም እንዲህ ይላል።
'' ሰላማዊ ብእሲሁ ቅዱሳት እደዊሁ እለ አጥመቃሁ ለመድኃኔዓለም።''
ትርጉሙም፦ ዮሐንስ ሰላማዊ ሰው ነው የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስንም ያጠመቁ እጆቹ የተቀደሱ ናቸው ማለት ነው።

#፯ኛ #ወርኃ_ሚያዚያ
ወርኃ ሚያዚያ እነዚህን በዓላት ይይዛል።
ዘፋሲካ ፣ ዘሰናብስት ፣ ዘዘወትር ፣ ዘቶማስ ፣ ዘአልአዛር ፣ ዘአዳም ፣ ዘቤተክርስትያን ፣ ዘአንስት ፣ ዘክብረ ቅዱሳን ፣ ዘርክበ ካህናት ና ዘማርቆስ ናቸው።

፰ኛ #ወርኃ_ግንቦት
ወርኃ ግንቦት እነዚህን በዓላት ይይዛል።
ዘልደታ ፣ ዘበአተ ግብጽ ፣ ዘዕርገት ፣ ዘዕርግት ሰንበት ፣ ዘበዓለ ፶ ዘሰናብት ፣ ዘዘወትር ናቸው።

፱ኛ #ወርኃ_ሰኔ
ወርኃ ሰኔ እነዚህን በዓላት ይይዛል።
ዘርክበተ አጽሙ ለቅዱስ ዮሐንስ ፣ ዘጰራቅሊጦስ ፣ ዘክብረ ቅዱሳን ፣ ዘቅዱስ ሚካኤል ፣ ዘአባ ገሪማ ፣ ዘጴጥሮስ ወጳውሎስ ናቸው።

፲ኛ #ወርኃ_ሐምሌ
ወርኃ ሐምሌ እነዚህን በዓላት ይይዛል።
ዘ፲ወ፪ቱ ሐዋርያት፣ ዘዘወትር ፣ ዘአባ ብሶይ፣ ዘናትናኤል ፣ ዘቅዱስ ቂርቆስ ፣ ዘአባ ሰላማ ናቸው።

፲፩ #ወርኃ_ነሐሴ
ወርኃ ነሐሴ እነዚህን በዓላት ይይዛል።
ዘደናግል ፣ ዘሶፍያ ፣ ዘዘወትር ፣ ዘማርያም መግደላዊት ፣ ዘማኅበር ፣ ዘቅዱስ ሚካኤል ፣ ዘደብረ ታቦር ፣ ዘመስቀል ፣ ዘጉቡዓን ፣ ዘፍልሰታ ፣ ዘዘወትር ፣ ዘሰናብት ፣ ዘተክለሐይማኖት ፣ ዘአብርሃም ፣ ዘይስሐቅ ፣ ዘያዕቆብ ፣ ዘአበው ፣ ዘእንድርያስ ፣ ዘዮሐንስ ፣ ዘቅዱስ ሩፋኤል ፣ ዘሰናብት ፣ ዘዘወትር እና አንቀጽ ሃሌታ ናቸው።
ይህን አቀማመጥ ማካተት የተፈለገበት ምክንያት ከዘመን ብዛት አንዳንድ አዋልድ ክብረ በዓላት ቢጨመሩ አዋልድ መሆናቸውን በቀላሉ ለማወቅ እንዲያስችል ታስቦ ነው።
#በአሁን_ሰዓት_የሚገኙ_አዋልድ_ክብረ_በዓላት__ወይም_ኁልቈ_አዋልድ_፲፫_ናቸው።
እነርሱም፦
፩ መስከረም ፲፩ ፋሲለደስ
፪ መስከረም ፲፰ ኤዎስጣቴዎስ
፫ ኅዳር ፯ ቅዱስ ጊዮርጊስ
፬ ኅዳር ፲፩ ቅድስት ሐና
፭ ኅዳር ፲፮ ወለተ ጴጥሮስ
፮ ታኅሣሥ ፲፩ ሳሙኤል ዘዋልድባ
፯ የካቲት ፲፮ ኪዳነምህረት
፰ መጋቢህ ፭ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፱ ዘጻድቃን ሰንበት ዘተረስዓ
፲ ዘናግራን ወኢየሱስ ሞዓ
፲፩ ዘግንቦት ፲፩ የቅዱስ ያሬድ
፲፪ ዘሐምሌ ፯ የቅድስት ሥላሴ
፲፫ ዘነሐሴ ፳፬ አቡነ ተክለሃይማኖት ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪም በየመሐሉ የሚገኙ አየለ ጠፉም ነገር ግን በቤተልሔም በፀሎተ ፍትሐት እንኳን አየጠቀሙባቸውም።
እነዚህ አዋልድ ክብረ በዓላት የሚገኙት #በዓፄ_ኃይለ_ሥላሴ ዘመነ መንግስት በታተመው #ጥቁሩ_ድጓ ላይ ነው እንጂ በዋናው #በምስክሩ ሩ_ድጓ ላይ አይገኙም ለዚህም ነው አዋልድ የተባሉት።
#ማጠቃለያ፦ ከአከፋፈሉና ከይዘቱ በተጨማሪ ድጓ በዮሐንስ ጀምሮ በዮሐንስ ነው የሚጨርሰው።
ይኽም የሆነበት ምክንያት ይህ ዓለም በዘመነ ዮሐንስ ተፈጥሮ በዘመነ ዮሐንስ የማለፉ ምሳሌ ስለሆነ ነው። አንድም ብፁዕ አንተ ዮሐንስ ብሎ ጀምሮ እለ አጥመቃሁ ለመድኃኔዓለም ብሎ ይጨርሳል።
''ብ'' ብሎ መጀመሩ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት ''ም'' ብሎ መጨረሱ ድኅረ ዓለም ከድንግል ማርያም ያለ አባት የመወለዱ ምሳሌ ነው።
®ፀሐፊ ዲያቆን ሱራፊ
ምንጭ፦ ከመልአከ ስብሐት ተክሌ ሲራክ ፍኖተ ዜማ መጽሐፍ

ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሰባት አባላት ያሉት የአጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴን ሰየመ
ግንቦት ፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
ለ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ጉባኤ አጀንዳ በማርቀቅ እንዲያቀርቡ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን የሰየመ ሲሆን ኮሚቴው በቋሚ ሲኖዶስ ተዘጋጅቶ የቀረበውን አጀንዳ በመመርመርና በማሻሻል ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በማቅረብ የሚያጸድቅ ይሆናል። የኮሚቴው አባላትም፦
፩.አቡነ ጎርጎርዮስ
፪.አቡነ ቀሌምንጦስ
፫.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ
፬.አቡነ ኤልያስ (አርባ ምንጭ)
፭.አቡነ ሩፋኤል
፮.አቡነ ዜና ማርቆስ
፯.አቡነ ኤልሳዕ ሲሆኑ ምልአተ ጉባኤው ከአጀንዳዎቹ መጽደቅ በኋላ የቅዱስ ፓትርያርኩን
የመግቢያ መልእክትና የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትን ሪፖርት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ