Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ሳሙኤል ኤቶ ከእርሱ ጋር ግጭት ዉስጥ ገብቶ የነበረዉ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አጋሩ ለ 5 አመታት ወደ እግርኳስ ዝር እንዳይል አስቀጣ
የካሜሩን እግርኳስ ፌደሬሽን የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ፣ የቼልሲ እና የሪያል ማድሪድ ተጨዋች የነበረዉን ጄሬሚ ሶሬል ለአምስት አመታት ወደ ሀገሪቱ የእግርኳስ ዘርፍ ዝር እንዳይል አግዶታል።
የካሜሩን እግርኳስ ፌደሬሽን ከዚህ ዉሳኔ የደረሰዉ ጄረሚ ፤ ከቀድሞ የብሔራዊ ቡድን አጋሩ እና ከአሁኑ የካሜሩን እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ከሳሙኤል ኤቶ እና ቦርድ አባላት ጋር ግጭት ዉስጥ ከገባ በኋላ ነዉ።
በ 2023 በተፈጠረው በዚህ ዉዝግብ ወቅት ካሜሩን ከ ጋምቢያ ጋር ጨዋታ ነበራት። በጨዋታዉ ላይ በተፈጠረው ግጭት ጄረሚ በስተመጨረሻ በጸጥታ ሀይሎች ከስታዲየሙ እንዲወጣ ተደርጓል።
በዚህ ምክኒያት ለአምስት አመታት ወደ እግርኳስ እንዳይመጣ እንዲሁም 10 ሚሊዮን የካሜሩን ፍራንክ ወይንም 13 ሺህ ፓዉንድ ቀጥቶታል። በተመሳሳይ የጄረሚ የቅርብ ረዳትም የ 2 አመት ቅጣት እና የ 6 ሺህ 500 ፓዉንድ ቅጣት ተጥሎበታል።
ጄረሚ ከሪያል ማድሪድ ጋር 2 ሻምፒዮንስ ሊግ ያሳካ ሲሆን ለኒዉካስትልም ተጫዉቷል።
በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

ሩሲያ በዩክሬን ዋና ከተማ በፈፀመችው ጥቃት ሰባት ሰዎች ተገደሉ
በኪየቭ ክልል በአንድ ሌሊት በተፈፀመ የሩስያ የሚሳኤል እና የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት ቢያንስ ሰባት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆስለዋል ሲሉ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ኢጆር ክላይመንኮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፉት ጽሁፍ የመኖሪያ አካባቢዎች፣ ሆስፒታሎች እና የስፖርት መሠረተ ልማቶች በጥቃቱ ተጎድተዋል።
ከሞቱት መካከል ቢያንስ ስድስቱ በዋና ከተማው ባለ ከፍተኛ ፎቅ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች መሆናቸውን የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊችኮ ገልፀው ሌሎች 22 ሰዎች በከተማዋ ቆስለዋል ብለዋል። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች ላይ ከፍተኛ የአየር ላይ ጥቃቶችን እየፈፀመች ትገኛለች። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ሰኞ እለት ስለግጭቱ ለመወያየት ወደ ለንደን አቅንተዋል።
በቅርቡ ቀናት ውስጥ ሩሲያ 352 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና 16 ሚሳኤሎች በዩክሬይን ግዛቶች በተለይም በኪየቭ አካባቢ ላይ ጥቃት መፈፀሟን የዩክሬን አየር ሃይል አስታውቋል። የዩክሬን የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የተደናገጡ ነዋሪዎች እየነደደ ካለው እና ከፈራረሰው ህንጻ ሲወሰዱ የሚያሳይ ምስል አጋርቷል። በርካታ ነዋሪዎች በሜትሮ የባቡር ጣቢያ ውስጥ ተጠልለው አድረዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል

በሁሉም ክልሎች 125 የኤም ፖክስ የለይቶ ማከሚያ ማዕከላት ተደራጅተው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኑ
የኤም ፖክስ በሽታው በተከሰተባቸው ክልሎች የለይቶ ማከሚያ ማዕከላትን በማቋቋም ለታማሚዎች ህከምና እየተሰጠ እንዲሁም በሽታው ባልተገኘባቸው ክልሎች ደግሞ በሽታው ቢከሰት ለማከም የሚያስችሉ የለይቶ ማከሚያ ማዕከላትን በማዘጋጀት ዝግጁ ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የኤምፖክስ ታማሚ ከተገኘበት ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአጠቃላይ ለ324 በበሽታው ለተጠረጠሩ ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 22ቱ በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡
ከነዚህም መሃል የአንድ ህጻን ህይወት ሲያልፍ፣ 15ቱ ከበሽታው ሙሉ በሙሉ አገግመው ከለይቶ ህከምና ማዕከላት የወጡ ሲሆን የተቀሩት 6 ታማሚዎች በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ለይቶ ማከሚያ ማዕከላት ውስጥ ህክምናቸውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ኤም ፖክስ ወረርሽኝ ከተከሰተባቸው 7 ሀገራት በአለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች ለመጡ 179 ሺ 228 መንገደኞች የኤምፖክስ በሽታ ማጣራት የተደረገ ሲሆን በሁሉም የጎረቤት ሀገራት መግቢያና መውጫን ጨምሮ የየብስ እና አየር መንገድን በመጠቀም ወደ ኢትዮጵያ ለገቡ ከ6 ሚሊዮን በላይ መንገደኞች የማጣራት ስራ በማከናወን ሊከሰት የሚችለውን ድንበር ተሻጋሪ የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ መቻሉን ተገልፃል።
ለበሽታው አጋላጭ ሁኔታዎች ተብለው ከተለዩት መንገዶች መካከል በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር የሚደረግ የሰውነት ንክኪ፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲሁም ከታማሚ ሰው ጋር ንክኪ ያለውን ቁስ በጋራ መጠቀም በዋነኝነት እንደሚጠቀስ ሚኒስቴር መስራቤቱ የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ የበሽታውን አሳሳቢነት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስባል።
ህብረተሰቡም ከፍተኛ ትኩሳት ፥ራስ ምታት፥ የጀርባና የጡንቻ ህመም ፥ የእጢ ማበጥ፥ ለመተንፈስ መቸገር እና የቆዳ ላይ ሽፍታ ሲያሳዩ ወዲያዉኑ ራስን ከሌሎች ሰዎች መለየት እና ወደ ጤና ተቋም በመሄድ የሕክምና እርዳታ ማግኘት፣ እንዳለበትም ተገልፃል።

የኢራን ጦር ዩናይትድ ስቴትስ ኃይለኛ ምላሽ እንደሚጠብቃት አስጠነቀቀ
የኢራን ጦር ካታም አል-አንቢያ ክፍል ቃል አቀባይ ዩናይትድ ስቴትስ በሦስት ዋና ዋና የኒውክሌር ቦታዎች ላይ የቦምብ ድብደባ ከፈጸመች በኋላ “ከባድ መዘዞችን የሚያስከትሉ ተግባራት ይኖራሉ” ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የኢራን የዜና ኤጀንሲዎች ስማቸውን ያልተጠቀሷቸውን ቃል አቀባይ ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤልን ወክላ “ወንጀለኛ” ድርጊት ፈጽማለች በማለት ክስ ሰንዝረዋል፣ይህም የኢራንን ሉዓላዊነት “በአደባባይ ይጥሳል” ሲሉ አክለዋል።
ቃል አቀባዩ ስለ እስራኤል ሲናገሩ "ይህ የጥላቻ ተግባር የተፈፀመው እየሞተ ያለውን የጽዮናዊ አገዛዝ ለማንሰራራት በማለም ነው። የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት የኢራንን “ህጋዊ እና የተለያዩ ኢላማዎች” እንደሚያሰፋም አክለዋል። ኻታም አል-አንቢያ ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኮርፖሬሽን ተለይቶ የሚንቀሳቀስ በኢራን ጄኔራል ስታፍ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስር የሚገኝ የወታደራዊ ሃይል ልዩ ክፍል ነው።
በሌላ በኩል ታይምስ ኦፍ እስራኤል እንደዘገበው የእስራኤል ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን "ስትራቴጂያዊ የመሠረተ ልማት ተቋማት" አቅራቢያ መመታቱን አረጋግጧል። በአካባቢው በሚገኙ በርካታ ከተሞች የኃይል መቆራረጥ እንዳለ ገልጿል። "ቡድኖች በተቻለ ፍጥነት የኃይል አቅርቦትን ወደነበረበት ለመመለስ በማቀድ መሬት ላይ ወደተለያዩ ቦታዎች በመጓዝ ላይ ናቸው፤ ኦፕሬሽኑ የመሠረተ ልማት ጥገና እና የደህንነት አደጋዎችን ማስወገድን ያካትታል እንዲሁም ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት እየተካሄደ ነው" ሲል የእስራኤል ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

ኢትዮጲያ በ 2018 የጋዝ ምርትን ወደ ገበያ ልታቀርብ ነው ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ተናገሩ
👉🏼ጠ/ሚኒስትሩ ከሰባት አመታት በፊትም ኢትዮጵያ ድፍድፍ ነዳጅ ማዉጣት ሙከራ እና ሽያጭ እንደምትጀምር ተናግረዉ ነበር
ኢትዮጲያ የራሷን ጋዝ ለማምረት ጥረት ስታደርግ መቆየቷ የተገለፀ ሲሆን በመጪው መስከረም የ 2018 ዓ/ም አዲስ አመት ላይ ወደ ገበያ ሊቀርብ መሆኑን ሰምቻለሁ ሲል ኢትዮ ኤፍኤም ዘግቧል፡፡
ይህ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በሀገሪቱ ከሚገኙ የሚዲያ አመራሮች እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር በዛሬው ዕለት እያደረጉት ባለው የጋራ ውይይት ላይ ነው፡፡
ይህ ምርት የት አካባቢ እንደሆነ በቀጥታ ባይናገሩም በንግግራቸው ወቅት " ላለፉት ሁለት ሦስት ዓመታት እኔ የምጎበኘው ጋዙን ነው እናንተ የምታዩት ስንዴውን " ሲሉ ተናግረዋል።
ከሰባት አመታት በፊትም ጠ/ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ድፍድፍ ነዳጅ የማምረት ሙከራ እና መሸጥ እንደምትጀምር ተናግረዉ ነበር። በተለያዩ ምክኒያቶች ስራ ላይ ባይዉልም።
በዚህ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጲያ ማዳበሪያን ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር ለማምረት ከስምምነት ላይ መድረሷንም አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ለመገንባት ውጥን መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የመንግስትን የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡበት ወቅት መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
በወቅቱም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታው ከ2.5 እስከ 3 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚጠይቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረው ነበር፡፡
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጪው የ 2018 መስከረም ወር ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ሪቫኑ እንደሚቆረጥ በዚሁ መድረክ ላይ ተናግረዋል።

በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን
ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/SUqCVs3MXf4?si=f2OYdsn7uOPosB31

በአዲስ አበበ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አልፏል
ከሟቾቹ መካከል የ3 ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን የሚገኝበት ሲሆን በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ/ም ረፋድ ላይ በግምት 3 ሰዓት ገደማ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባጋጠመ የተሽከርካሪ አደጋ የሞት እና የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡
በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መርዕድ ደበሌ እንደተናገሩት አደጋው ሊከሰት የቻለው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-78979 ኢት የሆነ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-04273 ኢት ከሆነ ሌላ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ እና መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ ነው፡፡
አውቶቡሱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ከገባ በኋላ ከዩኒሳ አደባባይ ወደ ሃይሌ ጋርመንት ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-77970 ኦሮ ከሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ በዶልፊኑ ውስጥ ከነበሩት ተሳፋሪዎች መካከል አሽከርካሪውን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ዋና ኢንስፔክተር መርዕድ አስረድተዋል፡፡
ከሟቹቹ መካከል የ3 ዓመት ህፃን እንደሚገኝበት የጠቀሱት ዋና ኢንስፔክተሩ፤ በሌሎች 8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው ላይ የቆመ እና በጉዞ ላይ የነበረ ሌሎች ሁለት ተሽከርካሪዎች በአውቶቡሱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተር መርዕድ ደበሌ አስታውቀዋል፡፡

በወሊድ ምክንያት የሚከሰት የእናቶችን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን የአዳማ ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት አስታወቀ
ባለፋት 10 ወራት 22 ሺህ እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ማግኘታቸዉን የአዳማ ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት አስታዉቋል ።
የአዳማ ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሲስተር ሰሚራ መሀመድ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በወሊድ ምክንያት የሚከሰት የእናቶችን እና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ሰፊ ስራ በመሠራቱ ከአቅም በላይ ከሆነ ምክንያት ዉጪ በወሊድ ወቅት የሚከሰት የእናቶችን ሞት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል ።
ነፍሰጡር እናቶች ከእርግዝና ወቅት አንስቶ እስከ ወሊድ ባለዉ በጤና ተቋማት ክትትል እንዲያደርጉ በሰለጠነ ባለሙያ ተገቢዉን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል ብለዋል ። ከሆስፒታሎች ዉጪ በ2015 በጀት ዓመት በአንድ ጤና ጣቢያ ላይ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ይሰጥ አንደነበረ የገለፁት ሀላፊዋ በዚህ ዓመት አዋሽ መልካሳ በተባለ ጤና ጣቢያ ላይ የቀዶ ማዋለድ ህክምና የተጀመረ ሲሆን ይህም የህፃናትንና የእናቶችን ሞት በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል ።
በተጨማሪም የጤና መድህን ኢንሹራንስ አባላት ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም አዳዲስ አባላትን በማፍራት ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል ። ባለፉት 10 ወራት ከ76ሺህ በላይ አባላትን በማፍራት 96 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ሲስተር ሰሚራ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።
በመባ ወርቅነህ

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የስፖርት ጋዜጠኛ አሉላ ፍሬዉ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ድሬዳዋ ከተማ እና ስሁል ሽረ ያደረጉት ጨዋታ የጨዋታ መጭበርበር የነበረበት ነዉ ሲል ማስረጃዎችን በማቅረብ እየተሟገተ ነዉ።
ጋዜጠኛዉ ጨዋታዉን ድሬዳዋ ከተማ 4 ለ 2 አሸንፎ ይጠናቀቃል ብለዉ በርካቶች ትክክለኛ ዉጤትን እየገመቱ አቋማሪ ድርጅቶችን ገንዘብ በልተዋል ሲልም በኤንቢሲ ቴሌቪዥን በሚተላለፍ የስፖርት ፕሮግራም ላይ ተናግሯል።
በማህበራዊ የትስስር ገጽም በሚሊዮኖች ገንዘብ ያሸነፉ ሰዎች አሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ስፖርት ከተመልካቾች አስተያየቶች/ኮሜንቶች ላይ ተመልክቷል።
በቪዲዮዉ ላይ እንደሚታየዉም ሀብታሙ የተሰኘዉ የስሁል ሽረ ተከላካይ ራሱ ላይ ለማግባት ሙከራ ሲያደርግ በግልጽ ይታያል።👇🏼

አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ኤሌክትሪክ ተቋርጧል
አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
የኤሌክትሪክ ሃይል በከፊል የተቋረጠው ከዋናው ግሪድ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ነው፡፡
አሁን ላይም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያጋጠመውን ብልሽት ለማስተካከል ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ይገኛል፡፡
ለተፈጠረው ችግር ደንበኞችን ይቅርታ የጠየቀው አገልግሎቱ÷ በትዕግስት እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኢራን ጠቅላይ መሪ ፑቲን ከአሜሪካ ጥቃት በኋላ የበለጠ ግፊት እንዲያደርጉ ጠየቁ
የኢራን ጠቅላይ መሪ እ.ኤ.አ. ከ1979 አብዮት በኃላ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ከደረሰው ትልቁ የአሜሪካ ጦር እርምጃ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ሩሲያ ተጨማሪ እርዳታ ለኢራን እንድታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ሰኞ ዕለት ወደ ሞስኮ ልከዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና እስራኤል ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሚኒን ስለመግደል እና የስርዓት ለውጥን በተመለከተ በአደባባይ መናገራቸው ሩሲያ መካከለኛው ምስራቅን ወደ ገደል ሊያስገባ ይችላል የሚል ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ፑቲን የእስራኤልን ጥቃት ቢያወግዙም፣ አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ ስላደረሰችው ጥቃት እስካሁን አስተያየት አልሰጡም። ባለፈው ሳምንት መረጋጋት እንዲሰፍን ጠይቀው የነበረ ሲሆን የሞስኮን ሚና በኒውክሌር መርሃ ግብሩ ላይ አስታራቂ አድርገው አቅርበዋክ። ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ ለሮይተርስ እንደገለፀው የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራክቺ ከካሜኒ የተላከላቸውን ደብዳቤ ለፑቲን በማድረስ የፑቲንን ድጋፍ የሚሹ ናቸው ብለዋል። ቴህራን ምን ዓይነህ እርዳታ እንደምትፈልግ ግን ምንጮቹ አላብራሩም።
ክሬምሊን ፑቲን የኢራንን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እንደሚቀበሉ ቢናገሩም በምን ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩ ግን አላሳወቀም። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አግራቺን ጠቅሶ ታስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ኢራን እና ሩሲያ አሁን ባለው የመካከለኛው ምስራቅ መባባስ ላይ አቋማቸውን አንድ ለማድረግ እየሰሩ ነው። ፑቲን በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል ለማደራደር ደጋግመው ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፥ ኢራን የሲቪል ኒውክሌር ኢነርጂ ተጠቃሚነቷን ቀጣይነት ባለው መልኩ በማረጋገጥ ሞስኮ ውዝግብ መፍታት ላይ ሃሳብ ማቅረቧ ይታወሳል።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የነዳጅ እጥረት የፈጠሩ ማደያዎች ታሽገዋል
ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ህብረተሰቡን ሲያማርሩ የነበሩ የነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል! የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አስቴር ደሳለኝ እንዳስታወቁት፣ በቂርቆስ ነዳጅ በመደበቅ እጥረት እንደተፈጠረ በማስመሰል የንግድ አሻጥር ሲፈጽሙ የነበሩ ማደያዎች ታሽገዋል።
የታሸጉት ማደያዎች እና የተፈጸመው ጥፋት፦
1. ባምቢስ ኖክ ነዳጅ ማደያ (ወረዳ 01)፦ ከ12 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚንና ናፍጣ እያለ "አይሰራም" በማለት ለህገ ወጥ ንግድ አመቻችቷል።
2. OLA ነዳጅ ማደያ (ደምበል ፊት ለፊት)፦ ነዳጅ እያለ "የለም" በማለት እና ሰራተኛ ባለማስገባት ሰልፍ እንዲበዛ በማድረግ የንግድ አሻጥር ፈጽሟል።
ወይዘሮ አስቴር አክለውም፣ የእነዚህ ማደያዎች ስራ አስኪያጆች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰቡ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እንደሌለ በመረዳት፣ "ናፍጣም ሆነ ቤንዚን የለም" በማለት አላስፈላጊ የንግድ አሻጥር የሚፈጥሩ የማደያ ባለቤቶች ሲኖሩ፣ በነፃ የስልክ መስመር 8588 እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጥቆማ እንዲሰጥ ወይዘሮ አስቴር ደሳለኝ ጥሪ አስተላልፈዋል።
መረጃው የቂርቆስ ክፍል ከተማ ነው

በአሰላ ከተማ የመስረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ከፍተኛ የሆነ ጭማሪ ማሳየቱ ተነገረ
👉 ከዚህ ቀደም 900 ብር ሲሸጥ የነበረ አንድ ኪሎ ቡና በአሁኑ ሰዓት እስከ 1300 ብር እየተሸጠ ይገኛል
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመዲናችን አዲስ አበባ ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ከፍተኛ ጭማሬ እያሳየ መሆኑ ተገልፆል። በዚህ ጉዳይ ብስራት የአሰላ ከተማ ነዋሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳሳቢና ዝቅተኛ ኑሮ ላላቸው ሰዎች ብም ሳይሆን መካከለኛ ገቢ አለው ለሚባለው ማህበረሰብም ከባድ በሚባል ደረጃ በተለያዩና በዕለት ተዕለት ውሎ በጥቅም ላይ የሚውሉ ሸቀጦች ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መስተዋሉ ተገልጿል።
ብስራት ያነጋገራቸው የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች እንደጸናገሩት ከሆነም እስከ ቅርብ ጊዜ ከ 500 እስከ 700 ብር ሲሸጥ የነበረ አንድ ኪሎ በርበሬ አሁን እስከ 1200 ብር እየተሸጠ ነው ያሉ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም እስከ 900 ብር ድረስ ሲሸጥ የነበረ አንድ ኪሎ ቡና አሁን ላይ ከ1200 እስከ 1300 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን አንስተዋል።
ከዚህ ቀደም ከ6ሺ እስከ 8ሺ ብር ሲሸጥ የነበረ 100 ኪሎግራም ገብስ አሁን ላይ እስከ 12 ሺ ብር ድረስ እየተጠየቀ መሆኑ ጣብያችን ያነጋገራቸው የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም ከዚህ ቀደም 17 ብር ይሸጥ የነበረ አንድ እንቁላል አሁን ላይ በ23 ብር እንደሚሸጥ ገልፀዋል።
የዋጋ ጭማሬው ምክንያት ለማወቅ በተደረገ ጥረት ጣቢያችን በከተማይቱ ያሉ ነጋዴዎችንን ያነጋገረ ሲሆን ከጅምላ አከፋፋዮች እቃ ለማምጣት በሚሄዱበት ወቅት የዋጋ ጭማሬ ከመመልከታቸው ውጭ የዋጋ ጭማሬው ምክንያት ይህ ነው ብለው ለመግለፅ እንደማችይሉና እነሱም ከአከፋፋዮች የሚያመጡበት ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ዋጋ ለመጨመር እንደተገደዱ ነግረውናል።
ከአሰላ ከተማ በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማም በቡና ዋጋ ላይ ጭማሪ መኖሩ የገበያ ዉሎ የሚያሳይ ሲሆን በአንድ አንድ አከባቢዎች አንድ ኪሎ ቡና እስከ 1200 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን ታዝበናል።
በሰብል አበበ

ከእስር ለማምለጥ ሞክሮ በፍሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ተቀርቅሮ የቀረው ሰው ግርምትን ፈጥሯል
ብራዚል ውስጥ ያጋጠመው ክስተት ከእስር ለማምለጥ ሲል በፎሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ለውስጥ እያተጓዘ በነበረበት ሰዓት ተቀርቅሮ የቀረው ሰው ማምለጡ ቀርቶብኝ አዱኑኝ ያለ ስለመሆኑ ተሰምቷል።
የ32 ዓመቱ ግለሰብ አለን ሊአንዶሮ ዳ ሲልቫ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከሪዮ ባርናኮ ማረምያ ቤት ለማምለጥ በሞከረበት ሰዓት በፍሳሽ ማስወገጃ ውስጥ ራቆቱን ተቀርቅሮ መገኘቱ ተነግሯል። ታድያ ወጣቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሊያድኑት በሄዱበት ሰዓት የሚታዩ ቁስሎች እንደነበሩት የገለፁ ሲሆን ግለሰቦ ለማምለጥ ባደረገው ሙከራ ጉዳት ማስተናገዱም ተገልፆል።
የእስር ቤቱ ሀላፊዎች ከኩነቱ በኃላ በሰጡት መግለጫ የማረምያ ቤቱ ጠባቂዎች በሌላ ስራ ተወጥረው በነበሩበት ወቅት የማምለጥ ሙከራ መፈፀሙን የገለፁ ሲሆን ነገር ግን ሊያመልጥ የሞከረበት የፍሳሽ ማስወገጃ ቀዳዳ ስፋት በልክ አለማወቁ እንዲያዝ እንዳደረገው ተገልፆል።
አለን የተባለው እስረኛ ምንም እንኳ ለህይወቱ አስጊ በነበረ ሆኔታ ውስጥ ገብቶ የነበረ ቢሆንም በተቀናጀ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥረት ተጨማሪ ጉዳት ሳያስተናግድ ሊያወጡት መቻላቸው ተነግሯል። በዚህም የመጀመርያ እርዳታ ተደርጎለት ወድያዉኑ ወደ እስር መመለሱ መረጃው አሳይቷል።
በሚሊዮን ሙሴ

በአፋር ክልል ባለፉት ሰባት ዓመታት ከ300 በላይ ፋብሪካዎች መገንባታቸው ተገለፀ
በአፋር ክልል ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ከ300 በላይ አምራች ፋብሪካዎች መገንባታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ መሐመድ ዓሊ ቢኢዶ እንደገለጹት፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የአፋር ክልል ህዝብ በኢኮኖሚ እኩል ተጠቃሚ መሆን መቻሉ ተገልጿል፡፡
እንደ አቶ መሐመድ አሊ ገለጻ በክልሉ ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ከ300 በላይ አምራች ፋብሪካዎችና አንድ ኢንደስትሪ ፓርክ ተገንብተው ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።
ከእነዚህ ከተገነቡ ፋብሪካዎች መካከል የጨውና የብሮሚን ማምረቻ ፋብሪካዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ፤ አፍዴራ ላይ ብቻ ከ20 በላይ ፋብሪካዎች መገንባታቻውን ገልጸዋል፡፡
ይህም ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል የፈጠረ፣ የስራ ባህልን ያጠናከረ እንዲሁም እንደ ትምህርት ቤትና ንፁሕ የመጠጥ ውሃ የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ያስቻለ መሆኑን አብራርተዋል።
በሰመኃር አለባቸው