በሀረሪ ክልል የወንጀል ምዝገባና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ስራ ማስጀመሪያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ
በሐረሪ ክልል የወንጀል ምዝገባና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ስራ ማስጀመሪያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል።ስምምነቱ የተደረሰው በሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ፣በፖሊስ ኮሚሽን እና በክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ መካከል ነው።የወንጀል ምዝገባና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ሶፍትዌሩ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የበለጸገ ሲሆን በፍትህ ተቋማት ውስጥ የወንጀል ምርመራና የመረጃ አያያዝ ሂደትን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት ያስችላል።
የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ አዩብ አህመድ ስምምነቱ የወንጀል ምርመራ ስርዓቱን በማዘመን ዜጎች በእውነታ ላይ የተመሠረተ የፍትህ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል። የፍትህ ተቋማቱ በቀጣይ አገልግሎቱን ስራ ላይ ለማዋል አስፈላጊውን የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ለማሟላት እቅድ ተይዞ እንደሚሰራም ገልጸዋል። የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን በበኩላቸው ስርዓቱ ፍትሐዊ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ በማገዝ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
በተለይ ወቅቱ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ውጤት መታጠቅ ከፍትህ ዘርፉ የሚጠበቅ መሆኑን አክለዋል። ኮሚሽኑ አሰራሮቹን ወደ ዲጂታል በማሳደግ ረገድ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በክልሉ የሚገኙ ተቋማትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ዘመኑን የዋጁ እንዲሆኑ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለጸዉ ደግሞ የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ነዉ። በክልሉ ያሉ ተቋማትን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ ወደ ስራ መገባቱንና ይህ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ይጠበቃል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የምርምርና እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተማም ስምምነቱ በቴክኖሎጂ የተመራ ዘመናዊ አሰራርን ለማላበስና ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳ ገልጸዋል። ዩኒቨርስቲው በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተለያዩ ድጋፍና እገዛዎችን እያደረገ ይገኛል ያሉ ሲሆን በቀጣይም የተሻሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አሰራሮች እንዲኖሩ በማገዝ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በሰመኃር አለባቸዉ
#ዳጉ_ጆርናል

Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለምን የእግሩን ጥፍሮች የጥፍር ቀለም ይቀባቸዋል?
በትናንትናው እለት የአባቶች ቀንን ምክኒያት በማድረግ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከልጁ ጋር በመሆን ያጋራዉ ምስዕል ነበር። በዚህም ምስዕል ላይ የክርስቲያኖ ሮናልዶ የእግር ጥፍሮች የጥፍር ቀለም ተቀብተዉ ይታያሉ። ከዚህ ቀደምም ሮናልዶ የሴት ልጆቹ ጥፍር ቀለም ሲቀቡት በአንድ ቪዲዮ ላይ ታይቶ ነበር።
ታድያ የዳጉ ጆርናል ስፖርት አንድ ተከታያችንም ሮናልዶ ለምን የእግሩን ጥፍር ቀለም ይቀባል? ሲል በኮሜንት መስጫ ቦታችን ላይ ጠይቆ ነበር። እኛም ምክኒያቱ ምን ሊሆን ይችላል የሚለዉን ለማጣራት ሞክረናል።
እንደ ጀርመኑ ቢልድ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ፣ ሮናልዶ ረጅም ሰዓታትን በሽፍን ጫማ እና በስፖርት እንቅስቃሴ የሚያሳልፍ በመሆኑ በእግር ላብ ምክኒያት ከሚመጣ የፈንገስ አይነት ራሱን ለመጠበቅ ነዉ ይለናል።
እንደ ሮናልዶ ያሉ አትሌቶች የእግር ጣት ጥፍርቸውን ቀለም መቀባት የሚመርጡበት ምክንያት ላብ ያደረባቸውን ጫማዎችን አድርገዉ ሰዓታትን ከቆዩ በኋላ በፈንገስ ኢንፌክሽን እንዳይያዙ ለመከላከል ነው።
የጥፍር ቀለም ባክቴሪያ ወደ ቆዳ ውስጥ እንዳይገባ የሚያግድ መከላከያ ሽፋን እንደሚጨምር ይታመናል።
በተጨማሪም ቀለሙ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት የጥፍር መሰንጠቅ ወይም መከፈት እንደሚከላከል ይታሰባል። እንደ ቢልድ ዘገባ ከሆነ ሮናልዶ በነዚህ ምክኒያቶች የእግር ጥፍሩን ቀለም ይቀባል።
በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

ኢራን ከአርብ ጀምሮ በእስራኤል ላይ በወሰደችው ጥቃት 24 እስራኤላውያን ተገደሉ
በእስራኤል እና በኢራን መካከል ግጭት ከጀመረ ወዲህ በእስራኤል ወገን 24 ሰዎች ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል። በኢራን ደግሞ 224 ሰዎች ተገድለዋል። የቴህራን ነዋሪዎች ደህንነትን ፍለጋ ዋና ከተማዋን ለመሸሽ እየሞከሩ መሆኑም ተሰምቷል።
እስራኤል አንድ ሶስተኛውን የኢራን ሚሳኤል ማስወንጨፊያ ማውደሟን ተናግራለች። የእስራኤል ጦር ከ120 በላይ የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን አውድማለች። ይህም ኢራን ካላህ አጠቃላይ ቁጥር አንድ ሶስተኛውን የሚያህለውን ሲሆን የመጀመሪያው ጥቃቱን ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ ደርሷል።የአየር ሃይሉ እሁድ ምሽት ብቻ ከ20 በላይ አውድሟል። እስራኤል በማዕከላዊ ኢራን እስፋሃን ውስጥ ወደ 100 የሚጠጉ ወታደራዊ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማድረስ 50 የሚጠጉ ተዋጊ ጄቶች የሚሳኤል ማከማቻ ስፍራዎችን፣ ማስወንጨፊያዎችን እና የማዘዣ ማዕከሎችን መታለች።
ከኢራን አብዮት ጠባቂዎች ኮርፖሬሽን (IRGC) ጋር ግንኙነት ያለው የታስኒም የዜና ወኪል እስራኤል ከኢራቅ ጋር በሚያዋስነው ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው ኢላም ግዛት ያለውን የሙሲያን ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ መከላከያ ክፍል ህንፃ ላይ አሰቃቂ ጥቃት ፈፅማለች ብሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፋርስ የዜና ወኪል እንዲሁም ከኢራን አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ሆስፒታል መጎዳቱን ዘግቧል።
በስምኦን ደረጄ

የኢራን መንግስታዊ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ በእስራኤል በተፈፀመ ጥቃት በርካቶች ተገደሉ
የኢራን መንግስታዊ ቲቪ እንዳስታወቀው ቴህራን በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤቱ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት "ቁጥራቸው በውል" ያልተገለፁ ሰራተኞቹ መገደላቸውን አስታውቋል። የስርጭት ዘጋቢ "ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ እየሰሩ ነበር" ሲሉ የስርጭቱ ኃላፊ ፔይማን ጀቤሊ በማንሳት በመንግስታዊው ቲቪ ላይ በደም የተበከለ ወረቀት አሳይቷል።
የመንግስት ቴሌቪዥን እና ሰራተኞቹ "እስከ መጨረሻው ሲሰሩ ነበር " ብለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ቲቪ ሰራተኞች በሚሰሩበት አነስተኛ መንደር ውስጥ ጥቃቱ ደርሷል። እስራኤል ቀደም ሲል የቴህራን ዲስትሪክት 3 ክፍል ከጥቃቱ በፊት ለቀው እንዲወጡ የሚነግራትን ካርታ አሳትማ ነበር፤ የመንግስት ቲቪም እዚህ ካርታ ውስጥ ተካቷል።
የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር የኢራን የመንግስት ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ላይ ጥቃት ማድረሱን አረጋግጧል። ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትስ በሰጡት መግለጫ ጥቃቱ የተፈፀመው “በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎችን መጠነ ሰፊ መፈናቀልን ተከትሎ ነው” ያሉ ሲሆን እስራኤል “የኢራኑን አምባገነን ባለበት ትመታለች” ብለዋል።

አቋማሪ ድርጅቶች ፊታቸውን ወደደቡብ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማድረጋቸው ተነገረ
በአዲስ አበባና በተለያዩ አካባቢዎች ቢሯቸው የተዘጋባቸው የስፖርት ውርርድ አቋማሪ ድርጅቶች ፊታቸውን ወደ ደቡብ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አስታውቋል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በውርርድ አጫዋቾች ፈቀድ አሰጣጥና ቁጥጥርን በተመለከተ በቀረበለት የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ውይይት አድርጓል።
በወቅቱ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤዛ ግርማ፤ በአዲስ አበባ፤ በድሬዳዋ፤ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች፣ በትግራይና በአማራ ክልሎች አቋማሪ ድርጅቶች ቢሮ መዘጋቱን መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከኢቢሲ ዘገባ ተመልክቷል።
አቋማሪ ድርጅቶች አሁን ላይ በደቡብ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝ እና በኦንላይንም በስፋት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ባለፉት 11 ወራት ከአወራራጆቹ የተገኘው የኮሚሽን ገቢ 2.2 ቢሊዮን ብር መድረሱንም ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ አስታውቀዋል።

የእናቴን ድርሻ የጫት መሬት ሊሰጠኝ ፍቃደኛ አይደለም በማለት አባቱን በስለት ወግቶ የገደለው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ ጎሮ አካባቢ ተወልዶ ያደገው ኢብራሂም ሀሰን ለቤተሰቡ ብቸኛ ልጅ ቢሆንም ወላጅ እናቱ በልጅነቱ ህይወታቸው አልፎ አባቱ ሌላ ትዳር መስርተው አክስቱ ጋር እንዳደገ ተገልጿል።
ወጣቱ ጎጆ መውጫ የእናቴን ድርሻ የጫት መሬት ይሰጠኝ ብሎ አባቱን ይጠይቃል። በአካባቢው አንድ ትዳር ሊመሰርት ያሰበ ወጣት ለሚያገባት ልጅ የሚቆጥረው ሀብት እና ንብረት መሬት መገለፅ የግድ በመሆኑ ለአባቱ ድርሻዬን የሚል ጥያቄ ያቀርባል።አባትም የተጠየቁትን የጎጆ መውጫ ጥያቄ ለመቀበል ያንገራግራሉ፣ በዚህ ጊዜ ኢብራሂም የሰርጉ ጊዜ መድረስና የሰርጉ ቀን ለጎጆ መውጫ የሚያቀርበው መተዳደርያ የእናቱ ድርሻ የሆነው የጫት መሬት ነበረና ያንን አባት ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆናቸው ቂም እንዲቋጥር እንዳደረገው በሰጠው ቃል ማረጋገጡን የዞኑ ፖሊስ ዋና መምሪያ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ተከሳሹ መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከለሊቱ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ላይ የአባቱን ግቢ በር ከፍቶ በመግባት አባቱን በተኙበት የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻቸውን በያዘው ስለታም መጥረቢያ በመምታት ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጎ ይሰወራል።የአባት መኝታ ለብቻ በተሰራ ቤት በመሆኑ ጠዋት የመነሳት ልማድ የነበራቸው አባት በዚያ ዕለት አርፍደው መዋላቸው ያጠራጠራቸው ቤተሰብ ወደ መኝታ ቤታቸው ሲደርሱ የሚተኙበት ቤት ተከፍቶ አባትም የተለያየ ቦታ ተመተው ህይወታቸው ማለፉን ሲያዩ የድረሱልኝ ጩኸት በማሰማት የአካቢው ሰው እንዲሰባሰብ አደረጉ።ፖሊስም ከአካባቢው ሰው በደረሰው መረጃ በስፍራው በመገኘት አስክሬኑን በማስነሳት ለምርመራ ወደ ሆስፒታል ልኳል።
ፖሊስ ከአካባቢ ሰዎች እና ቤተሰብ የተለያዩ መረጃዎችን በማሰባሰብ ተጠርጣሪውን ኢብራሂም በቁጥጥር ለማዋል ክትትል ይጀምራል። በዚህም ከአራት ቀን በኋላ ተፈላጊው ኢብራሂም በሱማሌ በኩል ከሀገር ሊወጣ ሲል በቁጥጥር ስር ውሎ የድርጊቱን አፈፃፀምና ምክንያት በመናገር ለፖሊስ ቃሉን ይሰጣል። ፖሊስ አስፈላጊውን የምርመራ ሂደት አጠናቆ የምርመራ መዝገቡን ለዓቃቢ ሕግ ይልካል። ዓቃቢ ህግ በከባድ ሰው መግደል ወንጀል ክስ ይመሰርታል።
የተመሰረተውን ክስ ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎት ተከሳሽ ኢብራሂም ሀሰን ሰውን ለመግደል፣ አስቦ፣ አቅዶ ተዘጋጅቶ ወላጅ አባቱን ድምፅ በሌለው ስለታም መሳሪያ መግደሉ ሙሉ በሙሉ በማስረጃ በመረጋገጡ ተከሳሹ ጨካኝ፣ አደገኛ እና ነውረኛ በመሆኑ በ 20 አመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ

Forwarded from ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal (#Me_Lion)
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/kdOk0mCXBao?si=HvJ7F3JLOhE8Eet7

የቴል አቪቭ ቅርንጫፍ በመጎዳቱ በእስራኤል የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ተዘጋ
በእስራኤል የአሜሪካ አምባሳደር እንደተናገሩት የቴል አቪቭ ኤምባሲ ቅርንጫፍ ከኢራን በተፈፀመበት ጥቃት መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል። ማይክ ሃክካቢ በኤክስ ላይ እንዳሰፈሩት ቆንስላ ጽ/ቤቱ በቴል አቪቭ በሚገኘው ህንፃ አቅራቢያ “በኢራን ሚሳኤል በመመታቱ” ተጎድቷል። በእየሩሳሌም የሚገኘው ዋናው የአሜሪካ ኤምባሲም ተዘግቶ ይቆያል ብለዋል። በጥቃቱ ግን የአሜሪካ ሰራተኛ አልተጎዳም ተብሏል።
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ኢራን በእስራኤል ዜጎች ላይ ባደረሰችው ጥቃት አምስት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ እንል በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውን ተከትሎ የቴህራን ነዋሪዎች ዋጋ እንደሚከፍሉ አስጠንቅቀዋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ኢዝራኤል ካትስ የኢራን መሪ አሊ ካሜኔይን ሆን ብለው በሲቪል አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንዲፈፀም አድርገዋል ሲሉ ከሰዋል።
ካትስ ካሜኔይን "ፈሪ ነፍሰ ገዳይ" እና "ጉረኛ አምባገነን" በማለት ጠርተዋቸል። እስራኤል “በቅርብ ጊዜ” አጸፋውን እንደምትመልስ ተናግረዋል።የቴህራን ነዋሪዎችን በአካል የመጉዳት አላማ የለምን ሲሉ ካትስ በኤክስ ላይ ፅፈዋል።ኢራናውያን የአምባገነኑን ስርዓት ዋጋ ለመክፈል እና በቴህራን ውስጥ የአገዛዙን ኢላማዎች እና የፀጥታ መሰረተ ልማቶችን ማጥቃት አስፈላጊ ከሆነ ግን ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ይገደዳሉ ብለዋል። የእስራኤልን ነዋሪዎች መጠበቃችንን እንቀጥላለን ሲሉ አክለዋል።

የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች አርባምንጭ ከተማን ለመጎብኘት የክረምት ወቅትን ይመርጣሉ ተባለ
በበጋ ወቅት በርካታ የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች አርባምንጭ ከተማን የሚጎበኙ ቢሆንም ከተማዋ ካላት ሞቃታማ የአየር ንብረት ጋር ተያይዞ በክረምት ጉብኝት የሚያደርጉ የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች በየዓመቱ ከፍተኛ ቁጥር እንደሚኖራቸዉ ተገልጿል ።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 46ሺህ 2መቶ 87 የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ታቅዶ 25ሺህ 3መቶ 11 ቱሪስቶች ጉብኝት ማድረጋቸዉንና የቱሪስቶቹ ቁጥር ከዕቅድ በታች ቢሆንም ከገቢ አንፃር የተሻለ አፈፃፀም የነበረዉ መሆኑን በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤት የልማት ዕቅድ ባለሙያ ህይወት ወንድሙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
261ሺህ 286 የሀገር ዉስጥ ቱሪስቶች ጉብኝት ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን ከሀገር እና ከዉጪ ቱሪስቶች በአጠቃላይ ከ530 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል ። በከተማዋ ዉስጥ በርካታ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ሲኖሩ የአዞ እርባታ ፣የጫሞ ምንጮች ፣አባያ እና ጫሞ ሀይቅ የትራንስፖርት ችግር ስለሌለባቸው በዘጠኝ ወሩ በይበልጥ ከተጎበኙ ስፍራዎች መካከል ዋነኞቹ መሆናቸውን ባለሙያዋ ተናግረዋል ።
በሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወይንም ከትናንሽ ቁርስ ቤቶች አንስቶ እስከ ትላልቅ ሆቴሎች ደረስ ክትትል በማድረግ የመስተንግዶ እንዲሁም የመኝታ ክፍል እድገት ላይ ተሰርቷል ተብሏል ።
በመባ ወርቅነህ

ትራምፕ ግጭቱን የማስቆም ስልጣን አላቸው ሲሉ የቀድሞ የእስራኤል ዲፕሎማት ተናገሩ
በእስራኤል እና በኢራን መካከል ያለውን ግጭት የማስቆም ሥልጣን በአብዛኛው ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ነው ሲሉ ለሁለት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ምክር የሰጡት የቀድሞ ዲፕሎማት አሎን ፒንካስ ተናግረዋል። ትራምፕ በሰላም ስምምነት ለመደራደር በሚያስችል ሁኔታ ላይ ናቸው ሲሉ ፒንካስ ለኒውስዴይ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ገልፀዋል።
ፕሬዚዳንቱ በድርድር ላይ የተመሰረተ ሰላምን ለመቀበል የሚያስችል ሁኔታን ለቴህራን ሊያቀርቡ ይችላሉ። ነገር ግን ኢራን ደካማ የመደራደር ቦታ ላይ በመሆኗ ትግሉን እንድትቀጥል እና በእስራኤል ላይ የበለጠ ጉዳት ለማድረስ ማበረታቻ ነው በማለት "በአንጻሩ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልኩን አንስተው ኔታንያሁ 'በቃህ ይህን ለመጨረስ 24 ሰአት አለህ' ሊላቸው ይችላሉ ሲሉ ተደምጠዋል።
በሌላ በኩል የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኢል ባቃኢ እንዳሉት የኢራን ፓርላማ የኒውክሌርን መከላከል ስምምነትን ለመተው ህግ ለማውጣት እየሰራ ነው ብለዋል። ሆኖም ግን ቴህራን ጅምላ ጨራሽ የጦር መሣሪያዎችን ማምረት እንደምትቃወመው ገልፀዋል። እ.ኤ.አ. በ1968 የተፈረመው እና በ1970 ሥራ ላይ የዋለው 190 አባላት ያሉት ስምምነት ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ ውጪ ያሉ ፈራሚዎች የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዳይገዙ ከልክሏል። በምላሹ በተባበሩት መንግስታት የሚመራውን ሰላማዊ የኒውክሌርየር ፕሮግራሞችን በሃይል ማመንጨት እንዲቀጥሉ ይፈቅዳል።

እስራኤል አዲስ የተሾሙትን የአብዮታዊ ዘብ ከፍተኛ አዛዥን መግደሏን አስታወቀች
የእስራኤል ጦር በቴህራን ላይ ባደረሰው ጥቃት የአብዮታዊ ዘብ ኻታም አል-አንቢያ ማዕከላዊ ዋና መሥሪያ ቤት ኃላፊ አሊ ሻድማኒ መግደሏን ገልፃለች። ሻድማኒ የኢራን “ከፍተኛ የጦር አዛዥ” እና “የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔይ የቅርብ ሰው” ነበሩ ተብሏል።
የእስራኤል መረጃ ተከትሎ ዘገባው እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከኢራን በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም።
አሁን ተገድለዋል የተባሉት ሻድማኒ የተሾሙት እስራኤል የካታም አል-አንቢያ ማዕከላዊ ዋና መሥሪያ ቤት አዛዥ የነበሩትን ጎላም አሊ ራሺድን አርብ ዕለት ከገደለች በኋላ ነው።
በተያያዘ መረጃ እስራኤል ኢስፋሃን ላይ በፈፀመቺው ጥቃት 3 ሰዎች ተገድለዋል ተብሏል። የኢራኑ መህር የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ እስራኤል ዛሬ ማለዳ በካሻን ከተማ በማዕከላዊ ኢስፋሃን ግዛት የፍተሻ ኬላ ላይ በፈፀመችው ጥቃት በትንሹ 3 ሰዎች ሲሞቱ 4 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል።
የታስኒም እና የISNA የዜና ኤጀንሲዎችም ስለሞቱት ሰዎች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ግን አልሰጡም። እንደዘገበነው ከሆነ እስራኤል በኢራን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ከ220 በላይ ሰዎች ተገድለዋል የተባለ ሲሆን ከሟቾቹ መካከልም ቢያንስ 70 ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል ተብሏል።
በሚሊዮን ሙሴ

በ2017 በጀት ዓመት በ11 ወራት ከግብር ከፋዩ ማህበረሰብ 91 ቅሬታዎች ቀርበው ሁሉም መፈታታቸውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ
ቢሮው በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ችግሮች ካጋጠሙት በየደረጃው ለሚገኙ ለቅሬታ የስራ ክፍሎች በማቅረብ እንዲፈታ ማድረግ ላይ እንዳለነት አስታውቋል።
በቢሮው የአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወይዘሮ አበባዬነሽ መልሴ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በ2017 በጀት ዓመት በ11 ወራት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች 68 እንዲሁም በዋና መስሪያ ቤት 23 በድምሩ 91 ቅሬታዎች ቀርበው 59ኙ ተገቢነት ያላቸው እና 32ቱ ተገቢነት የሌላቸው ሆነው ተገኝተዋል።
ቢሮው የቅሬታ አቀራረቡን በቴክኖሎጂ ለማዘመን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ በመሆኑ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ እንዲህ ዓይነት ቅሬታ ፣ ጥቆማ ወይም አስተያየት ሲኖራቸው ቅሬታዎችን በሀሳብ መስጫ ላይ ከመፃፍ ይልቅ ለአሰራርና ለግልፀኝነት ያመች ዘንድ በፅሁፍ ቢያቀርቡ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
አጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ በታክስ ቅሬታ ላይ የሚቀርብ አቤቱታ እና የሠራተኛ ቅሬታን እንደማይጨምር ተገልጿል።
በትግስት ላቀዉ

በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/kdOk0mCXBao?si=HvJ7F3JLOhE8Eet7
#ዳጉ_ጆርናል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/kdOk0mCXBao?si=HvJ7F3JLOhE8Eet7
#ዳጉ_ጆርናል
ራሚስ ባንክ የሞባይል መተግበሪያ እና የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በይፋ አስጀመረ
ራሚስ ባንክ ቅዳሜ ሰኔ 7 1 2017 ዓ.ም የሞባይል መተግበሪያ እና የካርድ ባንኪንግ አአገልግሎቶቹን ስራ ለማስጀመር በተካሄደው ፕሮግራም ላይ የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ራቢ ሁሴን እና የባንኩ ስራ አስፈፃሚ አቶ አሊ አሀመድ አሊ ባደረጉት ንግግር ራሚስ በይፋ ስራ ከጀመረ ገና ሁለት አመት የሞላው ቢሆንም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ላይ በስፋት እየሰራ መሆን የሚያሳዩ አመላካች ውጤቶችን በዚሁ መልክ እያዳበረ ማቅረቡን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።
ለደንበኞቹ ክፍት ካደረጋቸው ሁለት የዲጂታል አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ ራሚስ ሞባይል አፕ የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ ደንበኞች ስማርት ስልክ በመጠቀም ብቻ ያለምንም የጊዜ ገደብ ገንዘብ እንዲያንቀሳቅሱ፣ ክፍያ እንዲፈፅሙ፣ የሞባይል ካርድ እንዲሞሉ እንዲሁም ወደ ቴሌ ብር ዋሌት እንዲያስተላልፉ በማስቻል የደንበኞችን እርካታ በእጥፍ እንደሚጨምር ተገልጿል።
የራሚስ ካርድ ባንኪንግ ደንበኞች ባሻቸው ቦታ እና በፈለጉት ባንክ በመጠቀም በኤቲኤም ገንዘብ እንዲያወጡ የሚረዳ መሆኑና በተጨማሪም በፈለጉት የፖስ ማሽን በሱፐርማርኬቶችና በተለያዩ የግብይት ላይ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉ ይረዳቸዋል ተብሏል።
ራሚስ ባንክ ለትግበራ ያበቃቸው ፕሮጀክቶች ደንበኞችን ወደ ላቀ የዲጂታል ምህዳር የሚመሩና ባንኩ በዲጂታሉ ዘርፍ ልቆ ለመታየት ያለውን ቁርጠኝነት በጉልህ ያሳዩ እንደሆኑ የባንኩ ስራ አስፈፃሚ ተናግረዋል።
በቅድስት ደጀኔ

እስራኤል ኢራንን ስታጠቃ በጋዛ እንደሚገኙት የመጠለያ ድንኳን መስለዋት ነበር ሲል አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ
የኩዊንሲ ስቴት ክራፍት ተጠያቂነት ኢንስቲትዩት ስራ አስፈፃሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ትሪታ ፓርሲ በኢራን ጥቃቶች የሚደርሰው ጉዳት እየጨመረ በመምጣቱ የእስራኤል የሚፈሩ የሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶች ስንጥቅ እያሳዩ እንደሆነ ግልፅ ነው ብለዋል ። ፓርሲ ለአልጀዚራ እንደተናገሩት "የተከሰተ የሚመስለው ኢራናውያን የእስራኤልን የአየር መከላከያ ስርአቶችን አዋርደዋል፣ እናም በጥቂት ሚሳኤሎች የብዙ ሚሳኤሎችን ውጤት እያገኙ ነው ብለዋክ።
የቪዲዮ ማስረጃዎች የዴቪድ ወንጭፍ፣ የአይረን ዶም እና የአሜሪካ መከላከያ ስርዓቶች THAAD "ውጤታማ አለመሆንን" ያሳያል ብለዋል። "በአጠቃላይ እስራኤላውያን በግልፅ የተሳሳተ ስሌት ሰርተዋ። ይህ ቀላል እንደሚሆን አስበው ነበር ምልክ አሁን ለአንድ አመት ተኩል ያህል ስደተኞችን በድንኳን ውስጥ በጋዛ ላይ በቦምብ ከማፈንዳት ጋር ተመሳሳይ አድርገውት ነበር።
ይልቁንስ እውነተኛ ፍልሚያ እያገኙ ነው። እናም ጥያቄው የእስራኤል መንግስትን ስሌት ምን ያህል ቀይሮታል?" የሚለውን ነው ሲሉ ተደምጠዋል።ፓርሲ እስካሁን ድረስ እስራኤል ያደረገችው ብቸኛው እርምጃ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ጦርነቱ እንድትገባ መጠየቅ ነው፣ "ነገር ግን አሜሪካ እንደዛ ለማድረግ ምንም አይነት ምልክት አላሳየችም" ብለዋል።

የኃይል ስርቆት በሚፈፅሙ በመካከለኛ ኢንዱስትሪ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚዎች ላይ የ1 ሚሊዮን ብር ቅጣት ይተላለፋል ተባለ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት ፣ጥራት ያለዉና ያልተቆራረጠ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ቢሆንም የኃይል እና የመሠረተ ልማት ስርቆት ፈተና እንደሆነበት አስታዉቋል ።
ተቋሙ በዛሬዉ ዕለት በኢነርጂ አጠቃቀም ፣ቆጣሪና ተያያዥ ዕቃዎች ምርመራ መመሪያ ላይ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከዚህ በኋላ በኃይል እና በመሠረተ ልማት ላይ በሚፈፀሙ ስርቆቶች ላይ ትዕግስት እንደማይኖረዉ ገልጿል ።
ይህን እኩይ ተግባር በሚፈፅሙ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ታርፍ መደብ ተጠቃሚዎች ላይ የ1ሚሊዮን ብር ቅጣት እንደሚተላለፍ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሽያጭና የደንበኞች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይህይስ ስዩም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። ለዝቅተኛ ኢንዱሰትሪ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚዎች 750ሺህ ብር ፣ለጠቅላላ ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ 500ሺህ ብር ፣ለመኖሪያ ቤት ታሪፍ መደብ ተጠቃሚ 20 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚተላለፍ አቶ ይህይስ አክለዋል ።
ይህንን የስርቆት ተግባር በተደጋጋሚ በሚፈፅሙ አካላት ላይ የቅጣት መጠኑ እጥፍ እየሆነ እንደሚሄድ ተገልጿል ። የኤሌክትሪክ ኃይል ስርቆት መፈጸሙ ለተረጋገጠበት ደንበኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦቱ በጊዜያዊነት ከምሰሶ ወይም ከአቅርቦት መነሻ ላይ የሚቋረጥ ሆኖ የድርጅቱ የህግ አካል የምርመራ ሂደቱን ማጠናቀቁን በጽሑፍ እስኪያሳውቅ እንዲሁም ደንበኛው የሚጠበቅበትን ክፍያ እስኪፈፅም እና መተማመኛ የውል ሠነድ ላይ እስኪፈርም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ ይሆናል ተብሏል፡፡

ኢራን በከፍተኛ ደረጃ የበለጸገውን ዩራኒየም የምትከማችበትን ቦታ በተመለከተ የምናውቀው የለም ሲል የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ አስታወቀ
የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጥበቃ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ውስጥ ነገሮች የት እንዳሉ በትክክል አናውቅም ብለዋል። ኦሊ ሄይኖን እስራኤል በቴህራን የኒውክሌር አቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሳ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
በናታንዝ የሚገኘው ተቋም "ለመመለስ ቢያንስ አመታትን ይወስዳል" ሲሉ ተደምጠዋል። "እኔ እንደማስበው ከእነዚህ የቦምብ ጥቃቶች በኋላ በጣም መጥፎ ቅርፅ ላይ ነው" ነገር ግን ቁልፉ ጥያቄ ይቀራል የሚሉት ሄይኖን ኢራን በከፍተኛ ደረጃ የበለጸገውን ዩራኒየም ከ400 ኪሎ ግራም በላይ የምትከማችበትን ቦታ በተመለከተ የምናውቀው የለም ብለዋል።
ሚስጥራዊ ጣቢያ ካላቸው እና የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ የማያውቀው በሚስጥር የጦር መሳሪያ ደረጃ ዩራኒየም ማበልጸግ ከቻሉ በእጃችን ላይ ትልቅ ችግር አለብን ሲሉ ተደምጠዋል።