Telegram Web Link
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

19 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል !

ታዳጊዋ አያንቱ ቱና ላይ የግበረስጋ ድፍረት የፈጸመው ግለሰብ በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሻፋሞ ወረዳ የ13 ዓመቷን ታዲጊ አያንቱ ቱና ላይ የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረውና በፖሊስ ተባባሪነት ጭምር አምልጦ ከ1 ዓመት በላይ ተሰዉሮ የነበረዉ ወጣት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ መረጃው ከተሰራጨ በኋላ በተደረገ ክትትልና ፍለጋ ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር ዉሎ ክስ ተመስርቶበት እንደነበር የአያንቱ ታላቅ ወንድም ወጣት ጴጥሮስ ቱና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ይኸው ግለሰብ አርብ ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቦ ዉሳኔ እንደተላለፈበት የአያንቱ ወንድም ተናግሯል።

የሻፋሞ ወረዳ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደምሴ ፉና ስለጉዳዩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲያስረዱ " የወረዳዉ ፖሊስ እና ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ ያቀረቡትን ጠንከር ያለ ምርመራ፣ የሰነድ እንዲሁም የሕክምና ማስረጃዎችን የተመለከተዉ የወረዳዉ ፍርድ ቤት ግለሰቡን ጥፋተኛ ነዉ በማለት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል " ብለዋል።

" ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ በማቆያ ዉስጥ የምትገኘዉ አያንቱ ደፋሪዋ እንደተያዘ ከተነገራት በኋላ ጥሩ መሻሻል ታይቶባታል " የሚለዉ የታዳጊዋ ወንድም ጴጥሮስ " ከዚህ በኋላ ከማቆያ ወጥታ ወደ ትምህርት ገበታዋ ትመለሳለች " ብሏል

" የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ለታዳጊዋ ድምፅ ለሆናችሁ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ " ብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
1.67K😡1.15K👏343🙏161😭65💔60🕊45😢24🤔16🥰14
#SafaricomEthiopia

አሁንም በSMS ጨዋታ ፈታ💬🎊 እያልን በየቀኑ እንሸለም! 🎁

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'START’ ብለን ወደ 34000 በመላክ  ወይም ወደ *799# በመደወል እንወዳደር! እናሸንፍ! በአንድ መልስ 1ብር ብቻ!

#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
155😡11🕊7🥰6😭5👏2🙏1
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጦርነት ከተጀመረ ከዚህ በፊት እንደምናቀው አይደለም ነገር ይበላሻል !! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በነበረው የህ/ተ/ም/ቤት ጉባኤን አንድ አባል " በትግራይ ክልል ዳግም ጦርንት እንዳይነሳ ስጋት አለ " በማለት በክልሉ ስላለው አሁናዊ የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራርያ እና ምላሽ ጠይቀዋል። " ህወሓት ለዳግም ግጭት ቅስቀሳ እያደረገ ነው "  በማለት " ከሰላም…
#Tigray

" በትግራይ በኩል የሚከፈት ጦርነት የለም ፤ ከሌላው ወገን የሚተኮስ ጥይት እንዳይኖር ጥንቃቄ ያሻል " - የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት

" በትግራይ በኩል የሚከፈት ጦርነት የለም ፤ ከሌላው ወገን በተሳሳተ ውሳኔ  ትግራይ የሚተኮስ ጥይት እንዳይኖር ጥንቃቄ ያሻል " ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ተናገሩ።

ፕሬዜዳንቱ " ሁሉም ነገር በሰላማዊ መንገድ ይፈታል ብለን ስለምናምን በትግራይ በኩል የሚጀመር ትንኮሳ እና ጦርነት አይኖርም " ብለዋል። 

" በክልሉ ደቡባዊ ዞን ያለው ችግር የመላው ትግራይ እንጂ የአከባቢው ብቻ አይደለም " ያሉት ፕሬዜዳንት ታደሰ " ጊዚያዊ አስተዳደሩ በዞኑ ካለው አስተዳደር በመነጋገር በሰላማዊ መንገድ ይፈታዋል " ሲሉ ተናግረዋል ።

ራሱን " የትግራይ የሰላም ሃይል " በሎ ከሚጠራውና በዓፋር ክልል ሆኖ የትጥቅ ትግል ከሚያካሂደው ሃይል ጋር ያለውን ችግር " በሰላማዊ ውይይት ይፈታል " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጪ ያለው አማራጭ ግን ህዝብን ለአደጋ የሚዳርግ ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል " ብለዋል።

" የትግራይ ሉአላዊነት ተደፍሮ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ወደ ቄያቸው ባልተመለሱበት ሁኔታ ላይ ተሆኖም ችግሮች በሰላማዊ መንገድ የመንፍታት ጉዳይ አንደኛ አማራጫችን ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ተፈናቃዮችና ስደተኞች ወደ ቄያቸው መመለስ  ከሁሉም ስራዎቻችን ቅድምያ የምንሰጠው ነው ጉዳዩ ጊዜ በወሰደ ቁጥር የሰላም በር እንዳያጠብ የፌደራል መንግስት የበኩሉን ሃላፊነት በመወጣት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
730🕊138😡22🥰19🤔17👏13💔10🙏8😱4😭3😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ቡድኑ ትግራይን ለማተራመስና ኢትዮጵያን ለመውጋት ከኤርትራ መንግስት ጋር እየሰራ ነው " - ስምረት ፓርቲ

የኢፌዴሪ መንግስት ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ የተሰረዘው ' #ህወሓት ' ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንጂ ማስታመም አይገባውም አለ ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ።

በቀድሞ የህወሓት ምክትል ሊቀ-መንበርና የትግል ጓደኞቻቸው በቅርቡ ከብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የቅድመ እውቅና ምዝገባ የተሰጠው ስምረት " ለህግ የማይገዛ ወመኔ " ሲል የገለፀው ህወሓት ትግራይን ለማተራመስና ኢትዮጵያ ለመውጋት ከኤርትራ መንግስት እየሰራ ነው " ሲል ከሶታል።

" ኋላ ቀር ቡድን " በማለት በገለፀው ህወሓት ምክንያት የትግራይ ህዝብ መልሶ ወደ ጦርነት  እንዳይገባ የፌደራል መንግስት ሃላፊነቱ እንዲወጣ አሳስቧል።

" ከአሁን በኋላ በትግራይ ላይ የሚፈፀሙ ጥፋቶች ብቸኛው ተጠያቂ ከዓለም አቀፍና አገራዊ ህጎች የተቃረነው ወመኔው ኋላ ቀር ቡድን እና መሰሎቹ መሆናቸው የኢትዮጵያ መንግስት መገንዘብ አለበት " ሲልም ስምረት ፓርቲ ገልጿል።

" የሃይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ወጣቶች በአገር ውስጥና በመላ ዓለም የሚገኙ ትግራዎት ቡድኑ በስልጣን የሚቆይባቸው እያንዳንዱ ቀናት በህዝብ ላይ አስከፊ መከራና ስቃይ የሚያስከትሉ መሆናቸው በመረዳት ትግላችሁ አጠናክሩ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ፓርቲው ለታጠቀው ሰራዊት ባስተላለፈው ጥሪ " ሌት ተቀን የጦርነት ነጋሪት ከሚጎስመው ኋላ ቀር ቡድን  ራሳችሁን በማራቅ ከሰላም ፈላጊ ህዝብ ጎን ተሰለፉ " ብሏል።

" ከአሁን በኋላ በትግራይ ህዝብ ላይ የሚፈፀም ወንጅልም ይሁን የሚቀሰቀስ ጦርነት በዝምታ ማየት በህዝብ ላይ የሚያስከትለው ከባድ አደጋ መዘንጋት ነው " ያለው ስምረት ፓርቲ " አደጋውን አስቀድሞ ለማስቀረት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ሚናቸው ከወዲሁ እንዲወጡ " በማለት ለአገር አቀፍና ዓለምአቀፍ ተቋማት ጥሪውን አቅርቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
1.38K😡307🕊147👏52🤔45🙏29😭27💔20🥰18😱9😢4
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#HoPR🇪🇹

" ድንጋጌውን ' ትክክል ነው ' ብለው ሲከራከሩ የነበሩ የፓርላማ አባላት ነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መደገፋቸው በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ያስብላል "  - የፓርላማ አባል

በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን " በሽፋን ስር " ሆኖ የመመርመር ኃላፊነት የተሰጠው ሰው፤ " ከግድያ በስተቀር " የሚፈጽማቸውን የወንጀል ድርጊቶች ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው ድንጋጌ ተሰረዘ።

ድንጋጌው የተሰረዘው አዋጁ " በሰፊው እንዲተረጎም ስለሚያደርግ " እና በአተገባበሩም ላይ " አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያስከትል ስለሆነ ነው " ተብሏል። 

አወዛጋቢው ድንጋጌ ተካትቶ የነበረው፤ በወንጀል የተገኘ ንብረትን ህጋዊ ማስመሰል እንዲሁም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣ አዋጅ ላይ ነበር።

አዲሱ አዋጅ በፓርላማ የጸደቀው ሰኔ 10፤ 2017 ዓ.ም. ነበር።

የተሰረዘድ ድንጋጌ " በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ ወይም በቁጥጥር ስር የሚደረግ ማስተላለፍን እንዲያስፈጽም የተመደበ ሰው፤ በግዴታው ላይ እያለ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት እና ከፈቃዱ ውጭ ሆኖ ከግድያ ወንጀል በስተቀር ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት የወንጀል ክስ አይቀርብበትም " ይላል።

አዋጁ በጸደቀበት ዕለት የውሳኔ ሃሳብ ለፓርላማ አባላት ያቀረበው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚቴ፤ ድንጋጌው እንዲካተት የተደረገው " ልዩ የምርመራ ስራን " " ውጤታማ የሚያደርግ በመሆኑ "ምክንያት እንደሆነ ገልጾ ነበር።

ቋሚ ኮሚቴው " ልዩ የምርመራ ዘዴን " በመጠቀም ስራውን የሚያከናውን ሰው፤ " የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚሰራ መሆኑን " እንደ ደጋፊ ምክንያት አቅርቦ ነበር።

ይሁንና ቋሚ ኮሚቴው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30 በተደረገ የተወካዮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ፤ ድንጋጌው እንዲሰረዝ የሚያደርግ የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል።

ድንጋጌው " አዋጁ በሰፊው እንዲተረጎም የሚያደርግ እና አተገባበሩ ላይም አሉታዊ ተጽእኖ የሚያስከትል ስለሆነ፤ አዋጁ ለህትመት ያልበቃ እና በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ፤ ቀሪ እንዲሆን ይህ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል " ብሏል።

የውሳኔ ሀሳቡ በአንድ ድምጽ ተዐቅቦ ፀድቋል።

የፓርላማ አባላት ምን አሉ ?

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፓርላማ ተወካይ አቶ ባርጠማ ፈቃዱ ፦

" አዋጁ ተመልሶ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምጣቱ የምክር ቤቱን አቅም ጭምር የሚያሳይ ነው።

አዋጁ በሚጸድቅበት ወቅት ድንጋጌውን ' ትክክል ነው ' ብለው ሲከራከሩ የነበሩ የፓርላማ አባላት ነበሩ፤ ዛሬ ደግሞ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መደገፋቸው በአንድ ራስ ሁለት ያስብላል "  ብለዋል።

ሌላ የፓርላማ አባል ፦

" አዋጁ በሚጸድቅበት ጊዜ በድንጋጌው ላይ በመሰረታዊነት ክርክር ተደርጓል። በድንጋጌው ላይ የተለያየ መልክ ያለው ጫጫታ በብዛት ሲሰማ ነበር።

በምርመራ ወቅት የሚመረምረው አካል አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ባለበት ጊዜ፤ ከዚህ ውጪ ሊያደርግ የሚችለው ጉዳይ እንደሌለ፣ ዋስትና ሊያገኝ እንደሚገባ በደንብ ማብራሪያ የተሰጠበት ጉዳይ ነበር።

ድንጋጌው ከአዋጁ ውስጥ እንዲወጣ ሲደረግ፤ መርማሪዎች የተሰጣቸውን ዋስትና የሚያስቀር በመሆኑ ቀድሞ የጸደቀው ባለበት ቢቀጥል ይሻል ነበር።

የሚመረምሩ ሰዎች፣ አደገኛ ችግር ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ውስጥ፤ የእዚህ አይነት ዋስትና ሊያገኙ የማይችሉ ካልሆነ ሊመረምሩ ፍቃደኛ ይሆናሉ ወይ? ሊገቡ ፍቃደኛ ይሆናሉ ወይ? የሚመረምሩ ሰዎች አደገኛ ችግር ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ዋስትና የማንሰጣቸው ከሆነ፤ እንደዚህ አይነት risk ሊወስድ የሚችል አካል ላይኖር ይችላል። " ብለዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ምን አሉ ?

" ለእንደዚህ አይነት የምርመራ ስራዎች ዋስትና የሚሰጥ ህግ አለ። ዋስትና መስጠት እና ሌላ ነገር እንዲያደርግ ማድረግ የተለያየ ነገሮች ናቸው። ድንጋጌው መሰረዙ ተገቢ ነው። "

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገጽ ነው።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.14K🤔117👏58😭31🕊23😡12🥰11💔5😱4😢4🙏2
#AcademicCalendar

በመዲናዋ ለ2018 የትምህርት ዘመን የነባር እና አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ እንዲሁም የመፀሀፍ ስርጭት የሚካሄደው ከሐምሌ 1 እስከ ነሃሴ 23/2017 ዓ/ም መሆኑ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ/ም የትምህርት ቀናትን ዛሬ ይፋ አድርጓል ለ11ዱም ክ/ከተማ የትምህርት ፅ/ቤቶች ልኳል።

በዚሁ ካላንደር መሰረት ምዝገባ ከሃምሌ 1 እስከ ነሔሴ 23 /2017 ዓ/ም ይካሄዳል።

መምህራን በትምህርት ቤታቸው ተገኝተው ሪፖርት የሚያደርጉበት እንዲሁም አጠቃላይ የመምህራን ጉባኤ የሚደረገው ነሃሴ 28 እና ነሃሴ 29/2017 ዓ/ም እንደሆነ ተመላክቷል።

ከነሃሴ 24 እስከ ጳጉሜ 5/2017 ዓ/ም ደግሞ የ7ኛና የ9ኛ ክፍል ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚመጡ አዲስ ተመዝጋቢዎች ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል።

መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ/ም የመጀመሪያው ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ  (day one class one) እንደሆነ ይፋ ተደርጓል።

በ2018 ዓ/ም የሚሰጠው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና እንደሚሰጥ በትምህርት ካላንደሩ ላይ ታሳቢ ተደርጓል።

(ሙሉውን ከላይ ይመለከቱ)

@tikvahethiopia
1.17K😭83😡60🙏50👏31🕊31😱21🤔19😢19💔18🥰3
#Wolaita

ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በም/ማዕረግ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነ ተሾሙ። ወ/ሮ እታገኝ ሀ/ማሪያምን ደግሞ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ ሆነዋል።

የወላይታ ዞን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን አፅድቋል።

በዚህም ፦
1. ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በም/ማዕረግ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

2. አማረ አቦታ (ዶ/ር) የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ

3. አቶ ተስፋሁን ታዴዎስ የወላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ

4.ወ/ሮ እታገኝ ሀ/ማሪያምን የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ አድርጎ በሙሉ ድምጽ ሾሟቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
534👏38😡25🥰15🙏14🕊10🤔9😭5😱4😢3💔3
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NationalExam🇪🇹
#SocialScience

የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የማኀበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ ዙር ፈተና ዛሬ ከጥዋት ጀምሮ መሰጠት ተጀምሯል።

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው የማኀበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
294🕊27😭15🤔14🙏8💔7🥰5😡4
TIKVAH-ETHIOPIA
የዘውዱ ሃፍቱ ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ከዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ የመጨረሻ ውሳኔ ዛሬ ሰኔ 3/2017 ዓ.ም ሊሰጥ ቀጠሮ ቢያዝለትም ለሰኔ 30/2017 ዓ.ም ተሸጋግሯል። ዛሬ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል የችሎት ውሎውን ተከታትሏል። የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ግንቦት 8/2017 ዓ.ም ለመጨረሻ ውሳኔ ተቀጥሮ ነበር ሆኖም የተከሳሽ ቤተሰቦች በቀሰቀሱት ግርግርና ረብሻ…
#Update

" የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል ! " - ሂደቱን የሚከታተሉ ታዛቢዎች

አሁንም የእንስት ዘወዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል የፍርድ ውሳኔ ሌላ ቀጠሮ ተይዞለታል።

የግድያ ወንጀሉ ከተፈፀመ የፊታችን ነሀሴ ወር የሚከበረው የአሸንዳ 2017 ዓ.ም በዓል ሁለት ዓመት ይሞላዋል።

አሰቃቂ የግድያ ወንጀሉ የአሸንዳ በዓል በሚከበርበት ወርሃ ነሀሴ 2015 ዓ.ም ነበር የተፈፀመው።  

የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል ችሎት የትላንት ውሎ ምን ይመስል ነበር ? 

የእንስት ዘውዱ ሃፍቱ የግድያ ወንጀል በመመልከት ላይ የሚገኘው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም በተከሳሾች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ ላይ ጥፋተኛ የተባሉት ግለሰቦች የሚያቀርቡት የፍርድ የማቅለያ ለመስማት ነው ለሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የተቀጠረው።

የችሎቱ ዳኞች በያዙት ቀጠሮ ተከሳሾች ለፍርድ ማቅለያ የሚሆናቸውን የህክምናና ሌሎች ሰነድ እንዲያቀርቡ ባዘዙት መሰረት በጠበቃቸው በኩል አቅርበዋል።

አንደኛ ተከሳሽ የልብ ህመም ታማሚና የኪንታሮት ህመምተኛ ፣ ሁለተኛው ተከሳሽ ደግሞ የስኳርና የኪንታሮት ህመምተኛ መሆናቸውን በቃል ቢገልጹም በሃኪሞች ማስረጃ እንዲረጋገጥ ለሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

በግድያ ወንጀሉ በመፈፀመ የተጠረጠሩ ሁለቱ ወጣቶች ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ/ም በሃኪም የተረጋገጠ የፅሁፍ ማስረጃ ያቀርቡ እንደሆነ ያኔ የሚታይ ሆኖ የችሎት ሂደቱን የተከታታሉ የሚድያ ባለሙያዎች ፣ የሴቶች ጥቃት እንዲቆም የሚሰሩ ግለሰቦችና ተቋማት " ይህንን ሁሉ በሽታ ተቋቁመው ይህን መሰል ዘግናኝ ግድያ ለመፈፀም እንዴት ጉልበትና አቅም አገኙ ? " የሚል ጥያቄ ጭረዋል።

የችሎቱ የውሎ መረጃ  በማህበራዊ ሚዲያ የተከታተሉ በርካቶች የፍርድ ሂደቱ ለሁለት አመታት መራዘሙ በመቃወም "  የዘገየ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል " ብለዋል።

የአሰቃቂ የግድያ ወንጀሉ የፍርድ ሂደት ሀምሌ 3 ቀን 2017 ዓ.ም መቋጫ ይብጀለት ይሆን ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ጉዳዩ ተከታትሎ ያቀርባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
769😭194😡57🕊22🙏19😢10🥰9💔9😱5👏4
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ምን ውሳኔ አሳለፈ ? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ዛሬ ውይይት አካሂዶ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል። 1. በሁሉም ንግድ ባንኮች ላይ የተጣለው አስገዳጅ የቦንድ ግዥ እንዲነሳ ወስኗል። ሁሉም ንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ (Treasury Bond) እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ (MFAD/TRBO/001/2022)…
#Ethiopia🇪🇹

አስገዳጅ የቦንድ ግዢ መመሪያው መነሳቱ ለባንኮች ምን ትርጉም አለው ?

ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ባካሔደው ሶስተኛ ስብሰባ፣ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ከውሳኔዎቹ አንዱም የንግድ ባንኮች ሲገዙት ከነበረው የግምጃ ቤት ቦንድ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡

ኮሚቴው፣ የንግድ ባንኮች የረጅም ጊዜ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ የሚያስገድደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ እንዲነሳ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ይህም የሆነው በአሁኑ ወቅት የመንግስት ገቢ የማሰባሰብ አቅም በእጅጉ በመሻሻሉና መንግስት የበጀት ጉድለቱን ለማሟላት የውጭና ገበያ መር ከሆኑ የሀገር ውስጥ የመበደሪያ አማራጮችን እየተጠቀመ በመሆኑ ነው ብሏል፡፡

የንግድ ባንኮች ቦንድ እንዲገዙ ሲደርግ የነበረው አስገዳጅ መመሪያ በመነሳቱ፣ ለባንኮቹ ምን ፋይዳ አለው ? በማለት ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው አንድ ከፍተኛ የባንክ ባለሙያ፣ " አሰራሩ በባንኮች ዘንድ የገንዘብ እጥረት እንዲፈጠር አስተዋፅኦ ስለነበረው፣ ይህ ውሳኔ በጣም ጠቃሚ ነው " ሲሉ ገልፀዋል፡፡  

የባንክ ባለሙያው በዝርዝር ምን አሉ ?

" ቦንዱ እንኳን ተነሳ፡፡ በቦንዱ ምክንያት ለአምስት አመት ታስሮ የሚቀመጥ ገንዘብ ነበር፡፡ ባንኮቹ ቦንድ የገዙበት ገንዘብ ከአምስት አመት በኋላ ነው የሚመለስላቸው፡፡

ይህ አስገዳጅ የቦንድ ግዢ መመሪያ፣ በባንኮች የገንዘብ እጥረት/የሊኩዲቲ ችግር እንዲመጣ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ለሊኩዲቲ ችግር መከሰት አንዱ መንስኤ የነበረው እሱ ነው፡፡

የሆነ ብድር በሰጠህ ቁጥር የተወሰነ ፐርሰንት ቦንድ እድትገዛ ትገደድ ነበር፡፡ ብድር በሰጠህ ቁጥር የብድሩን 20 በመቶ ቦንድ ግዛ ትባላለህ፡፡ እስከ 20 በመቶ እንድተገዛ ትገደድ ነበር፡፡ ለአንድ ሰው አምስት ጊዜ ካበደርክ ያስቀመጥከውን ገንዘብ በሙሉ ወሰደው ማለት ነው የቦንድ ግዢው፡፡ በዚህ መልኩ ባንኮች ብድር በሰጡ ቁጥር ተደራራቢ የቦንድ ግዢ ስለሚፈፅሙ እና ገንዘቡም የሚመለሰው ከአምስት አመት በኋላ ስለነበረ ለገንዘብ እጥረት አጋልጧቸዋል።

አሁን ይኼ በመቆሙ ትልቅ እፎይታ ነው የሚሰጣቸው፡፡ ለችግራቸው መፍትሔ ይሆናል፡፡ ለገንዘብ እጥረቱ ማስተንፈሻ ነው፡፡ ብሔራዊ ባንክ የወሰደው እርምጃ በእጅጉ አጋዥ ነው፣ የሚያስመሰግነው ነው፡፡

በቦንድ ግዢ ከባንኮች ሲሔድ የነበረው የገንዘብ መጠን፣ ባንኮቹ በሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የሚመሰረት ነበር፡፡ አሁን ይሔ አሰገዳጅ የቦንድ ግዢ መመሪያ በመቅረቱ፣ የባንኮቹን የገንዘብ እጥረት በምን ያህል መጠን ሊያቃልለው እንደሚችል ማወቅ ይከብዳል፣ ግን በእጅጉ ያቃልላል፡፡

ይሔ ጥሩ እርምጃ ሆኖ፣ የንግድ ባንኮች የሚሰጡት ዓመታዊ የብድር ዕድገት ጣሪያ ደግሞ አልተነሳም፡፡ ከ18 በመቶ እንዳይበልጥ የተቀመጠው የብድር ጣሪያ እስከ መስከረም ወር እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

ብሔራዊ ባንክ በዚሁ እርምጃው ይህንንም 18 በመቶ የሚለውን የብድር ጣሪያ ቶሎ ቢያነሳው ጥሩ ነበር፡፡
የብድር ጣሪያው በባንኮች አሰራር ላይ ችግር እየፈጠረ ነው ያለው፡፡ ለምን ብትል ተበዳሪዎች ብድራቸውን ከመለሱ በኋላ በባንኮች ላይ በተጣለው የብድር ጣሪያ ምክንያት መልሰው እንደማይበደሩ ስለሚያውቁ የመጀመሪያውንም ብድራቸውን አይከፍሉም፡፡ ለባንክ የሚከፍሉትን እዳ ለሌላ አገልግሎት ያውሉታል፡፡

ይልቁንም ለባንክ መክፈል የነበረባቸውን ገንዘብ ለሌላ ንግድ እያገላበጡ ይጠቀሙበታል፡፡ ለዚህ ነው እዳ ውስጥ የሚገቡት፡፡ ባንኮቹ በተቀመጠው የ 18 በመቶ የብድር ጣሪያ ምክንያት ተጨማሪ ብድር መስጠት አይችሉም ብቻ ሳይሆን ቀድመው ያበደሩትን ገንዘብ ማስመለስ አልቻሉም፡፡

ብሔራዊ ባንክ ይህንን የብድር ጣሪያ የሚያነሳበትን ጊዜ በጉጉት ነው የምንጠብቀው፡፡ እርምጃው ለኢንቨስትመንትና ለስራ ፈጠራም አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ የግሉ ዘርፍ ከባንኮች እየተበደረ ኢንቨስት ካላደረገ ኢኮኖሚው አይንቀሳቀስም፣ የስራ እድል ሊፈጠር አይችልም፣ ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖው ብዙ ነው፡፡ " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
1.02K🙏67👏36🤔21😢17😭17🕊13😡13🥰11😱11
2025/07/12 12:47:42
Back to Top
HTML Embed Code: