300 ሺህ ብር ተቀጡ
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በትላንትናው እለት በቂርቆስ ክፋለ ከተማ ወረዳ 03 ወሎ ሰፈር አካባቢ በተሠራው የኮሪደር ልማት መሰረተ ልማት የእግረኞች መንገድ ላይ በተሽከርካሪ በመሄድ ደንብ ተላልፈው የተሰወሩ አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ፖሊሶች ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር በማዋል መቅጣቱን አስታወቀ ።
ግለሰቦቹ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ክትትል በማድረግ 3 አሽከርካሪዎች ከነ ተሽከርካሪአቸው በቁጥጥር ስር በማዋል እያንዳንዳቸው 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) በድምሩ 300,000/ሦስት መቶ ሺህ/ ብር መቀጣቱን ገልጸዋል ።
#ዳጉ_ጆርናል

ሩሲያ በኪየቭ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ቆሰሉ
ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ቆስለዋል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ከሦስት ዓመታት በፊት ሙሉ በሙሉ ወረራ ሩሲያ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ ዛሬ ማክሰኞ ድረስ ከተፈፀሙት ጥቃቱ በኪዬቭ ላይ የደረሰው ትልቁ የቦምብ ጥቃት አንዱ ነው። የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኢጆር ክላይመንኮ በሀገሪቱ በአጠቃላይ 440 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 32 ሚሳኤሎች መተኮሳቸውን ተናግረዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩስያ አየር መከላከያ ሰራዊት በአንድ ምሽት 147 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጥለፍ ማውደሙን የሞስኮ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።በኪየቭ ላይ የተካሄደው ጥቃት ከዘጠኝ ሰአት በላይ ፈጅቷል። ነዋሪዎችን ከእኩለ ሌሊት በፊት ጀምሮ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ወደ ድብቅ መጠለያዎች እንዲሸሹ አድርጓል። ባለሥልጣናቱ ባሊስቲክ ሚሳኤል በአንድ ወረዳ የሚገኝ ባለ ዘጠኝ ፎቅ ሕንጻን መምታቱን ገልፀው ፤ በ27 የከተማዋ ወረዳዎች ጥቃር እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። የዩክሬን ፓርላማ ሌሲያ ቫሲሊንኮ በኤክስ ላይ “በፍፁም ቅዠት ውስጥ ሆነን ነቅተናል፤ በፍርስራሹ ውስጥ የታገቱ ሰዎች አሉ ፤ ሙሉ ህንፃዎች ወድቀዋል ብለዋል። ክላይመንኮ እንዳሉት የነፍስ አድን ቡድኖች አሁንም ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስሕ ለማውጣት እየሰሩ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ሩሲያ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በዩክሬን ከተሞች ላይ የአየር ጥቃትን አጠናክራለች፣ የዩክሬይን የአየር መከላከያዎችን ለማጨናነቅ የተነደፉ ትልቅ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ማታለያዎችን በመላክ ታክቲክ በማድረግ ጥቅቷን ፈፅማለች። በተፋላሚ ወገኖች መካከል ቀጥተኛ ውይይት የተኩስ ማቆም ወይም ጉልህ ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ኪየቭ የራሷን የአፀፋ ጥቃት ጀምራለች። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የሩስያ የጥቃት ማዕበል “ግልፅ ሽብርተኝነት” ብለውታል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን ለመቀጠል የሚያስችል አቅም ስላላቸው ብቻ ነው ትልቁን ጥቃት የፈጸሙት ሲሉ ከሰዋል።
በስምኦን ደረጄ

ሚኪያስ ጎማ ፣ ባትሪና ከመነዳሪ አከፋፋይ
#ለቪትስ
#ለያሪስ
#ለዲዛየርና ስዊፍት
#ለኮሮላ
#3L & 5L እንዲሁም ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ ጎማዎች እና ባትሪዎችን ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን
👉የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎማዎች (ትሪያንግል ፣ ስፖርትራክ ፣ ኮምፈርሰር ፣ አፖሎ ፣ ብሪጅስቶን እና ሌሎችም)
👉 የተገለገሉበት ጎማ ን ዋጋ ተምነን በአዲስ እንቀይርሎታለን
👉 በስልክ ቁጥር 📞...+251-913-701702 / +251-975293297 ይደውሉልን አልያም ተክለሀይማኖት ከሚገኘው ሱቃችን ይምጡ በደስታ እናስተናግድዎታለን

በጌድዮ ዞን በቤት ሰራተኝነት የምትሰራውን የ18 ዓመት ታዳጊ አስገድዶ በመድፈር የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ኮቾሬ ወረዳ በአስገድዶ መድፈር እና በግድያ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የዞኑ ፖሊስ አስታዉቋል።
ተከሳሽ ደሳለኝ አሰፋ የተባለ ሲሆን በኮቾሬ ወረዳ በሐማ ቀበሌ ልዩ ቦታ ድንጋቴ ህዋስ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7:00 ሠዓት አከባቢ የግል ተበዳይን አስገድዶ በመድፈር ለሞት የዳረጋት መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።
የወረዳው ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሹ ግለሰብ የግል ተበዳይ በምትሰራበት ቤት ዉስጥ ሰዉ አለመኖሩን ካረጋገጠ በኃላ ወደ ቤት በመግባት የኃይል ድርጊት በመጠቀም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈፀም ለሞት ከዳረጋት በኃላ ለመሰወር ሞክሯል፡፡ የኮቾሬ ወረዳ ፖሊስ በደረሠው ጥቆማ መሠረት ተጠሪጣሪውን ተከታትሎ በሕግ ቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ አጣርቶ በሰውና የሰነድ መረጃ በማደራጀት ለወረዳ አቃቤ ህግ ይልካል።
ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ የደረሰው የወረዳው ዓቃቤ ሕግ ተከሳሹ አስነዋሪ ድርጊት በመፈፀሙ ክስ በመመስረት ለወረዳው ፍ/ቤት ያቀርበዋል።የኮቾሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ስከታተል ቆይተው በተከሳሽ ደሳለኝ አሰፋ ሰኔ 6/2017 ዓ/ም በዋለው ወንጀል ችሎት ተከሳሹ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ ወስኖበታል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ ካሜኔይ እንደ ሳዳም ሁሴን ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ሊገጥማቸው እንደሚችል እስራኤል ዛተች
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትስ እስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመዉ ጥቃት እንደሚቀጥል በመግለጽ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኒ እ.ኤ.አ. በ2003 በአሜሪካ መሪነት የተደረገውን ወረራ ተከትሎ ከስልጣን የተባረሩት እና የተገደሉት የኢራቅ መሪ ሳዳም ሁሴን ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፍጻሜ ሊጠብቃቸዉ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
"የኢራናዊው አምባገነን የጦር ወንጀሎችን መፈጸምን እና በእስራኤል ሲቪሎች ላይ ሚሳኤል ከማስወንጨፍ እንዲቆጠቡ አስጠነቅቃለሁ" ሲሉ ካትዝ መናገራቸዉን የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ባለፈው ሳምንት እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመረችነት ጊዜ አንስቶ የኢራን ሲቪሎች ተገድለዋል ።
ካሜኔ በእስራኤል መንግስት ላይ ይህንኑ መንገድ ከመረጡ የአምባገነኑን እጣ ፈንታ ቢያስታውሱ ጥሩ ነዉ ሲሉ ካትዝ ሳዳም ሆሴይንን በመጥቀስ ተናግረዋል።"እኛ ዛሬ እንቀጥላለን እንዲሁም ቴህራን ውስጥ ገዥው አካል እና ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉ ካትዝ አክለዋል:: ነዋሪዎች ቴህራን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

የመላው ኢትዮጲያ ጨዋታ ከዘጠኝ አመታት መቋረጥ በኋላ ዛሬ በውቢቷ ጅማ በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል
👉 ከዘጠኝ አመታት በፊት አምስተኛው የመላው ኢትዮጲያ ጨዋታ በሀዋሳ ተካሂዶ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።
ዛሬ በጅማ ዩንቨርስቲ ስቴዲየም የመክፈቻ መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አወሉ አብዲ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በኦሎምፒክ መርህ የሚካሄደውን መላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመስገን ጥሩነህ የኦሎምፒክ ችቦውን በመለኮስ ለአትሌት ጌጤ ዋሚ እና አትሌት ኢብራሂም ጄይላን አስረክበዋል
“ስፖርት ለህብር ኢትዮጵያ አርበኝነት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው
በዚህ ውድድር ከ4500 በላይ ተሳታፊዎች በኦንላይን ምዝገባ ማድረጋቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከዛሬ ከሰኔ 10-19 በጅማ ከተማ በሚካሄደው ውድድሩ ሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 26 የስፖርት አይነቶች የውድድሩ አካል እንደሚሆኑም ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
የባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ እንዲሳተፍ የተደረገ ሲሆን በስድስት የስፖርት አይነቶች በሁለቱም ጾታ ይሳተፋል።
ውድድሩ ኢትዮጵያ ለ2027 የመላው አፍሪካ ጨዋታ የምታደርገው ዝግጅት አካል መሆኑንም ተገንዝበናል።
በዳንኤል መምሩ

Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የ 17 አመቱ ላሚን ያማል 30 አመት ከሆናት የበረራ አስተናጋጅ ከሆነች እንስት ጋር ግንኙነት መጀመሩ ተጠርጥሯል። ላሚን እና የተጠቀሰችዉ ሴት በጣሊያን በተመሳሳይ ቦታ ሆነዉ በኢንስታግራም ገጻቸዉ ላይ ፎቶ ከለቀቁ በኋላ በተከታዮቻቸዉ ግንኙነታቸው ተጠርጥሯል።
ሆኖም ላሚን ያማል ስለ ሁለቱ ሰዎች ግንኙነት ጥየቄ ቀርቦለት የሀሰት ነዉ ሲል አጣጥሎታል።
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

የሩስያ የጸጥታ ሃላፊ ከ2 ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ሰሜን ኮሪያ አቀኑ
የሩሲያ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን ሰርጌ ሾይጉ የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለማግኘት ፒዮንግያንግ እንደደረሱ የሩሲያ መንግስታዊ መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ እለት ዘግበዋል። በዚህ ወር ባለፈው አመት በሁለቱ ወገኖች የተፈረመው አጠቃላይ የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት የመጀመሪያ አመት በመሆኑ የሾይጉ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ ፒዮንግያንግ ያደረጉት ጉዞ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ በጁን 4 የሰሜን ኮርያም መዲና ጎብኝተዋል።
ጉብኝቱ በድጋሚ "በሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መመሪያ" የተደረገ ስለመሆኑ የሩሲያው ታስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የሩስያ የፀጥታው ምክር ቤት መሪ የሆኑት ሾይጉ በቅርብ ወራት ውስጥ ወደ ሰሜን ኮሪያ በርካታ ጉዞዎችን አድርገዋል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም በፒዮንግያንግ የተፈራረሙትን የትብብር ስምምነት ተከትሎ ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ላይ በተከፈተው ጦርነት ሩሲያን ለመርዳት በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን አሰማርታለች።
ስምምነቱ ከሁለቱ ሀገራት በአንዱ ላይ በሶስተኛ ወገን ከተጠቃ ወታደራዊ ድጋፍን መስጠትን የሚያስችል ነው።