TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ የ2018 ዓ/ም የኢሬቻ #ሆራ_ፊንፊኔ በዓል አከባበር #Irreechaa2018 #AyyaanaGaari ! #HappyIrreechaa ! Photo Credit - Social Media @tikvahethiopia
#Irreechaa2018
Baga Ayyaanaa Irreechaa Nagaan Geessan !
Ayyaana Gaari !
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
መልካም በዓል !
@tikvahethiopia

❤660😡470😭34👏22🙏15😢11🕊11😱7💔5🥰2
TIKVAH-ETHIOPIA
#ታርጋ በኢትዮጵያ የሚመዘገቡ ሁሉም ተሽከርካሪዎች 'ኢት' የሚል መለያ እና የኢትዮጵያ ካርታ ያለበት አዲስ የመለያ ሠሌዳ ቁጥር እንዲኖራቸው ሊደረግ ነው። በአገሪቱ ያሉ ተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሠሌዳ እንደሚቀየር ተነግሯል። በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የወጣው መመሪያ ምን ይዟል ? - አዲሱ መመሪያ በአሁኑ ሰዓት በሥራ ላይ ያሉ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች ላይ የሚቀመጠውን የተለያዩ ክልሎች…
#ኢት
አዲሱን የተሸከርካሪ ሰሌዳ የመቀየር ሥራ ከሁለት ወራት በኋላ ይጀመራል ተብሏል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ባወጣው የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ መመሪያ መሠረት አዲሱ የተሸከርካሪ ሰሌዳ የመቀየር ሥራ ከሁለት ወራት በኋላ እንደሚጀመር በሚኒስቴሩ የትራንስፖርት አገልግሎት እና ቁጥጥር ዘርፍ አማካሪ አቶ አሰፋ ሀዲስ #ለአሐዱ ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት የተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች የቀድሞውን ሠሌዳ በመመለስ አዲስ የተሸከርካሪ የመለያ ቁጥር ሠሌዳ እንዲወስዱ የማድረግ ሥራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሰሌዳ አይነቶችና ምልክቶች መወሰኛ እና የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 1050/2017 ሆኖ መጽደቁ ይታወሳል።
በመመሪያው መሰረት አሁኑ በሥራ ላይ ያሉ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች ላይ የሚቀመጠው የተለያዩ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መለያዎች ተመሳሳይ መለያ እንዲኖራቸው ያስገድዳል።
በሀገሪቱ የሚመዘገቡ ሁሉም ተሸከርካሪዎች የሚለጥፉት የመለያ ቁጥር ሠሌዳ ላይ ፤ የኢትዮጵያ ካርታ እንዲሁም ኢትዮጵያ ባጸደቀችው ዓለም አቀፍ ስምምነት መሠረት የተሰጣትን ሀገራዊ ልዩ ምልክት " ETH " እና " ኢት " የሚል የግእዝ ፊደላት እና የላቲን ፊደላት ይዘት እንዲኖረው ይደረጋል።
መመሪያው አሁን በሥራ ላይ ያሉ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች ላይ የሚቀመጠውን የተለያዩ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች መለያዎችን አላካተተም።
#ኢትዮጵያ #ETH #ኢት #ሰሌዳ #አሐዱ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

❤3.24K🙏146😡146👏130🤔57🕊56😭31😢20😱19🥰6
በስራ ቦታዎች ላይ እኩልነትን ማስፈን ከመቅጠርም ይልቃል
ለዚህም ነዉ ህጉ አሰሪዎች የመጸዳጃ ቤቶችን ፣ካፍቴሪያዎችን እንዲሁም ሁሉን መገልገያዎችን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲሆኑ ግዴታን በአሰሪዎች ላይ የሚጥለዉ
ሰብአዊ፣ሞራላዊ እና ህጋዊ ግዴታዎችን መወጣት የሰለጠነ ማህበረሰብ መገለጫ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ከሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ ባገኘዉ የገንዘብ ድጋፍ
Website: https://elda-eth.com/
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=61579398676431
Twitter: https://x.com/toelda2024
Linkdin: [https://www.linkedin.com/company/ethiopian-lawyers-with-disabilities-association/]

❤398🙏37🕊7🥰6🤔6😱5😢2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Irreechaa2018 Baga Ayyaanaa Irreechaa Nagaan Geessan ! Ayyaana Gaari ! እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! መልካም በዓል ! @tikvahethiopia
ፎቶ፦ የ2018 ዓ/ም የኢሬቻ #ሆረ_ሀርሰዴ በዓል አከባበር #Irreechaa2018
የ2018 ዓ.ም የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔና ሆረ ሀርሰዴ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ አሳውቀዋል።
Photo Credit - ኤፍ ኤም ሲ እና ኢቲቪ

❤1.43K😡989😭88💔69🕊61👏35🤔35🥰33🙏32😢13
#SafaricomEthiopia
✨ 3 የስኬት ዓመታት✨
ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ የእርስዎ እምነት ጉዟችንን አቀጣጥሎታል! 🚀
በአብሮነት ወደፊት!! 💚
#SafaricomEthiopia
#Furtheraheadtogether
#3rdAnniversary
#MissionPossible

❤288🤔14🥰13🕊12😡8😢3😭3🙏1💔1
" ለቢል ቦርድ ማስታወቂያ መስቀያ የተዘጋጀው ብረት ጉዳት ሳያደርስ የመፍትሔ እርምጃ ቢወሰድበት ጥሩ ነው " - ነዋሪዎች
➡️ " የጉዳዩን አንገብጋቢነት በመግለፅ በተደጋጋሚ ለባለድርሻ አካላትና አመራሮች ብናሳውቅም የመፍትሔ እርምጃ አልተወሰደም !! " - የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተባበሪያ
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ከቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ' ሱሙዳ ' አጠገብ የሚገኘው ግዙፍ የመንግስት ቢል ቦርድ ማስታወቂያ የሚሰቀልበት ብረት ከማርጀቱ የተነሳ በዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ላይ በመደገፉ በሰውና በንብረት ላይ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል ፈጣን የመፍትሔ እርምጃ እንዲወሰድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት አሳስበዋል።
" የማስታወቂያ መስቀያ ብረቱ ከ20 ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል " ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ " በአገልግሎት ብዛት አርጅቶ እየወደደቀ ነው። መብራት ሃይልም ሆነ የከተማ አስተዳደሩ በአደባባይ ለተከሰተ ችግር መፍትሔ ሳይሰጡ መቆየታቸው ተገቢነት የለውም " ሲሉ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ሲዳማ ክልላዊ ማስተባበሪያ ባገኘው መረጃ ፤ ቸግሩ አሳሳቢና በሰውና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል በመግለፅ የጉዳዩን አሳሳቢነት ለክልሉና ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ቢያሳውቅም መፍትሔ አልተሰጠውም።
" የማስታወቂያ መስቀያ ብረቱ ግዙፍና ባለቤትነቱም የመንግስት በመሆኑ መብራት ሃይል ለማስነሳት ኃላፊነት አይወስድም " ያለዉ ማስተባባሪያው " ያለንን የአሰራር ሂደት ተከትለን በተደጋጋሚ ብናመለክትም መፍትሔ አልተበጀለትም " ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያን ኃላፊን በስልክ በማናገር በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማኘት ቢሞክርም ለጊዜዉ አልተሳካም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ

❤722🙏86😭30🕊17🤔15😱11🥰2😢2